No summary available.
ጥቅምት 19 ቀን 2003ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- እነ አቶ ላሪ ሮላንድ ቻፔማን ጠበቃ ከድር ቡል ቀረበ ተጠሪ፡- አቶ ዜና ወልደማሪያም የቀረበ የለም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የሰበር አቤቱታ የቀረበው አመልካቾች በስር ፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በላለንበት ታይቶ የተሰጠው ውሳኔ ተነስቶ ክርክሩ ባለንበት ይታይልን በማለት ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ የተደረገው ያላግባብ ነው በሚል በጠበቃቸው አማልካኝነት መጋቢት 15 ቀን 2002ዓ.ም የተፃፈ ሶስት ገጽ የሰበር አቤቱታቸውን ስላቀረቡ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል የተጠሪ ጠበቃ ቀርበው ሐምል 13 ቀን 2002ዓ.ም በተፃፈ ሶስት ገጽ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል። በመልሳቸውም ላይ መጥሪያ በአግባቡ ደርሶ ተገቢው ሰው ለክርክር ሳይቀርብ በመቅረቱ ጉዲዩ በላለበት ታይቶ ውሳኔ የተሰጠ ስለሆነ እና በፍርደ መሰረት ከፉለም የተፈፀመ በመሆኑ የፍርድ አፈፃፀሙን ለማጓተት የቀረበ አቤቱታ በመሆኑ ውድቅ ላሆን የሚገባው መሆኑን ገልፀው የበታች ፍ/ቤቶች ውሳኔ ሉፀና ይገባል ሲለ ተከራክረዋል።
ይህ ችልትም ግራ ቀኙ በዚህ ችልት ያደረጓቸውን የጽሁፍ ክርክሮች ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደሚታወቀው የፍትሐብሕር ክርክሮች የሚመሩት በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ መሰረት ነው። ይኽው የሥነ ሥርዓት ሕግ አካቶ ከያዛቸው ጉዲዩች ውስጥ አንደ የተከራካሪ ወገኖች በክርክሩ ወቅት ያለመቅረብና ውጤቱ ነው። በዚህም መሰረት መጥሪያ ተልኮለት በተገቢው መንገድ የደረሰው መሆኑ በተረጋገጠበት ተከሳሽ ላይ ፍ/ቤቱ ሉከተለው የሚገባው ሥርዓት ጉዲዩ ተከሳሹ በላለበት የሚሰማበት ስለመሆኑ በፍ/ብሥ/ሥ/ሕ/ቁ 70/ሀ/ ስር ተመልክቷል። ላላው በሥነ ሥርዓት ሕጉ የተመለከተው ሥርዓት ተከሳሹ ሉከተለው የሚገባው መፍትሓ ነው። ክርክሩ በላለበት እንዱቀጥል የተደረገበት ተከሳሽ በተከታዩ ቀነ ቀጠሮ ቀርቦ በቂ ሆኖ በሚገመት እክል ምክንያት በመጀመሪያው ቀነ ቀጠሮ ያለመቅረቡን ካስረዲ መከላከያውን አቅርቦ የመከራከር መብት ያለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 72 ያስገነዝባል። እንዱሁም የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 78/1/ አንድ ተከሳሽ በክርክሩ ላይ ቀርቦ መልስ ሳይሰጥ ወይም ተገቢውን መከራከሪያ ሳያቀርብ በመቅረቱ በላለበት አንድ ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ የተሰጠ ከሆነ ውሳኔው ወይም ትዕዛዙ መሰጠቱን በተረዲው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ትዕዛዙ ወይም ውሳኔው እንዱነሳለት የማመልከት መብት እንዲለው ተደንግጓል። የዚሁ አንቀጽ ንዐስ ቁጥር 2 ደግሞ ተከሳሽ የጥሪው ትዕዛዝ በሚገባ ያልደረሰው መሆኑን ወይም ክርክሩ ሉሰማ በተቀጠረበት ቀን ቀርቦ መከራከሪያውን ያላሰማ ወይም መልስ ያልሰጠው በበቂ ምክንያት መሆኑን ለፍርደ ቤቱ ያስረዲ እንደሆነ ተከሳሹ በላለበት እንዱታይ የተሰጠው ብይን ወይም ትዕዛዙ እንደሚነሳለትና ክርክሩ እንደገና እንደሚሰማለት ይደነግጋል።
ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 78/1/ እና /2/ ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻለው ተከሳሽ በቀነ ቀጠሮ ያልቀረበው በበቂ ምክንያት መሆኑን ፍርድ ቤቱ ከተረዲው ተከሳሹ በላለበት ጉዲዩ እንዱታይ የተሰጠውን ትዕዛዝ ወይም ብይን በማንሳት ክርክሩ ተከሳሹ ባለበት እንዱቀጥል ማድረግ ያለበት መሆኑን ነው። የድንጋጌው ዓላማም የተከሳሹን የመከራከር መብት ለመጠበቅ መሆኑን መገንዘብ አያዲግትም። በመሆኑም ተከሳሹ ቀና ልቦና ያለው መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ በቂ ምክንያት የሚለው የድንጋጌው ሐረግ መታየትና መተግበር ያለበት የተለያዩ ነባራዊ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት የተከሳሹን የመከራከር መብት በሚጠበቅ መልኩ ነው። ወደተያዘው ጉዲይ ስመንለስም አመልካቾች በቀጠሮው ቀን ስላለመቅረባቸው ያቀረቡት ማስረጃ የቤተሰብ ጤና ችግር መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን የሥር ፍ/ቤትም ይህ ማስረጃ ተቀባይነት የለውም ወደሚለው ድምዲሜ አልደረሰም። የስር ፍ/ቤት በቀደመው ቀነ ቀጠሮ የቀረቡትን የአመልካቾችን ጠበቃ በፋዳራል ፍ/ቤቶች ለመቆም የሚያስችል የጥብቅና ፈቃድ የላቸውም በማለት ተገቢውን ፈቃድ አሟልተው እንዱመጡ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ጠበቃቸው አልቀረቡም። አመልካቾቹም በቤተሰባቸው የጤና መታወክ ችግር ምክንያት በተለዋጩ ቀነ ቀጠሮ አልቀረቡም። የስር ፍ/ቤት የአመልካቾችን ጉዲዩ ባለንበት ይታይልን ጥያቄ ውድቅ ያደረገው በጠበቃ መወከል ትችለ ነበር በሚል ምክንያት ነው።
No topics extracted.
በመሰረቱ በጠበቃ መወከል ግዳታ ሳይሆን መብት ነው። የስር ፍ/ቤት ከላይ እንደተገለፀው የአመልካቾች ቤተሰብ የጤና ችግር በወቅቱ መድረሱን ያረጋግጣል የተባለውን የህክምና ማስረጃ ተቀባይነት ሰጥቶ በጠበቃ መወከል ትችለ ነበር በሚል ምክንያት አመልካቾች በላለበት እንዱታይ የተሰጠውን ትዕዛዝ ሳያነሳ መቅረቱ የፍትሐብሕር ሥነ ስርዓት ዓላማንና የአመልካቾችን የመከራከር መብት ያላገናዘበ ሆኖ አግኝተናል። በመሆኑም የአመልካቾች ጠበቃ ተገቢውን ፈቃድ አልያዙም በሚል ምክንያት አመልካቾችን መወከል አይችለም ተብል ከተሰናበቱ በኋላና አመልካቾችም በቤተሰብ የጤና መታወክ ችግር ምክንያት በተለዋጬ ቀጠሮ አለመቅረባቸው ተረጋግጦ እያለ በተከራካሪ ወገን ፈቃድ ላይ የተመሰረተውን በጠበቃ የመወከል መብት እንደ አማራጭ በመውሰድ አመልካቾች ወደ ክርክሩ ሉገቡ አይገባም ተብል የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።