No summary available.
ጥር 26 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡
ተጠሪዎች፡-
ወ/ሮ መዓዛ አስፊው - አልቀረቡም።
አቶ ክብሮም ሙለ - አልቀረቡም።
አቶ አየለ ኮሮሶ - ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው። የክርክሩ መነሻ የፍርድ አፈፃፀምን የሚመለከት ነው። ተጠሪዎች ከድል የቆዲ ፊብሪካ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር ተከራክረው የፍርድ ባለመብት መሆናቸውን ገልፀው የአፈፃፀም መዝገብ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከፍተዋል። አፈፃፀሙን የያዘው የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፍርድ ባለዕዲው የሚገኝበት የምስራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በባለዕዲው ስም የሚገኘውን ንብረት በማሸጥ ብር 250,000 /ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ ለፍርድ ባለመብቶቹ እንዱያስከፍል በማለት በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 371 እና በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 392/1/ሀ መሰረት ውክልና ሰጥቷል።
ከዚህ በኋላ አፈፃፀሙ በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀጥሎል። የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቆዲ ፊብሪካ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ንብረት እንደሚሸጥ የጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል። በሀራጅ ማስታወቂያው መሰረት ሽያጭ ፈጽሟል። ስለ ሽያጭ ሑደቱም ውክልናውን ለሰጠው ፍርድ ቤት ሪፕርት አድርጓል። አመልካች በዕዲ የተሸጠው የእኔ ንብረት ነው ሽያጩ የተከናወነው የካቲት 14 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ነው። እኔ በማይመለከተኝ ዕዲ ንብረቴ መሸጡን ያወቅሁት ገዥው ስመ ንብረቱን ለማዛወር እንቅስቃሴ ሲያደርግ ነው። ስለዚህ የሀራጅ ሽያጩ እንዱሰረዝልኝ በማለት አመልክተዋል የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በሁለት መሰረታዊ ምክንያቶች ውድቅ አድርጏታል። የመጀመሪያው አቤቱታው መቅረብ ያለበት በውክልና ቤቱን ላሸጠው ለምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መሆን አለበት በማለት የፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 374 ንዐስ አንቀጽ 1ን በመጥቀስ የወሰነ ሲሆን፣ ሁለተኛው አቤቱታው ሽያጩ በተከናወነ በሁለት ወር ውስጥ በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 447 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት አቤቱታው አልቀረበም በማለት ነው። አመልካች በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበዋል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካች ይግባኝ ፍሬ ነጥብ የላለው መሆኑን በመግለጽ በፍታብሓር የሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች ግንቦት 13 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የጨረታ ማስታወቂያው የፍርድ ባለዕዲውን ስም በግልጽ መያዝ ሲገባው ‛የቆዲ ፊብሪካ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር“ በሚል ስያሜ በአዱስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ወጥቷል። የፍርድ ባለዕዲው በትክክል ባልተገለፀበት ሁኔታ የእኛ ንብረት ላይ የሃራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ ያወጣ መሆኑን አውቀን ልንከታተል እና በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 447/1/ በተደነገገው ጊዜ ውስጥ ሀራጁ እንዱሰረዝ ለማመልከት የምንችልበት ሁኔታ የለም። ስለዚህ የበታች ፍርድ ቤቶች ጥያቄያችንን ተቀብለው ሁኔታውን አጣርተው መወሰን ሲገባቸው ባለዕዲ ባልሆንበት ፍርድ ንብረታችን እንዱሸጥ መደረጉና ሽያጩ ይፀናል ማለታቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት አመልክተዋል።
ተጠሪዎች በበኩላቸው ጥያቄው መቅረብ ያለበት በውክልና ንብረቱን በሸጠው ፍርድ ቤት መሆን ይገባዋል። ይህንንም በተለያዩ ምሁራን የተፃፈ የህግ ትንታኔዎችን በማየት ለመገንዘብ ይቻላል። የምስራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዱሸጥ የታዘዘው በተለይ በአዋሳኝ የተገለፀው ቦታ የአመልካችን ንብረት አይደለም። የተሸጠው የባለዕዲው ንብረት ነው። አመልካች በስም ስህተት የእኔ ንብረት ነው የተሸጠው በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ተገቢ አይደለም በሀራጅ የተሸጠው ንብረት በእነ አዜብ ሙለ አውራሽ በአቶ ሙለ በአቶ ደረጃ ደመቀና በአቶ ስለሺ ሀይላ በተቋቋመው ድል የቆዲ ፊብሪካ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሥር የተያዘ ነበር። ይህ የንግድ ማህበር ሳይፈርስ እንደፈረሰ በማስመሰል ሉሲ ታነሪ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በሚል ስም ይዘነዋል እያለ የሚያቀርቡት ክርክር የህግ መሰረት የለውም በማለት ተከራክረዋል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው የጽሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች የሀራጅ ሽያጩ እንዱሰረዝ አቤቱታውን ማቅረብ ያለበት ሀራጁን እንዱያስፈጽም ለተወከለው ለምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥና የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 447 ንዐስ አንቀጽ 1 በተደነገገው የጊዜ ገደብ ውስጥ ጥያቄውን አላቀረበም በማለት የሰጡት ውሣኔ ለጉዲዩ አግባብነት ያለውን የህግ ድንጋጌ መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም? የሚለት ጭብጦች እልባት ማግኘት ያለባቸው ሆነው አግኝተናቸዋል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ይህንን ብይን መስጠት የነበረበት የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማብራሪያ እንዱሰጠው ከመጠየቁ በፉት አመልካች አቤቱታውን ወዱያውኑ እንዲቀረበ መሆን ነበረበት። የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የአመልካችን አቤቱታ ተቀብል ጉዲዩን ለማጣራት ረጅም ጊዜ ከወሰደ በኋላ አመልካች ወደ ምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቤቱታ እንዱያቀርብ መወሰኑ ተገቢ አይደለም። ከዚህ በተጨማሪ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዋቢነት የጠቀሰው የፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 374 ንዐስ አንቀጽ 1 አፈፃፀሙ በውክልና የሚያከራክረው ፍርድ ቤት የስልጣን ወሰንን የሚገልጽ እንጅ የሃራጅ ሽያጭ ተከናውኖ ካለቀ በኋላ ጉዲዩን በውክልና ካስፈፀመው ፍርድ ቤት ሙለ ማብራሪያ የተሰጠው ወካዩ ፍርድ ቤት የሀራጅ ሽያጩ ይሰረዝልኝ ጥያቄ ሲቀርብለት ጉዲዩን እንዲያከራክር እና ውሣኔ እንዲይሰጥ የሚከለክል ድንጋጌ አይደለም። ድንጋጌም ሁለቱም ፍርድ ቤቶች እኩልና አቻ ስልጣን ያላቸው መሆኑን የሚደነግግ ድንጋጌ ነው። ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤቶች አመልካች ያቀረበውን አቤቱታ ተቀብለው ውሣኔ የመስጠት ሥልጣን እንደላላቸው በመግለጽ የሰጠውን ብይን ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በያዝነው ጉዲይ የፍርድ ባለዕዲ የሆነው ድል የቆዲ ፊብሪካ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሲሆን በጋዜጣ የወጣው የሀራጅ ማስታወቂያ ‛የቆዲ ፊብሪካ ኃላፉነቱ የግል ማህበር“ በሚል ስያሜ መሆኑንና የሀራጅ ማስታወቂያው በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 423 በሚደነግገው መሰረት የፍርድ ባለዕዲውን ስም በትክክል የሚገልጽ አለመሆኑ ተረጋግጧል። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች ንብረቴ ነው የሚለው የማይንቀሳቀስ ንብረት በሃራጅ እየተሸጠ መሆኑን ለማወቅ የሚችልበት ሁኔታ የነበረ መሆኑን የሥር ፍርድ ቤት አላጣራም። የሀራጅ ማስታወቂያው በህጉ የተደነገገውን መስፈርት የማያሟላ በሆነበት ሁኔታ የሀራጅ ሽያጩ በፍርድ ባለዕዲው ድል የቆዲ ፊብሪካ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ንብረት ላይ ሳይሆን በእኔ ንብረት ላይ ነው የሚለው የሚለውን የአመልካች ጥያቄ ለመወሰን አግባብነት ያለው የህግ ድንጋጌ የፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 447/1/ ሳይሆን የፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 453 ድንጋጌ ነው።
አመልካች የፊብሪካውን ስመ ንብረት ሐራጅ አሸናፉ ሆኖ ወደ ገዛው ሰው ለማዛወር የሚደርገውን እንቅስቃሴ በመቃወም ንብረቱ የፍርድ ባለዕዲው ሳይሆን የእኔ ሀብት ስለሆነ ልለቅ አይገባኝም የሚል አቤቱታ ማቅረብ እንደሚችል የፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 453 ንዐስ አንቅጸ 1 ይደነግጋል። የሥር ፍርድ ቤት የአመልካች አቤቱታ ለፍርድ ባለመብትና ንብረቱን ለገዛው ሰው እንዱደርስ በማድረግና ግራ ቀኙ የሚከራከሩበትን ቀነ ቀጠሮ በመያዝ ማከራከር እንዲለበት የፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 453 ንዐስ አንቀጽ 2 የሚደነግግ ሲሆን የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ህግ ቁጥር 453 ንዐስ አንቀጽ 3 መሰረት ተገቢ ነው የሚለውን ውሣኔ የማሰጠት ግዳታና ሀላፉነት አለበት። በያዝነው ጉዲይ የሥር ፍርድ ቤት የአመልካችን አቤቱታና ማስረጃ በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 453 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት በመቀበል የግራ ቀኙን ክርክር በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 453 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት በመስማት በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 453 ንዐስ አንቀጽ 3 መሰረት መወሰን ሲገባው ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን የፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 447 ንዐስ አንቀጽ 1 በመጥቀስ የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የአመልካችን አቤቱታና ማስረጃ እንደዚሁም የተጠሪዎችን መልስና ማስረጃ በመቀበልና የሚያቀርቡትን ክርክር በመስማት በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 453 ንዐስ አንቀጽ 3 መሰረት ውሣኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343/1/ መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.