No summary available.
ሚያዚያ 03 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ዋልደ አልማው ወላ ዓሉ መሀመድ ነጋ ደፍሣ አመልካች፡- አቶ አደኛ አጃው የቀረበ የለም።
ተጠሪ፡- ቀስቅስ አየነው የቀረበ የለም።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የከብቶች ግምት ይከፈለኝ ጥያቄን የሚመለከት ስሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በአሁኑ ተጠሪና ለጉዲዩ ዋስትና ገብተውላቸዋል በሚሎቸው ግለሰብ ላይ በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የአመልካች የስር ክስ ይዘትም ባጭሩ፡- የግላቸው የሆኑት ሶስት ከብቶች ጠፍተውባቸው ተጠሪን ጠርጥረው በሽማግላ ሲጠይቋቸው በቤተክርስቲያን ለመማማል ፈቃደኛ ከሆኑ በኋላ እንደገና አልምልም፣ ወስጄአለሁ በማለት አምነው መስከረም 25 ቀን 2000 ዓ/ም በተደረገ ስምምነት መሰረት ብር 8000.00 (ስምንት ሺህ ብር) ለመክፈል መስማማታቸውን፣ ተጠሪ ይህንኑ ባይከፍለ ደግሞ በስር ሁለተኛ ተከሣሽ የነበሩት አቶ ባበዩ ሲሳይ የተባለት ግለሰብ የዋስትና ግዳታ መግባታቸውን፡ ሆኖም በውለ መሰረት ገንዘቡ ያልተከፈላቸው መሆኑን ዘርዝረው የከብቶቹ ግምት የሆነው ብር 8000. (ስምንት ሺህ ብር) እንዱከፈላቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መከላከያ መልስም ጉዲዩ ቀድሞ በማህበራዊ ፍ/ቤት ቀርቦ ውድቅ የተደረገ መሆኑን ገልጸው ክሱ በድጋሚ ላቀርብ እንደማይገባ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያነሱ ሲሆን በፍሬ ነገር ደረጃ ደግሞ ውለን በሃይል የፈረሙ መሆኑን ገልፀው ሕጋዊ አይደለም በማለት ተከራክረዋል። የስር ፍርድ ቤትም የተጠሪን መከራከሪያ ውድቅ አድርጎ ለክሱ መሰረት የሆነውን ገንዘብ ብቻቸውን እንዱከፍለ ሲል ወስኗል።
ከዚህ በኋላም ተጠሪ ይግባኛቸውን ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። ተጠሪ የሰበር አቤቱታቸውን ከክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበውም ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ጉዲዩ ቀድሞ የማሕበራዊ ፍርድ ቤት ቀርቦ ያለቀ ነው በሚል ምክንያት የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ተሽሮአል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር እቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ለክሱ መሰረት የሆነው የመስከረም 25 ቀን 2000 ዓ.ም ውል ሆኖ እያለ በ1998 ዓ/ም በቀበላ ማሕበራዊ ፍርድ ቤት ቀርቦ የመጨረሻ ውሳኔ አግኝቷል ተብል መወሰኑ ያላግባብ ነው በማለት የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ እንዱሻር ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው ነው ተብል በመታመኑ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው የጽሐፍ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የዚህን ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ የአመልካች ክስ በቀበላ ማሕበራዊ ፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ ያገኘ ነው ተብል መወሰኑ ባግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ሆኖ አግኝተናል።
ከክርክሩ ሂደት መዝገንዘብ የተቻለው አመልካች ለክሳቸው መሰረት ያደረጉት መስከረም 25 ቀን 2000 ዓ.ም ተደረገ የተባለውን ውል ሲሆን የቀበላ ማሕበራዊ ፍርድ ቤት ውሳኔ ስለመስጠቱ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የተገለፀው በ1998 ዓ/ም ተደረገ የተባለው ስምምነት መሆኑን ነው። ተጠሪ መስከረም 25 ቀን 2000 ዓ.ም የተደረገ ውል ስለመኖሩ ሳይክደ በኃይል የተደረገ ነው በማለት የሚከራከሩ ሲሆን ይህንኑ እንዱያስረደ እድል ተሰጥቷቸው በቀነ ቀጠሮው እለት ችልት ሳይቀርቡ የቀሩ መሆኑን የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በውሳኔው ላይ ከመዘገበው ተገንዝበናል።
በመሰረቱ የፍትሐብሕር የክርክር አመራር ሥርዓት ዓይነተኛ ዓላማ የክርክርን ሂደት ለማቀላጠፍና አንድ ደረጃ ላይ ሲደርስ መቋጫ ለማበጀት መሆኑ ይታመናል። የፍትሐብሕርን ክርክር አንድ ደረጃ ላይ ሲደርስ እልባት እንዱደረግበት በማቀድ ከተደነገጉት የፍትሐብሕር ሥነሥርዓት ጽንሰ ሐሳቦች አንደ የመጨረሻ ፍርድ ያገኙ ጉዲዮች /Res judicata/ የሚለው ሲሆን ይህ ጽንሰ ሀሣብ በ1958ቱ የፍትሒ ብሓር ሥነ ስርዓት ሕጋቸን ውስጥ በቁጥር 5 ድንጋጌ ስር በግልጽ ተቀምጦ እናገኘዋለን። በዚህ ድንጋጌ መሰረት የመጨረሻ ፍርድ ያገኙ ጉዲዮች ማለት በማናቸውም መልክ በሕግ በተቋቋመ ፍ/ቤት ቀርበው የመጨረሻ ውሳኔ ያገኙ ጉዲዮችን የሚሸፍን መሆናቸውንና በፍርድ፣ በብይን፣ በውሣኔ፣ በትአዛዝ፣ ወይም በጊዜያዊ አግለግልት ባለው ትእዛዝ የመጨረሻ ውጤት አግኝተው በልላ መልክ ለመንቀሣቀስ የማይችለ የክርክር ነጥቦችን ሁለ የሚያጠቃልል ጉዲይ መሆኑን መገንዘብ የምንችለው ጉዲይ ነው። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/ 5 ሥር በተመለከተው አኳኋን አንድ ጉዲይ አስቀድሞ በፍርድ ያለቀ ነው ለማለት መረጋገጥ ካለባቸው ሁኔታዎች ውስጥ፡- ቀደም ሲል ቀጥተኛ የፍሬ ነገር ጭብጥ የነበሩ ጉዲዮች በድጋሚ በቀረበው ክስም ላይ በቀጥታ በፍሬ ነገር ጭብጥ ሆነው መቅረባቸው ፣ቀደም ሲል የነበረው ክርክር አሁን በክርክር ተሳታፉ በሆኑ ወገኖች ወይም ከእነሱ መብት በተላለፈላቸው ወይም ተለለፍላቸው በነበረ ወገኖች መሆኑንና እነዚህ ጉዲዮች ቀደም ሲል በተካሄደው ሙግት የመጨረሻ ፍርድ ያረፈባቸው መሆኑን ነው።
No topics extracted.
ቀጥተኛ የፍሬ ነገር ጭብጥ በመጨረሻ ፍርድ መቃወሚያነት ሲቀርብ ተቀባይነት የሚኖረው ይኸው ጉዲይ በድጋሚ በቀረበው ክርክር ላይ መቅረቡ ሲረጋገጥ ነው። ‛ … ቀጥተኛ የፍሬ ነገር ጭብጥ …“ የሚለው ሐረግ አጠቃላይ ይዘቱ ሲታይም በመጀመሪያው ክርክር ላይ ከአንደኛው ወገን ተጠይቆ በልላኛው ወገን የተካደ ወይም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የታመነና በዚሁ ላይ የፍርድ ውሣኔ ያረፈበት የክርክር ነጥብ ነው። በመሆኑም በድጋሚ በቀረበው ክስ በቀድሞው ክርክር ተሣታፉ በነበሩ ወገኖች ወይም ከእነሱ መብት በተላለፈላቸው ወገኖች በሚካሄድ መሆኑና በሁለተኛው ክስም የተያዘው የፍሬ ነገር ጭብጥ ከመጀመሪያው ጋር ተመሣሣይ ሆኖ የመጨረሻ ፍርድ ያረፈበት መሆኑ ከተረጋገጠ እንደሁም ጉዲዩ የመጨረሻ ፍርድ አርፍበታል የሚል ተቃውሞ በተከራካሪ ወገን ከተነሣ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 5 እና 244(2) ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ነጥብ ነው።
በተያዘው ጉዲይ አመልካች በ15/07/2000 ዓ.ም ለሰሜን ጎንደር መስተዲድር ዞን ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ መሰረት ያደረጉት ከተጠሪ ጋር መስከረም 25 ቀን 2000 ዓ/ም ተደረገ የተባለውን ውል ሲሆን ይህ ውል በ1998 ዓ.ም ቀበላ ማሕበራዊ ፍርድ ቤት ላቀርብ እንደማይችል የጊዜው ቅደም ተከተል በራሱ አስረጂ ነው። ተጠሪ መስከረም 25 ቀን 2000 ዓ/ም የተደረገውን ውል ስለመኖሩ የካደት ሳይሆን ውለ በሕግ ጥበቃ ላደረግለት አይገባም ያለትን የኃይል ተግባር ጠቅሰው ቢከራከሩም በማስረጃ ያረጋገጡት ፍሬ ነገር አለመኖሩን ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ነጥብ ነው። በመሆኑም አመልካች በአቤቱታ ጽሐፊቸው የገለፁትና የዘረዘሩት ፍሬ ነገር በቀበላ ማህበራዊ ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር ከተባለው ጉዲይ ጋር ሲነፃፀር የተለየ ፍሬ ነገር ነው። በመሆኑም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 5 መሰረት የመጨረሻ ፍርድ ያረፈበት ጉዲይ ነው ሲል የበታች ፍ/ቤቶችን ውሳኔ መሻሩ ባግባቡ ባለመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስለአገኘን ተከታዩን ወስነናል።
የአማራ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመ/ቁ/ 4248 ጥቅምት 11 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በሰሜን ጎንደር አስተዲደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ታህሳስ 06 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ጥቅምት 03 ቀን 2003 ዓ/ም በትእዛዝ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/348(1) መሰረት ጽንቷል።
አመልካች መጋቢት 15 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈት የአቤቱታ ጽሐፍ (ክስ) መሰረት ያደረጉት መስከረም 25 ቀን 2000 ዓ.ም ተደረገ የተባለውን ውል በመሆኑ የመጨረሻ ፍርድ ያገኘ ጉዲይ አይደለም ብለናል።
ተጠሪ ብር 8000.00 (ስምንት ሺህ ብር) ከ