No summary available.
ሐምል 29 ቀን 2003ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ሻምበል ለታይ ገ/መስቀል - ጠበቃ ሣህለ ሀብቴ - ቀረቡ ተጠሪ፡- በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዲ 1 አስተዲደር ጽ/ቤት - ነ/ፈጅ ቴዎድሮስ ጸሀዬ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የአዱስ አበባ አስተዲደር ከተማ ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ ታህሳስ 14 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይሻርልኝ በማለት ጥር 05 ቀን 2003 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታ አመልካች በማቅረባቸው ነው።
የክርክሩ ፍሬ ጉዲይ አመልካች ነሀሴ 12 ቀን 2002 ዓ/ም ለአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፅፈው ያቀረቡት ክስ ሲሆን ይዘቱም ተጠሪ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ቁጥሩ 067 የሆነውን ቤት በወር ኪራይ እየከፈልን በመኖር ላይ እንዲለን ከቀድሞ ባለቤቴ ጋር አብሮ መኖር ስላልቻልን በመ/ በሆነው ሚያዚያ 30 ቀን 2001 ዓ.ም የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጋብቻችን እንዱፈርስ ውሳኔ ተሰጥቷል ፣ እንዱሁም ከፍቺው በኋላ የወለድናቸውን ልጆች ለማሳደግ የሞግዚትነት ስልጣን የተሰጠኝ በመሆኑ በባለቤቴ ስም ተመዝግቦ የነበረውን የመንግስት ቤት ኪራይ ተጠቃሚነት በስሜ ዞሮ እንድጠቀምበት ከፍቺው ጋር ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የሰጠ በመሆኑ የፍርድ ቤቱን የውሳኔ ግልባጭ ለተጠሪ በማድረስ የስም ዝውውሩን በመጠባበቅ ላይ እንዲለ የኮንድሚኒየም ቤት ከቀድሞ ባለቤትሽ ጋር የደረሰሽ በመሆኑ ቤቱን እንድትለቂ የሚል ማስጠንቀቂያ በተጠሪ የተሰጣቸው መሆኑንና ለባለቤታቸው የኮንድሚኒየም ቤት የደረሳቸው መሆኑን ከፍቺው በሁዋላ የተረደ መሆኑን ገልፀው በተጠሪ የተፈጠረው ሁከት እንዱወገድላቸው ፣ የቤቱ የኪራይ ስምም እንዱዞርላቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መከላከያ መልስም የመንግስት ቤት ኪራይ ተጠቃሚነትን የኮንድሚኒየም ቤት በባለቤታቸው ስም ትዲር ፅንቶ ባለበት ጊዜ ደርሶአቸው እያለ ሉጠይቁ እንደማይገባ ገልፆ ተግባሩ ሁከት አይደለም በማለት ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለተከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ማስረጃዎችን መርምሮ የአመልካች ተግባር እንደሁከት ተግባር ሉቆጠር የሚችል አይደለም በማለት የአመልካችን ክስ ውድቅ አድርጓል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የአመልካች ተግባር ሁከት ነው ተብል የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሽሯል።
ከዚህም በኋላ ተጠሪ የሰበር አቤቱታውን ለከተማው ሰበር ሰሚ ችልት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የከተማው ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ ተሽሮ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ጸንቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የኮንድሚኒየም ቤት ለቀድሞ ባለቤታቸው መድረሱን ያወቁት ከፍቺው በኋላ ሁኖ እያለ ኮንዱሚኒየም መድረሱን በመገናኛ ብዙሃን በግልጽ የእጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት የተደረገና በአዱስ ልሳን ጋዜጣ ለሕዝብ ይፊ የሆነ ጉዲይ በመሆኑ የሕግ ግምት የሚወሰድበት ጉዲይ ነው ተብል በከተማው ሰበር ሰሚ ችልት መወሰኑ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው መሆኑ ታምኖበት ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ግራ ቀኙ በጽሁፍ ክርክራቸውን አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የዚህን ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ ጉዲዩ በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የከተማ ፍርድ ቤቶች የስረ ነገር ሥልጣን ስር የሚወድቅ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች በክሱ የጠየቁት ዲኝነት የተከራይነት ስም እንዱዞርላቸው የሚመለከት ብቻ ሳይሆን የተጠሪ ማስጠንቀቂያ መስጠት የሁከት ተግባር በመሆኑ ሉወገድ ይገባል የሚገባው ጉዲይ መሆኑን ጭምር ነው። የከተማው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የሰበር ሰሚ ችልትም የተጠሪ ተግባር ሁከት ነው በማለት ዲኝነት ሰጥተዋል።
ተጠሪ ደግሞ ቤቱን ለማስለቀቅ ለአመልካች የሰጠው ማስጠንቀቂያ የሁከት ተግባር አይደለም በማለት ተከራክሯል። ከዚህ አንፃር ስንመረምረው የአዱስ አበባ ከተማ ነክ ፍርድ ቤቶች ስልጣንና ሐላፉነት በአዋጅ ቁጥር 361/1995 በአንቀጽ 41 የተዘረዘረ ሲሆን የከተማ ነክ ፍርድ ቤት ንብረትነቱ የከተማው አስተዲደር የሆነ ቤት ላይ የሚነሱ ክርክሮችን አይቶ የመወሰን ስልጣን እንዲለው በአዋጅ አንቀጽ 41(1)(ረ) በግልጽ ተደንግጓል። ከዚህም የምንረዲው የከተማ ነክ ፍርድ ቤቶች ንብረትነታቸው የከተማው አስተዲደር ለመሆናቸው ክርክር በማይቀርብባቸው ቤቶች ላይ የሚነሱ የይዞታ ፣ የኪራይ እና ላልች ክርክሮችን አይተው የመወሰን ስልጣን ያላቸው መሆኑን ነው።
ሆኖም ክርክር የተነሳበት ቤት የከተማው አስተዲደር ነው? ወይስ የላላ ግለሰብ? ወይም ድርጅት? የሚል መሰረታዊ ክርክር ያለበት ከሆነ የከተማ ነክ ፍርድ ቤቶች ይህንን የቤት ባለቤትነት ጥያቄ አስመልክቶ በከተማው አስተዲደርና በላልች ሰዎች መካከል የሚደረግ ክርክር በዲኝነት አይተው ለመወሰን የሚያስችል የሥረ ነገር ስልጣን የላላቸው መሆኑን ከአዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41 (1) (ረ) ድንጋጌ ለመረዲት ይቻላል። በያዝነው ጉዲይ የቤቱን ሕጋዊ ባለቤትነት አስመልክቶ በአመልካች በኩል ክርክር የቀረበበት ሳይሆን የተጠሪን ባለቤትነትን በማመን በቤቱ ላይ የተከራይነት መብታቸው እንዱረጋገጥላቸው በፍርድ ቤት ውሳኔ ተሰጥቶ እያለ አመልካች ለተጠሪ በትዲር ጊዜ የኮንድሚኒየም ቤት በባል ስም ደርሷቸዋል ተብል ቤቱን እንዱለቁ የተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ የሁከት ተግባር በመሆኑ ሉወገድ ይገባል በማለት በመሆኑ የጉዲዩ መሰረታዊ ጭብጥም የተጠሪ ተግባር ሁከት ነው? ወይስ አይደለም? የሚል ነው። ጉዲዩ የቤት ይዞታ አይደለም እንጂ ነው ቢባል እንኳ የከተማው አስተዲደር ፍርድ ቤቶች የቤት ይዞታ ክርክርን በተመለከተ የዲኝነት ስልጣን በሕጉ የተሰጣቸው ሁከት ይወገድልኝ በሚል የሚቀርብ የዲኝነት ጥያቄን መሰረት ባደረገ መልኩ ሲቀርብ አይደለም። የቦታ ይዞታ ክርክርን በተመለከተም የዲኝነት ሥልጣን ለፍርድ ቤቶቹ በሕጉ የተሰጠው ከከተማው መሪ ፔላን አፈፃጸም ጋር በተያያዘ እንደሆነ አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41((ሀ)) ይይደነግጋል ፣ እንዱሁም በዚህ ረገድ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀፅ 2(1)መሰረት አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
ስለሆነም የሁከት ይወገድልኝ ክስ ከከተማው መሪ ፔላን ጋር እስካልተያያዘ ድረስ በከተማው ፍርድ ቤቶች የስነ ነገር ስልጣን ስር የሚወድቅ አይደለም። አንድ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ከማየቱ በፉት የስረ ነገር የዲኝነት ስልጣን ያለው መሆኑን ማረጋገጥ ያለበት ሲሆን የስረ ነገር የዲኝነት ስልጣን በተከራካሪ ወገኖች ባይነሳም በማናቸውም የክርክር ደረጃ ፍርድ ቤቱ በራሱ ሉያነሳው የሚገባው ጉዲይ መሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 9 እና 231 (1(ለ)) ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። የሥረ ነገር የዲኝነት ስልጣን በላለው ፍርድ ቤት የተሰጠ ውሳኔ ደግሞ በመርህ ደረጃ እንዲልተሰጠ የሚቆጠር ነው። ስለሆነም በየደረጃው ያለ የአዱስ አበባ አስተዲደር ከተማ ነክ ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን የማየት የስረ ነገር ስልጣን ሣይኖራቸው ጉዲዩን ሰምተውና አከራክረው የሰጡት ውሣኔ ህጋዊ አስገዲጅነት የላለውና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ ስለአገኘን ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
ይፃፍ።
አመልካች ያቀረቡት የሁከት ይወገድልኝ ጥያቄን ሥልጣኑ ለሚፈቅድለት ፍርድ ቤት ወይም አካል አቅርበው ተገቢውን ዲኝነት የመጠየቅ መብታቸውን ይህ ውሣኔ አይገድብባቸውም ብለናል።
ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.