No summary available.
ኀዲር 16 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢት/ ቴላኮሙኒኬሸን ኮርፕሬሽን - ነ/ፈጅ አቶ ዓለምሰገድ ፍትህአወቅ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ወርቅነሽ ወ/ማርያም በላለበት የሚታይ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን፤ መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የቀረበው የአ/አበባ ከተማ ማኀበራዊ ፍ/ቤቶች አመልካች የኢትዮጵያ ኤላኮሙኒኬሽን ኮርፕሬሽን ተከራካሪ የሆነበትን ጉዲይ ተመልክተው ለመወሰን የሚያስችል ሥልጣን አላቸው ወይስ የላቸውም? የሚለውን ጭብጥ ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር አገናዝቦ ለመተርጎም ሲባል ነው።
የጉዲዩም መነሻ የአሁን ተጠሪ የስልክ አገልግልት ክፍያና የስልክ ቀፍ እንዱመለስለት አመልካች ክስ መሥርቷል። በክሱ የተካተተውም የገንዘብ መጠን ከብር 5ዐዐዐ.00 በታች በመሆኑ ለአዱስ አበባ ከተማ ማኀበራዊ ፍ/ቤት አቅርቧል።
ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት በጉዲዩ ላይ ሁለቱንም ወገኖች ካከራከረ በኋላ የመጨረሻ ወርሃዊ ክፍያ ስለመፈፀሙ ደረሰኝ ከቀረበ ከዚህ ወር በፉት ላለት አገልግልቶች ተገቢው ክፍያ እንደተፈፀመ ይቆጠራል የሚለውን መሰረት አድርጎ ወስኖበታል።
የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም ይህንኑ ውሣኔ በማጽናት ስላሰናበተው የሰበር አቤቱታውን ለአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች ሰበር ሰሚ ችልት አቅርቧል።
ይኸው ሰበር ሰሚው ችልትም ወደ ጉዲዩ ዘልቆ ከመግባቱ በፉት ክሱ በአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች ቀርቦ ላታይ የሚገባው ነው ወይስ አይደለም? የሚለው የሥልጣን ጉዲይ በቅድሚያ ሉመረመር የሚገባው ነጥብ መሆኑን ጠቅሶ የአሁን አመልካች በፋዳራል መንግሥቱ የተመዘገበ አካል ነው። ይህን መሰል ወገን ተከራካሪ የሆነበትን ጉዲይ ተመልክተው የመዲኘት ሥልጣን ያላቸው የፋዳራል ፍ/ቤቶች ስለመሆናቸው በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 5/6/ ሥር ተመልክቷል።
ስለሆነም የፋዳራል የሆነውን ጉዲይ የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች ተመልክተው ለመወሰን ከሕግ የመነጨ ሥልጣን የላቸውም በማለት በየደረጃው የተሰጠውን ውሣኔ ሽሮ አሰናብቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህ ከላይ የተጠቀሰው ትርጉም በአዋጅ ቁጥር 361/95 ለማኀበራዊ ፍ/ቤቶች የተሰጣቸውን ሥልጣን ያገናዘበ አይደለም በሁለቱም አዋጆች ላይ ሥልጣንን በሚመለከት ግጭት አለ እንኳ ቢባል አግባብነት ያለውን አተረጓጎም ልንከተል ይገባል። ከዚህ አንፃር ከዚህ ቅደም ተከተል አንፃር ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለው አዋጅ ቁጥር 361/95 እንጂ አዋጅ ቁጥር 25/59 አይደለም። ስለሆነም የሕግ ስህተቱ ይታረምልን በማለት ነው።
እኛም በዚህ የሰበር ቅሬታ መነሻ ጉዲዩን መርምረናል።
የፋዳራል ፍ/ቤቶች የወል የፍትሐብሕር ሥልጣንን በሚደነግገው በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 5/6/ መሰረት በጉዲዩ የተካተተው የገንዘብ መጠን ምንም ይሁን ምን በፋዳራል መንግሥቱ የተመዘገበ የንግድ ድርጅት ወይም ማኀበር ተከራካሪ የሆነበትን ማናቸውም ጉዲይ ተቀብለው ለማስተናገድ ብቸኛ ሥልጣን ያላቸው የፋዳራል ፍ/ቤቶች ናቸው። ከሥልጣን ጋር በተያያዘ ሥራ ላይ የሚገኘው የሕግ ዘርፍ ይህ ብቻ ቢሆን ኖሮ ይህ ጉዲይ በፋዳራል ፍ/ቤቶች ሥልጣን ሥር ሉወድቅ የሚቻል ስለመሆኑ ባላከራከረ ነበር።
ይሁን እንጂ የአ/አበባ ከተማ ፍ/ቤቶችን ለማደራጀት በወጣው አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 5ዐ ላይ ደግሞ ተከራካሪ ወገን ማንም ይሁን ማን እስከ ብር 5ዐዐዐ.00 ሉደርስ የሚችለውን የገንዘብ ክርክር ጉዲይ በአ/አበባ ከተማ ሥር እስከተነሣ ድረስ የአ/አበባ ከተማ ማህበራዊ ፍ/ቤቶች ተቀብለው ለመወሰን ሥልጣን የተሰጣቸው በመሆኑ ከላይ ከፍ ሲል በአዋጅ ቁጥር 25/85 የተመለከተውን ድንጋጌ ከዚሁ አዋጅ ይዞታ ጋር ተገናዝቦ ላታይ ይገባዋል። በሁለቱም አዋጆች መሰረት አሁን የቀረበውም ጉዲይ ለየትኛው የፍ/ቤት አደረጃጀት ላቀርብ ይገባዋል? የጉዲዩ ባለቤት ማን ነው?
የሚል ጥያቄ ከተነሣ አንድ ወጥ የሆነ ምላሽ አያገኝም። በሁለቱም ሕጎች መካከል ቅራኔ እንዲለ እንረዲለን። ይህም ከሆነ ጉዲዩን ተቀብል ለማስተናገድ ሥልጣን የሚኖረው በአንደኛው መስመር የተደራጀው ፍ/ቤት ላሆን ስለሚገባው ይህንኑ ለይቶ ለመወሰን ተገቢውን የሕግ አተረጓጎም ዘዳ መከተል የግድ ይላል። ከእነዚህም የአተረጓጎም ዘዳዎች መከተል አንደ አንድን ጉዲይ ይኸውም ክርክር ያስነሳውን ጉዲይ ተቀብል ለመወሰን ሥልጣን ያላቸው የትኞቹ ፍ/ቤቶች ናቸው የሚለውን አስመልክቶ በእኩል ደረጃ በሚገኙ ሕጎች /አዋጆች/ በተለያዩ ሁኔታ ደንግገው ከተገኙ ከጊዜ ቅደም ተከተል አንፃር በኋላ የወጣው ሕግ ከፉተኛው በልጦ ተፈፃሚነት ይኖረዋል የሚለው የትርጉም መርህ በመሆኑ ጉዲዩ በአዋጁ ቁጥር 361/95 ሥር የሚታቀፍ ሆኖ እናገኘዋለን። በተለይም በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 5/6/ ድንጋጌ መሰረት ይህን መሰል ጉዲይ በፋዳራል ፍ/ቤቶች ሥር እንደሚወድቅ እየታወቀ ሕግ አውጪው ዘግይቶ ሥልጣንን የገንዘብ መጠን ወሰን አበጅቶ በልላ አነስተኛ የፍርድ መድረክ ሥር ቀርቦ እንዱታይ ማድረጉ በክርክር ምክንያት የሚወጣው ወጪና የሚባክነው ጊዜ ክርክሮች ከያዙት የገንዘብ መጠን ጋር የተመጣጠነ ላሆን እንደሚገባው ታሳቢ በማድረግ የፋዳራል ፍ/ቤቶችን ሥልጣን ቀንሶ ለመስጠት ሲባል የወጣ ሕግ መሆኑን ያመለክታል በተለይም ይህንኑ የትርጉም መስመር ይበልጥ የሚያጠናክረው የፋዳራል ፍ/ቤቶች ሥልጣን ተፈፃሚ ከሚሆንበት ከድሬደዋ ከተማ ጋር በተያያዘ የድሬዲዋ ከተማ ቻርተርን ለማቋቋም በወጣው በአዋጅ ቁጥር 416/96 አንቀጽ 41 ሥር ስለ ቀበላ ማኀበራዊ ፍ/ቤቶች ሥልጣን ሲደነገግ ከተላላፉ የገንዘብ ሰነድች እና ከኢንሹራንስ ጉዲይ በቀር ላልች ግምታቸው እስከ ብር 25ዐዐ.00 ድረስ ያለትን ገንዘብ ነክ ክርክሮች ለማየት ሥልጣን ያላቸው የማኀበራዊ ፍ/ቤቶች ናቸው በማለት ከዚህ ቀድሞ በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 5 ሥር የፋዳራል ጉዲይ መሆኑን ለመለየት መነሻ ከሆኑት 1ዐ ንዐስ ጉዲዮች መካከል ተላላፉ የገንዘብ ሰነድና የኢንሹራንስ ጉዲዮች ሉያስነሱ ከሚችለት የተወሳሰበ የሕግ ጥያቄ አንፃር ሁለቱን ብቻ በመለየት የፋዳራል ሆነው እንዱቀሩ በላልች ጉዲዮች የሚነሳው ክርክር ግን ግምቱ እስከ ብር 25ዐዐ.00 እስካልበለጠ ድረስ ከፋዳራል ፍ/ቤቶች ወጥተው በድሬዲዋ ከተማ ቀበላ ማኀበራዊ ፍ/ቤቶች እንዱታዩ መደረግ በገንዘቡ መጠን ትይዩ የሚታይበትን ፍ/ቤት እና የክርክር ደረጃ ለመለየት ሆን ተብል የወጣ ሕግ መሆኑን አስረጂ ነው።
የአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 5ዐ ይዘት ከዚሁ ተለይቶ የሚታይ ሆኖ አላገኘነውም።
በመሆኑም ከሥልጣን አደላደል አንፃር የሕግ ጥበቃ የተደረገለት የአሁን አመልካች ሥልጣን አለው በማለት በቀበላ ማኀበራዊ ፍ/ቤት የቀረበው ጉዲይ በፋዳራል ፍ/ቤቶች እንጂ በአ/አበባ ፍ/ቤቶች ሥልጣን ሥር የሚወድቅ አይደለም በሚል የአ/አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ትርጓሜ ሕጎቹ ከወጡበት ዘመን አንፃርም ሆነ የሕግ አውጪውን ሃሣብ ከመፈለግ አንፃር ላሰጥ የሚገባውን የሕግ አተረጓጎም ዘይቤ ያልተከተለ ስለሆነ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የተሰጠውን ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ ሽረናል።
በዚህ ሰበር ደረጃ ግራ ቀኙ ያደረጉት ክርክር ስላስለከተለው ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።
No topics extracted.