No summary available.
ሰኔ 16 ቀን 2ዐዐ3ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አብደልፈታህ መሐመድ - ጠበቃ ጥበቡ ተስፊዬ - ቀረበ ተጠሪ፡- ኮልፋ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ፍትሕ ጽ/ቤት የቀረበ የለም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በገቢ ግብር አዋጅ ቁ 286/94 አንቀጽ 96 እና በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁ 285/94 አንቀጽ 49 እንደዚሁም በወንጀል ሕግ አንቀጽ 349/1/ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመተላለፍ ወንጀል ተፈጽሞአል በማለት ተጠሪ ባቀረበው ክስ መነሻነት የተደረገውን ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ ፍ/ቤቱ የግራ ቀኝ ወገኖቹን ክርክር ከሰማ በኋላ ተከሣሽ የነበረውን የአሁኑ አመልካችን ጥፊተኛ ነው ብልአል። በዚህ መሰረትም በአመልካች ላይ ተገቢ ነው ያለውን ቅጣት ወስኖአል። በልላ በኩል ደግሞ በቅጣቱ አወሳሰን ላይ ባለመስማማት ተጠሪ ለከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ክርክሩ በድጋሚ የተሰማ ሲሆን፣ ፍ/ቤቱም ይግባኝ የተባለበትን ውሣኔ አፅንቶአል። በመጨረሻም ተጠሪ ውሣኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ሰበር ችልት አቤቱታ በማቅረቡ በዚህ ደረጃም ክርክሩ ተሰምቶአል። በመቀጠልም ችልቱ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡትን የቅጣት ውሣኔ በመሻር አመልካች በስድስት ዓመት ፅኑ እስራት እንዱቀጣ ወስኖአል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች ነሐሴ 24 ቀን 2002 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች የተጨማሪ እሴት ታክስን በተመለከተ የሚቀርቡ የወንጀል ክሶችን ለማየት ሥልጣን አላቸው ወይ? በሚለው ጭብጥ ላይ ነው። በመሆኑም ይህን ጭብጥ ግራ ቀኝ ወገኖች ካሰሙት ክርክር ፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ አና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከላይ እንዲመለከትነው አመልካች የተከሰሰው በሁለት የተለያዩ አዋጆች የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመተላለፍ ወንጀል ፈጽሞአል ተብል ነው። አዋጆቹ የተለያየ ስያሜ እና ተግባር ያላቸው ሲሆኑ ፣ የመጀመሪያው የገቢ ግብር አዋጅ ፤ ሁለተኛው ደግሞ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ናቸው። የዲኝነት ሥልጣን ጥያቄ ያስነሳው የተጨማሪ እሴት ታክስን መሰረት በማድረግ የቀረበው ክስ ነው። በዚህ ረገድ የተነሳው ጥያቄ መታየት ያለበት የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶችን የዲኝነት ሥልጣን በሚመለከት ከተደነገገው የቻርተሩ/የተሻሻለው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ቻርተር አዋጅ ቁ 361/95 አንቀጽ 41 አንፃር ነው። በተጠቀሰው አንቀጽ 41/2/ የፍ/ቤቶቹ የወንጀል /የደንብ መተላለፍ የዲኝነት ሥልጣን በዝርዝር ተቀምጦአል። በዚህ መዝገብ ለተያዘው ጉዲይ አወሳሰን ተገቢነት ያለው ድንጋጌ በፉደል /ሀ/ ሥር የተመለከተው ሲሆን፣ ይዘቱም ፍ/ቤቶቹ በቻርተሩ አንቀጽ 52 በተመለከቱ የፊይናንስ ጉዲዮች ላይ በሚነሱ የወንጀል ጉዲዮች ላይ ሥልጣን ያላቸው መሆናቸውን ይገልጻል።
የቻርተሩ አንቀጽ 52 የከተማ አስተዲደር የፊይናንስ ሥልጣን በዝርዝር የሚያመለክት ሆኖ የዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ /4/ እና /5/ም ለተያዘው ክርክር አግባብነት እንዲላቸው መገንዘብ ይቻላል። ንኡስ አንቀጽ /4/ የከተማው አስተዲደር በራሱ የሚወሰነው እና የሚሰበሰበው የንግድ ትርፍ /የገቢ / ግብር ፣ የኤክሳይዝ ታክስ እና የተርን ኦቨር ታክስ ብቻ እንደሆነ ሲያመለክት ፤
ንኡስ አንቀጽ /5/ ደግሞ በከተማው ከሚኖሩ ግለሰብ ነጋዳዎች እና በከተማው ባለቤትነት ሥር ከሚገኙ የልማት ድርጅቶች የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚሰበሰበው የፋዳራል መንግስት እንደሆነ እና በመጨረሻ ታክሱ የሚሰጠው ለከተማው አስተዲደር መሆኑን ያመላክታል። እነዚህን ድንጋጌዎች አንድ ላይ አድርገን ስንመለከት መገንዘብ የምንችለው የተጨማሪ እሴት ታክስን የመሰብሰብ ሥልጣን ለከተማው አስተዲደር በሕግ አለመስጠቱን ነው። ታክሱን የመሰብሰብ ሥልጣን ካልተሰጠው ደግሞ ታክሱን የመክፈል ግዳታ ያለባቸውን ሰዎች የመከታተል፣ በታክስ ሕጉ አፈጻጸም ረገድ ጥፊት ፈጽመዋል የሚባለትንም የመክሰስ ሥልጣን ተሰጥቶታል ልባል አይችልም። እነዚህ ሁኔታዎች ከታክሱ አሰባሰብ ወይም ደግሞ ከታክሱ አዋጅ አፈጻጸም ጋር የተያያዙ በመሆናቸው ሉከታተላቸው የሚገባው ታክሱን የመሰብሰብ ሥልጣን የተሰጠው የፋዳራል መንግስቱ ነው። ይህን የማስፈጸም ሥልጣን የተሰጠው የገቢዎች እና ጉምሩክ ባለሥልጣን እንደመሆኑ የወንጀል ክሱ መቅረብ ያለበት በባለሥልጣኑ ዓቃቤ ሕግ ነው።
ጉዲዩ የፋዳራል መንግስቱ ሥልጣን ነው ከተባለም ክሱ መቅረብ ያለበት ለፋዳራል ፍ/ቤት ነው። በመሆኑም የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ በመተላለፍ ተፈጽሞአል የተባለውን ወንጀል በሚመለከት የቀረበላቸውን ክስ ያዩት በሕጉ ሥልጣን ሳይሰጣቸው ነው ለማለት ችለናል። ፍ/ቤቶቹ በአዋጅ ቁ 361/95 አንቀጽ 52/4/ እና /5/ የተቀመጡትን ድንጋጌዎች የተረጎሙበት አግባብ ትክክል አይደለም። ስለዚህም ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.