No summary available.
ግንቦት 04 ቀን 1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ አብደልቃድር መሐመድ ጌታቸው ምህረቱ መስፍን ዕቁበዮናስ ሑሩት መለሰ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሃዋ መሐመድ
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የባለሙያ አስተያየት የመጨረሻ ማስረጃ (conclusive evidence) መሆን አለመሆኑን የሚመለከት ነው።
አመልካች ለም/ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ አቶ መሐመድ አብደራህማን ከባንኩ ለወሰደት ብድር ተጠሪ ንብረታቸውን በዋስትና ስላስያዙ ተበዲሪው በሚፈለግባቸው ዕዲ ተጠሪ በዋስትናቸው መሰረት ግዳታቸውን እንዱወጡ ጠይቋል። ተጠሪም የገቡት የዋስትና ውል አለመኖሩን በመግለጽ የተከራከሩ ሲሆን ፍ/ቤቱም በዋስትና ሰነደ ላይ ያለው ፊርማ የተጠሪዋ አለመሆኑን በፕሉስ የቴክኒክ ምርመራ በመረጋገጡ ተጠሪ ሉጠየቁ አይችለም በማለት ወስኗል።
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤትም ይግባኙን ባለመቀበል መዝገቡን ዘግቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። ይህ ችልትም በባለሙያ የሚሰጥ አስተያየት የመጨረሻ ማስረጃ (conclusive evidence) ነው ወይ? የሚለውን የሕግ ነጥብ ለመመርመር ጉዲዩን ለሰበር ችልት አስቀርቧል። ግራ ቀኙም ክርክራቸውን በጽሐፍ ያቀረቡ ሲሆን ችልቱም አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ ከተገቢው ሕግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
በዚህ መዝገብ ዋነኛው አከራካሪ የሆነው ተጠሪ ንብረታቸውን በማስያዝ የዋስትና ግዳታ የመግባታቸው ጉዲይ ነው። አመልካች ተጠሪዋ ለተሰጠው ብድር የዋስትና ግዳታ መግባታቸውን ለማስረዲት የዋስትና ሰነደን እንዱሁም ምስክሮችን አቅርቧል። ምስክሮቹም ተጠሪ በዋስትና ውለ ላይ የፈረሙ ለመሆኑ ባል የላላቸው መሆኑን ከቀበላ ማስረጃ አቀርበው እንደነበር አረጋግጠዋል።
ነገር ግን ተጠሪ ፊርማውን የካደ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ፊርማው በፕሉስ የቴክኒክ ምርመራ ክፍል እንዱመረመር አድርጎ በሰነደ ላይ ያለው ፊርማ የተጠሪዋ አለመሆኑን የሚያረጋግጥ ውጤት ለፍ/ቤቱ ቀርቧል። ፍ/ቤቱም ፊርማው የተጠሪ አለመሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ስለቀረበ የሰው ማስረጃው ፊይዲ ከላለው መሰማታቸው ስህተት ነው በማለት የመስክሮቹን ቃል ሙለ በሙለ ውቅድ በማድረግ ተጠሪን ከተጠያቂነት ነፃ አድርጓቸዋል። በዚህም ምክንያት የባለሙያ አስተያየት ተቃራኒ ማስረጃ ላቀርብበት የማይችል የመጨረሻ ማስረጃ መሆን አለመሆኑን መመርመሩ አስፈላጊ ነው።
በአገራችን ራሱን የቻለ የማስረጃ ሕግ ባለመኖሩ በዚህ ጉዲይ በቀጥታ ተፈፃሚነት ያለው ድንጋጌ ሉጠቀስ ባይችልም በላልች አገሮች ተቀባይነት ካገኘው የማስረጃ ሕግ መርህ ግን መረዲት የሚቻለው የባለሙያ አስተያየት ብቻውን ለመቆም የሚችል ወይም በተቃራኒ ማስረጃ ሉስተባበል የማይችል ሳይሆን ይልቁንም ከላልች ማስረጃዎች ጋር ተገናዝቦ ብቃቱና ተአማኒነቱ ሉመዘን የሚገባ መሆኑን ነው። ምክንያቱም ምንም እንኳን በባለሙያ አስተያየቱ መሰረት የሚያቀርበው የሣይንሳዊ ጥናትና ምርመራ ውጤትን ቢሆንም ሣይንስ በራሱ ፍፁም እርግጠኛነት የላለውና ሙለ እምነት የሚጣልበት አይደለም። ይህም በመሆኑ የባለሙያ አስተያየት ብቻ እንደበቂ ማስረጃ ተቆጥሮ ላልች ማስረጃዎችን ያለበቂ ምክንያት ተቀባይነት ማሳጣቱ ወደ ተሣሣተ መደምደሚያ ሉያደርስ የሚችል ይሆናል።
በተያያዘው ጉዲይም ቢሆን ፍ/ቤቱ የቀረበለትን የፕሉስ ምርመራ ውጤት ብቻ ተቀብል የምስክሮቹ ቃል ተቀባይነት ወይም ተአማኒነት ሉያጣ የሚገባበትን በቂ ምክንያት ሣይገልፁ የምርመራ ውጤቱ በመቅረቡ ብቻ በደፈናው የሰው ማስረጃ ፊይዲ የለውም በማለት የደረሰበት መደምደሚያ ስህተት መሆኑን ተረድተናል።
በልላ በኩል ፍ/ቤቱ ከግራ ቀኙ የቀረቡትን ማስረጃዎች እንዱሁም ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት ጠቃሚ ነው የሚለውን ማስረጃ አስቀርቦ መመርመር የሚችል ቢሆንም የጠሪን ምስክሮች እንዱቀርቡ በማድረግ የምስክርነት ቃላቸውን ከሰማ በኋላ የባለሙያ አስተያየት በመቅረቡ ብቻ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 207 መሰረት የምስክርነት ቃለን ውድቅ ማድረጉ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን የተከተለ አካሄድ አልነበረም። ምክንያቱም የተጠቀሰው የሥነ-ሥርዓት ሕጉ ድንጋጌ ከሥነ-ሥርዓት ውጪ ክስ ሲቀርብ ወይም በክሱ ውስጥ ከደንብ ውጪ የሆነ ተግባር ሲፈፀም ስህተቱን ለማረም የተቀመጠ ነው። በተያዘው ጉዲይ ግን ምስክሮቹ በአመልካቹ የተቆጠሩ በመሆናቸው ቀርበው መሰማተቸው ስህተት አልነበረም። በአመልካች ባይቆጠሩ እንኳን ፍ/ቤቱ ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት ጠቃሚ ናቸው ብል ካመነ እንዲይሰሙ የሚከለክል ሥርዓት የለም /የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 264 ይመለከቷል/። በመሆኑም ፍ/ቤቱ ምስክሮቹ የሰጡት ምስክርነት ተአማኒነት የለውም ካለ ይህንኑ ገልፆ ውድቅ ከሚያደርገው በቀር ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን የሥነ-ሥርዓት ድነጋጌ መሰረት በማድረግ የሰው ማስረጃውን ውድቅ ማድረጉ ስህተት ነው።
No topics extracted.
በአጠቃላይ የስር ፍ/ቤቶች የባለሙያ አስተያየቱን እንደመጨረሻ ማስረጃ (conclusive evidence) አድርገው በመውሰድ የሰው ማስረጃውን ውድቅ በማድረጋቸው የሕግ ስህተት ፈጽመዋል።
ው ሣ ኔ 3. የም/ሸዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 24190 ግንቦት 28/1995 የሰጠው ውሣኔ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 00894 ታህሣስ 13/1996 የሰጠው ትዕዛዝ ተሽረዋል።
ተጠሪ በዋስትና ባስያዙት ንብረት ግምት ልክ ለሚፈለገው የዕዲ መጠን ተጠያቂ ናቸው።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።