No summary available.
ታህሳስ 27 ቀን 2003ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ግልባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ አያላው ወርቁ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የመድን ውልን የተመለከተ ነው። ክርክሩ የተጀመረው ተጠሪ በመሰረቱት ክስ ነው። የተጠሪ የክስ ምክንያት አመልካች የመድን ሽፊን የሰጠው የተጠሪ ንብረት የሆነ ታርጋ ቁጥር 3-10953 የሆነ መኪና የመኪናው ሹፋር ረዲት የነበረው አቶ በሪሁን ገ/ሚካኤል ፈቃድ ሳይሰጠው ቁልፍ ሰርቆ ለማሽከርከር ሲሞክር መኪናውን ከቴላኮሙንኬሽን ፕል ጋር በማጋጨት ጉዲት ስላደረሰበት ለጥገና እና ላልች ወጪዎች የወጣ በድምሩ ብር 146,998.50 አመልካች እንዱከፍል እንዱወሰን የሚል ሲሆን በአመልካች በኩል ስር ፍ/ቤት የቀረበው ክርክር ለመኪናው የመድን ሽፊን የሰጠ መሆኑን አምኖ መኪናው ላይ ጉዲት የደረሰው ረዲቱ መንጃ ፈቃድ ሳይኖረው ሲያሽከረከር በመሆኑ እና ይህም በመድን ውለ ክፍል 1 እና 2 መድን ሰጪን በሃላፉነት የማያስጠይቅ ስለመሆኑ እና ረዲት የመኪናውን ቁልፍ ሰርቋል ልባል አይችልም በሚል ክሱ ውድቅ እንዱደረግ ጠይቋል።
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ መድን ሰጪ በመድን ውል ማግለያ አንቀጽ መሰረት ከሃላፉነት ሉድን የሚችለው የሹፋሩ ረዲት መኪናውን ያሽከረከረው ተጠሪ /ከሳሽ/ አውቀውና ፈቅደው ስለመሆኑ አመልካች ማስረዲት ሲችል ብቻ ነው፤ ነገር ግን በዚህ ረገድ አመልካች /ስር ተከሳሽ/ አላረጋገጠም በማለት ሃላፉነት አለበት ሲል ወስኗል። እንዱሁም ጉዲት የደረሰው በተጠሪ ሰራተኛ ጥፊት ስለሆነ በንግድ ሕግ አንቀጽ 664/1/ መሰረት አመልካች ለደረሰው ጉዲት መድን የመሰጠት ሃላፉነት አለበት ብሎል። በዚሁ አግባብ ክስ የቀረበበት ገንዘብ እንዱከፍል ፈርዶል። ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የስር ፍ/ቤት ውሳኔን አጽንቷል።
ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ጉዲት ያደረሰው ሰራተኛ የመንጃ ፈቃድ አለው ወይስ የለውም? እና የመድን ፕሉሲ ክፍል 1ና2 ማግለያ ሁኔታ በአግባቡ ተተርጉሟል ወይስ አልተተረጎመም የሚለትን ነጥቦች ለመመርመር ተብል ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ተደርጓል።
የተጠሪ ጠበቃ መጋቢት 15 ቀን 2002ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅረበዋል። በይዘቱም ሲታይ የመኪናው ሹፋር ረዲት ተጠሪ ሳይፈቅደና ሳይስማሙ የመኪናውን ቁልፍ ሹፋሩ ደብቆ ካስቀመጠበት አንስቶ ለማሽከርከር ሲሞክር አደጋ የደረሰ ስለመሆኑ በመግለጽ ለደረሰው አደጋ የማግለያ አንቀጹ ተፈፃሚነት ሉኖረው እንደማይገባ እንዱሁም በንግድ ህግ አንቀጽ 664/1/ መሰረት አመልካች ሃላፉ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል። አመልካች አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቷል። የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ከፍ ሲል በአጭሩ የተመለከተው ነው።
እኛም ለዚህ ሰበር ችልት ሲቀርብ የተያዘውን ጭብጥ መሰረት አድርገን ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
ከመዝገቡ መረዲት እንደተቻለው አመልካች ለተጠሪ መኪና የመድን ሽፊን መስጠቱ አላከራከረም። የተጠሪ መኪና ላይ ጉዲት የደረሰው በሹፋሩ ረዲት እንደሆነም ተረጋግጧል። የሹፋር ረዲት መኪናውን ለማሽከርከር የሚያስችለው የመንጃ ፈቃድ እንደላለውም በስር ፍ/ቤት ተረጋግጧል።
ተጠሪ በስር ፍ/ቤት ክስ ሲያቀርብም ሆነ እዚህ ሰበር ችልት ሲከራከር የሹፋር ረዲት የመኪናውን ቁልፍ ሰርቆ ነበር መኪናውን ሉያሽከረክር የሞከረው በማለት ነው። እነዚህን በስር ፍ/ቤቶች የተረጋገጡትን እና የቀረቡት ክርክሮች መሰረት በማድረግ በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የመድን ውል ክፍል 1 እና 2 በአግባቡ ተተርጉሟል ወይስ አልተተረጏመም የሚለውን እንደሚከተለው መርምረናል።
በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የመድን ውል ፕሉሲ ለክፍል 1ና2 ልዩዎች በሚል "ኩባኒያው ለሚከተለት ማንኛቸውም ክፍያ የመክፈል ሃላፉነት አይኖርበትም" በሚለው ርዕስ ስር በንዐስ አንቀጽ ሁለት ------ በመድን ገቢው ወይም በመድን ገቢው እውቅናና ስምምነት በላለ ግለሰብ ከፈቃድ ሰጪ ባለስልጣን ወይም በልላ ሕግና ደንብ ለማሽከርከር ፈቃድ ሳይኖረው ወይም በአስካሪ መጠጦችና እጾች ተፅዕኖ ስር ሆኖ ሲሽከረከር በሚፈጠርና በሚደረስ አደጋ፣ ጉዲት፣ ብልሽትና ኃላፉነት በማለት ያመለክታል።
አመልካች በዚህ የማግለያ አንቀጽ መሰረት ሃላፉነት የለብኝም በማለት ተከራክሯል።
የተጠሪ መኪና ላይ ጉዲት የደረሰው በሹፋሩ ረዲት ሲሽከረከር መሆኑ ተረጋግጧል። የሹፋሩ ረዲት መንጃ ፈቃድ የለውም። ከፍ ሲል በተጠቀሰው የማግለያ አንቀጽ መኪናው መንጃ ፈቃድ በላለው ሰው ሲሽከረከር ጉዲት የደረሰበት እንደሆነ መድን ሰጪው ሃላፉነት እንደላለበት ተጠሪ ፈቅድ ውል ገብቷል። በልላ በኩል መኪናውን ያሽከረከረው ረዲት የተጠሪ እውቅናና ስምምነት ሳይኖር ስለመሆኑ ለማስረዲት ተጠሪ ስር ፍ/ቤት ያቀረቡት የፍሬ ነገር ክርክር የመኪናውን ቁልፍ ረዲቱ ሰርቆ ነበር የሚል ሲሆን እንደ ክርክሩ አቀራረብ የመኪናው ቁልፍ በረዲቱ የተሰረቀ ስለመሆኑ ተጠሪ በማስረጃ አላረጋገጠም።
ተጠሪ እንደክሱ አቀራረብ ፍሬ ነገሩ ስለመኖሩ ማስረዲት ግዳታ እንዲለበት የፍ/ብ/ሕግ ድንጋጌ ቁጥር 2001/1/ ይዘት ያመለክታል። ተጠሪ የማስረዲት ግዳታውን ባልተወጣበት ሁኔታ ረዲቱ መኪናውን ያሽከረከረው በተጠሪ እውቅናና ስምምነት ስለመሆኑ አመልካች አላስረዲም ሲል የስር ፍ/ቤት የደረሰበት ድምዲሜ ከተጠቀሰው ሕግ መንፈስና ይዘት ጋር የሚጣጣም አይደለም።
ስለሆነም መኪናው ከተጠሪ ፈቃድና ስምምነት ውጪ ተሰርቆ በረዲቱ ይሽከረከር የነበረ ስለመሆኑ ተጠሪ ሳያስረዲ በተቃራኒው አመልካች የማስረዲት ግዳታ እንዲለበት የስር ፍ/ቤት የወሰደው አቋም የስር ከሳሽ /ተጠሪ/ የማስረዲት ሸክምን ያለአግባብ ወደ ተከሳሽ /አመልካች/ ያስተላለፈ ስለሆነ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ውሳኔ ነው ለማለት ችለናል።
በልላ በኩል የሥር ፍ/ቤት ለውሳኔው ምርኩዝ ያደረገው የንግድ ሕግ ቁጥር 664/1/ ሲሆን በዚህ ድንጋጌ ይዘት መሰረት መድን ገቢው ሃላፉ የሚሆንባቸው ሰዎች ባደረጉት ጥፊት ምክንያት ለሚደርስ ጉዲት መድን ሰጪው መድን የሚሆን ስለመሆኑ ተመልክቷል።
በተያዘው ጉዲይ መኪናው ላይ ጉዲት የደረሰው መንጃ ፈቃድ በላለው የሹፋሩ ረዲት መኪናው ሲሽከረከር ስለመሆኑ ተረጋግጧል። መኪናው በማንኛውም ሰው ቢሆን መንጃ ፈቃድ በልላው ሰው ሲሽከረከር ጉዲት ከረደሰበት መድን ሰጪው ሃላፉነት እንደላለበት በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው ውል ማግለያ አንቀጽ ላይ በግልጽ የተመለከተ ስለመሆኑ ከፍ ሲል ተመልክተናል።
ከዚህ መረዲት የሚቻለው በመኪናው ላይ ጉዲት ያደረሰው የተጠሪ ተቀጣሪ በሆነ ሰራተኛ ቢሆንም በማግለያ አንቀፁ መሰረት ረዲቱ መንጃ ፈቃድ የላለው በመሆኑ ብቻ እንኳ አመልካች መድን የመስጠት ሃላፉነት የላለበት መሆኑን ነው።
በመሰረቱ መንጃ ፈቃድ የላለው ሰው ባለሞተር ተሽከሪካሪ ማሽከርከር እንደማይችል ይልቁንም ድርጊቱ በወንጀል ጭምር እንደሚያስጠይቅ በሕግ ተደንግጎ ይገኛል። ሕጉ በዚህ መልክ ሲደነገግ ጥበቃ ሉያደርግ የፈለገው ለባለ ንብረቱ ጥቅም ብቻ ሳይሆን ለማህበረሰቡ /ለሕዝብ/ አጠቃላይ ደህንነትም ጭምር እንደሆነ መገንዘብ አዲጋች አይደለም። በዚህ መዝገብ የተያዘው ጉዲይ ጋር ስናያይዘው የተጠሪ መኪና ላይ ጉዲት የደረሰው ሚያዝያ 6 ቀን 1999ዓ.ም ሲሆን በዚህ ጊዜ ሥራ ላይ የነበረው የትራንስፕርት አዋጅ ቁጥር 468/97 አንቀጽ 22 ላይ እንደተደነገገው ያለመንጃ ፈቃድ ባለሞተር ተሽከርካሪ መንዲት እንደማይፈቀድ እና ባለንብረቱም ይህንን መፍቀድ እንደላለበት በግልጽ ተደንግጎ እናገኛለን።
በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 29 እንደተመለከተው አዋጁንና አዋጁን ለማስፈፀም ተብል የወጡትን ደንቦች የተላለፈ ሰው የወንጀል ሕግ መሰረት እንደሚሰማ ተደንግጓል።
ስለሆነም ጉዲት አደረሰ የተባለው የሹፋሩ ረዲት በተጠሪ ስር የሚሆን ሰው ነው በሚል ምክንያት አመልካች የመድን ሃላፉነት አለበት ተብል በስር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ የማግለያ አንቀፁን የውል ድንጋጌ መንፈስ በአግባቡ ያላገናዘበና በላልች ሕጎች ለሕዝብ ጥቅም ተብለው የተደነገጉትን ሕጎች ዓላማና ግብ ያላጤነ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት ተችሎል።
No topics extracted.