No summary available.
ጥቅምት 3 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - ተሾመ መኩሪያ ቀረበ ተጠሪዎች፡-
በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የኔ ባልሆነ ሐሰተኛ ፊርማ እና ማህተም መሰረት ተደርጎ ከኔ የባንክ ሂሣብ ላይ ገንዘብ ወጪ ሆኖብኛል በማለት 1ኛ ተጠሪ ያቀረበውን ክስ የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን፣ ፍ/ቤቱ የሁለንም ወገኖች ክርክር ከሰማ በኋላ አመልካች ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ከእነወለደ ለ1ኛ ተጠሪ ይክፈል በማለት በአንድ በኩል ሲወስን፤ በልላ በኩል ደግሞ 4ኛ ተጠሪ ገንዘቡን ለአመልካች ይተካለት በማለት ወስኖአል። በልላ በኩል አመልካች በውሣኔው ባለመስማማት ለፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቦ የነበረ ሲሆን፣ ፍ/ቤቱ ይግባኝ የተባለበት ውሣኔ ጉድለት የለበትም በማለት ይግባኙን ሰርዞአል። የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
አመልካች ህዲር 11 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞአል የሚልባቸውን ምክንያቶች በመግለጽ ውሣኔው ይታረምለት ዘንድ ጠይቆአል። በበኩላችንም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ክርክሩን ሰምተናል። በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት የቀረቡት 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ብቻ ሲሆኑ 3ኛ እና 4ኛ ተጠሪ ባለመቅረባቸው ክርክሩ የተስማው በላለበት ነው። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተደረገው ገንዘቡ ከባንክ ወጪ ላሆን የቻለው የ1ኛ ተጠሪ ሰራተኛ በሆነው 4ኛ ተጠሪ ሆኖ ሣለ አመልካች ለገንዘቡ መውጣት ኃላፉ ነው መባለ አግባብ ነው ወይ? የሚለውን ጭብጥ ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ግራ ቀኝ ወገኖች ጭብጡን በማስመልከት ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከሥር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር እና ከተሰጠው ውሣኔ ይዘት መገንዘብ እንደቻልነው ለክሱ ምክንያት የሆነው ገንዘብ በተጭበረበረ መንገድ ከባንክ ሉወጣ የቻለው የ1ኛ ተጠሪ ሰራተኛ በሆነው በ4ኛ ተጠሪ አማካይነት ነው። 4ኛ ተጠሪ የ1ኛ ተጠሪን ምክትል ሥራ አስኪያጅ ፊርማ እና የኩባንያው /1ኛ ተጠሪ/ ማህተም አስመስል በተዘጋጀ ሲፑዮ እና የክፍያ መጠየቂያ ለባንኩ /አመልካች/ እንዲቀረበ፣ ይህን ሰነድ ያቀረበው በሁለት የተለያለ ጊዜያት ማለትም የብር 42ዐ,ዐዐዐ ክፍያ የታዘዘበት የመጀመሪያው በጃንዋሪ 8 ቀን 2ዐዐ5 /እ.ኢ.አ/ ታህሣሥ 3ዐ ቀን 97 ዓ.ም/፤የብር 347,2ዐ6.63 ክፍያ የታዘዘበት ሁለተኛው ደግሞ በማርች 17 ቀን 2ዐዐ5/እ.ኢ.አ. መጋቢት 8 ቀን 97 ዓ.ም/ እንደሆነ በፍሬ ነገር ረገድ ተረጋግጦአል። ክፍያዎቹም የተፈፀሙት እንደዚሁ እንደአመጣጡ ነው።
1ኛ ተጠሪ ክሱን የመሰረተው ታህሣሥ 25 ቀን 99 ዓ.ም ሆኖ ለገንዘቡ በተጭበረበረ መንገድ መውጣት ኃላፉነት መውሰድ ያለበት ባንኩ ነው በማለት የተከራከረውም የሚጠበቅበትን ጥንቃቄ አላደረገም። የሰነድቹን ትክክለኛነት ሣያረጋግጥ እና እኔን /ከሣሽን/ ሣያሣውቅ ከፍልአል የሚለትን ምክንያቶች መሰረት በማድረግ ነው። አመልካች ደግሞ ገንዘቡን ለታዘዘላቸው ወገኖች እንዱተላለፍ/ እንዱከፈል/ ያደረግሁት የባንኩን የተለመደ አሰራር እና ሥርዓት በመከተል ተገቢውን ጥንቃቄ ከወሰድኩ በኋላ ነው። በሰነድቹ ላይ ያለው ፊርማ እና ማህተም ትክክል አለመሆኑን ለመጠራጠር ወይም ለማወቅ የምችልበት የተለየ ሁኔታ አልነበረም በማለት ተከራክሮአል። ከዚህም በተጨማሪ በሕጉ እና በተለመደው አሰራር መሰረት ለ1ኛ ተጠሪ የባንክ ወርሃዊ የሂሣብ መግለጫ እየላከለት እና ከሂሣቡ ላይ ገንዘቡ መቀነሱን ሲያሣውቀው እንደቆየ፤ ይህም ሁኔታውን ለማወቅ የሚያስችለው ሆኖ ሳለ 1ኛ ተጠሪ ግን የራሱ ሰራተኛ ላይ ጥንቃቄ አለማድረጉን በመግለፁም ተከራክሮአል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ባየው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የተደረገው የግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር ተጠቃል ሲታይ ከላይ የተመለከተው ሲሆን፣ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ‛ተከሣሽ ባንክ ለክሱ መሰረት የሆነውን ሲፑዮ በከሣሽ ስም ሲዘጋጅ እና ክፍያ ሲፈፀም ተገቢውን የተለመደ የባንክ አሰራር ተከትልአል አልተከተለም?“ የሚል ጭብጥ በመያዝ ክርክሩን መርምሮአል። በውሣኔው ላይ በግልጽ እንዲመለከተው ከቀረበለት ማስረጃ አንፃር አመልካች /ባንኩ/ ተገቢውን የተለመደ የባንክ አሰራር አልተከተለም፣ ገንዘቡን የከፈለው ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ እና ቅን ልቦናን ተከትል አይደለም እሚል መደምደሚያ ላይ ሉደርስ አልቻለም። አመልካችን ኃላፉ በማድረግ ሉወስን የቻለው የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት በሰበር መ.ቁ. 253ዐ6 በሰጠው ውሣኔ የገንዘቡ አደራ ጠባቂ የሆነው ባንክ አደራ አስቀማጭ የሆነው ባለሂሣብ ሣይጠይቅ ወይም ሕጋዊ ትእዛዝ ሣይሰጥበት ገንዘቡ በተጭበረበረ መልኩ ወጪ ከሆነ የተጭበረበረው አደራ አስቀማጩ ባለሂሣብ ሣይሆን፣ አደራ አስቀማጩ ባንክ ነው በማለት ለሥር ፍ/ቤቶች ገዢ የሆነ የሕግ ትርጉም ሰጥቶአል በማለት እና ከሣሽ በተከሣሽ ባንክ ካለው ሂሣቡ ውስጥ ያለእሱ ትእዛዝ እና እውቅና ወጪ እንደሆነበት ሰነደን በማስመርመር አረጋግጦአል የሚል ምክንያት በመስጠት ነው።
No topics extracted.
ቀደምሲል እንደተገለፀው ለባንኩ የቀረቡት ሰነድች በማስመሰል የተዘጋጁ እንጂ እውነተኛ አይደለም ስለተባለ ነው 1ኛ ተጠሪ ወደ ክስ ያመራው በመሆኑም አከራካሪ የሚሆነው እና በውሣኔ እልባት ማግኘት ያለበት ሰነድቹ የተጭበረበሩ ናቸው ወይስ አይደለም የሚለው ሣይሆን፣ አመልካች ሰነድቹን መሰረት በማድረግ ክፍያ የፈፀመው የባንኩን የተለመደ አሰራር ሣይከተል እና ተገቢውን ጥንቃቄ ሣያደርግ ነው ወይ? የሚለው ነው። ይህ ነጥብ የፍሬ ነገር ጭብጥንም የሚመለከት በመሆኑ የሚነጥረው በማስረጃ ነው። ጭብጡን በማስረጃ የማንጠር ሥልጣን ያለው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች ተገቢውን ጥንቃቄ ሣያደርግ ወይም የባንኩን የተለመደ አሰራር ሣይከተል ገንዘቡ እንዱከፈል አድርጎአል እሚል መደምደሚያ ላይ አልደረሰም። በመሆኑም አመልካች በዚህ ረገድ ኃላፉ ሉያደርገው የሚችል ጥፊት ወይም የሕግ /የሥርዓት/ ጥሰት አልፈፀሙም ማለት ነው።
በመቀጠል የሚታየው የሰበር ችልቱ ሰጠው የተባለው የሕግ ትርጉም ነው። በሰበር መ.ቁ.
253ዐ6 የተሰጠውን ውሣኔ አስቀርበን ተመልክተነዋል። በመጀመሪያ የተገነዘብነው በዚህ መዝገብ /ቁ.253ዐ6/ የነበረው ክርክር እና የተያዘው ጭብጥ አሁን በያዝነው ጉዲይ ከተነሣው ክርክር እና ጭብጥ የተለየ እንደሆነ ነው። በሰበር መ.ቁ. 253ዐ6 ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ክስ በፍ/ቤት የተሰጠ ውሣኔ ሣይኖር ውሣኔ እንደተሰጠ በማስመሰል እና የተጭበረበረ የፍ/ቤት ትእዛዝ በማቅረብ ገንዘብ ከባንክ ወጪ ሆኖአል የሚል መነሻ ያለው ነው። ተከሣሾች የነበሩትም ፍ/ቤት እና ባንክ ናቸው። በሁለተኛ ደረጃ የተገነዘብነው እና ዋናው ቁም ነገር ደግሞ የሰበር ችልቱ በተጭበረበረ መንገድ ከባንክ ገንዘብ ወጪ በሆነ ቁጥር ያለምንም ምክንያት ባንኩ ኃላፉ ይሆናል የሚል የሕግ ተርጉም አለመስጠቱን ነው። እንደሚታወቀው ክርክሮች የሚወሰኑት እንደ የግል ባህሪያቸው እየታየ ነው። በአንድ ጉዲይ የተነሣውን ክርክር እልባት ለመስጠት የተሰጠ ውሣኔ በልላ ጉዲይ ለተነሣው ክርክርም እልባት ለመሰጠት ያስችላል ብል ሙለ በሙለ መደምደም ትክክልም ተገቢም አይደለም። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ወደ ድምዲሜ የደረሰው የሰበር ችልቱ ለውሣኔው መሰረት ያደረገው የፍሬ ነገር እና የሕግ ምክንያት በዝርዝር ሣይመለከት እንደሆነ ነው በበኩላችን መገንዘብ የቻልነው። በመሆኑም የሰበር ችልቱ በሰጠው የሕግ ትርጉም ነው በሚል አመልካችን ኃላፉ ማድረጉ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። ቀደም ሲል ተሰጠ በተባለው ውሣኔም ሆነ በሰበር ችልቱ እምነት ባንክ በተጭበረበረ መንገድ ለወጣ ገንዘብ በኃላፉነት ሉጠየቅ የሚችለው የተለመደውንና ተገቢውን የባንክ አሰራር ሣይከተል ወይም ተገቢውን ጥንቃቄ ሣያደርግ ከፍል ከተገኘ ነው።
በያዝነው ጉዲይ ባንኩ / አመልካች/ ገንዘቡን የከፈለው አሰራሩንና ሥርዓቱን ተከትል ነው።
ስለዚህም አመልካችን ኃላፉ በማድረግ የተሰጠው ውሣኔ በሕጉ አተረጓጎም ረገድ መሰረታዊ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 51654 ሚያዝያ 28 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. 38ዐ8ዐ ህዲር 8 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
አመልካች ለክሱ ምክንያት የሆነውን ገንዘብ እንዱከፍል የሚገደድበት የሕግ ምክንያት የለም ብለናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራ የቻቻለ።