No summary available.
ሐምል 29 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ተጠሪዎች፡-
የክርክሩን መነሻ በብድር የተሰጠን ገንዘብ ለማስመለስ የቀረበ ክስ ሆኖ በዚህ ሰበር ችልት እንዱወሰን ተይዞ የቀረበው ጭብጥ ክሱ በይርጋ ቀሪ የሆነ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነው።
ክሱ /ክርክሩ/ የጀመረው በምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን ከሣሽ የነበረው የአሁኑ አመልካች ነው። በክሱ እንደተመለከተው 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ከባንኩ ገንዘብ በብድር የወሰደ ናቸዉ። ላልች ተጠሪዎች ደግሞ ለብደሩ አመላለስ የዋስትና ግዳታ ገብተዋል። ብድሩ የተወሰደው በ24-7-88 ዓ.ም በተፈረመው ውል እንደሆነ መመለስ የነበረበት በ24-7-89 ዓ.ም መሆኑን ተበዲሪዎች ገንዘቡን ለመመለስ ባለመቻላቸው አመልካች በዋስትና የያዘው የ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ቤት በአዋጅ ቁ. 97/90 መሰረት አስገምቶ ሐራጅ ማወጣቱን ፣ የሐራጅ ማስታወቂያ ከማውጣቱ በፉትም በ19-5-92 ዓ.ም ለተጠሪዎች ማስጠንቀቂያ ጽፍ የነበረ መሆኑን በወጣው የሐራጅ ማስታወቂያ መሰረት ቤቱን የሚገዛ ሰው ባለመገኘቱ አመልካች በቀረበው ግምት ብር 52,525.10 ቤቱን መረከቡን በመጨረሻም አመልካች በቀሪ የሚፈለገውን ገንዘብ ይከፈለው ዘንድ በ21-2-2001 ዓ.ም ክስ መመስረቱን ክሱን የሰማው ፍ/ቤት በሰጠው ብይን ላይ በዝርዝር ተመልክቶአል።
ተጠሪዎች በበኩላቸው ለክሱ በሰጡት መልስ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኖአል የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና ላልች የመከራከሪያ ነጥቦች አቅርበዋል። ፍ/ቤቱም ወደላልች የመከራከሪያ ነጥቦች ከማለፈ በፉት ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ አድርጏአል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤትም ብይኑ ጉድለት የለበትም ብልአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች ግንቦት 1ዐ ቀን 2002 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። በመቀጠልም በጭብጥነት የተያዘውን ነጥብ ግራ ቀኝ ወገኖች ካሰሙት ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከህጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እንደምንመለከተው ተጠሪዎች የብድሩን ገንዘብ በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ባለመክፈላቸው አመልካች በ92 ዓ.ም ማስጠንቀቂያ ሰጥቶአቸዋል። ሆኖም በተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ መሰረትም ገንዘቡን ሉከፍለ ባለመቻላቸው በዋስትና በያዘው ቤት ላይ በአዋጅ ቁ.
97/90 መሰረት የሐራጅ ማስታወቂያ ያወጣ ቢሆንም ቤቱን የሚገዛ ሰው ባለመገኘቱ ለጉዲዩ አፈጻጸም አግባብ ባለው የሥነ -ሥርዓት ህግ መሰረት ቤቱን በግምቱ ልክ ተረክቦአል። አመልካች ቤቱን የተረከበው ሚያዝያ 20 ቀን 96 ዓ.ም ስለመሆኑም በተጠሪዎች መልስ ጭምር ተረጋጋጦአል። አመልካች ቤቱን ቢረከብም በዚህ ረገድ ተከፈለ ልባል የሚችለው ዕዲ በተጠሪዎች ላይ የሚፈለገውን አጠቃላይ ዕዲ የሚሸፍንለት ሆኖ ባለማግኘቱ ቀሪው ዕዲ እንዱከፈለው በመጠየቁ ክስ መስርቶአል። አመልካች ቤቱን በግምቱ ልክ ተረክቦ ቀሪ ዕዲ የሚፈልግ መሆኑን ባረጋገጠበት ጊዜ እና ክስ በመሰረተበት ቀን /ጊዜ/ መካከል ያለው ጊዜ ሲታሰብ አስር ዓመት አልሞላም። የስር ፍ/ቤቶችም ይህንኑ ስለመገንዘባቸው ከተሰጠው ብይን ይዘት ለመገንዘብ ችለናል። ይህም ሆኖ የይርጋውን ጊዜ ያሰለት ብድሩ ከተወሰደበት ቀን ጀምሮ በመሆኑ የአስር ዓመትን የይርጋ ጊዜ መሰረት በማድረግ ክስ የማቅረቢያ ጊዜው አልፍአል እሚል መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል።
በበኩላችን እንደምናየው አመልካች በዋስትና የያዘውን ቤት በአዋጅ ቁ. 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ሽጦ ለብድሩ መክፈያ ከማድረጉ በፉት ያልተከፈለ ቀሪ የብድር ገንዘብ የሚኖር ስለመሆኑ እርግጠኛ መሆን ይችል ነበር ለማለት አይቻልም። በመጀመሪያ ማድረግ የነበረበትም በመያዣነት የያዘውን ቤት ሽጦ ገንዘቡን መሰብሰብ እንደመሆኑ አመልካቹ ይህንኑ ፈጽሞአል።
ተጠሪዎችን ቀሪ የብድር ገንዘብ ይክፈለኝ በማለት ሉከስ የሚችለው በእርግጥም ያልተከፈለ ቀሪ ዕዲ መኖሩን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከያዘ በኋላ ነው። የይርጋ ቀን መቆጠር የሚጀምረው ግዳታውን ለመጠየቅ ተገቢ ከሆነው ወይም በውለ የሚሰጠው መብት ከተሰራበት ቀን ጀምሮ እንደሆነ በፍ/ብ/ሕግ/ቁ. 1846 ተደንግጏአል።
No topics extracted.
አመልካች ለብድር ገንዘቡ አመላለስ ዋስትና እንዱሆን የያዘውን ቤት በግምቱ ልክ ከተረከበ በኋላ ቀሪ ዕዲ እንደሚፈልግ እርግጠኛ የሆነው ከሚያዝያ 20 ቀን 96 ዓ.ም በኋላ ነው። በመሆኑም በተጠሪዎች ላይ ክስ መመስረት የሚችለው ከዚህ በኋላ ነው። የይርጋ ጊዜው መቆጠር የሚጀምረውም ከሚያዝያ 20 ቀን 96 ዓ.ም ጀምሮ ስለሆነ ክሱ እስከቀረበበት ጊዜ ድረስ ያለው ሲታሰብ ጊዜው አላለፈበትም። የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ ከዚህ አንጻር ሲታይም በህጉ አተረጓጏም ረገድ መሰረታዊ ስህተት ያለበት ነው። ስለዚህም ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 04301 መስከረም 21 ቀን 2002 የሰጠው ብይን እና የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. 77420 መጋቢት 7 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
አመልካች ያቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ አልሆነም ብለናል። በመሆኑም የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ክርክሩን በተጀመረው መዝገብ እንዱቀጥል በማድረግ በክሱ ስረ ነገር ላይ ግራ ቀኝ ወገኖች የሚያቀርቡለትን ክርክር እና ማስረጃ ከሰማ በኋላ ተገቢውን ይወስን ዘንድ ጉዲዩ ይመለስለት በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341/1/ መሰረት ወስነናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።