No summary available.
መጋቢት 22 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የአቃቂ ቃሉቲ ክፍለ ከተማ አቤቱታ ምርመራና ክስ አቀራረብ ንዐስ ሥራ ሑደት ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ስማቸው ከተራ ቁጥር 1 እስከ ተራ ቁጥር 1ዐ የተጠቀሱት ተጠሪዎች በይግባኝ መዝገብ ያቀረቡትን የይግባኝ ቅሬታ በመመርመር የሰጠው ውሣኔና ስማቸው አስራ አንደኛና አሥራ ሁለተኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ተጠሪዎች በይግባኝ መዝገብ ያቀረቡትን ይግባኝ በመመርመር የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት በሁለት መዛግብት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ውድቅ መደረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረበው አቤቱታ የሚጣራ ነጥብ ያለው መሆኑ ተገልፆ ለሰበር ችልት ስለቀረበ ነው።
ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በአዱስ አበባ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው።
በሥር ፍርድ ቤት አመልካች በሁለም ተጠሪዎች ላይ መጋቢት 17 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. ፅፍ የወንጀል ክስ አቅርቧል። የአመልካች የወንጀል ክስ ይዘትም ስማቸው ከተራ ቁጥር 1 እስከ ተራ ቁጥር 4 የተጠቀሱት ተጠሪዎች በአዋጅ ቁጥር 67/89 አንቀጽ 28/1/ለ አንቀፅ 33 እና አንቀፅ 46/3/ መጋቢት 11 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በተደረገው ፍተሻ ጫት ሲያስቅሙና ሺሻ ሲያስጨሱ ከነሺሻ ዕቃው የተገኙ በመሆኑ ከተፈቀደላቸው ንግድ ፈቃድ ውጭ የመነገድ ሕግ የመጣስ ተግባር ፈፅመዋል።
ስማቸው ከተራ ቁጥር 5 እስከ ተራ ቁጥር 12 የተጠቀሱት ተጠሪዎች በአዋጅ ቁጥር 67/89 አንቀፅ 21(1) እና አንቀፅ 46(1) የተመለከተውን በመተላለፍ ጫት በማስቃምና ሺሻ በማስጨስ ገንዘብ እየሰበሰቡ የተገኙ በመሆኑ ያለንግድ ፈቃድ በመነገድ የህግ መጣስ ተግባር ፈፅመዋል የሚል ይዘት ያለው ነው። ተጠሪዎች ጥፊተኝነታቸውን ያመኑ በመሆኑ የአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተከሰሱበትን ወንጀል የፈፀሙ ጥፊተኞች ናቸው በማለት የጥፊተኝነት ውሣኔ ሰጥቷል። የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪዎች በተናጠል ያላቸውን የቅጣት አስተያየት እንዱያቀርቡ ካደረገ በኋላ እያንዲንደን ተጠሪ ጥፊት ጋር ተመጣጣኝ ነው በሚለው በእስራትና በገንዘብ መቀጮ እንዱቀጡ ውሣኔ ሰጥቷል።
ስማቸው ከተራ ቁጥር 1 እስከ ተራ ቁጥር 10 የተጠቀሱት ተጠሪዎች የሥር ፍርድ ቤት በሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአዱስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የይግባኝ መዝገብ ያቀረቡ ሲሆን አስራአንደኛና አሥራሁለተኛ ተጠሪ ይግባኛቸውን በመዝገብ አቅርበዋል። የአዱስ አበባ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በሁለቱ መዝገቦች ተጠሪዎችና አመልካች ያቀረቡትን ክርክር ከሰማ በኋላ በአዋጅ ቁጥር 67/89 የወንጀል ቅጣት የሚያስከትለ ድንጋጌዎችን በመጣስ የሚፈፀሙ ወንጀልችን አስመልክቶ የሚቀርቡ የወንጀል ጉዲይ የአዱስ አበባ አስተዲደር ፍርድ ቤቶች አይቶ የመወሰን የዲኝነት ሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 67/89 ሆነ በልላ ህግ አልተሰጣቸውም። ስለሆነም የወንጀል ክሱ ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ላቀርብ ይገባል በማለት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ሽሮታል። አመልካች የሰበር አቤቱታውን በሁለት መዛግብት ለአዱስ አበባ አስተዲደር ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረበ ሲሆን የከተማው ሰበር ችልት የአዱስ አበባ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ የህግ ስህተት የላለበት መሆኑን በመግለፅ የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል።
አመልካች በተጣመሩት መዛግብት ባቀረበው የሰበር አቤቱታ አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀፅ 41(2)ሀ የከተማው ፍርድ ቤቶች የፊይናንስ መሰል ድርጊቶች ላይ የተፈፀሙ ወንጀልችን የማየት ሥልጣን እንዲላቸው ደንግጓል። ይህ ድንጋጌ የአዱስ አበባ አስተዲደር አስፈፃሚ አካላት ህግን የማስከበርና የመቆጣጠር ሥራ በሚሰሩበት ጊዜ ያጋጠማቸውን የህግ ጥሰት በከተማው ፍርድ ቤቶች ክስ አቅርቦ ለማስቀጣት በሚችለበት መንገድ መተርጎም ይገባዋል። ስለሆነም የአዱስ አበባ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና የከተማው ሰበር ችልት የሥር ፍርድ ቤት ጉዲዩን አይቶ የመወሰን የዲኝነት ሥልጣን የለውም በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱሻርልኝ በማለት አመልክቷል።
አንደኛ ሶስተኛና ስምንተኛ ተጠሪዎችና አስራ አንደኛና አሥራ ሁለተኛ ተጠሪዎች በበኩላቸው ባቀረቡት መልስ አዋጅ ቁጥር 67/89ን በመተላለፍ የተፈፀመ የወንጀል ጉዲይ የማየት ሥልጣን የአዱስ አበባ አስተዲደር ፍርድ ቤቶች አይደለም። በህግ በግልፅ ባልተደነገገ ወንጀል መከሰሳችንም ሆነ ጥፊተኛ ተብለን መቀጣታችን የህጋዊነት መርህን የሚጥስ ነው። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትና የሰበር ችልቱ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክረዋል። ላልቹ ተጠሪዎች በላለበት ጉዲዩ ታይቷል። አመልካች በህግ ረገድ ያለውን ክፍተት የሰበር ችልት ህጉን በመተርጎም ተገቢውን ማስተካከያ ሉያደርግ ይገባዋል የሚል ይዘት ያለው የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የአዱስ አበባ አስተዲደር ፍርድ ቤቶች በተጠሪዎች ተፈፀመ የተባለውን ወንጀል ለማየትና ለመወሰን የሚያስችል የዲኝነት ሥልጣን አላቸው ወይስ የላቸውም? የሚለው ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። ይህንን ጭብጥ ለመወሰን የአዱስ አበባ አስተዲደር ፍርድ ቤቶች የወንጀል የዲኝነት ሥልጣንን በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41 ንዐስ አንቀጽ 2 የተደነገገው ድንጋጌ መሰረታዊ ይዘት መመርመር አስፈላጊ ነው።
በአዋጁ አንቀጽ 41 ንኡስ አንቀጽ 2 የከተማው የወንጀል የዲኝነት ሥልጣን በአዋጅ አንቀጽ 52 በተመለከቱት የፊይናንስ ጉዲዮችን የሚመለከቱ ወንጀልችን አይተው እንደሚወስኑ የሚደነግግ ሆኖ አግኝተዋል። አመልካች ተጠሪዎች የተከሰሱበት ጉዲይ የደንብ መተላለፍ ተግባር እንደሆነ በማድረግ የሚከራከር ቢሆንም አዋጅ ቁጥር 67/89 የተደነገጉ የወንጀል ሃላፉነት የሚያስከትለ ድንጋጌዎችን በመተላለፍ ወንጀል ፈፅሞ መገኘት እንደወንጀለ ክብደት እስከ አስር ዓመት በሚደርስ እስራትና በገንዘብ መቀጮ የሚያስቀጣ መሆኑ የአዋጅ ቁጥር 67/89 አንቀጽ 46 ድንጋጌዎችን በማየት ለመገንዘብ የሚቻል በመሆኑ አመልካች ተጠሪዎች የተከሰሱት በደንብ በመተላለፍ ነው በማለት ያቀረበው ክርክር ህጋዊ መሰረት የላለው ሆኖ አግኝተነዋል።
ተጠሪዎች የተከሰሱትና በሥር ፍርድ ቤት ጥፊተኛ ተብለው የቅጣት ውሣኔ የተወሰነባቸው በአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41 ንዐስ አንቀጽ 2 እና በአዋጅ አንቀጽ 52 በተመለከቱት በከተማው አስተዲደር የፊይናንስ ጉዲዮች የሚመለከቱ ወንጀልችን ፈፅመዋል ተብለው እንዲልሆነ አመልካች ለሥር ፍርድ ቤት ያቀረበው የወንጀል ክስ ይዘትና የሥር ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ ከሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ ለመገንዘብ ይቻላል። ተጠሪዎች የተከሰሱትም ሆነ በሥር ፍርድ ቤት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ የተሰጠባቸው በአዋጅ ቁጥር 67/89 አንቀጽ 46 እና ላልች ድንጋጌዎችን በመተላለፍ ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ምክንያት ነው። የአዱስ አበባ አስተዲደር ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቀጥር 67/89ን በመተላለፍ የተፈጸሙ ወንጀልች የማየትና ዲኝነት ሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 67/89 እና በአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41 ንዐስ አንቀጽ 2 አልተሰጣቸውም።
ህግ አውጭው የአዱስ አበባ አስተዲደር ፍርድ ቤቶች ከላይ በተጠቀሱት ጉዲዩች የዲኝነት ሥልጣን እንዱኖራቸው ሀሣብና ፍላጏቱ ቢኖረው ኖሮ ጉዲዩን የማከራከርና የመወሰን ሥልጣን ያላቸው መሆኑን በህግ ማዕቀፍቹ በግልፅ በመደንገግ የዲኝነት ሥልጣን ያላቸው የአዱስ አበባ አስተዲደር ፍርድ ቤቶች ናቸው ብል ግልፅ ያደርገው ነበር። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 67/89ን በመተላለፍ የሚፈፀሙ ወንጀልችን የማየት የዲኝነት ሥልጣን ለአዱስ አበባ አስተዲደር ፍርድ ቤቶች ያልተሰጣቸው ሆኖ እያለ አመልካች ይህ የሰበር ችልት በትርጉም የዲኝነት ሥልጣን ለአዱስ አበባ አስተዲደር ፍርድ ቤቶች ነው ብል እንዱወሰንለት ያቀረበው አቤቱታ የህግ አተረጓጎም መርህን የሚጥስና ህግ ከውጭው አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀፅ 41 ንዐስ አንቀጽ 2 የደነገገበትን መሰረታዊ ዓላማ የማያሣካ በመሆኑ አልተቀበልነውም። ስለሆነም የአዱስ አበባ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት እና የከተማው ሰበር ችልት የከተማው ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 67/89ን በመተላለፍ የተፈፀሙ ወንጀልችን የማየት የዲኝነት ሥልጣን የላቸውም በማለት የወንጀል ክሱ ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት እንዱቀርብ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 11ዐን መሰረት በማድረግ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአዱስ አበባ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና የከተማው የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ፀንቷል።
አመልካች ተጠሪዎች ፈፅመውታል የሚለውን ወንጀል የማየት የዲኝነት ሥልጣን ላለው አካል የወንጀል ክሱ እንዱቀርብ ከማድረግ ይኼ ውሣኔ አያግደውም ብለናል።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.