No summary available.
ታህሣሥ 15 ቀን 2ዐዐ3 ዳኞች፡- ተሻገር ገብረሥላሴ ፀጋዬ አስማማው በላቸው አንሺሶ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ጭላል ሥራ ተቋራጭ የተወሰነ የግል ማህበር አልቀረበም ተጠሪ፡- አፍሪካ ኢንጅነርስ ኮንስትራክሽን ጠበቃ አቶ ተሰማ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው። የክርክሩ መነሻ የማሽነሪ ኪራይ ውል አፈፃፀምን የተመለከተ ነው ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት ከሣሽ በመሆን አንድ ግሬደር በሰዓት ሁለት መቶ ሃምሣ ብር ላንድሮለር በሰዓት ሁለት መቶ ብር አንድ ድዘር በሰዓት አራት መቶ ብር ሉከፍል የአሁን አመልካች /ተከሣሽ/ የወሰደ መሆኑን ገልፆ ያልተከፈለ የማሽነሪ ኪራይ ብር 1,327,5ዐዐ.ዐዐ/አንድ ሚሉዮን ሶስት መቶ ሃያ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር/ ያለበት ስለሆነ እንዱከፍለኝና ማሽነሪዎቹን እንዱያስረክበኝ በማለት ክስ አቅርቧል። አመልካች በተከሣሽነት ቀርቦ ከሣሽ /ተጠሪ/ የጠየቀው ማሽነሪዎቹ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በዝናብና በጎማ አለመኖር ለቆሙበት ሰዓት በመሆኑና የሰሩበት ሰዓት በሹፋሮቹ ተረጋግጦ የቀረበ ባለመሆኑ ክሱ ተገቢ አይደለም በማለት ተከራክሯል።
የከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሣሽ /ተጠሪ/ ያቀረበውን ክስ የሚያስረዲ ማስረጃ ያቀረበ በመሆኑና አመልካች /ተከሣሽ/ የኪራይ ገንዘብ ትክክል አይደለም በማለት ከሚከራከር በስተቀር ክርክሩን የሚያስረዲ ማስረጃ ያላቀረበ በመሆኑ አመልካች በክሱ የተጠቀሰውን ገንዘብ ለተጠሪ እንዱከፍል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት አመልካች ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚው ችልት ሑሣቡ በባለሙያ ተጣርቶ መቅረብ እንዲለበት በማመን አመልካች አንድ ባለሙያ ተጠሪ አንድ ባለሙያ እንዱመርጡና ሑሣቡን ሁለቱ ባለሙያዎች በጋራ አጣርተው እንዱያቀርቡ ትእዛዝ ሰጥቷል። ሁለቱ ባለሙያዎች በጋራ ሑሣብ እንዱያጣሩ የተሰጡትን ትእዛዝ ወደ ጎን በመተው አመልካች የመረጠው ባለሙያ ሑሣቡን ለብቻው በማጣራት አመልካች ለተጠሪ ያልከፈለው ብር 54,267.17 /ሀምሣ አራት ሺህ ሁለት መቶ ሥልሣ ብር ከአሥራ ሰባት ሣንቲም/ ነው በማለት የሑሣብ ሪፕርት ለብቻው ያቀረበ ሲሆን በተጠሪ የተመረጡት ባለሙያ በበኩላቸው አመልካች በተጠሪ ያልከፈለው ቀሪ ሑሣብ ብር 1,327,ዐዐ5 /አንድ ሚሉዮን ሦስት መቶ ሃያ ሰባት ሺህ አምስት ብር/ አለበት በማለት የብቻውን የሑሣብ ሪፕርት አቅርቧል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በአመልካች የተመረጠው ባለሙያ ያቀረበው ጥቅል የሑሣብ ሪፕርት መሆኑና በተጠሪ በኩል የተመረጡት ባለሙያ ዝርዝር የሑሣብ ሪፕርት ያቀረቡ መሆኑን በመግለጽ በተጠሪ የተመረጠው ባለሙያ ያቀረበው የሑባብ ሪፕርት አሣማኝነት አለው በማለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በማጽናት አመልካች ለተጠሪ ብር 1,327,ዐዐ5 እንዱከፍል ወስኗል።
አመልካች ባቀረበው የሰበር አቤቱታ ይግባኝ ሰሚው ችልት የኪራይ ሑሣቡ በባለሙያ ሣይጣራ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ መሰጠቱ በአግባቡ መሆኑን በማመን ሑሣቡ በባለሙያ እንዱጣራ ትእዛዝ ሰጥቷል። በባለሙያዎቹ ሑሣቡን በጋራ በማጣራት የሚስማሙባቸውን ሑሣብ ተስማምተው የተለያዩበትን ሑሣብ የልዩነታቸውን ምክንያት በመግለጽ በጋራ ማቅረብ ሲገባቸው ይግባኝ ሰሚው ችልት ከሰጠው ትእዛዝ ውጭ ለየብቻ ሰርተው ካቀረቡት ሪፕርት ውስጥ የአንደኛውን ባለሙያ ሪፕርት በመተው ላላውን ተቀብል የሰጠው ውሣኔ ስለ ልዩ አዋቂ ምስክር የተደነገገውን የማያሟላና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት አመልክተዋል። ለዚህ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ በቃል ክርክር ባቀረቡት መልስ ችልት ሑሣቡን በዝርዝርና በሚያሣምን ሁኔታ ሰርቶ ያቀረበለትን ባለሙያ በመቀበል ውሣኔ መስጠቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክረዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በጋራ ሑሣቡን እንዱያጣሩና ሪፕርት እንዱያቀርቡለት ትእዛዝ የሰጣቸው ባለሙያዎች ለየብቻ ሑሣብ በማጣራት ያቀረቡትን ሪፕርት በመቀበል የአንደኛውን ባለሙያ የሑሣብ መግለጫ ውድቅ በማድረግና የላላውን ትክክለኛ ነው በማለት ውሣኔ መስጠቱ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ከላይ የተያዘውን ጭብጥ እልባት ለመስጠት በአገራችን የሕግ ሥርዓት ልዩ አዋቂ ምስክር በፍርድ ቤቱ የሚሾምበትን ምክንያት በዝርዝር ማየት ያስፈልጋል። የኮመንልው የሕግ ሥርዓት በሚከተለ አገሮች ተከራካሪዎች ልዩ አዋቂ ምስክሮቻቸውን በራሣቸው የማቅረብና በተከራካሪዎች ምርጫና ክፍያ የማይቀርበው ልዩ አዋቂ ምስክር የቆጠራቸውን ተከራካሪ ሉረታ የሚችልበትን ሁኔታ ከሙያ አንፃር አቀነባብረው የሚያቀርቡ የሲቪል ልው በሚከተለ አገሮች የልዩ አዋቂ ምስክር የሚመድበው በፍርድ ቤት ሲሆን የልዩ አዋቂ ምስክሩ በማናቸውም ተከራካሪ ነፃና ገለልተኛ ሆኖ ከሙያ አንፃር ማጣራት የሚገባውን ነገር አጣርቶ ለፍርድ ቤቱ የሚያቀርብና የሙያ አበልም የሚታሰብለት በፍርድ ቤቱ በኩል እንደሆነ የሕግ ሥርዓቱን የሚከተለ የሥነ ሥርዓት ሕግጋት በማየት ለመረዲት ይችላል።
No topics extracted.
የአገራችን የሕግ ሥርዓት የሲቪል ልው የሕግ ሥርዓት የሚከተለ አገሮች የሚከተለትን መሰረታዊ መርህ የሚያራምድ ሲሆን አከራካሪ ጉዲይ የሚያጣሩ ልዩ አዋቂዎች /ባለሙያዎች/ ጉዲዩን አጣርተው እንዱቀርቡ የሚሾመው ፍርድ ቤቱ እንደሆነ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 136 ተደንግጓል። ፍርድ ቤቱ የሚሾማቸው ልዩ አዋቂ ምስክሮች ከተከራካሪዎቹ አንደኛውን ለመደገፍ ሣይሆን ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ትእዛዝ የሙያ ሥነ ምግባር የሚጥልባቸውን ግዳታ ተከትለው ገለልተኛ ሆነው ፍሬ ጉዲዩን በመመርመር ለፍርድ ቤቱ ሪፕርት የማቅረብ ግዳታ አለባቸው። በፍርድ ቤቱ የተመደቡ ልዩ አዋቂ ምስክሮች የሙያ ምግባር የሚጥስ ወይም ገለልተኛ በመሆን ከሙያ አንፃር ጉዲዩን መርምረው ማቅረባቸው አከራካሪ በሚሆንበት ጊዜ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩ በልላ ባለሙያ እንዱጣራ ማድረግ ይጠበቅበታል። በያዝነው ጉዲይ ይግባኝ ሰሚው ችልት ባለሙያዎቹን ሲመድብ ነፃና ገለልተኛ የሆኑ ባለሙያዎች በመምረጥ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 136/1/ መሰረት ባላቸው ልዩ የሑሣብ እውቀት ሑሣቡን መርምረው መመደብ ሲገባው አመልካች የራሱን ባለሙያ እንንዱያቀርቡ ማድረጉ ተገቢነት አልነበረውም። ይግባኝ ሰሚው ችልት ባለሙያዎቹ በጋራ ሑሣቡን ሰርተው እንዱያቀርቡ የሰጣቸውን ትእዛዝ ባለሙያዎቹ አላከበሩም።
ባለሙያዎቹ የፍርድ ቤቱ ልዩ አዋቂ ምስክር ሆነው ከተሰሙ በኋላ ከሁለም በላይ ለፍርድ ቤቱ ትእዛዝና መመሪያ ተገዥ በመሆን የሙያ ሥራቸውን ማከናወን አለባቸው የልዩ አዋቂ ሑሣብ አጣሪዎች የችልቱ ትእዛዝና በመመሪያ መጣስ አመልካች የመደበው ባለሙያ የአመልካችን ክርክር በመደገፍ የሑሣብ ሪፕርት ተጠሪ የመረጠው ባለሙያ ተጠሪን በመደገፍ የሑሣብ ሪፕርት አቅርበዋል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ሁለቱም ምስክሮች ችልቱ ከሰጣቸው ትእዛዝና መመሪያ ውጭ ሑሣቡን በተናጠል ሰርተው ሲያቀርቡለት የሁለቱንም ሪፕርት ውድቅ በማድረግ ሂሣቡ በልላ ባለሙያ ወይም ኦዱት ለማድረግ በተቋቋሙ ሕጋዊ ድርጅት በኩል ተጣርቶ እንዱቀርብ ትእዛዝ መስጠት ነበረበት። ይግባኝ ሰሚው ችልት በሰጣቸው ትእዛዝና መመሪያ ተመርተው ሑሣቡን ያላጣሩ መሆኑን እያወቀና ችልቱ ከሰጣቸው ትእዛዝ ውጭ ሁለቱም ባለሙያዎች በተናጠል የመሰላቸውን ሁለት የሂሣብ መግለጫ ካቀረቡለት በኋላ በአመልካች በኩል የተመረጠው ባለሙያ የቀረበው ጥቅል ሑሣብ ስለሆነ አሣማኝ አይደለም ከተጠሪ የተመረጠው ባለሙያ ያቀረበው ዝርዝር ሪፕርት ስለሆነ አሣማኝ ነው በማለት የሰጠው ውሣኔ ስለ ልዩ አዋቂ አጣሪ አመዲደብና አሰራርና የተዘረጋውን ሥርዓትና የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 136 ድንጋጌን የሚቃረን በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ብቃት ያለው ገለልተኛ የሑሣብ ባለሙያ ወይም ፈቃድ ያለው የኦዱት ድርጅት በመመደብ ሑሣቡ ተጣርቶ እንዱቀርብ በማድረግ ውሣኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343/1/ መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሣቸው ይቻለ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።