No summary available.
ሐምል 15 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ትዕዛዙ አርጋው - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ ም/ቤት - አልቀረበም።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የአሁኑ አመልካች ለሥር የአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ የአሁኑ ተጠሪ /የሥር ተከሳሽ/ በሕገ ወጥ መንገድ ከሥራዬ በማገደ ምክንያት ያልከተፈለኝ ውዝፍ ደመወዝ ብር 114,788 እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ ብለዋል።
የሥር ተከሳሽም በዋናነት ሁለት መቃወሚያዎችን አቅርቧል። መቃወሚያዎቹም ፍ/ቤቱ ጉዲዩን ለማየት የሥረ ነገር ዲኝነት ሥልጣን የለውም፣ የከሳሽ ክስ በይርጋ ይቋረጣል የሚለ ናቸው።
የሥር ፍ/ቤት ተከሳሽ ያቀረቧአቸውን የመቃወሚያ ነጥቦች ከመረመረ በኋላ ከሳሽ የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኛ በመሆናቸው በክልለ የሲቪል ሰርቪስ አዋጅ ቁጥር 29/95 አንቀጽ 71 መሰረት ክሱ መቅረብ ያለበት ለአስተዲደር ፍ/ቤት እንጂ ለመደበኛ ፍ/ቤት ባለመሆኑ ፍ/ቤቱ ሥልጣን የለውም ሲል የከሳሹን ክስ ውድቅ አድርጓል።፡ የሥር ከሳሽም ለክልለ የመንግስት ሰራተኞች አስተዲደር ፍ/ቤት ጉዲዩን ያቀረቡ ሲሆን የአስተዲደር ፍ/ቤቱ በአስተዲደር መ/ቤት የዱስፔሉን ኮሚቴ የተሰጠ ውሣኔ በመ/ቤቱ የበላይ ኃላፉ ከፀደቀ በኋላ በይግባኝ የሚቀርቡ ጉዲዮችን የማየት ሥልጣን ያለው ሲሆን የይግባኝ ባይ ቅሬታም ይኸንኑ ሥነ ሥርዓት ሳይጠብቅና በአሰሪው መ/ቤት የተሰጠ የዱስፔሉን ኮሚቴ ውሣኔ በላለበት በ3ኛ ወገን /በክልለ ም/ቤት/ ውሣኔ ከሥራ የተሰናበቱ በመሆናቸው የአስተዲደር ፍ/ቤቱ ጉዲዩን አከራክሮ ለመወሰን ሥልጣን የለውም በማለት ክሱን ሳይቀበል ቀርቷል።
የአሁን አመልካችም በክልለ የመንግስት ሰራተኞች አስተዲደር ፍ/ቤት በተሰጠ ብይን ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠ/ፍ/ቤት ያቀረቡ ቢሆንም የክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም መልስ ሰጪውን መጥራት ሳይስፈልግ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት የይግባኙን መዝገብ በመዝጋት ይግባኝ ባዩን አሰናብቷል። የአሁኑ አመልካችም በሥር የአስተዲደር ፍ/ቤትም ሆነ በይግባኝ ሰሚው ችልት ብይን ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት የሰበር አቤቱታቸውን ለሥር የክልለ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረቡ ቢሆንም የተፈፀመ የሕግ ስህተት የለም በማለት የሥር ፍ/ቤቶችን ብይን አጽንቷል።
አመልካች የሰበር አቤታቸውን ለዚህ ችልት ያቀረቡትም በሥር የአስተዲደር ፍ/ቤትና በክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ብይንና በክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ፍርድ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል በሚል ሲሆን በዋናነት የጠቀሱትም የቅሬታ ነጥብ፣ ተጠሪው አመልካችን ከሥራ አግድ ካቆየ በኋላ ማሰናበቱ አግባብ ባለመሆኑ ጉዲዩን አከራክሮ እንዱወስኑ በሚል ለአስተዲደር ፍ/ቤትም ሆነ መደበኛ ፍ/ቤቶች ክስ ባቀርብም አለመቀበላቸው አመልካች ፍትሕ እንዲላገኝ የሚያደርግ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም የሚል ነው።
ተጠሪው በበኩለ በሰጠው መልስ አመልካች የክልለ የፊይናንስ ቢሮ ኃላፉ ሆነው በሹመት በሚሰሩበት ወቅት በታማኝነት ማገልገል ሲገባቸው በፀረ ልማትና አፍራሽ በሆኑ ተግባራት ላይ ተሰማርተው በመገኘታቸው በተሰጠው የፕለቲካና የአስተዲደር ውሣኔ ከሥራቸው እንዱሰናበቱ የተደረገው በአግባቡ ነው በማለት የሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለም ሲል ተከራክሯል።
ከሥር ጀምሮ የተደረገው ክርክር ከዚህ በላይ እንደተጠቀሰው አጥሮ የቀረበ ሲሆን እኛም በሥር የአስተዲደር ፍ/ቤት ብይንም ሆነ በየደረጃው ባለ የክልለ ፍ/ቤቶች ብይንና ፍርድ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለ? ወይስ የለም? የሚለውን ጭብጥ ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
ከቀረበው ክርክር መገንዘብ እንደሚቻለው አመልካች ቀደም ሲል የመንግስት ሰራተኛ በመሆናቸው በክልለ የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ መሰረት የሚተዲደሩ ቢሆንም የክልለ መስተዲደር ም/ቤት ተመርጠው በተሰጣቸው ሹመት መሰረት የክልለ የፊይናንስ ቢሮ ኃላፉ በመሆን እየሰሩ ፈጽመዋል በተባለት ፀረ ልማትና አፍራሽ ተልዕኮ ከሥልጣናቸው ወይም ከሹመታቸው የሾሟቸው አካል አንስቶአቸዋል።
ይህ በመሆኑ ቀደም ሲል ሲሰሩበት ከነበረው የመንግስት መ/ቤት ለቀው በተሰጣቸው ሹመት ላይ እያለ በተወሰደባቸው የፕለቲካ እርምጃና የአስተዲደር ውሣኔ ከሥራቸው በመነሳታቸው ጉዲይ በክልለ የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ መሰረት ላታይ የሚገባ መሆን አለመሆኑን መመርመር ተገቢ ይሆናል።
በክልለ የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ መሰረት ለአስተዲደር ፍ/ቤት በይግባኝ የሚቀርበው ጉዲይ አስቀድሞ መታየት ያለበት ሰራተኛው በሚሰራበት የመንግስት መ/ቤት ውስጥ በተቋቋመው የዱስፔሉን ኮሚቴ ነው። አመልካች ግን ከፍ ተብል እንደተገለፀው የፊይናንስ ቢሮ ኃላፉ በመሆናቸው በሥራቸው ያለ የመንግስት ሰራተኞች የዱስፔሉን ግድፈት ሲፈጽሙ የመ/ቤቱ የዱስፔሉን ኮሚቴ ውሣኔን ሉያፀድቁ ሉያሻሽለ ወይም ውድቅ በማድረግ እንደገና እንዱታይ የማድረግ ሥልጣን ያላቸው ናቸው። በመሆኑም ራሳቸውን እንደ ሰራተኛ በመቁጠር የፕለቲካ ውሣኔን ለአስተዲደር ፍ/ቤት የሚያቀርቡበትና ጉዲያቸውን በክልለ የመንግስት ሰራተኞች አሰተዲደር አዋጅ እንዱታይ የሚጠይቁበት ሁኔታ የለም።
በልላ በኩል ተጠያቂነት አንደ የመልካም አስተዲደር ማዕቀፍ ሲሆን በኢ/ፋ/ዱ/ሪ/ሕገ መንግስት አንቀፅ 12/2/ ማንኛውም ኃላፉና የሕዝብ ተመራጭ ኃላፉነቱን ሲያጓድል ተጠያቂ እንደሚሆን በግልጽ የተደነገገ ሲሆን ተጠያቂነቱ ለሕግ እና ለመረጠው ሕዝብ ጭምር ላሆን ይችላል። በዚህ በተያዘውም ጉዲይ አመልካች የቢሮው ኃላፉ በነበሩበት ወቅት ፈጽመዋል ለተባለት ድርጊቶች የሕዝብ ውክልና ያለው የክልለ ም/ቤት ከሥልጣናቸው ወይም ከሹመታቸው አንስቷል።
ይህን የፕለቲካ ውሣኔ አመልካች በፍ/ቤት ለማስለወጥ ማቅረባቸው ያለአግባብ ሲሆን የፕለቲካ ውሣኔዎችን /political actions/ ፍ/ቤቶች ተቀብለው አከራክረው ተገቢውን ፍርድ ለመስጠት የዲኝነት ሥልጣንም አይኖራቸውም።
በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች ጉዲዩን አከራክሮ ለመወሰን የሥረ ነገር የዲኝነት ሥልጣን የለንም ሲለ በሰጡት ብይንም ሆነ ፍርድ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አላገኘንም።
ው ሣ ኔ
የክልለ የአስተዲደር ፍ/ቤት በይ/መ/ቁ/አስ/ፍ/ቤት 17/02/2001 በቀን 30/04/2001 ዓ.ም የሰጠው ብይን፣ የክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 19/05/2001 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝና የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 30/03/2003 ዓ/ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ፀንተዋል።
የሥር ፍ/ቤቶች አመልካች ያቀረቡትን ክስ ለማየት የዲኝነት ሥልጣን የለንም ሲለ የወሰኑት በአግባቡ ነው ብለናል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ የግራ ቀኙ ተከራካሪዎች የየራሣቸውን ይቻለ።
መዝገቡ የተዘጋ ስለሆነ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.