No summary available.
15/3/2ዐዐ2 ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡- አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግልት ድርጅት ነ/ፈጅ ፊሲካ በለጠ ተጠሪ፡-
ይህ ጉዲይ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች በተጠሪዎችና በሥር 3ኛ ተከሣሽ ላይ በቀረበው ክስ የሰ.ቁ. 3-153ዐ6 የሆነውን የከተማ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ንብረትነቱ የ1ኛ እና 2ኛ ተከሣሾች የሆነ መኪና በ3ኛ ተከሣሽ አማካይነት ሲሽከረከር በፈጸመው ጥፊት በከሣሽ አውቶቡስ ላይ ጉዲት ደርሷል። ከሣሽ አውቶቡሱን ብር 43,392.55 ወጭ አድርጎ ከማሰራቱም በላይ መኪናው ለጥገና በመቆሙ ብር 68,742.52 ከሣሽ ገቢ ሳያገኝ ቀርቷል። በመሆኑም ተከሣሾች ባልተነጣጠለ ኃላፉነት ብር 112,149.67 ከነወለደ እንዱከፍለ ይወሰንልን በማለት ጠይቋል።
2ኛ እና 3ኛ ተከሣሾች ቀርበው 1ኛ ተከሣሽ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ገልጸው አደጋው የደረሰው በ3ኛ ተከሣሽ ጥፊት ሳይሆን የከሣሽን መኪና ሲያሽከረክር የነበረው ሾፋር በፈፀመው ጥፊት ስለሆነ ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል። የተጠየቀውም የካሳ መጠን የተጋነነ ነው በማለት መልስ ሰጥተዋል። ከዚህም በተጨማሪ 2ኛ እና 3ኛ ተከሣሾች /የአሁን ተጠሪዎች/ የተከሣሸ ከሣሽነት ክስ አቅርበው አደጋው የደረሰው የከሣሽን መኪና ሲያሽከረክር በነበረው ሹፋር ጥፊት ስለሆነ የእኛ ንብረት በሆነው የሰ.ቁ. 1-01766 መኪና ላይ ጉዲት የደረሰ ስለሆነ ለእጅ ዋጋ፣ ለመለዋወጫና የተቋረጠ ጥቅም በድምሩ ብር 16,9ዐዐ የከሣሽ ተከሣሽ እንዱከፍል ይወሰንልን በማለት ጠይቀዋል።
የከሣሽ ተከሣሽም ጉዲቱ የደረሰው በተከሣሽ ተከሣሾች ሹፋር ጥፊት ስለሆነ ካሣ የመክፈል ግዳታ የለብኝም በማለት መልስ ሰጥቷል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ማስረጃ ከሰማ በኋላ ከሣሽ በማስረጃነት ያቀረበው የፕሉስ የምርመራ መዝገብ በአደጋው ቦታ በተነሳው ኘላን መሰረት ጥፊቱ የ3ኛ ተከሣሽ እንደሆነ ያስረዲል።
በልላ በኩል ተከሣሾች ያሰሟቸው ምስክሮች አደጋው የደረሰው የተከሣሾች መኪና በቆመበት የከሣሸ መኪና መትቶ በመግጨቱ መሆኑን በቦታው ተገኝተው በዓይናቸው እንዲዩ ገልጸዋል። የከሣሽ ማስረጃ የፕሉስ ምርመራ ሪፕርት ከአደጋው በኋላ ከነበረው ሁኔታ የተዘጋጀ በመሆኑ እና የተከሣሾች ማስረጃ ደግሞ በቦታው የነበሩ ሰዎች ቃል ስለሆነ ፍ/ቤቱ በተከሣሾች ማስረጃ ላይ የበለጠ እምነት ጥል አደጋው የደረሰው የከሣሽን መኪና ሲያሽከረክር በነበረው ሾፋር ጥፊት ስለሆነ ከሣሽ ኃላፉ ነው ካለ በኋላ የካሳ ክፍያውን መርምሮ ተከሣሾች በአደጋው ምክንያት ብር 9,6ዐዐ ጥቅም ተቋርጦብናል ቢለም ይህንን የሚያስረዲ ማስረጃ አላቀረቡም ነገር ግን መኪናው የታክሲ አገልግልት የሚሰጥ እንደመሆኑ መጠን ገቢ ሉቋረጥ እንደሚችል ስለሚታመን በርትዕ ብር 2,000 ሺህ እንዱከፍል ለእጅ ዋጋና ለመለዋወጫ የተከፈለን በተመለከተ ተከሣሾች ማስረጃ ያቀረቡ ስለሆነ ይህንኑ ጨምሮ በጠቅላላው ብር 1ዐ,3ዐዐ ከወጭና ኪሣራ ጋር ከሣሽ ለ2ኛ እና 3ኛ ተከሣሾች እንዱከፍል ወስኗል። ከሣሽ በዚህ ውሣኔ ቅሬታ አድሮበት የይግባኝ ቅሬታውን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ተከራክረው ፍ/ቤቱ የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ ጉድለት የላለው ነው በማለት አጽንቶታል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህም ችልት አቤቱታውን መርምሮ 2ኛ ተጠሪ በትራፉክ ፕሉሱ ኘላን ላይ ጥፊታቸውን በማመን በሰነደ ላይ በፈረመበት ሁኔታና የተሽከርካሪው ባለቤት ናቸው የተባለትም ጥፊቱን በመቀበል በካሳው መጠን ላይ ከአመልካች ጋር ለመደራደር ጥያቄ ማቅረባቸው በተረጋገጠበት ሁኔታ ጥፊት የፈፀመው የአመልካች ሾፋር ነው ተብል መወሰኑ አግባብነቱ ለሰበር ቀርቦ ሉመረመር እንደሚገባው በማመኑ ተጠሪዎችን በመጥራት ግራ ቀኙን አከራክሯል።
በአጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከፍ ብል የተመለከተው ሲሆን አመልካች በተጠሪዎች ላይ ያቀረበው ክስ በሥር ፍ/ቤቶች ተቀባይነት ሳያገኝ የቀረው በአግባቡ ነው ወይንስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አመልካች ያቀረበውን ክስ ውድቅ በማድረግ በተጠሪዎች በኩል የቀረበውን የተከሣሽ ከሣሽነት ክሱ ተቀብል ውሣኔ የሰጠው ከፍ ብል እንደተመለከተው ተጠሪዎች ያሰሟቸው ምስክሮች አደጋው የደረሰው የተጠሪዎች መኪና በቆመበት የአመልካች መኪና መጥቶ በመግጨቱ መሆኑን በቦታው ስለነበሩ በዓይናቸው እንዲዩ የገለጹ ስለሆነና በአመልካች በኩል የቀረበው የባለሙያ ሪፕርት የተጠሪዎችን መኪና ሲያሽከረክር የነበረው ሹፋር ጥፊት መፈጸሙን ቢያረጋግጥም የምስክሮቹ ቃል ይበልጥ ዕምነት የሚጣልበትና ክብደት የሚሰጠው ነው በሚል ምክንያት ነው።
No topics extracted.
በማስረጃ ዓይነቶች ክፍፍል የአንድን ፍሬ ነገር መኖር ወይም አለመኖር ለማስረዲት ላቀርብ የሚችለት ማስረጃዎች ቀጥተኛ ማስረጃ /direct evidence/ ወይም የአካባቢ ማስረጃዎች /circusmstantial evidence/ ተብለው፣ ሉመደቡ የሚችለ ሲሆን ምስክሮች በስሜት ሕዋሳታቸው አማካይነት የተፈለገው ፍሬ ነገር መኖር ወይም አለመኖሩ እናውቃለን በማለት የሚሰጡት የምስክርነት ቃል ቀጥተኛ ማስረጃ ተብል ይወሰዲል። በልላ በኩል ደግሞ የአካባቢ ማስረጃ የላልች ፍሬነገሮችን መኖር ወይም አለመኖር በማስረዲት ለክርክሩ ግምት መውሰጃ መሰረት የሆነውን ፍሬ ነገር መኖር ወይም አለመኖር በተዘዋዋሪ መንገድ ለማስረዲት የሚቀርብ ማስረጃ እንደሆነ በመስኩ ከዲበረው ሥነ ሕግ /Jurisprudence/ መገንዘብ ይቻላል።
አመልካች ክሱን ለማስረዲት ያቀረበው ማስረጃ አደጋው ከደረሰ በኋላ በአደጋው ሥፍራ በተገኘ ባለሙያ /ኤክስፏርት/ አማካይነት የተዘጋጀ የባለሙያ ሪፕርት ነው። የባለሙያ ሪፕርት የኤክስፏርት ማስረጃ ተብል ሉወሰድ የሚችል ሲሆን አንድ ኤክስፏርት የሚሰጠው ቃል በፍ/ቤት እንዱረጋገጥ የተፈለገውን ጉዲይ በቀጥታ አይቻለሁ ወይንም ጉዲዩ በቀጥታ ሉረጋገጥ የሚችልበት በማንኛውም የስሜት አካልች አማካይነት ተረድቻለሁ በማለት ሳይሆን በሙያው ሉረጋገጡ የሚችለትን ነገሮች ተመራምሮ ውጤቱን ወይም ግኝቱን የሚገልጽ ስለሆነ የኤክስፏርት ማስረጃ በአካባቢ ማስረጃ ሥር ሉመደብ እንደሚችል ከዲበረው ሥነ-ሕግ መረዲት ይቻላል። የኤክስፏርት ማስረጃም ለፍ/ቤት በቀረበ ጊዜ ፍ/ቤቱ ይህን ማስረጃ ሳይጠረጥረው ባለበት ሁኔታ የሚቀበለው ሣይሆን እንደማንኛውም ማስረጃ የሚመዘን ነው።
የተጠሪዎች መኪና ቆሞ ባለበት በአመልካች መኪና የተገጨ ስለመሆኑ ተጠሪዎች የቆጠሯቸው ምስክሮች አረጋግጠዋል። በአመልካች በኩል የቀረበው የባለሙያ ሪፕርት ጥፊቱ የተጠሪዎችን መኪና ሲያሽከረክር በነበረው ሹፋር የተፈጸመ መሆኑ ቢረጋገጥም የባለሙያ ማስረጃ የኤክስፏርት ማስረጃ እንደመሆኑ መጠን ኤክስፏርቱ መጨረሻ ላይ የሚደርስበት መደምደሚያ /ግኝት/ ሙያዊ አስተያየት /opinion/ እንጂ ፍሬ ነገር /fact/ ላሆን አይችልም። የኤክስፏርቱ የሚደርስበት የመጨረሻ አስተያየት ከሚኖረው ሙያዊ ዕውቀት አድማስ ከሚታገዝበት መሣሪያና ከመሳሰለት ጋር የተሟላና ሙለ ዕምነት የሚጣልበት ማስረጃ /conclusive evidence/ ላሆን ስለማይችል በዓይን ምስክሮች የተነገረን ፍሬ ነገር ለማስተባበል የሚያበቃ አቅም አይኖረውም። ይህ ሰበር ችልትም ቀደም ሲል በሰበር መ.ቁ. 14981 የኤክስፏርት ማስረጃ ሙለ ዕምነት ሉጣልበት የሚችል ማስረጃ እንዲልሆነ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። ከዚህም ላላ የኤክስፏርት ማስረጃ በማስረጃነት በቀረበ ጊዜ ይበልጥ ተቀባይነት የሚኖረው ከቀጥተኛ ማስረጃ ጋር በተጣጣመ ጊዜ እንጂ ቀጥተኛ ማስረጃውን በሚፃረር ጊዜ የበለጠ ክብደት የሚሰጠው ለቀጥተኛ ማስረጃው ስለሆነ የኤክስፏርት ማስረጃው ተቀባይነት ሉኖረው እንደማይችል መገንዘብ ስለሚቻል የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት በቀጥተኛው ማስረጃ ላይ ተመስርቶ ጥፊት የተፈጸመው የአመልካችን መኪና ሲያሽከረክር በነበረው ሹፋር አማካይነት ነው ሲል የደረሰበት መደምደሚያ ከማስረጃ አቀራረብ መሰረታዊ መርህ አኳያ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት አልተቻለም።
በልላ በኩልም የተጠሪዎች ሾፋር ጥፊተኛ በተደረገበት በባለሙያ አስተያየቱ ላይ ፈርሞ መገኘቱ እንደዚሁም ተጠሪዎች ይህንኑ ተቀብለው ለአመልካች ካሣ ለመክፈል ተደራድረው ነበር መባለ የኤክስፏርት ማስረጃውን ከቀጥተኛ ማስረጃው የበለጠ ተቀባይነት ሉያደርገው ስለማይችል ውጤቱን ሉቀይረው የሚችል ሆኖ አላገኘውም።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. ዐ8549 በ28/6/2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ፍርድ እንደዚሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 674ዐ9 በ8/3/2ዐዐ1 ዓ.ም. የሰጠውን ፍርድ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 348/1/ መሰረት አጽንተነዋል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻለ ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።