No summary available.
29/09/2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሮ ራውዲ ሙሜ - ጠበቃ አበራ ማረኘ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አምባሳደር አብደላ አብደራህማን - ቀረበ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የባልና ሚስት ክርክር ሲሆን የተጀመረው በፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ ባቀረበው ክስ ነው። ቀርቦ የነበረው ክስ በአጭሩ በመካከላችን የነበረው ጋብቻ በፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት በመዝ.ቁ. 64296 ሚያዝያ 30 ቀን 1998 ዓ.ም በዋለው ችልት በሰጠው ውሣኔ ፈርሷል። የጋራ ንብረት ክፍፍልን በተመለከተ ተከሳሽ ካናዲ ቶሮንቶ ከተማ 4725 የቤት ቁጥር 1614 የሆነውን ኮንድምኒየም ተከሳሽ እንዱወስደና በአ/አበባ ን/ስል/ላ/ክ/ከተማ ቀበላ 05 የቤት ቁጥር 1775 የሆነውን ደግሞ ከሣሽ እንድወስድ የሚል ሃሳብ አቅርቤ ተከሳሽ ከሣሽ ያልተሳተፍኩበትን በካናዲ ፍ/ቤት የተሰጠ ውሣኔ በማቅረብ ለፍ/ቤቱ በማመልከታቸው በከፍተኛው ፍ/ቤት እንዱታይ የሚል ውሣኔ በመሰጠቱና በይግባኝም በመጽናቱ የቀረበ ነው። የተባለው የካናዲ ፍ/ቤት ውሣኔ ከሳሽ በላለበት የተሰጠ የጋራ ንብረቱን በሙለ ለአንደኛ ወገን የሚሰጥና የካናዲን ሕገ መንግስት የሚፃረርና ተቀባይነት የላለው በመሆኑ ከላይ ባቀረብኩት የክፍፍል ሃሳብ መሰረት እንዱወሰን በሚል ጠይቋል።
ክሱ ለተከሳሽ ደርሶ በሰጡት መልስ የከሳሽና የተከሳሽ ጋብቻ ከመፍረሱም በላይ የካናዲ ፍ/ቤት ሰኔ 23 ቀን 1998 ዓ.ም በዋለው ችልት በቀረበበት የንብረት ክርክር የካናዲውም ሆነ በአ/አበባ የሚገኘው ቤት ለተከሳሽ እንዱሰጥ የተባለ በመሆኑ አሁን የቀረበው ክስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 5 መሰረት ተቀባይነት የለውም በማለት የካናዲ ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ መሰረት አፈፃፀም የማቅረብ መብቴ ተጠብቆ የደረሰው ኪሣራ እንዱከፈለኝ በማለት ተከራክሯል።
የፋ/ከ/ፍ/ቤት ከላይ እንደተመለከተው ከክርክር በኋላ የፍች ውጤት መታየት የሚገባው ጋብቻ በተመሰረተበት ሀገር ህግ በመሆኑ እና በካናዲ ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ ሁለንም ንብረት ለአንድ ወገን ብቻ የተደረገ በመሆኑ በኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀጽ 34 መሰረት ባልና ሚስት በፍች ውጤት ላይ ያላቸውን እኩል ህገ መንግስታዊ መብት የሚነካ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት እኩል እንዱከፊፈለ ወስኗል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍርደ ቤቱም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 337 መሰረት አጽንቷል።
አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን አመልካች በጠበቃቸው አማካኝነት መጋቢት 3ዐ ቀን 2002 ዓ.ም በ2 ገጽ በፃፈት ማመልከቻ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
የቅሬታው ፍሬ ሃሳብ በዚህ ጉዲይ ቀድሞ በካናዲ ፍ/ቤት የተሰጠ ውሣኔ እያለ በማለፍ የበታች ፍ/ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ እንድሻርልን የሚል ነው። ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ በጠበቃ በኩል ጥቅምት 29 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ 2 ገጽ መልስ በካናዲ ተሰጠ የተባለው ፍርድ ያልተከራከርኩበትና የአንደኛውን ተከራካሪ ወገን መብት የሚስጥ መሆኑን ፍ/ቤቱ በመገንዘብ ውድቅ ያደረገው በመሆኑ የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ባለመሆኑ እንዱፀና በማለት ተከራክሯል። የመልስ መልስም ቀርቧል።
በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው ክርክር አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም በግራ ቀኙ የተነሱትን ክርክሮች ከተያዘው ጭብጥና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘበ መርምሮታል። በዚሁ መሰረት በግራ ቀኙ መካከል ያለው ጋብቻ በፍርድ ቤት ውሣኔ መፍረስ ተከትል ያለው የንብረት ክፍፍል ክስ ቀድሞ በፍርድ ያለቀ ጉዲይ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ተይዞ መፍትሓ ማግኘት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዚሁ መሰረት ይሄንን ጉዲይ ስንመረምረው አመልካች ቀድሞ በፍርድ አልቋል የሚለት በካናዲ ፍርድ ቤት ተሰጠ የተባለውና በኢትዮጵያም ሆነ በካናዲ የሚገኙትን መኖሪያ ቤቶች ለአመልካች ወስኗል የተባለውን ፍርድ ነው።
አንድ የውጭ ሃገር ፍርድ ከአገራችን የፍትሐብሕር ስነ ሥርዓት እይታ አኳያ ሲታይ የክሱ መጀመር ወይም ከተወሰነ በኋላ ለአፈፃፀም ቢቀርቡ ያላቸው ተቀባይነት በተመለከተ አግባብነት ያላቸው የሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 8/2/ እና በውጭ አገር የተሰጠ ፍርድ ወይም ብይን ስለሚፈፀምበት ሁኔታ የሚደነግገው ከአንቀጽ 456 አስከ 461 ሥር የተደነገጉት ናቸው።
የመጀመሪያውን አንቀጽ ማለትም አንቀጽ 8/2/ በምናይበት ጊዜ በውጭ አገር ክስ መጀመሩ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ተቀብል ከመመልከት እንደማያግደው የሚያመለክት በመሆኑ በዚሁ እናልፈዋለን። ከላይ በሁለተኛ ደረጃ የተመለከቱትን የህግ ድንጋጌዎች በምናይበት ጊዜ አንድ የውጭ ሃገር ፍርድ የመጨረሻ ውሣኔ ተሰጥቶበት መቅረቡ ብቻ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት ሉያስገኝለት የማይቻል ስለመሆኑና የተለያዩ መመዘኛዎችን ማሟላት እንዲለበት ይደነግጋለ።
የተመለከተው ፍርድ ደግሞ በሥነ ሥርዓት ሕጉ ላይ የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ያሟላል ወይስ አያሟላም ማለት ደግሞ የሚቻለው የተሰጠው ፍርድ ይጠቅመኛል ወይም መብት ያጏናጽፈኛል ባይ የአፈፃፀም ማመልከቻ ከላይ በተጠቀሱት የሥነ ሥርዓት ሕጏች መሰረት ብታቀርብ ኖር እንጂ ለቀረበባቸው ክስ እንደመከራከሪያ በማቅረብ አይደለም።
በመሆኑም በካናዲ ፍርድ ቤት ተሰጠ የተባለው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 456 እስከ 416 በተመለከተው አግባብ ተቀባይነቱ ለፍርድ ቤት ቀርቦ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ አመልካችም ይሄንን ባለፍፀሙበት ሁኔታ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 5 መሰረት የመጨረሻ ውሣኔ ያገኘ ጉዲይ ነው በማለት የቀረቡት መከራከሪያ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች ከዚህ አኳያ የተነሳውን ተቃውሞ ውድቅ በማድረግ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አላገኘነውም። ስለመሆነም ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፋ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 51738 የካቲት 17 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በዋለው ችልት እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 71195 ጥቅምት 30 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
ግራ ቀኙ ያላቸውን የጋራ ንብረት በኢትዮጵያ የፋዳራል ቤተሰብ ህግ መሰረት እኩል ይካፈለ መባለ በአግባቡ ነው ብለናል።
በግራ ቀኙ ላይ በዚህ ችልት ለደረሰው ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.