No summary available.
የካቲት 22 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ዩኒሉበር ፑ.ኤል.ሲ.ፏርት ሰንላይት ዊራል ሜርሲ ሳይድ - ጠበቃ ተሾመ ገ/ማርያም - ቀረበ ተጠሪ፡- ጌት እሸት ዱተርጀንት ማምረቻና ማከፊፈያ ኋ/የተ/የግል/ማህበር - ጠበቃ አድማሱ መአዛ ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር ተፈጽሞብኛል በማለት አመልካች በተጠሪ ላይ ያቀረበውን ክስ መነሻ በማድረግ የተካሄደውን ክርክር የሚመለከት ነው። ክሱ የቀረበው ለንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሽን ጽ/ቤት ሆኖ ኮሚሽኑም የሁለቱን ወገኖች ክርክር ከሰማ በኋላ፣ ከሣሽ /የአሁኑ አመልካች/ ያቀረበውን ጥያቄ ተቀብልአል። በዚህ መሰረትም ተጠሪ በንግድ አሰራር አዋጅ ቁ.329/95 አንቀፅ 10/2/ሀ/ የተደነገገውን በመተላለፍ አመልካች የሚጠቀምበትን የንግድ ምልክት አስመስል በመለጠፍ ምርቱን መሸጡን እንዱያቆም፤ ለዚህ ድርጊቱም በአዋጁ አንቀፅ 26/1/ መሰረት ብር 1ዐ,000/አስር ሺህ ብር/ መቀጫ እንዱከፍል ወስኖአል። በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪ ውሣኔውን በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ክርክሩ በድጋሚ የተሰማ ሲሆን ፍ/ቤቱም የንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሽን ጉዲዩን ለማየት /ለመዲኘት/ ስልጣን የለውም በማለት ይግባኝ የተባለበትን ውሣኔ ሽሮአል። በዚህ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤትም በበኩለ ክርክሩን ከሰማ በኋላ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሣኔ አጽንቶአል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።አመልካች ሚያዝያ 12 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ በስር ፍ/ቤቶች በተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞአል የሚልበትን ምክንያት በመግለጽ አቤቱታውን አቅርቦአል። ስህተቱ ይታረምለትም ዘንድ ጠይቆአል።
በበኩላችንም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው ጉዲይ የንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሸን የዲኝነት ስልጣን ስር አይወድቅም የተባለው በህጉ አግባብ ነው ወይ? በሚለው ጭብጥ ላይ ነው። በመሆኑም በዚህ ረገድ ግራ ቀኙ ወገኖች ያሰሙትን ክርክር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና ከህጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከስር ጀምሮ የተደረገውን የግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር እና የተሰጡትን ውሣኔዎች ይዘት በዝርዝር ተመልክተናል። ከዚህም በቅድሚያ ልንገነዘብ የቻልነው አመልካች ክስ የመሰረተው የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ መብትን ለማስከበር ወይም የንግድ ምልክት ባለቤትነት መብትን ለማረጋገጥ ሣይሆን ፣ ከህግ አግባብ ውጪ ተፈጽሞብኛል ያለውን የማይገባ የንግድ ውድድር እንዱገታለት /እንዱቆም/ እና ተጠሪም ለዚህ ድርጊቱ ተገቢው እርምጃ እንዱወሰድበት በመጠየቅ እንደሆነ ነው። ክሱን የሰማው የንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሽንም የቀረበለት የዲኝነት ጥያቄ የተፈጸመውን እና በመፈጸም ላይ ያለውን ያልተገባ የንግድ ውድድር እንዱቆም፣ ተጠሪም በአዋጁ መሰረት እርምጃ ይወሰድበት የሚል እንደሆነ በመገንዘቡ የንግድ ምልክት ጥበቃን /አዋጅ ቁ.
501/98/ በሚመለከት የሚነሣውን ክርክር የመዲኘት ስልጣን የለህም በማለት ከተጠሪ ቀርቦለት የነበረውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ በጉዲዩ ስረ ነገር ላይ አከራክሮ ውሣኔ ሰጥቶአል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ደግሞ የስር ከሣሽ /አመልካች/ ክስ የንግድ ምልክት ባለቤትነት ማዕከል ያደረገ ነው የሚል ምክንያት በመስጠት ጉዲዩ በኮሚሽኑ የዲኝነት ስልጣን ስር አይወድቅም በማለት ወስኖአል።
የኮሚሽኑ ውሣኔ እንዲየነው የተመሰረተው በንግድ አሰራር አዋጅ ቁ. 329/95 አንቀጽ 10 እና 15 በተቀመጡት ድንጋጌዎች ላይ ነው። አመልካችም ክሱን የመሰረተው በእነዚህ ድንጋጌዎች እና ያልተገባ የንግድ ውድድርን በሚመለከት በንግድ ህግ ቁ. 133 የተቀመጠውን ድንጋጌ በመጥቀስ ነው። ተጠሪ የፈጸመው እና እየፈጸመው ነው ያለውን ድርጊትም በዝርዝር በመግለጽ አቅርቦታል።
የንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሽን ያልተገባ የንግድ ውድድርን በሚመለከት የሚነሣውን ክርክር የመዲኘት ስልጣን ያገኘው በአዋጅ ቁ. 329/95 አንቀጽ 15 መሰረት ነው።
በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1/ሀ/ እና /ሰ/ እንደተመለከተው ኮሚሽኑ ከማንኛውም ወገን የሚቀርቡለትን አቤቱታዎች የአዋጁ ድንጋጌዎችን የመተላለፍ ድርጊት ተፈጽሞአል በሚል እስከቀረቡ ድረስ አቤቱታዎቹን የመመርምር እና በመጨረሻም እንደአግባቡ አስተዲደራዊ እርምጃዎች እና /ወይም የቅጣት ውሣኔ የመስጠት ስልጣን ተሰጥቶታል። በዚህ ረገድ አግባብነት ያላቸው ማለትም ለአቤቱታው መቅረብ መነሻ ሉሆኑ የሚችለት የአዋጁ ድንጋጌዎችም ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድርን በተመለከተ ዝርዝር ነገሮችን የያዘው አንቀጽ 1ዐ ፣ ገበያን በበላይነት ያለአግባብ ስለመጠቀም በሚል የተደነገገው አንቀጽ 11 ‘ን’ መጥቀስ ይቻላል። ከዚህም በተጨማሪ የአዋጁን ዓላማ በዝርዝር ያስቀመጠው አንቀጽ 3 ‘ንም’ መመልከቱ ተገቢ ይሆናል። የአዋጁ ዓላማ ፡- /1/ ለነጻ ገበያ ውድድር እንቅፊት የሆኑ ድርጊቶችና ተገቢ ያልሆኑ የንግድ ስራዎች እንዲይፈጸሙ በመከላከልና በማስወገድ ተገቢ የንግድ ውድድር እንዱሰፍን ለማድረግ እና /2/ በንግድ ዕቃዎች እና አገልግልቶች አቅርቦት እና ስርጭት ላይ ገደብ የሚፈጥሩ ድርጊቶችን በመከላከልና በማስወገድ የተጠቃሚውን ህብረተሰብ ጥቅም ማስጠበቅ ነው።
በሚል በዝርዝር ተቀምጦአል።
ቀደም ሲል እንዲመለከትነው ተጠሪ በአዋጅ ቁ. 329/95 አንቀጽ 1ዐ/2//ሀ/ የተቀመጠውን ድንጋጌ ስለመተላለፈ በአመልካች ክስ ተገልጾአል። የድርጊቱ አፈጻጸም ምን እንደሚመስልም በክሱ በዝርዝር ተመልክቶአል። የተጠቀሰው አንቀጽ 1ዐ/2/ሀ/ በልላው የንግድ ድርጅት ወይም በንግድ ድርጅቱ ተግባሮች፣ በተለይም ድርጅቱ ከሚያቀርበው ምርት ወይም አገልግልት ጋር በተገናኘ ሁኔታ ማደናገርን ያስከተለ ወይም ሉያስከትል የሚችል ማናቸውም ድርጊት ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር ሆኖ እንደሚቆጠር ያመለክታል። ተጠሪ ፈጽሞታል ወይም እየፈጸመው ነው ተብል በአመልካች ክስ የተነገረውም ይኸው በድንጋጌው የተመለከተው ድርጊት ነው። የአመልካች የክስ መነሻ ተጠሪ እኔ የምጠቀምበትን የንግድ ምልክት አመሣስል በመለጠፍ ምርቱን እየሸጠ ነው የሚል ነው በአጠቃላይ የአመልካች በአዋጅ ቁ. 329/95 የተመለከቱትን ድንጋጌዎች የመተላለፍ ድርጊት ተፈጽሞብኛል በሚል ብቻ የሚያቆም ሣይሆን፣ ተፈጸሙ የሚላቸው ድርጊቶች ከህጉ ጋር ያላቸውን ግንኙነት /አግባብነትም/ በግልጽ እና በዝርዝር የሚያሣይ ነው። የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዲዩ ከንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ መብት አከባበር አንጻር የሚታይ ነው /አዋጅ ቁ 501/98/ ለማለት የቻለው ተጠሪ የአመልካችን የንግድ ምልክት አመሣስል በመለጠፍ ምርቱን እየሸጠ ነው የሚለውን በአመልካች ክስ የተቀመጠውን አባባል አጉልቶ በማውጣት እንደሆነ ከውሣኔው ይዘት ለመገንዘብ ችለናል።
በበኩላችን እንደምንገነዘበው በተያዘው ጉዲይ የንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሽን የዲኝነት ስልጣን አለው ወይም የለውም? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ በዋናነት መታየት ያለበት የክሱ አጠቃላይ ይዘት እና የተጠየቀው ዲኝነት ነው። ላላው በመቀጠል መታየት ያለበት ጉዲይ አመልካች እና ተጠሪ በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ብቻ ሣይሆኑ፣ ተመሣሣይነት ያለው ዕቃም ለገበያ እያቀረቡ ናቸው። አመልካች ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር ተፈጽሞብኛል የሚለውም ተጠሪ የሱ ያልሆነውን የንግድ ምልክት /አመልካች ባለቤት የሆነበትን/ አመሣስል በሚሸጠው ምርት መያዣ ዕቃ ላይ በመለጠፍ እየሸጠ /ለገበያ እየቀረበ/ ነው በማለት ነው። ድርጊቱ ያልተገባ ውድድር ነው እየተባለ ያለውም አመልካች ከሚያቀርበው ምርት ጋር ማደናገርን አስከትልአል ስለተባለ ወይም ሉያስከትል የሚችል ሆኖ በመታየቱ ነው። በመሆኑም በክሱ አቀራረብ ወይም በክርክር ሂደት ስለንግድ ምልክት በመነሣቱ ጉዲዩ የንግድ ምልክት ባለቤትነት መብት ወይም ምዝገባና ጥበቃን የሚመለከት ነው ማለት አይችልም። በመሆኑም በዚህ ረገድ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት የደረሱበት መደምደሚያ የህግ መሰረት የለውም። ጉዲዩ በንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሽን የዲኝነት ስልጣን ስር የሚወድቅ ነው።
በመጨረሻም ተጠሪ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያለበትን ምክንያት አይተናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ እንደተመለከተው የንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሽንን የዲኝነት ስልጣን በሚመለከት ብቻ ነው ተጠሪ ቅሬታውን ያሰማው። ከዚህ ባለፈ ኮሚሽኑ በስረ ነገር አጣርቶ በደረሰው መደምደሚያ ላይ ክርክር /ይግባኝ/ አላቀረበም። በመሆኑም ከዚህ በኋላ በስረ ነገር ላይ የሚደረግ ክርክር የለም። ጉዲዩ በህጉ አተረጓጏም ረገድ የተፈጸመውን መሰረታዊ ስህተት ማረም ከዚሁ የሚቋጭ ሆኖ አግኝተነዋል። ስለዚህም ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 67927 ሚያዝያ 15 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 46554 የካቲት 25 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
አመልካች በተጠሪ ላይ የመሰረተው ክስ በንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሽን የዲኝነት ስልጣን ስር የሚወድቅ ነው ብለናል። ስለዚህም ኮሚሽኑ በን.አ.አ.ኮ/1-2-58 መጋቢት 26 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ጸንቶአል።
በዚህ ሰበር ችልት በተደረገው ክርክር ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሣቸውን ይቻቻለ።
No topics extracted.