No summary available.
ህዲር ዐ1 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢት/ያ መድን ድርጅት - ነገረፈጅ ክንፈ ታደለ ቀረበ ተጠሪ፡- አቶ ሰለሞን ያዕቆብ - አልቀረቡም መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን፤ መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር መዝገብ ላቀርብ የቻለው አንድ የፋዳራል ፍ/ቤቶች የሆነን ጉዲይ በሕገ መንግሥቱ በተሰጠው የውክልና ሥልጣን መሰረት በክልል ከፍተኛ ፍ/ቤት ቀርቦ በታዩ ጊዜ የይግባኝ ክርክሩን ተመልክቶ ለመወሰን የይግባኝ ሰሚነት ሥልጣን ያለው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው ወይስ የዚያው ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት? ለሚለው የሕግ ጥያቄ አግባብነት ያለው የሕግ ትርጉም ለመስጠት ሲባል ነው።
የጉዲዩ መነሻ ከውል ውጪ በሚደርስ ኃላፉነት ክስ ምክንያት የአሁን ተጠሪ ባቀረበው የገንዘብ ክርክር የአሁን አመልካች በጉዲዩ ላይ ጣልቃ ገብቶ ተከራክሯል። ጉዲዩ የቀረበለትም የአላባ ልዩ ወረዲ ከፍተኛ ፍ/ቤት የቀረበለትን ጉዲይ ከመረመረ በኋላ ኃላፉ የሆነውን ወገን ለይቶና የካሣ መጠኑን ወስኖ የአሁን አመልካች በገባው የዋስትና ሽፊን መሰረት ለተጠሪ ይክፈል በማለት በመወሰኑ ምክንያት የኢት/ያ መድን ድርጅት ኃላፉነትና የካሣ መጠኑን አስመልክቶ በተሰጠው ውሣኔ ቅር ተሰኝቶ የይግባኝ አቤቱታውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቧል። በዚህም የይግባኝ ቅሬታ መነሻ የአሁን መልስ ሰጭ ቀርቦ እንዱከራከር ሲደረግ በመጀመሪያ ደረጃ ያቀረበው የይግባኝ ክርክር የፍ/ቤቱን የይግባኝ ሥልጣን የሚመለከት ነው።
ከውሣኔው ግልባጭ ይዘት እንደምንረዲው ለክርክሩ መሰረት ያደረገው ከዚህ ቀደም በተመሣሣይ ጉዲይ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰበር ሰሚው ችልት በሰበር መ/ቁ. 2ዐ465 ሰኔ 26 ቀን 1999 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ በክልል ፍ/ቤት በውክልና ሥልጣን የታዬ ጉዲይ በይግባኝ ተቀብል የማስተናገድ ሥልጣን ያለው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት እንጂ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት አይደለም በማለት የወሰነ ስለሆነ በአዋጅ ቁጥር 454/97 መሰረት ይህም የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህንኑ ጉዲይ ተቀብል ለማየት የሚያስችለው ሥልጣን የለውም የሚለውን ነው።
የይግባኙ ጉዲይ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይህንኑ በሚመለከት የሚከተለውን ዲኝነት ሰጥቷል፡ ክርክር ባስነሣው ጉዲይ ሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች የሁለት የተለያዩ ክልል ኗሪ ናቸው።
በመሆኑም በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 5/2/ መሰረት ጉዲዩ የፋዳራል ነው የፋዳራል የሆነውን ጉዲይ የክልል ከፍተኛ ፍ/ቤት በውክልና ሥልጣኑ ተመልክቶ ከወሰነ ክሱ የሚታይበትን ክልል ጨምሮ በአምስቱም ክልልች ተሰጥቶ የነበረው የውክልና ሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 322/95 የተነሣ ስለሆነ በዚህ መንገድ በተሰጠው ውሣኔ ላይ የሚቀርበውን የይግባኝ ክርክር ተቀብል ለማስተናገድ ሥልጣን ያለው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት እንጂ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት አይደለም የሚለውን ትንታኔ ምርኩዝ በማድረግ በሥልጣን ረገድ የቀረበውን የመከራከሪያ ነጥብ በኮ/መ/ቁ. 67947 ሚያዚያ ዐ5 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በዋለው ችልት ውድቅ አድርጎታል።
የፋዳራል ከፍተኛው ፍ/ቤት ጉዲዩን በይግባኝ የማየት ሥልጣን አለኝ ሲል በሰጠው ውሣኔ የአሁን መልስ ሰጭ ቅር ተሰኝተው የይግባኝ አቤቱታ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት በማቅረባቸው ይህ ችልት ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በመ/ቁ.46679 በዐ4/5/2ዐዐ2 ዓ.ም በዋለው ችልት በተመሣሣይ ጭብጥ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መ/ቁ.
2ዐ465 ሰኔ 26 ቀን 1999 ዓ.ም በሰጠው ትርጉም መሰረት የአላባ ልዩ ወረዲ ከፍተኛ ፍ/ቤት ባገኘው የውክልና ሥልጣን ተመልክቶ ውሣኔ በሰጠበት የፍደራል ጉዲዩ የሚቀርበውን የይግባኝ ክርክር ተመልክቶ የመዲኘት ሥልጣን ያለው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ስለሆነ የአሁን አመልካች የይግባኝ አቤቱታውን በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ማቅረቡ ተገቢ አይደለም። ስለሆነም ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የይግባኝ አቤቱታ ከሚያቀርብ በቀር ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ማቅረብ አይችልም በማለት ውሣኔውን ሽሮታል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሣኔውን ለመሻር መሰረት ያደረገው የሰበር ሰሚ ውሣኔ ለዚህ ጉዲይ ተዘማጅነት የለውም። በዚህ ጉዲይ ሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች የተለያዩ ክልል ኗሪ በመሆናቸው ጉዲዩ የፋዳራል ነው የፋዳራል የሆነን ጉዲይ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በይግባኝ ተቀብል ለማስተናገድ የሚከለክለው ሕግ የለም ስለሆነም ከጉዲዩ ጋር ተገቢነት የላለውን የሰበር ውሣኔ ጠቅሶ የሰጠው ዲኝነት መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ ይታረምልኝ የሚል ነው።
በዚህ የሰበር ቅሬታ መነሻ መልስ ሰጭ ቀርቦ በሥር ፍ/ቤቶች አቅርቦት የነበረውን ክርክር በማጠናከር ውሣኔው ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ ባጭሩ የተገለፀው ሲሆን እኛም ከይግባኝ ስልጣን ጋር በተያያዘ የተነሣውን የሕግ ክርክር ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
ለክርክሩ መነሻ የሆነው ጉዲይ ከአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 5 አኳያ የፋዳራል ጉዲይ ስለመሆኑ በግራ ቀኙ መካከል የተካደ ነጥብ አይደለም።
አከራካሪ የሆነው ጉዲይ የአላባ ልዩ ወረዲ ከፍተኛ ፍ/ቤት በውክልና ሥልጣኑ ተመልክቶ በሰጠው ውሣኔ ላይ ላቀርብ የሚገባውን የይግባኝ ክርክር ተቀብል የማስተናገድ ሥልጣን ያለው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ነው ወይስ የፋዳራል ከፍተኛው ፍ/ቤት? የሚለውን ጥያቄ አስመልክቶ በኢት/ያ ፋዳራላዊ ዱሞክራሲያዊ ራፏብሉክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 8ዐ፤ 78/2/ እና አንቀጽ 78/2/ ተከትል ከወጣው አዋጅ ቁጥር 322/95 ጋር በማጣቀስ ላሰጥ የሚገባውን የሕግ ትርጓሜ ላይ ያተኮረ ነው።
በሕገ- መንግሥቱ አንቀጽ 78/2/ እንደተደነገገው ክርክር የተነሣበትን ክልል ጨምሮ በአምስቱም ክልልች የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ስለመደራጀቱ በአዋጅ ቁጥር 322/95 ተደንግጓል።
በዚሁ አዋጅ መሰረት የተደረገው አደረጃጀት በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ብቻ የተወሰነ እንጂ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትን ጨምሮ ያደራጀ ባለመሆኑ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 78/2/ ሁለተኛ ክፍል ላይ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በክልልች እንዱደራጅ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ካልተወሰነ ለክልል ፍ/ቤቶች የተሰጠው የውክልና ሥልጣን እንደፀና የሚዘልቅ መሆኑ በመደንገጉ፣ በሕገ- መንግሥቱ አንቀጽ 8ዐ/4/ እንደተመለከተው የእነዚህ ክልልች የከፍተኛ ፍ/ቤቶች በፋዳራል ጉዲይ እንደ ፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሆነው በዲኝነት የማየት የውክልና ሥልጣናቸው የተነሣ አይደለም ሕገ መንግሥታዊ መሰረት ያለው ነው።
ከዚህ አንፃር በአንድ በኩል በእነዚህ ክልልች የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የተደራጀ መሆኑን ጠቅለል ባለ መልኩ ብቻ በአዋጅ ቁጥር 322/95 የተደነገገ በመሆኑ የተነሣ፤ በልላ በኩል ከላይ እንደተገለፀው የክልል ከፍተኛ ፍ/ቤቶች በፋዳራል ጉዲይ ላይ የተሰጣቸው ሕገ መንግሥታዊ የውክልና ሥልጣን እንደፀና ያለ ለመሆኑና በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 8ዐ/5/ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ጉዲዩን በውክልና የማየት ሥልጣን ያለው መሆኑ፣ እንደ አሁኑ ባለው ጉዲይ የክልለ ከፍተኛ ፍ/ቤት በውክልና ሥልጣኑ ተመልክቶ ውሣኔ የሰጠበትን ጉዲይ ተቀብል ለማስተናገድ ሥልጣን ያለው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ወይስ የፋዳራል ከፍተኛው ፍ/ቤት ነው? የሚለውን ጥያቄ ያስነሣል።
በእነዚህ ክልልች የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ብቻ ተለይቶ በአዋጅ ቁጥር 322/95 የተደራጀ እንደመሆኑ መጠን የዚህ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሥልጣን ወሰን በይግባኝ ተመልክቶ የመወሰንን ሁለ የሚጨምር ስለመሆኑና አለመሆኑ በሕጉ በግልጽ ሉሰፍር ይገባ እንደነበረ የክርክሩ ይዘት ያስረዲል።
ይሁን እንጂ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በፋዳራል ጉዲይ ላይ ያለው የውክልና ሥልጣን ጠቅለል ባለመንገድ በሕገ - መንግሥቱ አንቀጽ 8ዐ/2/ ላይ ይቀመጥ እንጂ በሕገ- መንግሥቱ አንቀጽ 8ዐ/2/ እና 8ዐ/5/ እንደቅደም ተከተለ በመጀመሪያ ደረጃ በሚነሳ የክርክር ጉዲይ እንደ ፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በይግባኝ ደረጃ ባለክርክር ደግሞ እንደ ፋዳራል ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍ/ቤት ሆኖ መመለከት እንደሚችል ዘርዘር ባለ ሁኔታ ያለው የውክልና ሥልጣን አይነት ተለይቶ ተቀምጧል።
በመሆኑም የክልል ከፍተኛ ፍ/ቤት በፋዳራል ጉዲይ በሕገ- መንግሥቱ አንቀጽ 8ዐ/2/ የተሰጣቸው የውክልና ሥልጣን አሁንም ያልተነካና በዚህ መንገድ ታይቶ በሚሰጥ ውሣኔ ላይ ይግባኙ ለማን ይቀርባል የሚለውን ጥያቄ የአዋጅ ቁጥር 322/95 ጥቅል አነጋገር ጥያቄ የሚያስነሣ ቢሆንም፤ እንዱሁም ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሰጠው የውክልና ሥልጣን በሁለት የክርክር እርከን ዓይነት ተለይቶ በሕገ- መንግሥቱ አንቀጽ 8ዐ/2/ እና 8ዐ/5/ በግልጽ የተሰጠ እስከሆነ ድረስ በአዋጅ ቁጥር 322/95 የተደራጀው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሥልጣን የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤቶች በሕገ- መንግሥቱ አንቀጽ 8ዐ/2/ መሰረት በመጀመሪያ ደረጃ የሚቀርቡትን የፋዳራል ጉዲይ ክርክሮችን ተቀብለው እንዱያስተናግደ ተሰጥቷቸው የነበረውን ሥልጣን የወሰደ፤ የተካ እንጂ ለክልል ጠቅላይ ፍ/ቤቶች በሕገ - መንግሥቱ አንቀጽ 8ዐ/5/ መሰረት በይግባኝ ያላቸውን ሥልጣን ሁለ ያስቀረ አይደለም ብል ለመተርጎም የሚያበቁ በቂ መነሻዎች ናቸው።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በክልልች የተደራጀ መሆኑ በአዋጁ በግልጽ እስከተደነገገ ድረስ በይግባኝ ደረጃ ያለውን ሥልጣን ሁለ የሚጨምር ነው እንዲይባል ከአንድ የፋዳራል ጉዲይ የሚመነጭን የመጀመሪያ ደረጃ ክርክር በክልለ ከፍተኛ ፍ/ቤት እንዱታይ አድርጎ የይግባኙን ጉዲይ ለማከራከር በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 8ዐ/5/ መሰረት የውክልና ሥልጣን የተሰጠው መሆኑ እየታወቀ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤትን ወደ ጎን ትቶ ወይም አስቀርቶ ይግባኙ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ላቀርብ ይገባል የሚለው መደምደሚያ ትርጉም አልባ ከመሆኑም በላይ የሕጎችን ዐውደ ንባብ ትርጓሜ ያልተከተለ፤ አዋጁ ውጤት እንዱኖረውና በአዎንታዊ መንገድ ታይቶ ሥራ ላይ እንዱውል ለማድረግ የሚያስችል የአተረጓጎም መንገድ ሆኖ አይገኝም።
በዚህ ሁለ ምክንያት የአላባ ልዩ ወረዲ ፍ/ቤት በተሰጠው የውክልና ሥልጣን መሰረት ተመልክቶ ውሣኔ በሰጠበት የፋዳራል ጉዲይ ላይ የአሁን አመልካች ቅሬታ ካለው የይግባኝ አቤቱታውን ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ከሚያቀርብ በቀር የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በይግባኝ ተመልክቶ ለማየት የሚያስችለው ሥልጣን የለውም ሲል የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በይ/መ/ቁ.
46679 በዐ4/5/2ዐዐ2 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አላገኘነውም።
ው ሣ ኔ 1/ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በ
በዐ4/5.2ዐዐ2 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
2/ የሰበር አመልካች የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ መዝገቡ ዘግቷል።
No topics extracted.