No summary available.
ጥር 09 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ማሞ ደምሴ ወኪል ወ/ት አዱስ ማሞ ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 349 መሰረት የሚቀርበውን የተወሰደ ነገር የማስመለስ ጥያቄንና አፈፃፀሙን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በአሁኑ ተጠሪዎች ላይ በሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግስት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው።
የክሱ ይዘትም ባጭሩ በሐረር ከተማ ቀበላ 14 ውስጥ የቤት ቁጥር 700 የሆነ መኖሪያ ቤትን በሚመለከት ክርክር ላይ የነበሩ መሆኑንና ክርክሩም በመ/ቁጥር 84/88 ታይቶ በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቤቱን የአሁኑ አመልካች ለ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች እንዱያስረክቡ የሚል ውሳኔ ተስጥቶ ፍርደ እንዱፈፀም በመ/ቁጥር 14/90 በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ቤቱን አመልካች ያስረከቡ ቢሆንም በቀጥታ ክስ ላይ በተሰጠው ውሳኔ የአሁኑ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ በጉዲዩ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ በመ/ቁጥር 5390 ጥር 29 ቀን 1999 ዓ.ም ሙለ በሙለ መሻሩን በመግለፅ ቤቱን ተጠሪዎች መልሰው እንዱያስረክቡ ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ 3ኛ ተጠሪ ጉዲዩ ቀደም ብል በፍርድ ያለቀ ነው፣ አመልካች በቤቱ ላይ መብት ወይም ጥቅም የላቸውም (ባለቤት አይደለም)፣ ቤቱን በሕግ አግባብ በተደረገ የሽያጭ ውል ከባለቤቶቹ ገዝቼ ቤቱን በመረከብ ስመሃብቱን በማዛወር እየተጠቀምኩ የምገኝ በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክረዋል። የስር ፍርድ ቤትም የ3ኛ ተጠሪን ክርክር ባለመቀበል ውድቅ አድርጎ ቤቱን ለአሁኑ አመልካች ሉያስረክቡ ይገባል ሲል ብይን ሰጥቷል። በዚህ ብይን የአሁኗ 3ኛ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። ከዚህም በኋላ 3ኛ ተጠሪ ይግባኛቸውን ለሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ፍርድ ቤቱ በጉዲዩ ላይ በተለያዩ ጊዜያትና በተለያዩ መዛግብት የቀረቡትን ክርክሮችና የተሰጡትን ውሳኔዎችን ይዘት በመመርመር ለአሁኑ አመልካች መብት የሚሰጥ ውሳኔ አለመሰጠቱን እና የአሁኗ 3ኛ ተጠሪ ቤቱን በሕግ አግባብ መግዛታቸውን በመግለፅ የበታች ፍርድ ቤቶችን ብይን ሽሮ አመልካች ቤቱን የሚረከቡበት አግባብ የለም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች መጋቢት 04 ቀን 2001 ዓ.ም በተጻፈ ሶስት ገፅ የሰበር አቤቱታ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ የቤት ሽያጭ ውል ይፍረስ ጥያቄ ቀርቦ በበላይ ፍርድ ቤት በተሰጠው ውሳኔ ተጠሪዎች ይግባኝ ብለው ተቀባይነት ባላገኙበት ሁኔታ 3ኛ ተጠሪ ቤቱን በሕግ አግባብ ገዝተዋል ተብል የተሰጠው ውሳኔ ሥነ ሥርዓታዊ ባለመሆኑ ሉሻር ይገባዋል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል ለተጠሪዎች በተገቢው መንገድ ጥሪ ሲደረግ 1ኛና 2ኛ ተጠሪዎች ሳይቀርቡ በመቅረታቸው ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን 3ኛ ተጠሪ ግን ቀርበው የጽሐፍ መልሳቸውን ታህሳስ 07 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ ሰጥተዋል። አመልካችም 3ኛ ተጠሪ ባቀረቡት መልስ ላይ የመልስ መልሳቸውን በጽሐፍ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም ጉዲዩን በበታች ፍርድ ቤቶች ከተደረጉት ክርክሮችና ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እንዱሁም አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደመረመረውም የችልቱን ምላሽ የሚያስፈልገው አብይ ነጥብ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ወይስ አልተፈፀመም የሚለው ሁኖ አግኝቶታል። ለዚሁ ጭብጥ ምላሽ ለመስጠት ይቻል ዘንድም በጉዲዩ ላይ የተደረጉትን ክርክሮችን በእየእርከኑ ባለት ፍርድ ቤቶች የተሰጡትን ውሳኔዎችን መመልከቱ አስፈላጊ ነው።
No topics extracted.
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የአሁኑ አመልካች ከአቶ አያላው ገ/እግዚአብሓር (ከአሁኑ 1ኛ ተጠሪ) ጋር ያደረገው የቤት ሽያጭ ውል እንዱጸድቅላቸው ስመ ሀብቱ እንዱዞርላቸው ይወሰን ዘንድ በጊዜው ለነበረው ፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርበው አቤቱታ የቀረበለት ፍርድ ቤቱም ተቃዋሚ ካለ እንዱቀርብ በጋዜጣ ጥሪ አድርጎ ባለመቅረቡ ውለን በማፅደቅ ስመ ሀብቱ በአሁኑ አመልካች እንዱዞር ውሳኔ የሰጠ ሲሆን በዚህ ውሳኔ መሰረት ከመፈፀሙ በፉት ቤቱን ሸጠ የተባለው ግለሰብ፣ የግለሰቡ ሚስት(ወ/ሮ ታየች ብርሃኑ) እና የአሁኗ 3ኛ ተጠሪ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት ፍርደን በመቃወም አቤቱታ አቅርበው ፍርድ ቤቱም የተቃውሞ አቤቱታቸውን በመቀበል ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ የቤት ሽያጭ ውለ ሻጭ የሆኑትን ግለሰብ (አቶ አያላው ገ/እግዚአብሓር) ሚስት ወ/ሮ ታየች ብርሃኑ ፈቃድ የላለበት በመሆኑ ፈራሽ ነው በሚል የቀድሞውን ውሳኔ በመሰረዝ ወስኗል። ከዚህም በኋላ የአሁኑ አመልካች ይግባኛቸውን ለክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቢያቀርቡም ተቀባይነት ባያገኙም የሰበር አቤቱታቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበው ጉዲዩ ከታየ በኋላ አመልካች መጀመሪያውኑ የቤት ሽያጭ ውል ይፅደቅልኝ በማለት ለአውራጃ ፍርድ ቤት ያቀረቡት አቤቱታ የክስ ምክንያት የላለው ነው በሚል ምክንያት መዘጋት ሲገባው ጉዲዩ መታየቱ ያላግባብ ነው በሚል ምክንያት በበታች ፍርድ ቤቶች የሽያጭ ውለ ፈራሽ ነው ተብል የተሰጠው ውሳኔ ተሽሯል። ይህ በእንዱህ እንዲለ አመልካች ውለ በፍርድ ቤት ውሳኔ ይጽደቅልኝ በማለት ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ቤቱን ተረክበው የነበሩ ሲሆን ውለ ፈራሽ ነው ተብል ከተወሰነ በኋላ የአሁኑ 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ቤቱን አመልካች ያስረክበን በሚል ጥያቄ አቅርበው ፍርድ ቤቱ አመልካች ቤቱን ለእነዚህ ተጠሪዎች እንዱያስረክቡ በማለት ግንቦት 26 ቀን 1989 ዓ.ም ውሳኔ ሰጥቶ በዚህ ውሳኔ መሰረት የአፈጻጸም መዝገብ ተጠሪዎች አቅርበው አመልካች ቤቱን ለተጠሪዎች መስከረም 20 ቀን 1990 ዓ.ም አስረክበዋል። ከዚህም በኋላ 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በጋራ ሁነው ለአሁኗ 3ኛ ተጠሪ ሰኔ 17 ቀን 1984 ዓ.ም በተደረገና ሐምል 22 ቀን 1984 ዓ.ም በፍርድ ቤት በተመዘገበ የሽያጭ ውል ቤቱን ሽጠው 3ኛ ተጠሪ ቤቱን በመረከብ ስመ ሀብቱን ሁለ አዙረው መጠቀም ቀጥለዋል።
ይሁን እንጂ ግንቦት 26 ቀን 1989 ዓ.ም 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ያገኙት ፍርድ በአሁኑ አመልካች ይግባኝ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርቦበት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ የስረ ነገር ሥልጣን ሳይኖር የተሰጠ ውሳኔ ነው በሚል ምክንያት የተሻረ ሲሆን የአሁኗ 3ኛ ተጠሪም በዚህ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቀርቦበት ተቀባይነት ያላገኘ መሆኑን ችልቱ ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ ችሎል። ከዚህ በኋላ ነው እንግዱህ የአሁኑ አመልካች አከራካሪው ቤት ላይ የስር ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ በበላይ ፍርድ ቤት የተሻረ ስለሆነ ተጠሪዎች በፍርድ ኃይል የተረከቡትን ቤት መልሰው ያስረክቡኝ በሚል ጥያቄ ያቀረቡት።
በመሰረቱ የተወሰደ ነገር ለማስመለስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 349(1) መሰረት አቤቱታ የሚቀርበው ይግባኝ የተባለበት ፍርድ ወይም ውሳኔ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተለወጠ ወይም የተሻሻለ የሆነ እንደሆነ ሲሆን ይኸው ሲረጋገጥ ማናቸውም ተከራካሪ ወገን ነገሩን በመጀመሪያ ደረጃ ላየው ፍርድ ቤት ሲያመለክት የተሻሻለው ወይም የተለወጠው ፍርድ ከመሰጠቱ በፉት ክርክር የተነሳበት ነገር ወደ ነበረበት ሁኔታ ለመመለስ እንዱችል በመጀመሪያው ፍርድ መሰረት የተወሰደው ንብረት ወይም ገንዘብ ለባለመብቱ እንዱመለስ ወይም የተከራካሪዎቹ ወገኖች መብት በይግባኙ ፍርድ መሰረት እንዱስተካከል ተስማሚ መስል የታየውን ትዕዛዝ ፍርድ ቤቱ መስጠት ያለበት መሆኑ በዚሁ ድንጋጌ ስር ተመልክቷል። ተጠቃሹ የንዐስ ቁጥር 3 ድንጋጌ ስር አቤቱታው የሚቀርብበትን ሥርዓት አስቀምጧል። ይኸውም ለማስመለስ የሚቻለውን ሀብት ወይም ለማስተካከል የሚቻለውን መብት ለማስፈጸም ላላ የክስ መዝገብ መክፈት አስፈላጊ አለመሆኑ በሕጉ ተመልክቷል። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 349(1) መሰረት የተወሰደን ንብረት ለማስመለስ መሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ በይግባኝ መሻሻል ወይም መለወጥ እና ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ንብረት ይመለስልኝ የሚለው አቤቱታ አቅራቢ የንብረቱ ባለመብት መሆን መረጋገጥ ስለመሆናቸው ከድንጋጌው ይዘትና መንፈስ መገንዘብ የምንችለው ነጥብ ነው።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካች ቤቱን ከ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪ በግዥ አግኝቼአለሁ፣ እነዚህ ተጠሪዎች ቤቱን የተረከቡበት ፍርድ በበላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሽሯል ቢለም አመልካች በየትኛውም የክርክር መስመር ወይም ደረጃ የአከራካሪው ቤት ባለንብረት መሆናቸው ተረጋግጦ የተሰጠ ፍርድ የላለ መሆኑን ከላይ የተመለከተው የክርክሩ አመጣጥ በግልፅ ያሳያል።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 349 መሰረት አቤቱታ የሚያቀርበው ወገን ደግሞ የንብረቱ ባለመብት የሆነ መሆኑን ሉያረጋግጥ ይገባል። የአሁኗ 3ኛ ተጠሪ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት ውሳኔ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የስረ ነገርን ስልጣን መሰረት ባደረገ ምክንያት በመሻሩ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበው ተቀባይነት ያለማግኘታቸውም የአሁኑን አመልካች የአከራካሪው ቤት ሕጋዊ ባለንብረት ናቸው ወደሚለው ድምዲሜ ሉያደርስ የሚችል ሕጋዊ ምክንያት አይደለም። ይልቁንም 3ኛ ተጠሪ የቤቱ ሕጋዊ ባለቤት ናቸው ከተባለት ከአሁኑ 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች (ባልና ሚስት) ቤቱን ከአመልካች ከተረከቡ በኋላና አመልካችም በየደረጃው በነበሩት ፍርድ ቤቶች ክርክር ሲያደርጉ በቤቱ ላይ በሕጉ አግባብ የእግድ ትዕዛዝ ባላሰጡበት ሁኔታ ስልጣን ባለው አካል ፉት በሕጉ አግባብ በተደረገው የሽያጭ ውል ቤቱን ገዝተውና ተረክበው እንዱሁም ስመ ሀብቱን በማዛወርና ለውጦችንም በማድረግ ለበርካታ ጊዜያት የሚጠቀሙበት መሆኑ መረጋገጡ ሦስተኛ ወገን የሆኑት ግለሰብ እጅ የገባን ንብረት አመልካች የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 349ን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ጥያቄ የማቅረብ መብት የላላቸው መሆኑን የሚያሳይ ነው።
አመልካች በሕጉ አግባብ ከ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ጋር ያደረጉት ግንኙነት ካለና በዚህ ግንኙነት መሰረት ወጪ ያደረጉት ገንዘብ ካለም እነዚህን ተጠሪዎች ከሚጠይቁ በስተቀር ቤቱን ከ3ኛ አመልካች ሉወስደ የሚችለበት አግባብ የለም። በመሆኑም የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጉዲዩ ላይ የሰጠው ውሳኔ በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡትን ፍሬ ጉዲዮችንና የትኛው ወገን ከቀድሞ ባለቤቶች ጋር ሕጋዊ ግንኙነት መስርቷል ከሚለው ጥያቄ ምላሽ እና ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 349 ድንጋጌ መንፈስና ይዘት ጋር ያገናዘበ ነው ከሚባል በስተቀር ሉነቀፍ የሚችልበትን መሰረታዊ የሕግ ነጥብ አላገኘንም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ታህሳስ 07 ቀን 2001 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።