No summary available.
መጋቢት 22 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ዲኜ መላኩ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ አባይነሽ ገ/ህይወት - ወኪል ወ/ት ትዕግስት ደመወዝ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ እታገኝ ደሣለኝ - አልቀረቡም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገብ ለሰበር የቀረበው ክርክር በፍትሐብሕር ክስ ክርክሩ ሉሰማ በተወሰነው ቀነ ቀጠሮ ከሣሽ ወገን አልቀረበም ተብል በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 መሰረት ተከሣሽ ተሰናብተዋል በተባለበት ጉዲይ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 74/2/ መሰረት እንደገና ክሱ እንዱታይ ሣይጠየቅ በቀጥታ ለይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ይግባኙ ቀርቦ ላታይ የሚችል ስለመሆን አለመሆኑ የሚመለከት ነው።
ክርክሩ የተጀመረው ደቡብ ጏንደር መስተዲደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሆኖ ከሣሽ የነበሩት የአሁኗ አመልካች ናቸው። ተከሣሾች የነበሩት ደግሞ ሀብታሙ ጌትነት እና የአሁኗ ተጠሪ ናቸው።
1ኛው ተከሣሽ ሀብታሙ ጌትነትና የአሁኗ ተጠሪ እናትና ልጅ ናቸዉ። ከሣሽ ሁለቱን እናትና ልጅ በአንድነት የከሰሷቸው ልጅየው ሰርቆ ወስዶል የተባለትን የተለያዩ የወርቅ ጌጣጌጦች ዋጋ ብር 13,49ዐ እንዱከፍሎቸው ነው። የአሁኗ ተጠሪ ልጃቸው ሰርቋል በተባለው ወርቅ ጉዲይ ገንዘቡን ሉከፍለ ይገባል ተብል የተከሰሱት በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 2125 መሰረት ሃላፉነት አለባቸው በሚል ምክንያት ነው። ሁለቱ ተከሣሾች ክሱ ደርሷቸው በጽሁፍ መልስ ሰጥተው በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 መሰረት ክርክሩ ሉሰማ በተወሰነው ቀነ ቀጠሮ ከሣሿ የአሁኗ አመልካች ባለመቅረባቸውና የአሁኗ ተጠሪም በጽሁፍ በሰጡት መልስ ሃላፉ ልሆን አይገባም ብለው ክደው በመከራከራቸው የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህንኑ ከፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 ጋር በማገናዘብ መርምሮ የአሁኗ ተጠሪ ሃላፉነት የለባቸውም ወደሚለው ጭምር የገባ ቢሆንም በእርሳቸው ላይ ክሱ አይቀጥልም ብል አሰናብቷቸዋል። በመጨረሻም ፍርድ በሚለው የተወሰነውና መዝገቡም ሣይዘጋ የቆየው አንደኛው ተከሣሽ በጽሁፍ በሰጠው መልስ ወንጀለን ስለመሰረቱ ማመኑ በፍትሐብሕር የቀረበበትን ክስም እንዲመነ ይቆጠራል ተብል በመወሰደ ሲሆን በተሰጠው ፍርድም በክሱ ለተጠየቀው ገንዘብ ሃላፉነት አለበት ተብል ተወስኗል። የአሁኗ አመልካች 2ኛዋ ተከሣሽ የአሁኗ ተጠሪ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 መሰረት ታይቶ ከከሱ እንዱሰናበቱ የተደረገበትን የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ፍርድ በመቃወም በቀጥታ ለአማራ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኙን አቅርበው ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙ እንዱቀርቡ አድርጏ ክርክሩን ከሰሙ በኋላ መርምሮ በሰጠው ውሣኔ የአሁኗን ተጠሪ በሚመለከት የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመጨረሻ አጠቃል በሰጠው ፍርድ ክርክሩ ሉሰማ በተቀጠረበት ቀነ ቀጠሮ ከሣሿ ስላልቀረቡና ተከሣሿም በጽሁፍ በሰጡት መልስ ክሱን ስለካደ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
73 መሰረት ታይቶ ተሰናብተዋል ስላለው ያነሣው ነገር ሣይኖር በቀጥታ ወደ ሃላፉነቱ ክርክር በመግባት በወቅቱ አካለመጠን ያልደረሰው ልጅ ለሰረቀው ወርቅ በፍትሐብሕር በኩል ስላለው ሃላፉነት የልጁ እናት የአሁኗ ተጠሪ በፍ/ብሓር ህግ ቁጥር 2125/1/ መሰረት ሃላፉነት አለባቸው ብል የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ፍርድ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት በመሻር ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ብር 13,490 ለአሁኗ አመልካች ሉከፍለ ይገባል በሚል ወስኗል።
ቀጥል ጉዲዩ የቀረበለት የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ደግሞ ክርክሩን መርምሮ በሰጠው ፍርድ የደቡብ ጏንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁኗ ተጠሪ በሚመለከት የክሱን መዝገብ የዘጋው በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 መሰረት ስለሆነ ከሣሽም የአሁኗ አመልካች በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.74/2/ መሰረት የክሱ መዝገብ ይከፈትልኝ የሚል ጥያቄ ሣያቀርቡ በቀጥታ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኙን ያቀረቡት ትክክል አይደለም፤ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤትም ወደ ፍሬ ነገሩ መግባት አልነበረበትም፤
ይግባኙን መቀበለም የስነስርዓት ህጉን የተከተለ አይደለም በማለት በዚሁ ስነስርዓት ምክንያት የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ፍርድ አጽንቶታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የአማራ ክልላዊ መንግስት የጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት በህገ መንግስቱ አንቀጽ 8ዐ/3/ መሰረት የቀረበ ሲሆን ጉዲዩም ለሰበር ችልት የሚያስቀርብ ነው በመባለ ግራ ቀኙ እንዱቀርቡ ተደርጏ መልስ እና የመልስ መልሱን በጽሁፍ በመለዋወጥ ክርክራቸውን አድርገዋል።
ጉዲዩም ከህጉ ጋር ተገናዝቦ ተመርምሯል።
No topics extracted.
ክሱን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው የደቡብ ጏንደር መስተዲደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሁለተኛ ተከሣሽ የነበሩት የአሁኗን ተጠሪ በሚመለከት የክሱን መዝገብ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 መሰረት ነው የዘጋው ለማለት ይቻላል አይቻልም? የአሁኗን ተጠሪ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 መሰረት ነው ያሰናበታቸው የሚባል ሆኖ ከተገኘስ ከሣሽዋ የአሁኗ አመልካች በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 74/2/ መሰረት የመዝገብ ይከፈትልኝ ጥያቄ ሣያቀርቡ በመጨረሻ በተሰጠው ፍርድ መነሻ በቀጥታ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ማቅረቡ ስነስርዓት ህጉን የተከተለነው የሚባል ነው ወይንስ አይደለም? የሚለውን በተመለከተ፡ከሣሽ የሆኑት የአሁኗ አመልካች በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 መሰረት ክርክሩ በቃል ሉሰማ በተወሰነው ቀነ ቀጠሮ ሣይቀርቡ መቅረታቸውንና ሁለተኛ ተከሣሽ የነበሩት የአሁኗ ተጠሪ ደግሞ በጽሁፍ በሰጡት መልስ ሃላፉ ልሆን አይገባም ብለው ክሱን ሙለ በሙለ በመካድ መከራከራቸውን የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመጨረሻ የሰጠው ፍርድ ከመዝገቡ ጋር ተያይዞ የቀረበው ኮፑው የሚያስረዲ ሲሆን ፍ/ቤቱ በዚህ ፍርድ ላይ የአሁኗን ተጠሪ ክድ የመከራከር ሁኔታ የተመለከተው የአሁኗ አመልካች ክርክሩ ሉሰማ በተቀጠረበት ቀነ ቀጠሮ ባለመቅረባቸው ከፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 ጋር በማያያዝ ነው። ፍ/ቤቱ በፍርደም ላይ የጀመረው ከሣሽ ለቃል ክርክር ስላልቀረቡ መዝገቡ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 መሰረት ተመርምሯል በማለት ነው። ቀጥልም 2ኛዋ ተከሣሽ በጽሁፍም ሆነ በቃል ሃላፉ ልሆን አይገባም ብለው ስለመከራከራቸው ከሣሽ ደግሞ በቃል ክርክሩ ላይ ቀርበው በዚህ ላይ ተቃውሞ እንዲላቀረቡ በመግለጽ 2ኛዋ ተከሣሽ ሃላፉነት የለባቸውም ብለናል በማለት ከክሱ አሰናብቷቸዋል። ከዚህም የአጻጻፍና የአገላለጹ ሁኔታ እንጅ 2ኛዋን ተከሣሽ የአሁኗን ተጠሪ የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ያሰናበታቸው በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 መሰረት መሆኑን መረዲት ይቻላል።
ላሰጥበት በማቆየቱ ነው። የአሁኗን ተጠሪ በሚመለከት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 መሰረት የክሱ መዝገብ ተዘግቷል ለማለት የሚቻል ሆኖ ስለተገኘ አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረቡት የሰበር ክርክር ተቀባይነት የሚሰጠው አይደለም። ተጠሪን በተመለከተ የክሱ መዝገብ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 መሰረት ተዘግቷል የሚባል ሆኖ ከተገኘ ከሣሽዋ የአሁኗ አመልካች በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 74/2/ መሰረት ጥያቄ በማቅረብ እንደገና መዝገቡ ተከፍቶ ነገሩ እንዱቀጥል ማድረግ ይኖርባቸዋል።
አመልካች ይህንን ሣይፈጽሙ ተጠሪ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 መሰረት በተሰናበቱበት ላይ በቀጥታ ይግባኝ ለማቅረብ የሚያስችላቸው ስነስርዓት የለም። የአማራ ክልላዊ መንግስት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔም ሲታይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አልተገኘም።
ው ሣ ኔ 1ኛ/ የአማራ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 0469 ሐምል 5 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
2ኛ/ ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።