No summary available.
መስከረም 24 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጏስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የሉዝ ውልን መሰረት አድርጏ ለአንድ ሰው የተሰጠ ቦታ ለላላ ሰው ሲሰጥ ጉዲዩን አይቶ የመወሰን ሥልጣን ያለው አካል የትኛው ነው? የሚለውን የሕግ ክርክር የሚመለከት ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን ከሳሽ የነበረው የአሁኑ ተጠሪ ማህበር ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- በአዱስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበላ 01/19 በተለምድ ባንቢስ አጠገብ ስፊቱ 1194 ካ.ሜ የሆነ ቦታ ላይ ሕንፃ ለመስራት ቦታውን ከአሁኑ 2ኛ አመልካች ጋር የሉዝ ውል በመፈረም ቦታውን በመረከብ ስራ ከጀመረ በሁዋላ 1ኛ ተጠሪ ከመስከረም 25 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ ምንም ዓይነት የቦታ ጥያቄ እንዲያስተናግድ ታግድ ሳለ፣አስፈላጊውን መረጃዎች ሳይቀርቡለት ከተጠሪ መሬት ጋር አጏራባች ለሆኑት የሆቴል ዱልፕል ባለቤት ለሆኑት ለአቶ ዲመና ሲማ ቦታውን እንዱወስደ፣ተጠሪ ቦታውን እንዱያስረክብ መወሰኑን፣አመልካቾች በሕግ ከተሰጣቸው ሥልጣን ውጪ ተጠሪ በሉዝ ውል መሰረት የወሰደውን የልማት ቦታ በመቀማት ለላላ ግለሰብ ለመስጠት የወሰኑትን እንዱያርሙ ቢጠየቁ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን በመግለጽ ከዚህ አድርጏታቸው እንዱቆጠቡ ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካቾችም ለክሱ በሰጡት መከላከያ መልስም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ነጥቦችንና የፍሬ ነገር ክርክሮችን በመዘርዘር ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል። በሚል ተከራክረዋል። የስር ፍርድ ቤትም በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት የቀረቡትን የአመልካቾችን መከራከሪያ ነጥቦችን በመመርመር ጉዲዩ በፋዳራል ፍርድ ቤቶች ስልጣን ስር የሚወድቅ አይደለም በማለት መዝገቡን ዘግቶታል።
ከዚህም በኋላ የአሁኑ ተጠሪ ይግባኙን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቅሬታውን አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ጉዲዩን የማየት ሥረ ነገር ስልጣን የአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ናቸው በማለት ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነው።
የአመልካቾች ነገረ ፈጅ ሚያዝያ 01 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት አምስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ጉዲዩ በፋዳራል ፍርድ ቤቶችም ሆነ በአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ሥልጣን ስር የማይወድቅ የአስተዲደር አካለ ሥልጣን ነው በማለት መከራከራቸውንና የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሳኔ እንዱታረም ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ጉዲዩ የአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ስረ ነገር ሥልጣን ስር የሚወድቅ ነው ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጏ ተጠሪ መስከረም 04 ቀን 2003 ዓ.ም በጠበቃቸው አማካኝነት በተፃፈ ሦስት ገጽ ማመልከቻ የጽሁፍ መልሱን አቅርቧል።
የአመልካቾች ነ/ፈጅም መስከረም 14 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመልጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀረብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ በአዱስ አበባ ከተማ፣በቀድሞው አጠራር በወረዲ 15 ቀበላ 34 ክልል ውስጥ በተለምድ አጠራር ባምቢስ አጠገብ ስፊቱ 1194 ካ.ሜትር ቦታ ለማልማት በቅድሚያ ሰኔ 28 ቀን 1996 ዓ.ም ከአዱስ አበባ አስተዲደር የመሬት አስተዲዲር ባለስልጣን ጋር በተፈረመ ጊዜያዊ መተማመኛ ውል ቀጥልም መስከረም 25 ቀን 1998 ዓ.ም ከአዱስ አበባ ከተማ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዲደር ጽ/ቤት ጋር በተፈረመ የከተማ ቦታ የሉዝ ውል አድርገው ቅድሚያ የሉዝ ክፍያ ተከፍል ካርታ እና የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቅት የተሰጣቸው ሁኖ እያለ በውለ መሰረት ግዳታቸውን አልተወጡም ወይም የውለ ጊዜ አብቅቷል ባልተባለበት ሁኔታ እንዱሁም ለመንግስት ልማት የሚፈለግ ስለመሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ መሬቱን አመልካቾች ከተጠሪ ነጥቀው ለሆቴል ዱሉኦፕል ባለቤት ግለሰብ ለመስጠት ደብዲቤ የፃፈላቸው መሆኑን ጠቅሰው የአመልካቾች እርምጃ ከሕግ ውጪ ነው በማለት ተጠሪ የሚከራከሩ መሆኑን፣አመልካቾች በበኩላቸው ይህ ለተጠሪ የተሰጠው የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የሉዝ ቦርደ ከተጠሪ ጋር የነበረው የሉዝ ውል እንዱቋረጥ በመወሰኑ መሰረዙን ገልፀው ጉዲዩ በፍርድ ቤት ሉዲኝ የማይችል መሆኑን ጠቅሰው የሚከራከሩ መሆኑን ነው።
እንዱሁም ተጠሪ ጉዲዩ የሉዝ ውል እንጂ የአስተዲደር ውል ባለመሆኑ መዲኘት ያለበት በፋዳራል ፍርድ ቤቶች ነው የሚለውን ክርክር፣አመልካቾች ደግሞ ጉዲዩ በፍርድ ቤት ይታያል ከተባለም መታየት ያለበት በፋዳራል ፍርድ ቤቶች ሳይሆን በአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ነው የሚል ክርክር በስር ፍርድ ቤት አቅርበው የነበሩ መሆኑንም ተመልክተናል።
በመሰረቱ ማንኛውም ሰው በፍርድ ሉወሰን የሚገባውን ጉዲይ ለፍርድ ቤት ወይም ለላላ በሕግ የዲኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 37/1/ ድንጋጌ በግልጽ የሚያሳየው ጉዲይ ነው። ከዚሁ የሕገ መንግስት ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለው ደግሞ ፍርድ ቤቶች አንድን ጉዲይ(አቤቱታ) ተቀብለው ውሳኔ መስጠት የሚችለት ዲኝነት የተጠየቀበት ጉዲይ በሕግ ለላላ አካል ያልተሰጠ ጉዲይ በሚሆንበት ጊዜ እንደሆነ መሆኑን ነው። በሕግ ተለይተው በአስተዲደራዊ ውሳኔ እንዱቋጩ በተባለ ጉዲዮች ላይ መደበኛ ፍርድ ቤት የመዲኘት የስረ ነገር ስልጣን ስለላለው በሕጉ መሰረት ለአንድ አስተዲደር አካል ቀርቦ አስተዲደራዊ ውሳኔ የተሰጠበትን ጉዲይ ወይም ለአስተዲደር መቅረብ የሚገባውን ጉዲይ ፍርድ ቤት ሉያስተናግደውም ሆነ አከራክሮ ውሳኔ ላሰጥበት አይችልም። ለአንዲንድ የመንግስት አካላት በተወሰኑ ጉዲዮች ላይ የመወሰን ስልጣን የሚሰጡት ሕጏች መጠበቅና መከበር ያለባቸው ሲሆን የዲኝነት አካል ስልጣንም በሕግ የተወሰነ ስለሆነ ሕግ የመተርጏም ስራው በሕጉ በተመለከተው አድማስ የሚመራ ይሆናል። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.4 ድንጋጌ የሚያሳየውም ፍርድ ቤቶች በልላ ሕግ በግልጽ በታገደ ጉዲዮች ላይ አከራክሮ የመወሰን ስልጣን የላላቸው መሆኑን ነው። በመሆኑም በአስተዲደራዊ ውሳኔ የመጨረሻ እልባት እንዱያገኙ በሕግ ተለይተው የተቀመጡ ጉዲዮችን ፍርድ ቤቶች የመዲኘት ስልጣን የላላቸው መሆኑ ሉስተዋል የሚገባው ጉዲይ ነው።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም የተጠሪ የዲኝነት ጥያቄ(ክርክር) መሰረት ያደረገው ከአመልካቾች ጋር ባደረጉት የሉዝ ውል የተሰጠውን መሬት ከሕግ ውጪ ተወስድ ለላላ ግለሰብ እንዱሰጥ መደረጉ ያላግባብ ነው የሚል ነው። በዚህ መልኩ የሚቀርበውን የዲኝነት ጥያቄ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር በሚሰጠው አስተዲደራዊ ውሳኔ የመጨረሻ እልባት የሚሰጥበት መሆኑን ወይም ጉዲዩ በመደበኛ ፍርድ ቤት ላታይ የማይገባው መሆኑን የሚደነግግ ሕግ አለ በሚል በአመልካቾች የሚቀርበው ክርክር መሰረት ያደረገው አዋጅ ቁጥር 272/1994 ነው። በዚህ አዋጅ የሉዝ ቦታ የሚሰጥበትና ውለ የሚቋረጥበት አግባብ ተዘርግቷል። የአዋጁ አንቀጽ 15፣16 እና 17 ድንጋጌዎች ሲታዩ የሉዝ ውል የሚቋረጥበትንና ካሳ የሚከፈልበትን አግባብ፣ጉዲዩን ሉመለከቱ የሚችለ ወገኖችንና የይግባኝ አቀራረብን ሥርዓት ደንግገው እናገኛለን።
በተያዘው ጉዲይ የሉዝ ውል እንዱቋረጥ ተደርጓል የሚባለው ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ነው በሚል ምክንያት በመሆኑ ለጉዲዩ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት ያላቸው የአዋጅ ቁጥር 272/94 ድንጋጌዎች አንቀጽ 15/1/ለ/ እና 16 ናቸው። የአንቀጽ 15/1/ለ/ ድንጋጌ የከተማ ቦታ የሉዝ ይዞታ ቦታው ለሕዝብ ጥቅም ተብል ለላላ ስራ ወይም አግልግልት እንዱውል ሲወሰን ሉቋረጥ እንደሚችል የተመለከተ ሲሆን በአንቀጽ 16/1/ደግሞ አግባብ ያለው አካል ለሕዝብ ጥቅም ይውላል ተብል በሚወስነው መሰረት ለሚመለከተው አካል የማስለቀቂያ ትእዛዝ ወይም ማስጠንቀቂያ በጹሐፍ በመስጠት የሚፈልገውን የከተማ ቦታ ማስለቀቅና መረከብ እንደሚችል አስቀምጧል። የአዋጅ አንቀጽ 17/1/ ድንጋጌ ሲታይም በአንቀጽ 16 መሰረት የማስለቀቅ ትእዛዝ የደረሰው ወይም ትእዛዝ በተሰጠበት ንብረት ላይ መብት ወይም ጥቅም አለኝ የሚል ወገን የካሣም ሆነ ማንኛውንም ለፍርድ ሉቀረብ የሚገባው ላላ አቤቱታ ከዝርዝር ምክንያቱ እና ማስረጃው ጋር ትእዛዙን ለሰጠው አካል የማቅረብ መብት እንዲለው ያስገነዝባል። በዚህ መልኩ ቀርቦ የታየ ጉዲይም በአንቀጹ ንኡስ ቁጥር ሁለት ስር የተመለከተው ተገቢ ዲኝነት የሚሰጥበት ሲሆን በውሳኔው የማይስማማ ሰው ለጉባኤው ይግባኙን ማቅረብ እንደሚችል በአንቀጽ 18/1/ ስር ተደንግጏ ያለ ከመሆኑም በላይ ይህ አካል የሚሰጠው ውሳኔ ካሣ አነሰኝ፣ ወይም ካሣ በዛብኝ ወይም ካሳ ተከለከልኩ በሚለ ክርክሮች ላይ ካልሆነ በስተቀር በሕግም ሆነ በፍሬ ነገሮች ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ስለመሆኑ የተጠቀሰው አንቀጽ ንኡስ ቁጥር ሦስት ድንጋጌ ያሳያል። ከዚህ ሁለ መገንዘብ የሚቻለው በሉዝ የተሰጠ ቦታን የሚመለከተው አካል ማስለቀቅ የሚችለውና ጉዲዩ ላይ ጉባኤው የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ እና በፍርድ ቤት ላቀርብ የማይገባው ቀድሞ የቦታ ማስለቀቁ እርምጃ የተወሰደው ለሕዝብ ጥቅም ተብል ሲረጋገጥ ስለመሆኑ ነው።
አዋጅ ቁጥር 272/94 አንቀጽ 2/7/ ስር ለህዝብ ጥቅም ትርጉም አስቀምጧል። በዚህም መሰረት የሕዝብ ጥቅም ማለት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ሕዝቦች በመሬት ላይ ያላቸውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና የከተማ ልማትን በቀጣይነት ለማጏልበት አግባብ ያለው አካል በመሪ ፔላን ወይም በልማት እቅድ የሕዝብ ጥቅም ብል የሚወስነው ነው በሚል ትርጓሜ የተቀመጠ ሲሆን አዋጅ ቁጥር 455/97ም ተመሳሳይ ይዘት ያለውን ትርጉም በአንቀጽ 2/5/ ስር ይዞ እናገኛለን። በተያዘው ጉዲይ አመልካቾች ጉዲዩ ከሕዝብ ጥቅም ጋር የተገናኘ በሚል ያቀረቡት ክርክር በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተቀባይነት ያላገኘው መሬቱ ላሰጥ የታሰበው ሆቴል ለሕዝብ ጥቅም የሚለውን ትርጉም በሚያሟላ መልኩ የሚታወቅ ስለመሆኑ አላስረደም በሚል ነው። ይህ ግልጽ የማስረጃ ጉዲይ መሆኑን የምንገነዘበው ሲሆን ፍሬ ነገርን የማጣራትና የማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያለው ይግባኝ ሰሚው ችልት የአመልካቾች ክርክር በማስረጃ የተደገፈ አለመሆኑን አረጋግጧል። ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ደግሞ በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ/ እ 25/1988 አንቀጽ 10 የተሰጠው ስልጣን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሲፈፀም ማረም በመሆኑ የአመልካቾች ያቀረቡት ክርክርና ማስረጃ አሳማኝ ነው? ወይስ አይለም? የሚለውን ጉዲይ የሚመለከተው ሆኖ አላገኘውም። በተለይ አመልካቾች የተጠሪ ቦታ የሚወሰድ መሆኑን የገለፁት ተጠሪ በሉዝ በወሰደት ቦታ ላይ የፈለጉትን ግንባታ ቢያካሂደ በስተጀርባ ያለውን የአቶ ዲመና ሲማ ንብረት የሆነውን ዱሉኦፕል ሆቴል ስለሚጋረድ በሆቴለ ሥራ ላይ እንቅፊት ይፈጥራል በሚል ምክንያት ስለመሆኑ ይግባኝ ሰሚ ችልት በፍሬ ነገር ደረጃ ያረጋገጠው ጉዲይ ሆኖ አግኝተናል።
እንዱህ ከሆነ ቦታው ላይ የተሻለ ልማት የሚካሄድ መሆኑን፣በከተማው መዋቅራዊ ፔላን ቦታ ላይ የሚካሄደውን ግንባታ ለሆቴለ ለመስጠት ማስፈለጉን አመልካቾች ያላረጋገጡት ጉዲይ ሲሆን በሉዝ አዋጅና ደንብ መሰረት የገባውን ውል ባለማክበሩ ወይም መሬቱ መንግስት ለሚያካሄደው የልማት ሥራ አስፈላጊ ሆኖ ካልተገኘ በቀር መሬት በሉዝ የተከራየ ሰው የሉዝ ዘመኑ ከማለቁ በፉት መሬቱ የማይወሰድበት ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 455/97 አንቀጽ 3/2/ ከመደንገጉ ጋር ተዲምሮ ሲታይ የአመልካቾች ክርክር ተቀባይነት የሚያገኝ ሁኖ አልተገኘም።
ከላይ እንደተጠቀሰው ጉዲዩ በፍርድ ቤት የሚታይ ነው ከተባለ ጉዲዩን የማየት የሥረ ነገር ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች የትኞቹ ናቸው የሚለው ነጥብም ምላሽ የሚያስፈልገው ሁኖ አግኝተናል። ይህንኑ ነጥብም ምላሽ የሚያስፈልገው ሆኖ አግኝተናል። ይህንኑ ነጥብ ለመመለስ የተጠሪ የዲኝነት ጥያቄ ይዘቱ ምን እንደሆነ ማየቱ ጠቃሚ ይሆናል። ተጠሪ የአመልካቾችን እርምጃ ሕገ ወጥ ነው በማለት የሚከራከሩት ከሉዝ አዋጁና ደንብ ውጪ የተፈጸመ ነው በማለት ነው።
ተጠሪ ከአመልካቾች ጋር የሉዝ ውል ያላቸው መሆኑና ተያያዥ ማስረጃዎችም ያላቸው መሆኑን ጠቅሰዋል። አመልካቾች ደግሞ የተጠሪ የሉዝ ውል እንዱቋረጥ ተደርጏ ካርታና የይዞታ ምስክር ወረቀት መሰረዙን ገልጸው የሚከራከሩ መሆኑን የክርክር ሂደቱ ያሳያል። በመሆኑም ሉነሳ የሚችለው ጥያቄ ተጠሪ ከአመልካቾች ያገኙት የሉዝ ቦታ ምስክር ወረቀት የተሰረዘው በአግባቡ ውለን መሰረት ባደረገ መልኩ ነው ወይም ከውለና አግባብነት ካላቸው ሕጏች ውጪ ነው?
የሚለው ነው።
የከተማው አስተዲደር ካርታ የመስጠት፣የመሰረዝ፣የማሻሻል፣የማምከን፣ የማገድ እና አሻሽል የመስጠት ሙለ ስልጣን ያለው ቢሆንም የሉዝ ውልን መሰረት አድርጏ የተሰጠውን ካርታና የምስክር ወረቀት መልሶ ከሕግ ውጪ ሰርዞ ሲገኝ በእርምጃው ላይ ቅሬታ ያለው ወገን ጉዲዩን ለፍርድ ቤት እንዱያቀርብ የሚከለከልበት ስርዓት የላለ ስለመሆኑ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር አስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አግልግልት አካላት ስልጣንና ኃላፉነትን ለመደንገግ የወጣው፣ክርክሩ ሲጀመርም ሆነ ከተጀመረ በኋላ በስራ ላይ ያለው ሕግ ያሳያል። ይልቁንም የተሻሻለው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41/1/ሀ/ እና/መ/ ድንጋጌዎች ሲታዩ የተያዘውን ጉዲይ አይነት የአዱስ አበባ ከተማ ነክ ፍርድ ቤት ተቀብልና አከራክሮ ለመወሰን የስረ ነገር ሥልጣን ያለው ስለመሆኑ ያስገነዝባለ። አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት በአማራጭ ባቀረቡት ክርክርም ይህንኑ ደግፈው ሲከራከሩ የነበሩ መሆኑ ግልጽ ነው። ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልቱ ቀርቦ ላታይ ይገባል ሲባል የተያዘው ጭብጥ ሰበር ችልቱ ከሰጠው አስገጃጅ የሕግ ትርጉም አንፃር ለማየት ተብል ሲሆን ይህ ሰበር ችልት አስገዲጅ የሆነ የሕግ ትርጉም ሰጥቶባቸዋል ተብለው ሉጠቀሱ የሚችለት መዛግብት የመ/ እና በመ/ በተያዘው ጉዲይ ካለው ፍሬ ነገር እና የሕግ ክርክር ሙለ በሙለ ግንኙነት አላቸው ሉባለ የሚችለ አይደለም። ምክንያቱም የተጠሪ ክስ መሰረቱ የሉዝ ውል ሆኖ ውለ ተጥሷል በሚል ዲኝነት የጠየቁ ናቸውና። በመሆኑም በዚህ ረገድ የቀረበው የአመልካቾች ክርክር ተቀባይነት ያለው ሁኖ አልተገኘም። ስለሆነም የተጠሪ ጥያቄ የክፍለ ከተማው አስተዲደር ከሕግ ውጪ በሉዝ የተወሰደ ቦታ ለመውሰድ ካርታና የምስክር ወረቀት በመሰረዝ ሕገ ወጥ እርምጃ ወስዶል በማለት በሉዝ ውል ያገኙት የንብረት መብታቸው (የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 40/6/ ይመልከቷል) በፍርድ እንዱጠበቅላቸው የሚጠይቅ በመሆኑ በፍርድ ቤት ሉያስተናግድ የሚገባው እና ውሳኔ የሚሰጥበት ጉዲይ በመሆኑ እና መታየት ያለበትም በአዱስ አበባ ከተማ ነክ ጉዲዮች ፍርድ ቤቶች በመሆኑ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የደረሰበት ድምዲሜም ከአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41/1/ሀ/ እና/መ/ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ አንፃር ህጋዊ ሁኖ አግኝተናል። በዚህ ምክንያት በውሳኔው ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ባለመኖሩ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ጥር 04 ቀን 2002 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ት እ ዛ ዝ ይህ ችልት ሐምል 14 ቀን 2002 ዓ.ም ሰጥቶት የነበረው እግድ ተነስቷል።
ለሚመለከታቸው አካላት ይፃፍ።
No topics extracted.