No summary available.
ሐምል 11 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ዶ/ር አልሐሴን በድልገዋድ - ጠበቃ 1. በሻዲ ገመቹ ቀረቡ፡ 2. ጥላሁን ምትኩ ቀረቡ።
ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ፍርድ ቤት እግድ የሰጠበት የማይንቀሳቀስ ንብረት እግደ ተጥሶ ውል ለማዋዋል ሥልጣን ባለው አካል ፉት በተደረገ ሽያጭ ውል ለሶስተኛ ወገን ንብረቱ ተላልፍ ሲገኝ ያለውን ውጤት የሚመለከት ነው። የክርክሩ መነሻና ይዘትም የሚከተለው ነው። አመልካች አቶ ጥበቡ እሸቴ በተባለት ግለሰብ ላይ ብር 1,598,470.00 (አንድ ሚሉዮን አምስት መቶ ዘጠና ስምንት ሺህ አራት መቶ ሰባ ብር) ለማስከፈል በኮ/መ/ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኔ 05 ቀን 1999 ክስ መስርተው የፍርድ ባለመብት መሆናቸውን አረጋግጠው እንደ ፍርደ እንዱፈፀምላቸው የአፈጻጸም ማመልከቻ ለፍርድ ቤቱ አቅርበው አሁን ለክርክሩ መሰረት በሆነው ቤት ላይ ሐራጅ ወጥቶ አፈጻጸሙ እንዱቀጥል ባቀረቡት ማመልከቻ መሰረት ፍርድ ቤቱ እግድ ተሰጥቶበት የነበረ መሆኑን ተገንዝቦ የሐራጅ ማስታወቂያውን አውጥቶ አፈጻጸሙን በመምራት እንዲለ የአሁኑ ተጠሪዎች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 418 መሰረት የተቃውሞ አቤቱታ አቅርበዋል። የአሁኑ ተጠሪዎች የተቃውሞ ምክንያት የሆነው ነገር ለአፈጻጸሙ መሰረት የሆነውና በቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 02 ክልል ውስጥ የሚገኘው ቁጥሩ 274 የሆነውን መኖሪያ ቤት በሕግ አግባብ በተደረገ የሽያጭ ውል ከአቶ ጥበቡ እሸቴ የገዙትና ስመ ሀብቱንም ወደራሳቸው ያዞሩት መሆኑን የሚገልፅ ሁኖ አፈጻፀሙ በንብረታቸው ላይ ሉቀጥል አይገባም የሚል ነው። የስር ፍርድ ቤትም በዚህ መልኩ በቀረበው የተጠሪዎች አቤቱታ ላይ አመልካች መልስ እንዱሰጡበት አድርጓል። አመልካች በሰጡት መልስም ዋናውን ክስ በአቶ ጥበቡ እሸቴ ላይ ሲመሰርቱ ክሱ ለቀረበለት ፍርድ ቤት ባቀረቡት የእግድ አቤቱታ መሰረት ሰኔ 06 ቀን 1999 ዓ/ም በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት በቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 02 ክልል ውስጥ ቁጥሩ 274 የሆነ መኖሪያ ቤት በግለሰቡ ስም የሚታወቅ መሆኑ ተጣርቶ በማናቸውም መንገድ ለሶስተኛ ወገን እንዲይተላለፍ በማለት ያዘዘ ሲሆን ይኸው የእግድ ትዕዛዝ ለቦላ ክፍለ ከተማ መሬት አስተዲደር ደርሶት በቤቱ ማህደር መያያዙንና ይህ የእግድ ትዕዛዝ በሕግ አግባብ ያልተነሳ መሆኑን ዘርዝረው እግደ በተጭበረበረ መንገድ ተነስቷል ተብል በተገለፀበት ሁኔታና ጊዜ የተከናወነው የሽያጭ ውል ሕጋዊ ባለመሆኑ የተጠሪዎች ተቃውሞ ተቀባይነት የለውም፣ አፈጻጸሙ በቤቱ ላይ መቀጠል አለበት በማለት ተከራክረዋል። ጉዲዩ በዚህ መልክ የቀረበለት የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በአከራካሪው ቤት የፍርድ ቤት እግድ መተላለፈ የተረጋገጠ ቢሆንም በሕግ አግባብ ሳይነሳ እንደተነሳ ተደርጎ ትእዛዝ ተላልፍ እግደ ተነስቷል ተብል በተገለጸበት ሁኔታና ጊዜ የሽያጭ ውለ በውልና ማስረጃ ፅ/ቤት ተደርጎ ስመ ሀብቱ ሁለ ወደ ተጠሪዎች መዛወሩን፣ እግደ በመጣሱ ተጠያቂ ላሆን የሚችለው ደግሞ እግደን የጣሰው ወገን እንጂ ገዥ ላሆን እንደማይገባ ዘርዝሮና የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 156፣ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1566 እና የአዋጅ ቀጥር 334/95 አንቀጽ 15(2) እና 27(1) ድንጋጌዎችን በዋቢነት በመጥቀስ ቤቱ በሐራጅ ሉሸጥ አይገባም ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ጸንቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ ታህሳስ 07 ቀን 2003 ዓ.ም ተሻሽል በተፃፈ አምስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት አመልካች በሕግ አግባብ አስከብረው የነበረና በሕግ አግባብ እግደ ሳይነሳ በተጭበረበረ መንገድ የተነሳ መሆኑ በግልጽ ተረጋግጦ እያለ ሽያጩ ቀሪ ላሆን አይገባም፣ እግደን የጣሰው ወገን እንጂ ገዥ ተጠቂያነት የለበትም ተብል መወሰኑ የእግድን ዓላማና ውጤቱን ያላገናዘበና ሕጋዊነት የላለው ስለሆነ ሉታረም ይገባዋል በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሐራጅ እንዱሸጥ የተባለው ቤት ለሁለተኛ ተጠሪ በግዥ ተላልፎል ተብል ሐራጁ እንዱቋረጥ የስር ፍርድ ቤቶች የመወሰናቸውን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጏ ተጠሪዎች ጥር 17 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ ሦስት ገጽ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የመልሳቸው ይዘትም ባጭሩ፡- ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት ሽያጩ የተከናወነው እግደ የተነሳ መሆኑ በተረጋገጠበትና በውልና ማስረጃ በተደረገ የሽያጭ ውል ሁኖ ስመ - ሐብቱም ለገዥው የዞረ በመሆኑ ሽያጩ ሕጋዊ አይደለም ልባል የሚችልበት ምክንያት ስለላለ የበታች ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም ተብል ሉፀና ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። የአመልካች ጠበቃም በተጠሪዎች መልስ ላይ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል። ይህ ችልትም የስር ፍርድ ቤት ጉዲዩን የመራበትን መዝገብ ን አስቀርቦ የክርክሩን ሂደት ተመልክቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች በአቶ ጥበቡ እሸቴ ላይ የገንዘብ ይከፈለኝ ክስ ሰኔ 05 ቀን 1999 ዓ.ም መስርተው አሁን እያከራከረ ያለው እና ላላ ቤት ሰኔ 06 ቀን 1999 ዓ/ም በፍርድ ቤት ትእዛዝ እንዱከበር ያደረጉ መሆኑን፣ ይህ የእግድ ትዕዛዝም ለሚመለከታቸው አካላት መተላለፈ የተረጋገጠ ቢሆንም እግደ መነሳቱን ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ስለማስተላለፈ ያሳያል የተባለ ማስረጃ በመኖሩ ምክንያት ውልና ማስረጃ ፅ/ቤት በተደረገው የሽያጭ ውል መጋቢት 10 ቀን 2001 ዓ/ም አከራካሪው ቤት ለተጠሪዎች መተላለፈን፣ ከዚህም በኋላ ተጠሪዎች የስመ ሃብቱን ወደ ራሳቸው አዙረው እየተጠቀሙበት የሚገኙ መሆኑ በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጡ ፍሬ ጉዲዮች መሆናቸውን ነው። የአመልካች ክርክር መሰረቱም የፍርድ ቤት እግድ ያለበትን ቤት በተጭበረበረ መንገድ እግደ ተነስቷል ተብልና እግደ የተነሳው ከፍርድ ቤት ከወጣ ትዕዛዝ ስለመሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ሽያጩ መከናውኑም ሆነ የቤቱን ስመ - ሃብት ገዢዎች ማዞራቸው ሽያጩን ሕጋዊ አያደርገውም በሚል ምክንያት ስለመሆኑም ተገንዝበናል። እኛም በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች ከሕጉ ጋር በሚከተለው መልኩ በማዛመድ ተመልክተናል።
በመሰረቱ በፍርድ ቤት የእግድ ትዕዛዝ የሚሰጠው በክርክሩ ሂደት ረቺ የሚሆነው ወገን ለፍርድ አፈጻጸም ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እንዱያስችለው ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 154 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መንፈስና ይዘት የምንገነዘበው ጉዲይ ሲሆን የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ደግሞ ሉከበር የሚገባ መሆኑ የሚያከራክር አይደለም። ፍርድ ደግሞ ሉፈጸም የሚገባው በፍርድ ባለእዲውና በሕግ አግባብ እንዲይያዙ ከሚጠቀሱት ንብረቶች/መብቶች ውጪ ባለት የፍርድ ባለእዲ ንብረቶች/መብቶች ስለመሆኑ በቁጥር 378 ተከታዮቹ በተመለከቱት የፍትሐ ብሓር ስነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። አንድ ሰው በሕግ አግባብ ለላላ ሰው ሉያስተላለፍ የሚችለው መብትም በሕግ አግባብ ገደብ ያልተደረገበትንና ያለውን መሆኑ እሙን ነው።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስም የስር የፍርድ ባለእዲ የሆኑት አቶ ጥበቡ አከራካሪውን ቤት የሸጡት በፍርድ ቤት የተላለፈው እግድ በፍርድ ቤቱ መነሳቱን አረጋገጠው ባይሆንም የፍርድ ቤቱ የእግድ ትዕዛዝ የተነሳ መሆኑን የሚያሳይና ከፍርድ ቤቱ የወጣ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ በቤቱ ማህደር ተያይዞ በመገኘቱ ሲሆን እግደን የጣሰው አካል ማን እንደሆነም በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ አይደለም። የፍርድ ቤቱ እግድ የተነሳ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ሽያጩም ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፉት የተደረገ ስለመሆኑ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። ሽያጩ ሲከናወን አቶ ጥበቡ እሽቴ የአከራካሪው ቤት ባለሃብት ሲሆኑ በዚሁ ሰፉው መብታቸው ደግሞ በሕግ ያልተገደቡ መብቶቻቸውን መጠቀም የሚችለ መሆኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1204፣1206፣1184 እና 1185 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1195 ድንጋጌ መሰረት ደግሞ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሃብትነትን በማወቅ በአስተዲደር ክፍል የምስክር ወረቀት ሲሰጥ የምስክር ወረቀቱን ያገኘው ሰው የማይንቀሳቀሰው ንብረት ባለሃብት ሁኖ ሉቆጠር እንደሚገባ ተመልክቷል። ከላይ የተገለጹትን ድንጋጌዎች ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1195 ጋር አጣምረን ስንመለከት የባለሃብትነት የምስክር ወረቀት የያዘ ሰው በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1196 ስር የተመለከቱት ሁኔታዎች መኖራቸው እስካልተረጋገጡ እና ላልች ሕጋዊ ክልከላዎች እስከላለ ድረስ ሃብቱን በሕጉ አግባብ ከሸጠ ተግባሩ ሕገ ወጥ የሚባልበት ምክንያት የለውም። አንድ ሰው በሕግ ጥበቃ የተደረገለትን መብት በሕጋዊ መንገድች ለላላ ለማስተላለፍ መብት አለውና። በዚህ መንገድ መብቱ የተላለፈለት ሰውም በሕግ ጥበቃ ላደረግለት ይገባል። በተያዘው ጉዲይ አመልካች በቤቱ ላይ እግድ ማሰጠታቸው የተረጋገጠ ቢሆንም ከዚህ በሁዋላ ደግሞ እግደ መነሳቱ ተረጋግጧል። አመልካች እግደ ከፍርድ ቤት በወጣ ትዕዛዝ የተነሳ አይደለም በማለት ከመከራከራቸው ውጪ ለእግደ መጣስ ወይም የይነሳልኝ ጥያቄው የቀረበው ወይም እግደ ስለመነሳቱ የሚገልጸው ደብዲቤ ጋር ተጠሪዎች ያላቸው ግንኙነት ስለመኖሩ ያቀረቡት ክርክርም ሆነ ማስረጃ አለመኖሩን የክርክሩ ሂደት በግልጽ ያሳያል።
ከሻጭ ጋር የመመሳጠር ሁኔታ ስለመኖሩ ያልተረጋገጠበትና የተለየ ግንኙነት የላለው ሰው በቤቱ ላይ እግድ መነሳቱን የሚያሳይ ማስረጃ ከሚመለከተው የቤቱ ማህደር አይቶና ይህን ማስረጃ በመመልከት ንብረቱን ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፉት የሚገዛ ገዥ ሽያጩን ያከናወነው ከሕግ ውጪ ነው ልባል የሚችልበት የሕግ አግባብ የለም። በቤቱ ላይ ሕጋዊ መብት የላለው ሰው ሽያጩን አከናውኖ ሲገኝም ትክክለኛው ባለሃብት ሉጠይቅ የሚችለው ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጏ የገዛውን ገዥ ላሆን አይገባም። ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጎ በሕጋዊ ተግባር መብት ያገኘ ሰው ከራሱ እውቅና ውጪ ለተፈፀመ ሕገ ወጥ ተግባር ተጠያቂ ማድረግ የግብይት ሥርዓቱንም ጭምር ዋስትና የሚያሳጣው ይሆናል። ከሁለም በላይ የፍርድ ቤት እግድ ተጥሶ ሲገኝ ኃላፉነት ሉወስድ የሚገባው የእግድ ትዕዛዙ እንዱጣስ ምክንያት የሆነ ተግባር የፈፀመ አካል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 156 ድንጋጌ ይዘት ያስገነዝባል። በውልና ማስረጃ ጽ/ቤትም በሕግ የባለቤትነት መብት ማረጋገጫ የሚሰጥባቸውን ንብረቶች ለማስተላለፍ የሚዘጋጁ ሰነድች ከመዘጋጀታቸው በፉትም ሰነድ አረጋጋጩ ንብረቱ በመያዣነት ያልተሰጠ ወይም በፍርድ ቤት ያልታገደ መሆኑን ሉያረጋገጥ እንደሚገባ አዋጅ ቁጥር 334/95 አንቀጽ 15(2) ድንጋጌ በኃይለ ቃል አስቀምጦ እናገኛለን። በመሆኑም ተጠሪዎች አከራካሪውን ቤት የገዙት በሕግ ፉት ተቀባይነት ያለውን ማስረጃ ከያዙት ግለሰብ ሆኖ ሽያጩም የተከናወነው ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፉት ሲሆን በዚህ ጊዜም የፍርድ ቤቱ እግደ ስለመነሳቱ የሚያረጋገጥ ማስረጃ ከቤቱ ማህደሩ ጋር በመገኘቱ በመሆኑ የአከራካሪው ቤት ሽያጭ ውል ቀሪ የሚሆንበት ሕጋዊ ምክንያት የለም።
ተጠሪዎች በቤቱ ላይ በሕግ አግባብ በተፈጸመ የሽያጭ ውል ያቋቋሙት የባለሃብትነት መብት ያላቸው መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን አመልካች ያላቸው መፍትሄ የእግደን ትእዛዝ በጣሰው አካል ላይ ተገቢውን ጥያቄ በተገቢው አካል አቅርበው የደረሰባቸው ጉዲት ካለ መብታቸውን ማስከበር እንጂ አፈጻጸሙ በአከራካሪው ቤት እንዱቀጥል ማስደረግ ላሆን አይገባም። አመልካች በሰ/መ/ የተሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ለጉዲዩ ተፈፃሚነት አለው በማለት ያቀረቡት ክርክርም በተጠቀሱት መዛግብት ላይ የተሰጠው የሕግ ትርጉም ከመያዣ ቀዲሚ መብት ጋር የተያየዘ በመሆኑና በዚህ መዝገብ የተያዘው ጉዲይ ደግሞ በፍርድ ቤት የተሰጠ እግድ ከገዥው እውቅና ውጪ ተነስቷል ተብል ማረጋገጫ በመቅረቡ እግድ የተላለፈበት የማይንቀሳቀስ ንብረት በውልና ማስረጃ ፅ/ቤት በተደረገ የሽያጭ ውል ለሶስተኛ ወገን ተሽጦ ቢገኝ ውለ በሕግ ስለሚኖረው ጥበቃ የሚመለከት በመሆኑ ከላይ የተጠቀሱት አስገዲጅ የሰበር ሰሚ ችልት የሕግ ትርጉሞች ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸው አይደለም። በመሆኑም በዚህ ረገድ የቀረበውን የአመልካች ክርክር የምንቀበልበትን ሕጋዊ ምክንያት አላገኘንም።
ላላው የአመልካች ጠበቆች የሚከራከሩበት ነጥብ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአከራካሪው ቤት ላይ የተደረገው ሽያጭ ሕጋዊ የሚሆንበት አግባብ የለም፣ በማለት ሐራጁ እንዱቀጥል ትዕዛዝ ከሰጠ በሁዋላ ችልቱ ላይ የነበሩት ዲኛ ሲለወጡ በሽያጭ ውለ ላይ ክርክር ተደርጎ የቀድሞው ትዕዛዝ ተመሳሳይ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ችልት ቀሪ እንዱሆን መደረጉ ሥነ ሥርዓቱን የተከተለ አይደለም በማለት ነው። እኛም ይህንኑ ክርክር መሰረት አድርገን የስር ፍርድ ቤትን መዝገብ አስቀርበን ጉዲዩን ስንመለከተው ተጠሪዎች በአከራካሪው ቤት ላይ ሕጋዊ መብት አለን በማለት ወደ ክርክሩ የገቡትና በግራ ቀኙ መካከል ክርክር ተደርጎ የሽያጭ ውለ ሕጋዊ ነው ተብል ውሳኔ የተሰጠው ሕዲር 11 ቀን 2002 ዓ/ም በዋለው ችልት እንጂ ከዚህ ቀን በፉት በነበረው የክርክር ሂደት አለመሆኑን አረጋግጠናል። አንድ ሰው በሕግ አግባብ የክርክሩ ተሳታፉ ባልሆነበት ሁኔታ የተሰጠ ብይን ይኸው ሰው መብት አለኝ በሚል ሥርዓቱን ጠብቆ ሲቀርብ ላላ ወገን ተከራክሮ ተገቢ ትዕዛዝ ተሰጥቶበታል በሚል ምክንያት ብቻ በልላ ወገን ላይ የተሰጠ ትእዛዝ ተፈጻሚነት ሉኖረው ይገባል የሚል ሕጋዊ ምክንያት የለም። እንዱህ ከሆነ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጉዲዩ ላይ ሁለት ጊዜ የተለያየ አቋም መያዙ ስነ ሥርዓቱን የተከተለ አይደለም በማለት የሚቀርበው ቅሬታ እውነትነትና ሕጋዊ መሰረት የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም።
በአጠቃላይ ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ስለእግደ መጣስ ተጠሪዎች ያደረጉት ድርጊት አለመኖሩንና የሽያጭ ውለም እግደ በተነሳበት ሁኔታና ጊዜ በተገቢው አካል ዘንድ የተከናወነ መሆኑን በማረጋገጥ የሰጡት ውሳኔ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አላገኘነውም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
No topics extracted.