No summary available.
መጋቢት 19 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ በቀለ ጃፊር - ቀረቡ ተጠሪ፡- እነ ወ/ሮ ሙለነሽ ማሞ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የውርስ ንብረት ክርክርን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ ሲጀመር ከሣሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪዎች ናቸው፣ ተከሣሽ ደግሞ አመልካች ነበሩ። ተጠሪዎች በአመልካች ላይ ያቀረቡት ክስ ይዘቱ ሲታይ የእናታችንን የውርስ ሀብትና ይዞታ አመልካች ይዞ ስለሚገኝ እንዱለቅልን ይወስንልን የሚል ሲሆን የአሁን አመልካች ለክሱ በሰጡት መከላከያ መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርበዋል። በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያቀረቡት የውርስ ሀብት ይገባናል ጥያቄ በይርጋ የሚታገድ መሆኑን የሚገልጽ ሲሆን በፍሬ ነገር ደረጃ ደግሞ የውርስ ሀብቱን ያልያዙ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የሱልልታ ወረዲ ፍርድ ቤትም በአመልካች በቀረበው የይርጋ መቃወሚያ ብይን ሳይሰጥ በማለፈ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅረበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት በአመልካች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ብይን ሳይሰጥ ማለፈ ሥነ ስርዓቱን የተከተለ አይደለም በማለት በስር ፍርድ ቤት የተፈፀመውን የስነ ስርአት ግድፈት በማረም በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ተገቢውን ማጣራት በማድረግ የስር ፍርድ ቤት ብይን እንዱሰጥ ጉዲዩን መልሶታል። ከዚህም በሁዋላ የስር ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የአመልካች ማስረጃ እንዱሰሙ ያዘዘ መሆን ያለመሆኑን ማብራሪያ እንዱሰጥና ትእዛዙንም አመልካች አድርሰው ማብራሪያውን እንዱያቀርቡ የስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቶ አመልካች ይህንኑ ትዕዛዝ አልፈፀሙም፣ ይልቁንም ቀድሞ ዘርዝረው ያላቀረቡትን የመከላከያ ማስረጃ ዝርዝር አቅርበዋል በማለት መዝገቡን ዘግቶታል። በዚህ ብይን አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ የሰበር አቤቱታቸውን ደግሞ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ነሐሴ 11 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በፃፊት ሦስት ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ብይን ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። አቤቱታቸው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው ነው ተብል በመታዘዙ ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው የፅሐፍ መልሳቸው ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ወሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የአሁኑ አመልካች ተጠሪዎች ባቀረቡባቸው የውርስ ንብረት ይልቀቅልን የዲኝነት ጥያቄ የይርጋ ክርክር አንስተው የሥር ፍርድ ቤት በዚሁ ላይ ብይን ሳይሰጥ በማለፊ የበላይ ፍርድ ቤት በአመልካች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ተገቢው ብይን እንዱሰጥ ለስር ፍርድ ቤት ጉዲዩን ከመለሰለት በሁዋላ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ብይን ለመስጠት ማስረጃ መስማት እንደአለበት የስር ፍርድ ቤት አምኖ ተገቢ ነው ያለውን ትዕዛዝ የሰጠ መሆኑ ነው። የስር ፍርድ ቤት ወደዚህ ድምዲሜ የደረሰው ይግባኙን ተመልክቶ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ተገቢው መጣራት ተደርጎ ብይን ላሰጥበት ይገባል በማለት ውሣኔ የሰጠው የበላይ ፍርድ ቤት ተገቢው መጣራት ተደርጓል ሲል ማስረጃ ተሰምቶ መሆን ያለመሆኑን ማብራሪያ እንዱሰጥበት፣ ይህንኑም አመልካች ተከታትለው እንዱያስፈፅሙ በማለት ትዕዛዝ ሰጥቶ አመልካች ይህንኑ ትዕዛዝ ሳያስፈፅሙ አዱስ የማስረጃ ዝርዝር አቅርበዋል በሚል ነው። ይሁን እንጂ የአመልካች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መሰረት ያደረገው የጊዜ ማለፍ ሲሆን ይህ የጊዜ ማለፍ ደግሞ ተጠሪዎች ካቀረቡት ክስ ባሕርይ እና ክስ ከተመሰረተበት ጊዜ አንፃር ታይቶ አግባብነት ባለው ሕግ ምላሽ የሚሰጠው ከመሆን ውጪ የተከሣሽ ማስረጃ ሉሰማ የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት የላለው ነው። ተጠሪዎች የጊዜውን ማለፍ አምነው የይርጋ ጊዜውን ሉያቋርጡ የሚችለ ሕጋዊ ምክንያት ያላቸው ስለመሆኑ ጠቅሰው ተከራክረው አመልካች ይህንኑ ሉያስተባብል የሚችል ክርክርና ማስረጃ ያላቸው ስለመሆኑ ጠቅሰው መከራከራቸውን የሚያሳይ የክርክር ሂደትም የለም።
No topics extracted.
የሥር ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ብይን እንዱሰጥ ይግባኙን የተመለከተው የበላይ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሲሰጥም በጊዜው ማለፍ ላይ ማስረጃ እንዱሰማ ብል የገለፀው ነገር የላለ መሆኑ ግልጽ ነው። በመሆኑም በአመልካች በኩል የይርጋ ጊዜ አልፎል በሚል የቀረበው ክርክር ተቀባይነት ያለው መሆን ያለመሆኑን የክሱን አይነትና ክሱ የቀረበበትን ጊዜ ለጉዲዩ አግባብነት ካለው ሕግ ጋር በማዛመድ ብይን የሚሰጥበት ሆኖ እያለ የስር ፍ/ቤት የሰው ማስረጃ መቅረብ አለበት ያለበት አግባብ ሕጋዊ ምክንያት ሳይኖረው መሆኑን ከመዝገቡ ተረድተናል። ይህ ደግሞ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 244/2/ሰ/ እና 234 ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎችን ይዘትና መንፈስ እንዱሁም አላማቸውን ያላገናዘበ ከመሆኑም በላይ የአመልካችን የመከራከር መብት ያጣበበ ሆኖ አግኝተናል። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት ጉዲዩ ከተመለሰለት በሁዋላ መዝገቡን የዘጋበት ሥርዓት መሰረታዊ የሆነ የሥነ ስርዓት ሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ስለአገኘን ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በሱልልታ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ ጥር ዐ6 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. ተሰጥቶ በፉንፉኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር ዐዐ52ዐ መጋቢት ዐ9 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም.፣ በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁጥር 1ዐ3687 ሐምል ዐ3 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በትዕዛዝ የጸናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የተጠሪዎችን የክስ አይነትና ለጉዲዩ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት ያለውን ሕግ መሰረት በማድረግ ተገቢው ብይን ከሚሰጥበት በስተቀር የአመልካች የመከላከያ ማስረጃ እንዱሰማ የሚደረግበት ህጋዊ ምክንያት የለም ብለናል።
የሱልልታ ወረዲ ፍርድ ቤት መዝገቡን በማንቀሳቀስ ጉዲዩን ከዚህ በፉት ባላዩት ዲኛ እንዱታይ በማድረግና በአመልካች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ተገቢውን ብይን በመስጠት ጉዲዩን እንዱዲኝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 341/1/ መሰረት ተመልሶለታል።
በዚህ ችልት ግራ ቀኙ ለአደረጉት ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።