No summary available.
መጋቢት 05 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ብርሃኔ አደላ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ግርማ አብዱሣ - አልቀረቡም መዝገቡ የተቀጠረው ለመመርመር ሲሆን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የቀረበው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜን አስመልክቶ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ 323(2) የተደነገገውን ድንጋጌ አፈፃፀም ከግራ ቀኙ ክርክር አንፃር ተመልክቶ ተገቢውን ትርጉም ለመስጠት በሚል ነው።
የአሁን አመልካች ባቀረበቺው የአፈፃፀም ክስ መነሻ የጋምቤላ ከተማ ዙሪያ ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍ/መ/ መጋቢት 27 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችልት ዲኝነቱን በትዕዛዝ መልክ ሰጥቷል።
በዚህ ትዕዛዝ ላይ የአሁን አመልካች ቅር ተሰኝተው ሚያዝያ 18 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ትዕዛዝ የተሰጠበት የመዝገብ ግልባጭ እንዱሰጣቸው ስለመጠየቃቸውና በጥያቄው መሰረት ግንቦት 11 ቀን 2002 ዓ.ም ግልባጩ እንደተሰጣቸው ትዕዛዙን በሰጠው ፍ/ቤት በፍ/መ/ ግንቦት 11 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ሸኚ ላይ ከተዘረዘረው መረዲት ችለናል።
እንዱሁም ይህ ግልባጭ ከደረሳቸው በኋላ ሰኔ 02 ቀን 2002 ዓ.ም የተፃፈ ዝርዝር የይግባኝ አቤቱታ አዘጋጅተው ይግባኙን እንዲቀረቡ ይግባኝ ሰሚው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በአፈ/ይ/መ/ ሰኔ 03 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችልት ከሰጠው ዲኝነት ተገንዝበናል።
ከላይ እንደተመለከተው ለይግባኙ ምክንያት የሆነው ዲኝነት መቼ ተሰጠ፤ ይግባኝ ባይ ቅሬታ እንዲላቸው ገልፀው ግልባጭ እንዱሰጣቸው መቼ ጠየቁ፤ በጥያቄው መሰረት የመዝገቡን ግልባጭ ፍ/ቤቱ መቼ ሰጣቸው፤ ግልባጩ ከተሰጣቸው በኋላ የይግባኝ ቅሬታ አዘጋጅተው ለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት መቼ አቀረቡ፤ የሚለውን አስመልክቶ ለማረጋገጥ ማስረጃ ሆነው የቀረቡት በፍ/ቤቶች የተሰጡት ማረጋገጫዎች ከመሆናቸውም በላይ ተጠሪ ይህንን ለማስተባበል የሚያስችል የተለየ ክርክር አላቀረበም።
ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም የአመልካች የይግባኝ መዝገብ እንደቀረበለት ለይግባኙ ምክንያት የሆነው ዲኝነት የተሰጠበትን መጋቢት 27 ቀን 2002 ዓ.ም እና የይግባኝ ቅሬታ የቀረበበትን ሰኔ 02 ቀን 2002 ዓ.ም በፍሬ ነገር ረገድ የቀረቡትን ጊዜዎች መነሻ በማድረግ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 323(2) የተመለከተው የሁለት ወር የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ካለፈ በኋላ የቀረበ የይግባኝ መዝገብ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም በማለት መዝገቡን ዘግቶ አሰናብቷል። የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም ይህ የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሰጠው ዲኝነት የይግባኝ አቤቱታን አቀራረብ ጊዜን አስመልክቶ ከተቀመጠው ድንጋጌ ጋር ተገናዝቦ ሲታይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት አይደለም ሲል የበኩለን ዲኝነት ሰጥቶበታል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ ባጭሩ የተመለከተው ሲሆን፤ እኛም ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል።
ለጉዲዩ አግባብነት ባለው ድንጋጌ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 323(2) ላይ የይግባኝ አቤቱታ ለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት መቅረብ የሚገባው ይግባኝ የሚባልበት ጉዲይ በተፈረደ በ60 ቀን ውስጥ ነው በማለት ተደንግጓል። የዚህን ድንጋጌ አነጋገር በቀጥታ ከወሰድን በማናቸውም ሁኔታ ቢሆን የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ይግባኝ የሚባልበት ፍርድ በተፈረደ በ60 ቀን ጊዜ ውስጥ መሆን ይኖርበታል ወደሚለው መደምደሚያ የሚያደርሰን በመሆኑ ተከራካሪው ወገን ግልባጭ በመጠየቅና በማግኘት ረገድ ያሳየው ጉድለት ሳይኖር ፍ/ቤቶች ባላቸው አሰራር ምክንያት የባከነውን ጊዜ ሁለ በስላት ውስጥ የሚያስገባ ሆኖ ስለሚገኝ ድንጋጌው ትርጉም የሚያስፈልገው ሆኖ ተገኝቷል።
ድንጋጌው ሥነ ሥርዓታዊ እንደመሆኑ መጠን ሥነ ሥርዓታዊ ድንጋጌዎችን ሥራ ላይ በምናውልበት ጊዜ ትርጉም ካስፈለገ በተለይ የሥነ ሥርዓት ህግ ግብን መሰረት በማድረግ ውጤታማ እና ትርጉም ባለው አኳኋን ተግባራዊ ፊይዲውን በማየት ላልች መሰረታዊ ህጎችን ከምንተረጉምበት መደበኛ የአተረጓጎም ዘዳ በተለየ ሁኔታ ልንተረጉም ስለሚገባ ይህ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 323(2) ድንጋጌ በግልፅ የተቀመጠ ስለሆነ ትርጉም ሳያስፈልገው እንዲለ በሥራ ላይ ሉውል ይገባል የሚያሰኝ አይደለም።
ስለሆነም ፍርድ እንደተፈረደበት ይግባኝ እንደሚጠይቅ ገልፆ የይግባኝ መጠየቂያ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ የመዝገብ ግልባጭ እስኪሰጠው ድረስ ያለው ጊዜ ለይግባኝ ማቅረቢያ ተብል ከተሰጠው 60 ቀን ስላት ውስጥ ሉካተት አይገባውም።
ይህ በፍ/ቤት አሰራር ምክንያት የባከነው ጊዜ ከይግባኝ ጥያቄው አቅም ውጭ የሆነና እንደበቂ ምክንያት ስለሚቆጠር የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ እንዲለፈበት በይግባኝ ማስፈቀጃ አቤቱታ አማካኝነት ይግባኙ እንዱቀርብ ያድርግ የሚለውን መስመር መከተል ይኖርብናል እንዲይባል ከላይ እንደተጠቀሰው አስቀድሞ ውጤቱ ለሚታወቅ ጉዲይ ትርጉም አልባ የሆነ ሥርዓት እንዱፈፀም ለማድረግ ብቻ ከሚሆን በቀር ተግባራዊ ውጤት የሚያስከትል ሆኖ አይገኝም።
No topics extracted.
ስለሆነም ይህ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ 323(2) የተመለከተው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ይሰላ ከተባለ ፍርደ በተፈረደበት ቀን እና ይግባኝ ጠያቂው የይግባኝ አቤቱታ ሉያቀርብ እንደሚፈልግ ገልፆ የመዝገብ ግልባጭ በጠየቀበት ጊዜ መካከል የባከነውን ጊዜ፣ የመዝገብ ግልባጭ ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ የይግባኝ አቤቱታውን አዘጋጅቶ ለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት እስካቀረበበት ድረስ የባከነውን ጊዜ በማስላትና በመደመር 60 ቀን ማለፈ እና አለማለፈ እንዱለይ በማድረግ ላሆን ይገባል።
ከዚህም አንፃር አሁን በእጅ ያለውን ጉዲይ ስንመለከት ፍርደ ከተፈረደበት ከመጋቢት 27 ቀን 2002 ዓ.ም ጀምሮ የይግባኝ መጠየቂያ ለፍ/ቤቱ እስከቀረበበት እስከ ሚያዝያ 18/2002 ድረስ ያለው ጊዜ ሲታሰብ 21 ቀናት ያለፈ እንዱሁም ግልባጩ በአመልካች እጅ ከደረሰበት ከግንቦት 11 ቀን ጀምሮ የይግባኝ ቅሬታ ተዘጋጅቶ ለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት እስከቀረበበት እስከ ሰኔ 02 ቀን 2002 ዓ.ም ድረስ ያለው ጊዜ 21 ቀናት ብቻ በድምሩ 42 ቀናት ብቻ ያለፈ እንጂ በህጉ የተቀመጠውን የ60 ቀን ጊዜ የተላለፈ ሆኖ ባለማግኘታችን የአመልካች የይግባኝ ጉዲይ የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ካለፈ በኋላ የቀረበ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም በሚል የጋምቤላ ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍ/ቤት እና የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ሰበር ሰሚው ችልት የሰጡት ዲኝነት ድንጋጌውን በመተርጎም ረገድ ትክክለኛውን የትርጉም መስመር የተከተለ ሆኖ ስላላገኘነው የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።