No summary available.
መጋቢት 19 ቀን 2003ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ዓለም ገብሩ አልቀረቡም (ማ/ቤት ስለሆኑ) ተጠሪ፡- ትግራይ ዐቃቤ ህግ አልቀረቡም VC ስለማይሰራ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
ጉዲዩ የቀረበው የትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ስሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልካች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ የሚጣራ ነጥብ ያለው መሆኑ ተገልፆ ለሰበር ስለቀረበ ነው። የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ለዞኑ ዐቃቤ ህግ ያቀረበው የወንጀል ክስ ነው። ተጠሪ አመልካች ከላልች ግብረአበሮቹ ጋር በመሆን በወንጀል ህግ 32/3/ አንቀፅ 671 /1/ /ሀ/ /ሰ/ የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት አስበው በቡድን የጦር መሣሪያ በመያዝ በህዲር ወር 2000ዓ.ም ከቀፍታ ወረዲ ሁመራ ወደ ሀገረ ኤርትራ በመሻገር ከሁለት ኤርትራውያን ሰባት መቶ ድላር /700 ድላር/ በመዝረፍ የዘረፊ ወንጀል ፈፅሟል።
በኢፋድሪ የወንጀል ህግ አንቀፃ 27/1/ 32/1/ /ሀ/ /ለ/ ከላልች ግብረአበሮቹ ጋር ቡድን በመፍጠር ትጥቅ ይዘው ከሁመራ ወደ ሀገረ ሱዲን ሐምዲይት ከሚባል ቦታ ለዘረፊ ከሄደ በኃላ በሱዲን ወታደሮች ተኩስ ተከፍቶባቸው ስለሸሹ የመዝረፍ ሙከራ ወንጀል ፈፅሟል። ከ1994ዓ.ም እስከ 1999ዓ.ም ብዛቱ ያልታወቀ ማር ቅቤ በርበሬና ሽሮ ይዞ ከሁመራ በህገወጥ መንገድ ወደ ሱዲን ሐምዲይት የወሰደ በመሆኑ በተደጋጋሚ የአዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀፅ 66/1/ን በመተላለፍ የኮንትሮባንድ ወንጀል ፈፅሟል። ይህንን ወንጀል በ2000ዓ.ም ዕቃዎችን በህገወጥ መንገድ ወደ ሱዲን በመወሰድ በህገወጥ መንገድ ኮንትሮባንድ ወንጀል ፈፅሟል። በወንጀል ህግ አንቀፅ 481/1/ሀ የተመለከተውን በመተላለፍ 1800 ጥይት በአራት ብር ከሀምሣ ሣንቲም ገዝቶ በአምስት ብር ሸጧል። ከላልች ጋር በመሆን ቁጥሩ 7862 የሆነ ሁለት እግሯ ከላሽን ጠመንጃ ደብቆ በማስቀመጡ ተከስሷል በማለት የወንጀል ክስ አቅርቦበታል። አመልካች የወንጀለን ድርጊት አልፈፀምኩም ጥፊተኛ አይደለሁም በማለት ተከራክሯል። ዐቃቤ ህግ ከሳሽ መደበቁንና በሥር ስድስተኛ ተከሳሽ ከነበረው ሰው ቤት የተገኘ መሆኑን እናውቃለን የሚለ፣ ምስክሮችንና አመልካች ለፕሉስ ቃለን ሲሰጥ ሰምተናል የሚለ ምስክሩችን በማቅረብ አስመስክሮአል አመልካች ለፕሉስ ቃል የሰጠሁት በተፅዕኖ ነው በማለት የመከላከያ ምስክሮች አቅርቦ አሰምቷል። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራቀኙን ማስረጃ ከመዘነ በኃላ አመልካች የተከሰሰበትን አራት ወንጀልች የፈፀመ ጥፊተኛ ነው ብል በአሥር ዓመት ፅኑ እስራት እንዱቀጣ ፍርድ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ፍርድ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የግራቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አጽንቶታል። አመልካች የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት አቅርቧል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት ጉዲዩ የፋዳራል ጉዲይ በመሆኑ ጉዲዩን የማየት የሰበር ሥልጣን የለኝም በማለት አቤቱታውን ውድቅ አድርጎታል።
አመልካች ሚያዚያ 4 ቀን 2002ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የወንጀል ክሱ የቀረበውን የታየው ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን በላለው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። ክሱ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መታየት ያለበት እና በክልል ደረጃ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መታየት ነበረበት።
ስለዚህ በዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ታይቶ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት። ዐቃቤ ህግ በወንጀል ህግ አንቀፅ 18 /1/ሀ እና አንቀፅ 19/3/ የተቀመጡትን ሁኔታ ሣያሟላ ያቀረበውና ለፕሉስ በተፅዕኖ ከሰጠሁት የተከሳሽነት ቃል ውጭ ላላ ማስረጃ ያላቀረበበት ሆኖ እያለ ጥፊተኛ ተብዬ የተሰጠው የቅጣት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩለ የካቲት 17 ቀን 2003ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካች ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ከኢትዮጵያ ግዛት ውጪ በፈፀመው ወንጀል በኢትዮጵያ ፍርድ ቤትም መከሰሱም ሆነ ጥፍተኛ ተብል መቀጣቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክሯል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች ጥፊተኛ ከተባለባቸው አራት ወንጀልች መካከል አንደኛው ወንጀል በኤርትራ ግዛት ክልል ውስጥ ገብቶ ሰባት መቶ የአሜሪካን ድላር ከሁለት ኤርትራዊያን ዘርፎል የሚል ሲሆን ሁለተኛው በሱዲን ግዛት ክልል ሐምዲይት ከተባለ ቦታ መሣሪያ ታጥቆ ከግብረአበሮቹ ጋር በመሄድ የዘረፊ ወንጀል ለመፈፀም ሲሞክር በሱዲን መከላከያ ሀይል ተኩስ ተከፍቶበት የተመለሰ በመሆኑ የዘረፊ ወንጀል ለመፈፀም ሞክሯል የሚል ነው። እነዚህ ሁለት ወንጀልች በኢትዮጵያ ግዛት ክልል ውስጥ ወይም ኢትዩጵያዊ በሆነ ዜጋ ላይ የተፈፀሙ ወንጀልች አይደለም። እነዚህ ሁለት ወንጀልች የሱዲን ግዛት ክልልና በሱዲናዊ ዜጎች ላይ የተፈፀመ የዘረፊ ሙከራ ወንጀልና በኤርትራ ግዛት ክልል ውስጥ በኤርትራዊያን ላይ የተፈፀመ የዘረፊ ወንጀልች መሆናቸውን ከሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ለመገንዘብ ችለናል። እነዚህ ወንጀልች አመልካችና ግብርአበሮቹ የላላውን ለዓላዊ መንግስት የግዛት ክልል በመጣስ የተፈፀሙ መሆኑን የወንጀል ህጉን አንቀፅ 263 እና አመልካች ጥፊተኛ የተባለበትን የወንጀል ህግ አንቀፅ 71 በጣምራ በማየት ለመረዲት ይችላል።
በአዋጅ ቁ
No topics extracted.