No summary available.
ጥቅምት 04 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- ወ/ሮ ዘነበች ተመስገን - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ - ነ/ፈጅ መሰረት አበራ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የቤት ይለቀቅልኝ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ አመልካች በአሁኑ ተጠሪ ላይ በፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ ከቀኛዝማች ተመስገን ዲልኬሮ መስከረም 20 ቀን 1960 ዓ.ም በተደረገላቸው የስጦታ ውል በወረዲ ሶስት ቀበላ 47 ውስጥ የሚገኝ ቁጥሩ 790 የሆነ ቤት ተሰጥቷቸው ሥጦታው ፀድቆና ቤቱ ያላግባብ የተወሰደ መሆኑ ተረጋግጦ በስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ሕዲር 20 ቀን 1970 ዓ.ም በተጻፈ ደብዲቤ እንዱመለስላቸው የታዘዘ ቢሆንም ተጠሪ ቤቱ ሉመለስላቸው ያልቻለ መሆኑን ገልፀው ቤቱ እንዱመለስላቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ ተጠሪም ለክሱ በሰጠው መልስ አመልካች ክስ ለመመስረት የሚያስችላቸው መብት ወይም ጥቅም የላላቸው መሆኑን ቤቱን ከሀያ አመት በላይ በእጁ አድርጎ የሚያስተዲድረው እና ግብርም የከፈለበት በመሆኑ ክሱ በይርጋ እንደሚቋረጥ ጉዲዩ በፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ እየታየ መሆኑን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት የተከራከረ ሲሆን በፍሬ ነገር ደረጃም የአመልካች ክስ በማስረጃ ያልተደገፈ መሆኑን ገልጾ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤትም ጉዲዩን የማየት ሥልጣን የፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ መሆኑን ገልጾ መዝገቡን ቢዘጋውም የአሁኗ አመልካች በዚሁ ብይን ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ጉዲዩን የማየት የሥረ ነገር ሥልጣን ያለው መደበኛ ፍርድ ቤት ነው በሚል ምክንያት ቀደም ብል የተሰጠው የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሽሮ ጉዲዩ ለፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ተመልሶለታል። ጉዲዩ የተመለሰለት የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ጉዲዩን እንደገና መርምሮ የአሁኑ ተጠሪ ያቀረባቸውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ነጥቦችን ውድቅ አድርጎ በፍሬ ነገር ደረጃም የአመልካችን ክርክር ተቀብል ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት ተጠሪ ለአመልካች እንዱያስረክብ ሲል ወስኗል። በዚሁ ውሳኔ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ አመልካች ጉዲዩን ለፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ አቅርበው ጉዲዩ እየታየ ባለበት ሁኔታና ውጤቱ ሳይታወቅ በፍርድ ቤት ክስ መመስረታቸው ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 8 ድንጋጌ አኳያ ተገቢነት የለውም በሚል ምክንያት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሙለ በሙለ በመሻር ወስኗል። ከዚህ በኋላም አመልካች ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ነሐሴ 15 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ሦስት ገፅ የሰበር አቤቱታ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። የአቤቱታቸው መሰረታዊ ይዘትም ጉዲዩ በመደበኛ ፍርድ ቤት ሥልጣን ሥር የሚወድቅ መሆኑ ተረጋግጦ ከተወሰነ በኋላ ፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ እንደመደበኛ ፍርድ ቤት የማይቆጠር ሁኖ እያለ የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁጥር 8 ተጠቅሶ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ መሻሩ ስነ ስርአቱን የጠበቀ ስላልሆነ ሉለወጥ ይገባል በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል በመታዘዙ የተጠሪ ነገረ ፈጅ ቀርበው ጥር 13 ቀን 2002 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ የፁሐፍ መልሳቸውን ያቀረቡ ሲሆን አመልካች በበኩላቸው ጥር 14 ቀን 2002 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
አመልካች አከራካሪው ቤት ይመለስልኝ ጥያቄን በመደበኛ ፍርድ ቤት ክስ የመሰረቱበት ሲሆን ከዚሁ ጎን ለጎን ደግሞ ለፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ አቤቱታቸውን አቅርበው ጉዲዩ እየታየ መሆኑን አልካደም፤ ተረጋግጧል። አመልካች አጥብቀው የሚከራከሩት አቤቱታቸው በፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ቢቀርብም ይኸው አካል እንደ መደበኛ ፍርድ ቤት ላታይ አይገባውም ባሁኑ ጊዜም ጉዲዩን የማየት ሥልጣን የለኝም በማለት አቤቱታቸውን ያልተቀበለው መሆኑን በመግለፅ ነው።
በመሰረቱ አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት ከአዋጅ ውጪ ተወስድብኛል የሚል ወገን ጉዲዩን ማቅረብ ያለበት ለፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 110/87 እና ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 193/92 እና 572/2000 ያሳያለ። ይህ አካል ጉዲዩ ሲቀርብለት በሕጉ አግባብ የሚሰጠው ውሳኔ እንደ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሉቆጠር የሚችልና ለአፈፃፀምም የሚቀርብ ነው። እንዱህ ከሆነ ይህ አካል በሕግ ተለይቶ በተሰጠው ጉዲይ ላይ የዲኝነት ሥልጣን ያለው አካል ነው። አዋጅ ቁጥር 110/87 ስለኤጀንሲው ስልጣንና ተግባሩ በአንቀፅ 4 ስር በግልፅ ያስቀመጠ ሲሆን የዚሁ አንቀፅ ንዐስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌ ፉደል ‛ለ“ ከአዋጁ ውጪ የተወሰደ ንብረቶችን በተመለከተ የቀረቡለትን የመብት ጥያቄዎችና ሁኔታዎች በአዋጁ መሰረት ይመረምራል፣ ለምርመራው አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎችን ከማናቸውም የመንግስት ወይም የግል መስሪያ ቤት፣ ድርጅት ወይም ተቋም እንዱሁም ከማንኛውም ግለሰብ ለማግኘት የምስክር ቃል ለመቀበል ወይም የፅሁፍ ማስረጃን እንዱያቀርብለት ለማዘዝ እንደሚችል የተገለፀ ሲሆን በዚሁ ንኡስ ድንጋጌ ፉደል ‛ሐ“ ስር ደግሞ ከአዋጁ ውጭ የተወሰደን ንብረት ባለቤትነት በተመለከተ በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ መረጃዎችን እያጣራ ተገቢውን ውሳኔ ይሰጣል፣ ውሳኔው እንዱፈፀም አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዲል በሚል ተደንግጓል። ላላው በአዋጁ አንቀፅ 9 ስር ከአዋጁ የማይቃረን ህግ ወይም መመሪያ ተፈጻሚነት እንዲለው በሚያስገነዝብ መልኩ ተደንግጓል። ከዚህ ሁለ መረዲት የሚቻለው ይኸው አካል ጉዲዩን ሲመለከት የተለያዩ የማስረጃ አቀራረብና አቀባበል ሥርዓቶችን ሉከተል የሚችል መሆኑና አግባብነት ባላቸው የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች ሉመራ የሚችል መሆኑን ነው። እንዱህ ከሆነ ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን ያለው የየትኛው አካል ነው የሚል ክርክር ቀርቦ ባለበት ሁኔታ አንድ ጉዲይ ለሁለት የዲኝነት አካላት የሚቀርብበት አግባብ የለም።
አንድ ጉዲይ በተመሳሳይ ጊዜ በሁለት የዲኝነት ሥልጣን ባላቸው አካላት መቅረብ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ድንጋጌ አላማን የሚፃረር ነው። በመሆኑም የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩ በፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ቀርቦ ሳያልቅ በፍርድ ቤት መቀጠለ ያላግባብ ነው በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ መሻሩ በአግባቡ ነው። የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ጉዲዩ በፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ታይቶ ተገቢው ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ አመልካች ለሚመለከተው ፍርድ ቤት በሕጉ አግባብ ክርክራቸውን ከመቀጠል የማይገድብ መሆኑን የተገነዘብን ሲሆን አመልካች በአሁኑ ወቅት የፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ አቤቱታቸውን ያልተቀበለው መሆኑን በዚህ የሰበር ክርክር ደረጃ የገለፁ ስለሆነ ይህንኑ መሰረት በማድረግ ለስር ፍርድ ቤት ክርክራቸውን ከመቀጠል በስተቀር የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል ለማለት የሚያስችል ሁኖ አላገኘነውም።
በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
No topics extracted.