No summary available.
የሰ.መ.
ሐምል 14 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ሼህ አሽራቅ ሰይድ - ጠበቃ ዝኑር አብደልወሀብ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የቡታጅራ ከተማ ቀበላ 02 አስተዲደር - አበበ ነጋሽ ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦች ክልል የጉራጌ ዞን የቡታጅራ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። የክርክሩ መነሻ የኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብላክ ፔራይቬታይዜሸንና የመንግስት ልማት ድርጅት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የቡታጅራ አካባቢ ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔውን እንዱያስፈፅምለት የሰጠው ውክልና ነው። ኤጀንሲው ሕዲር 17 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈና ቁጥር 05/1506/88/8402/2002 በሆነ ደብዲቤ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 371 እና ተከታይ ድንጋጌዎች አማካኝነት እንዱፈፀም ስለመጠየቅ የሚል ርዕስ ያለውና በይዘቱም በደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ልዩ ከፍተኛ ቀበላ 02 ክልል ውስጥ የሚገኝ ቁጥሩ 112 የሆነ መኖሪያ ቤት ከሼህ አሽራቅ ሰይድ ከአዋጅ ውጭ የተወሰደባቸው በመሆኑ እንዱመለስላቸው መስከረም 7 ቀን 2002 ዓ.ም በቁጥር 05/1506/339/2000 የተሰጠውን ውሣኔ ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቀናል።
ሆኖም በኤጀንሲው ውሣኔ መሰረት ያልተፈፀመላቸው መሆኑን ባለጉዲዩ ካቀረቡት ማመልከቻ ስለተረዲን በአዋጅ ቁጥር 146/9/ እና አዋጅ ቁጥር 110/87 መሰረት ውሣኔያችንን ፍ/ቤቱ እንዱያስፈፅምልን የሚል መሆኑን የሥር ፍ/ቤቱ በውሣኔው አስፍሮታል። ከዚህ ደብዲቤ ጋር ኤጀንሲው ቤቱ እንዱመለስ የሰጠውን የውሣኔ ግልባጭ እንደላከ ከገለፀ በኋላ ተጠሪ በመቃወሙ ኤጀንሲው በቡታጅራ አካባቢ ፍ/ቤት ውሣኔውን እንዱያስፈፅምለት የሰጠው ውክልና ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ለጉዲዩ አግባብነት አላቸው የሚላቸውን የሕግ ድንጋጌዎች ከዘረዘሩና ከተረጏሙ በኋላ የኤጀንሲውን ውሣኔ የማስፈፀም ሥልጣን ያለው የሚኒስቴሮች ምክር ቤትና ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንጂ ፍርድ ቤት የኤጀንሲውን ውሣኔ የማስፈፀም ሥልጣን የለውም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። የቡታጅራ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ እንዱያይላቸው አመልካች አመልክተው ይግባኛቸው ተቀባይነት አላገኘም። አመልካች ለክልለ ሰበር ችልት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ውድቅ ተደርጓል።
አመልካች የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ፔራይቬታይዜሽንና የመንግስት ልማት ድርጅት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በፍትሐብሕር ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 371 በሰጣቸው ውክልና መሰረት የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጠሪ በውሣኔው መሰረት የማይፈፀምበትን ምክንያት በመጠየቅ ውሣኔውን ማስፈፀም ወይም ላላ ተገቢ ነው የሚለውን የአፈፃፀም ትዕዛዝ መስጠት ሲገባው በአዋጅ ቁጥር 146/9 እና በአዋጅ ቁጥር 110/87 ድንጋጌዎች የተዛባ ትርጉም በመስጠት ሥልጣኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ እንጂ የፍርድ ቤት አይደለም በማለት የሰጠውን ትዕዛዝ የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ማፅናቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩለ ፍርድ ቤት ግለሰቦችን እንጂ የአስተዲደር አካላትን በአፈፃፀም የማስገደድ እና የኤጀንሲውን ውሣኔ እንዱያስፈፅም እንዱያደርግ ኤጀንሲውን መወከል አይችልም። ስለዚህ የክልለ ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ ሥልጣን የለንም በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለውም በማለት መልስ አቅርበዋል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የኢትዮጵያ ፔራይቬታይዜሽንና የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በሰጠው የአፈፃፀም ውክልና መሰረት የኤጀንሲውን ውሣኔ የማስፈፀም ሥልጣን ፍርድ ቤቱ የለውም በማለት የተሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ኤጀንሲው ከአዋጅ ውጭ የተወሰደ ንብረቶችን በተመለከተ አከራክሮና አጣርቶ የመወሰን ሥልጣን በሕግ ተሰጥቶቷል። ስለሆነም ኤጀንሲው በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 37 ድንጋጌ አገላለፅ ከፍ/ቤት ውጭ ከአዋጅ ውጭ የተወሰደ ንብረቶችን በተመለከተ አከራክሮ የመወሰን የዲኝነት ሥልጣን በሕግ የተሰጠው የመንግስት አካል ነው።
የኢትዮጵያ ፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ከአዋጅ ውጭ የተወሰደ ንብረት ለባለቤቱ እንዱመለስ የመወሰን ብቻ ሳይሆን ውሣኔውንም ለማስፈፀም አስፈላጊውን እርምጃ የመውሰድ ሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 110/87 አንቀፅ 74/ሐ/ ተሰጥቶታል። በፍርድ ቤት ወይም በሕግ ዲኝነት ሥልጣን በተሰጠው ላላ አካል የተሰጠው ውሣኔ የሚፈፀመው ፍርደን በሰጠው ፍርድ ቤት /ወይም/ በሕግ የዲኝነት ሥልጣን በተሰጠው አካል ወይም እንደ ፍርደ እንዱያስፈፅም በታዘዘው ፍርድ ቤት እንደሆነ ከፍትሐብሕር ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 371 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማ ለመገንዘብ ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ ማናቸውም የመንግስት ተቋም ኤጀንሲው በአዋጅ ቁጥር 110/87 የተሰጠውን ሥልጣንና ኃላፉነት ለመወጣት እንዱችል ተገቢውን ትብብር የማድረግ ግዳታ ያለበት መሆኑን በአዋጅ ቁጥር 110/87 አንቀፅ 7 በግልፅ ተደንግጓል። እንዱሁም በአዋጅ ቁጥር 146/1991 አንቀፅ 26 /2/ ፍርድ ቤቶች ከአዋጅ ውጭ የተወሰደ ንብረቶችን ለባለቤታቸው እንዱመለሱ ኤጀንሲው የሰጠውን ውሣኔ የማስፈፀምና በንብረቱ ላይ ያለውን ባለይዞታ እንዱለቅ ለመወሰን እንደሚችለ ነገር ግን ይዞታው ወይም ንብረቱ የእኔ ነው ወይም በህግ መሰረት የተወሰደ ነው የሚል መቃወሚያ ቢቀርብላቸው ሉያስተናግደ እና አከራክረው ሉወስኑ እንደማይችለ ይደነግጋል። በልላ አነጋገር የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 87 ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማን በሚያሳካ መንገድ የአዋጅ ቁጥር 110/87 እና የአዋጅ ቁጥር 146/91 አንቀፅ 28 ንዐስ አንቀፅ 2 ድንጋጌዎች መተርጎምና ስራ ላይ መዋል ያለባቸው ሲሆን ፍርድን ስለማስፈፀምና ፍርድ እንዱፈፀም ውክልና ስለመስጠት ከፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 371 ጀምሮ ያለት አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 37 እና የሥነ ሥርዓት ሕጉ ከታወጁ በኋላ የወጡ ልዩ የህግ ማዕቀፍች አዋጅ ቁጥር 110/87 እና 146/91 ለማስፈፀም በሚያግዝ መልኩ መተርጎምና ሥራ ላይ መዋል ይገባቸዋል።
No topics extracted.