No summary available.
መስከረም 25 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አፍሪካ ኢንሹራንስ /አ.ማ/ ነ/ፈጅ ሜሮን ሰለሞን ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ጣይቱ አመዳ አልቀረቡም መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር። መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የሰሜን ወል ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው። የክርክሩ መነሻ በንብረት ላይ የሚደርስ ጉዲት ለመሸፈን የተደረገ የመድን ውል ነው። ተጠሪ ለዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረበው የክስ ማመልከቻ የሰላዲ ቁጥሩ 3-27956 አ.አ የሆነ ኤፍ ኤስ አር አይሱዚ መኪና እንዲላቸውና መኪናው በአደጋ ምክንያት ጉዲት በደረሰበት ተከሳሹ /አመልካች/ እስከ ብር 300,000 /ሶስት መቶ ሺህ ብር/ የመድን ሽፊን ለመስጠት በመስማማቱ ተጠሪ የአረቦን ክፍያ ሲከፍለ የቆዩ መሆኑን የተጠሪ መኪና ህዲር 10 ቀን 1999ዓ.ም በመውደቁ ተጠሪ አመልካች መኪናውን እንዱያስጠግን ወዱያውኑ ያሳወቁ መሆኑን ሆኖም አመልካች ሙለ በሙለ ሉተካ የሚገባውን የመኪናውን አካል በአዱስ ለመተካት ባለመፈለጉና መኪናው ሳይጠገን 198 ቀናት የቆየ በመሆኑ የመኪናውን አካል እንዱተካና መኪናውን ለመጠገን ከሚያስፈልገው ምክንያታዊ ጊዜ በላይ የቆመ በመሆኑ በቀን ብር 1500 /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/ ሑሳብ አመልካች ውለን ባለመፈፀሙ ምክንያት የደረሰብኝን ጉዲት ካሳ /የቀረ ገቢ/ እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርበዋል። አመልካች በስር ፍ/ቤት በተከሳሽነት ቀርቦ መኪናው አዱስ እቃ ተገዝቶ ካልተተካለት በማለት ተጠሪ /ከሳሽ/ በፈጠሩት ችግር ምክንያት ሳይጠገን የቆየ በመሆኑ ኃላፉነቱ የከሳሽ /ተጠሪ/ ነው። በመድን ፕሉሲው መሰረት የተቋረጠ ጥቅም የመክፈል ኃላፉነት የላለብን በመሆኑ የከሳሽ ጥያቄ የህግ ድጋፍ የለውም በማለት ተከራክሯል።
የስር ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃና ክርክር ከሰማ በኋላ መኪናው ሳይጠገን ለመቆየቱ የአመልካች /የተከሳሽ/ ጥፊትና ኃላፉነት ነው በማለት ከደመደመ በኋላ ተከሳሽ /አመልካች/ በመድን ውለ መሰረት የከሳሽን መኪና ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውስጥ ባለማስጠገኑ ምክንያት ከሳሽ /ተጠሪ/ ያቀረቡትን ገቢ የመሸፈን ግዳታና ኃላፉነት አለበት። ስለሆነም የመኪናውን መጠን የሚያስፈልገውን ገንዘብ ብር 139,000 /አንድ መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ ብር/ እና መኪናው ፍርድ እስከተሰጠበት ቀን ድረስ ያስገኝ የነበረው ገቢ በቀን በብር 1500 ታስቦ ብር 588,000 /አምስት መቶ ሰማኒያ ስምንት ሺ ብር/ እንዱከፍል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርቧል። የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ሁለት ጭብጦችን መስርቷል የመጀመሪያው ጭብጥ የከፍተኛው ፍ/ቤት አመልካች መኪናውን ለማስጠገን አስፈላጊ የሆነውን ብር 139,000 /አንድ መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ ብር/ ለተጠሪ ይክፈል በማለት የሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው በማለት ወስኗል። ሁለተኛው ጭብጥ መኪናውን ለማስጠገን የሚፈጀው ምክንያታዊ ጊዜ ምን ያህል ነው የሚል ሲሆን የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የከፍተኛው ፍ/ቤት አርባ አምስት ቀናት ብቻ ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ ተገቢ አይደለም በማለት መኪናውን ለማስጠገን የሶስት ወራት ጊዜ ይፈጃል ከዚህ በተጨማሪ መኪናው በቀን የሚያስገኘው ገቢ ብር 1300 እስከ ብር 1500 ስለሆነ ሑሳቡ መሰላት ያለበት በዝቅተኛው መጠን በብር 1300 መሆን አለበት በማለት ካሻሻለ በኋላ መኪናው ከየካቲት 6 ቀን 1999ዓ.ም ጀምሮ በቀን ብር 1300 /አንድ ሺህ ሶስት መቶ ብር/ እየታሰበ ጉዲዩ በይግባኝ ውሳኔ እስካገኘበት ግንቦት 26 ቀን 2001ዓ.ም ድረስ ይከፈል በማለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔን በማሻሻል ወስኗል።
አመልካች ሰኔ 24 ቀን 2001ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ በዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የክስ ማመልከቻ ከማቅረባቸው በፉት አመልካች የመኪናውን አካል እንዱቀይርልኝ የማይቀይር ከሆነ መኪናው ሙለ ውድመት እንደደረሰበት ተቆጥሮ የመድን ውለ ሙለ ገንዘብ ብር 300,000 /ሶስት መቶ ሺህ ብር/ ይክፈለኝ የሚል እንደሆነ ለአመልካች በጽሐፍ በሰጡት ማስጠንቀቂያ አሳውቀዋል። በዚህ መሰረት የመኪናውን ጋቢና ስፕንዲ በማስቀየር ወይም በማስጠገን የሚስተካከል ስለመሆኑ በባለሙያ አስጠንተን ሉጠገን የሚችል መሆኑ ተረጋግጧል። የስር ፍ/ቤቶች መኪናውን ለመጠገን እና ለማስተካከል ከሚያስፈልገው በላይ አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል የሰጡት ውሳኔ ተጠሪ መኪናውን ለማስጠገን ከሚያስፈልገው በላይ እንዱካስ የሚያደርግና መሰረታዊ መርህ የሚጥስ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት። በሁለተኛ ደረጃ አመልካች መኪናው ላይ በደረሰው ጉዲት ምክንያት ተጠሪ የቀረበትን ገቢ የመክፈል ኃላፉነት እንደላለበት በመድን ፕሉስው በግልጽ ተገልጾ እያለ የእኛን ምስክሮች ሳይሰማ ተጠሪ ጉዲቱን የመቀነስ ኃላፉነታቸውን የተወጡ መሆን አለመሆኑን ሳይመዝን የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1802ን በመጣስ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩለ አመልካች የበታች ፍ/ቤቶች ለመኪናው ማስጠገኛ ከሚያስፈልገው በላይ እንዱካስ ወስነዋል በማለት የቀረበው አቤቱታ የበታች ፍ/ቤቶች ፍሬ ጉዲዩን በማጣራትና በማስረጃ በማረጋገጥ የደረሱበትን መደምደሚያ የሚመለከት በመሆኑ የሰበር አቤቱታ የሚቀርብበትና የሚታይ ነጥብ አይደለም። በእኔ በኩል የጠየቅሁት መኪናው ላይ አደጋ በመድረሱ ምክንያት የቀረብኝን ገቢ /Consequential loss/ እንዱከፍለኝ ሳይሆን አመልካች መኪናውን አስጎትቶ ወስድ በማቆም በመድን ውለ መሰረት በምክንያታዊ ጊዜ ውስጥ አሰርቶ ማስረከብ ሲገባው መኪናውን አሰርቶ ባለማስረከቡ የደረሰብኝን ኪሳራ የሚመለከት በመሆኑ የአመልካች ክርክር የህግ ድጋፍ የለውም በማለት መልስ ሰጥተዋል።
አመልካች በጸሐፍ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች የተጎዲውን የመኪና ክፍል በአዱስ ለመተካት የሚያስችል ገንዘብ ለተጠሪ እንዱከፍል የበታች ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔና አመልካች መኪናውን ባለማስጠገኑ ተጠሪ ያቀረባቸውን ጥቅም በሙለ ይክፈል ተብል የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ መስርተናል።
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ በተጠሪ መኪና አካል ላይ የደረሰው ጉዲት በጥገና የሚስተካከል ሳይሆን አዱስ እቃ ገዝቶ በመተካት ሉስተካከል የሚችል መሆኑን በገለልተኛ ባለሙያ እንደተረጋገጠና ጉዲቱ በጥገና ሉስተካከል የሚቻል ነው በማለት ሐሳብ የሰጡት የአመልካች ኤክስፏርቶች መሆናቸውን በመግለጽ የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመኪናው ላይ የደረሰው ጉዲት አዱስ እቃ በመግዛትና በመተካት ሉስተካከል የሚችል ጉዲት ነው። ስለሆነም ጉዲቱን ለማስተካከል አስፈላጊ የሆነውን ብር 139,000 /አንድ መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ ብር/ አመልካች ለተጠሪ ይክፈል በማለት የወሰነው ፍሬ ጉዲዩን በማጣራትና ማስረጃ በመመዘን ሆኖ አግኝተነዋል። የከፍተኛው ፍ/ቤት ፍሬ ጉዲዩን በማጣራትና ማስረጃ በመመዘን የሰጠው ውሳኔ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ፀንቷል። ስለሆነም አመልካች የበታች ፍ/ቤቶች ማስረጃ በመመዘን ሑደት ሰርተውታል የሚለውን ስህተት የማጣራትና የማረም ስልጣን ይህ ችልት በህገ መንግስቱ አንቀጽ 80 ንዐስ አንቀጽ 3/ሀ/ እና በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10 ያልተሰጠው በመሆኑ አመልካች መኪናው እንዱጠገንና እንዱስተካከል ለማድርግ ብር 139,000 ለተጠሪ እንዱከፍል የተሰጠው ውሳኔ በመኪናው የደረሰውን ጉዲት ለማስተካከል ከሚያስፈልገው መጠን በላይ ነው በማለት ያቀረበውን ቅሬታ አልተቀበልነውም።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ ተጠሪ አመልካች በመድን ውለ መሰረት ባለመፈፀሙና መኪናውን ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውስጥ አስጠግኖ ባለመስጠቱ የቀረብኝ ገቢ ክርክሩ እስከተቋጨበት ጊዜ ድረስ ያለው ታስቦ እንዱከፈላቸው ጠይቀዋል። ይህ የተጠሪ ጥያቄ ተጠሪ መኪናቸው በአደጋው ጉዲት የደረሰበት በመሆኑ ምክንያት ያቀረባቸውን ጥቅም አመልካች እንዱከፍላቸው የቀረበ የ /Consequential loss/ ጥያቄ በመሆኑና የዚህ አይነት ጥያቄ በመድን ውለ እንደማይሸፈን ግልጽ የፕሉሲ ድንጋጌ ያለ በመሆኑ ተገቢ አይደለም በማለት አመልካች ተከራክሯል። በእኛ በኩል እንደተረዲነው ተጠሪ የጠየቁት መኪናው በአደጋው በመጎዲቱ ምክንያት ያቀረባቸውን ጥቅም አመልካች እንዱሸፍንና እንዱከፍላቸው አይደለም። የተጠሪ ክስ መሰረታዊ ይዘት አመልካች መኪናውን ከወደቀበት ካነሳ በኋላ ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውስጥ መኪናውን አስጠግኖ የማስረከብ የውል ግዳታ አለበት። አመልካች ይህንን የውል ግዳታውን በወቅቱ ባለመፈፀሙ ምክንያት የደረሰብኝን ኪሳራ እንዱከፍል ይወሰንልኝ የሚል ነው። ስለሆነም አመልካች የበታች ፍ/ቤቶች ከመድን ፕሉሲው ድንጋጌ ውጭ /Consequential loss/ እንድንከፍል ተወስነብን በማለት ያቀረቡት ክርክር ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም።
የተጠሪ ክርክር ውልባለመፈፀሙ ምክንያት የደረሰብኝ ኪሳራና ጉዲት በውለ መሰረት ግዳታውን ያልፈፀመው አመልካች ይክፈለኝ የሚልና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1790 እና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1791ን መሰረት ያደረገ መሆኑን ለመገንዘብ ችለናል። ሆኖም እዚህ ላይ ላታይ የሚገባውና የበታች ፍ/ቤቶች በአግባቡ ያላዩዋቸው መሰረታዊ የህግ ነጥቦች አለ። ይኽውም አመልካች በመድን ውለ መሰረት መኪናውን በምክንያታዊ ጊዜ ውስጥ በማስጠገን የማያስረክባቸው መሆኑን ካወቁ ተጠሪ መኪናው ተጠግኖ ለስራ ባለመሰማራቱ ምክንያት የሚያደርሰውን ኪሳራ/ጉዲት/ ለመቀነስ አስፈላጊ የሆኑ ተግባራትን የመፈፀም ግዳታ አለባቸው ወይስ የለባቸውም?
ተጠሪ ጉዲቱን ለመቀነስ አስፈላጊውን ጥረት ካላደረጉ ሉከፈላቸው የሚገባው የካሳ መጠን ምን ይሆናል የሚለት ናቸው።
ላላቸው ተዋዋይ ወገን የውል ግዳታውን ያልፈፀመለት ሰው ውለ ባለመፈፀሙ ምክንያት የሚደረሰውን የጉዲት ኪሳራ የመቀነስ ግዳታ እንዲለበት በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1802 ተደንግጓል።
የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1802 "የጉዲት ኪሳራን የመቀነስ ግዳታ" በሚል ርዕስ ስር በንዐስ አንቀጽ 1" ውል አልተፈፀመልኝም የሚለው ወገን ውለ ባለመፈፀሙ ምክንያት የሚደርሰው ኪሳራ ያነሰ እንዱሆን ተገቢ የሆነውን ጥንቃቄ ሁለ ማድረግ አለበት ይኸውም ይህንን የሚያደርገው ጥንቃቄ አስቸጋሪና ብዙ ወጭ እንዱያደርግ የማያስገድደው ሲሆን ነው" በማለት ይደነግጋል። ጉዲት የደረሰበትን መኪና ለመጠገን አስፈላጊ የሆነው ምክንያታዊ ጊዜ ሶስት ወር/ዘጠና ቀናት/ እንደሆነ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በማረጋገጥ ወስኗል። የተጠሪ መኪና ጉዲት የደረሰበት ህዲር 3 ቀን 1999ዓ.ም በመሆኑ አመልካች በመድን ውለ መሰረት መኪናውን ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውስጥ ያስጠግነዋል ብለው መጠበቅ ያለባቸው እስከ የካቲት 10 ቀን 1999ዓ.ም ነው። ተጠሪ ከየካቲት 11 ቀን 1999ዓ.ም በኋላ አመልካች መኪናውን በመድን ውለ መሰረት ባለማስጠገኑ ምክንያት የሚደርሰውን የኪሳራ /ጉዲት/ ለመቀነስ የበኩላቸውን እንቅስቃሴ ማድረግና መኪናውን በሶስት ወር ውስጥ በግል ወጫቸው አስጠግነው ወደ ስራ እንዱስማራ የማድረግ ህጋዊ ግዳታ ያለባቸው መሆኑ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1802 ንዐስ አንቀጽ 1 ተደንግጓል። ተጠሪ በዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ እስካቀረቡበት ጊዜ ድረስም ሆነ ጉዲዩ በይግባኝ ታይቶ እስከተወሰነበት ግንቦት 26 ቀን 2001ዓ.ም ድረስ መኪናውን በግል ወጭ ለማስጠገንና መኪናው ተጠግኖ ለስራ ባለመሰማራቱ ምክንያት የሚደርሰውን ጉዲት ለመቀነስ ያደረጉት እንቅስቃሴ የለም። ይህም ተጠሪ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1802 ንዐስ አንቀጽ 1 የተጣለባቸውን የጉዲት ኪሳራን የመቀነስ ግዳታ ያልተወጡ መሆኑን ያሳያል።
ተጠሪ መኪናው ባለመጠገኑ ምክንያት የሚደርስባቸውን ኪሳራ መኪናውን በራሳቸው ወጭ በማስጠገን ለመቀነስ እየቻለ ይህንን ግዳታቸውን ካልተወጡ የሚከፈላቸው የኪሳራ መጠን እንዱቀንስ አመልካች ለመከራከር የሚችል መሆኑን የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1802 ንዐስ አንቀጽ 2 "ይህንን ጥንቃቄ በቸልተኝነት ሳያደርግ ቢቀር ውለን ያልፈፀመው ሰው የላለውን ወገን ቸልታ መከራከሪያ አድርጎ ኪሳራው እንዱቀንስለት ለመጠየቅ ይችላል" በማለት በግልጽ ይደነግጋል።
አመልካች የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1802ን በመጥቀስ የተከራከረ ሲሆን የበታች የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት መኪናው በመድን ውለ መሰረት አስጠግኖ ባለማስረከቡ ተጠሪ የደረሰባቸውን ኪሳራ ለመቀነስ ያደረጉት እንቅስቃሴ አለመኖሩንና የጉዲት ኪሳራ የመቀነስ ግዳታቸውን ተጠሪ ያልተወጣ መሆኑን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የካሳውን መጠን መወሰን ሲገባቸው መኪናውን ለማስጠገን ከሚያስፈልገው ምክንያታዊ ጊዜ ከየካቲት 8 ቀን 1999ዓ.ም ጀምሮ ጉዲዩ በክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት እስከተወሰነበት ግንቦት 26 ቀን 2001ዓ.ም ድረስ በየቀኑ 1300 /አንድ ሺህ ሶስት መቶ ብር/ እየታሰበ አመልካች ለተጠሪ ካሳ እንዱከፍል በማለት የሰጠው ውሳኔ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1802 የተደነገገውን የጉዲት ኪሳራን የመቀነስ ግዳታ ያላገናዘበና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ስለሆነም ተጠሪ መኪናውን ለማስጠገን አመልካች ከሚወስድበት ምክንያታዊ ጊዜ ማለትም ከየካቲት 11 ቀን 1999ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 10 ቀን 1999ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ መኪናውን በግለ በማስጠገን መኪናው ያለስራ በመቆሙ ምክንያት የሚደርስበትን ኪሳራ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1802/1/ መሰረት መቀነስ ሲገባው ይህንን ግዳታውን ያልተወጣ በመሆኑ ኪሳራ የሚከፈለው ጉዲዩ በይግባኝ ውሳኔ እስካገኘበት ጊዜ ድረስ ሳይሆን በራሱ ወጭ መኪናውን በማስጠገን ኪሳራውን ለመቀነስ የሚያስፈልገው ምክንያታዊ ጊዜ ማለትም የሶስት ወር ወይም የዘጠና ቀናት ብቻ መሆን ይገባዋል በማለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወሰነውን የካሳ መጠን በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1802/2/ እና በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 348/1/ መሰረት በማሻሻል ወስነናል።
1/ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ችልት የሰጠው ውሳኔ ተሻሽሎል።
2/ አመልካች ለመኪናው ማስጠገኛ በዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤትና በክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የተወሰነውን ብር 139,000 /አንድ መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ ብር/ የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ ከሰጠበት የካቲት 3 ቀን 2000ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ዘጠኝ ፏርሰንት ወለድ ጋር ለተጠሪ የመክፈል ኃላፉነት አለበት ብለናል።
3/ አመልካች መኪናውን ባለማስጠገኑ ተጠሪ ለደረሰባቸው ጉዲት የዘጠና ቀናት ገቢ በቀን በብር 1300 /አንድ ሺህ ሶስት መቶ ብር/ ታስቦ ብር 117,000 /አንድ መቶ አስራ ሰባት ሺህ ብር/ ጉዲዩ በዚህ ፍ/ቤት ውሳኔ ካገኘበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ዘጠኝ ፏርሰንት ወለድ ጋር ይክፈል ብለናል።
4/ በዚህ ፍ/ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ። ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.