No summary available.
ሐምል 14 ቀን 2003 ዓ/ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ - ነገረ ፈጅ ክበሩ ደበበ ቀረቡ።
ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ ቀባንክ ብድር ጋር ተያያዥነት ያለው ክርክር ሲሆን የተጀመረው በደቡብ ብሓ/ብ/ሕ/ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት በቤንች አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአሁኑ አመልካች ከሳሽነት ነው። ቀርቦ የነበረው ክስ 1ኛው ተከሣሽ በተደረገው የብድር ውል የእህል ንግድ ለመሥራት ብር 30,000 የተበደረና 2ኛ ተከሳሽም የ1ኛ ተከሳሽ ባለቤትና ውለ እንዱፈቅድ ስምምነታቸውን ገልፀዋል፣ ለዋስትናም በሚዛን ተፈሪ ከተማ ያለው የመጋዘን ቤትና የመኖሪያ ቤት ባንኩ በመረከብ ከዕዲቸው ላይ ቀንሷል፣ ይሄም ሆኖ በውለ መሰረት ዋና ገንዘብ ብር 8,112.49 እና ወለድ 6,433.37 በድምሩ ብር 14,545.86 የሚፈለግባቸው በመሆኑ የቀረበ ክስ ነው።
ተከሣሾች በሰጡት መልስ ከሳሽ በዕዲው ምክንያት ንብረቱን የተረከበ በመሆኑ የቀረውን ዕዲም ከፍል ለመጨረስ ጊዜ ይሰጠን በማለት የመለሱ በመሆኑና በቃል ክርክር ወቅት ከሳሽ ንብረቶችን በእጅ ካስገባ በኋላ ተከሣሾች ኃላፉነት መውሰድ የለብንም የሚል ክርክር ያነሱና በወቅቱ በባንክ ነገረፈጅ ቀርቦ የነበረው ክርክር ንብረቱን የተረከብን ቢሆንም ወደ ገንዘብ ተሽጦ ያልተለወጠ በመሆኑ የቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱ ከላይ እንደተመለከተው ከክርክሩ በኋላ ከሳሽ ከላይ የተመለከቱትን መጋዘንና መኖሪያ ቤት ብረከብም ወደ ገንዘብ አልተለወጠም በማለት የተነሳው ክርክር ተቀባይነት የለውም በማለት ሐምል 09/1994 ዓ.ም ከተረከቡበት ጊዜ ጀምሮ በግምቱ መጠን ያለባቸው ሆኖ ተቀናሽ መሆን ይገባዋል በማለት የንብረቶቹ ግምት በአጠቃላይ ብር 41,209 ነው በማለት አመልክቷል።
ፍርድ ቤቱ በማያያዝ ከሳሽ ንብረቱን እስከተረከበበት ጊዜ ድረስ በተከሣሾች ላይ ያለው ዕዲ ብር 41 /አርባ አንድ/ ብቻ በመሆኑ ውሣኔውን እስከሰጠበት ድረስ ያለውን ወለድ በማስላት ወይም በማሰብ ብር 85.28 /ሰማኒያ አምስት ብር ከሃያ ስምንት ሣንቲም/ ብቻ ይቀራል በማለት ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ውሣኔ አፅንቷል።
አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን የአመልካች ነገረ ፈጅ ጥቅምት 08 ቀን 2003 ዓ.ም የተፃፈ የቅሬታ ፍሬ ሃሣብ ባንኩ በመያዣ የያዛቸውን ንብረቶች በአዋጅ ቁ.
97/90 እና አዋጅ 216/92 መሰረት የተረከባቸውንና የተረከበበትን የንብረት ግምትም ከዕዲው ላይ በማቀናነስ ቀሪውን ዕዲ ለመጠየቅ የቀረበ ክስ ሆኖ እያለ ፍርድ ቤቱ ከጭብጡ በመውጣት የሂሣብ ስላት ውስጥ በመግባት የወሰነው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ተሽሮ በክሳችን መሰረት እንዱወሰን የሚል ነው። ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ተጠሪዎች በቀን 02-5-2003 ዓ.ም የሰጡት 2 ገፅ የመልስ ፍሬ ሃሣብ አመልካች መጋዘን እና መኖሪያ ቤቱን ከተረከበ በኋላ ሰባት ዓመት ቆይቶ ንብረቶቹንም እያከራዩ ሲጠቀሙ ቆይተው በተሳሳተ ስላት ቀሪ ዕዲ አለባችሁ በማለት ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት የላለው በመሆኑ እንዱፀና በማለት ተከራክሯል። የአመልካች የመልስ መልስ ቀርቧል።
በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የክርክር ሂደት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም ከግራ ቀኙ የተነሱትን ክርክሮች ከተያዘው ጭብጥና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል። እንደተመረመረውም ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤት ተገቢውን ማጣራት ካደረገ በኋላ የተሰጠ ውሣኔ ነው? ወይስ አይደለም የሚለው ጭብጥ ተይዞ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል። ከዚህ አኳያ የተያዘውን ጉዲይ ስንመለከተው በመጀመሪያ ደረጃ ለዕዲው መክፈያ በአንደኛ ደረጃ ዋስትና የተያዙት መጋዘን ቤት እና መኖሪያ ቤት ባንኩ የተረከበው አጠቃላይ ግምታቸው ብር 41,209 ስለመሆኑ እና ሐምል 9/1994 ዓ.ም ባንኩ የተረከባቸው መሆኑ አላከራከረም። አመልካቹ ንብረቶቹን ከተረከበበት ቀን ጀምሮ በንብረቱ ግምት መጠን ዕዲውን ተቀናሽ ማድረግ ሲገባው ንብረቱን ብንረከብም ተሽጦ ወደ ገንዘብ የተለወጠ ባለመሆኑ ሉቀነስ አይገባም በማለት በከፍተኛው ፍርድ ቤት በቃል ክርክር ወቅት የተነሣውን ነጥብ በተመለከተ በዚህም ችልት ለማጣራት የአመልካች ነገረ ፈጅ ተጠይቀው በወቅቱ የቀረበው የአመልካች ተወካይ የፈፀሙት የክርክር ስህተት እንጂ ባንኩ ንብረቱን ሲረከብ በግምቱ መጠን ዕዲውን የሚቀንስ መሆኑን ገልፀዋል። በተጨማሪም በወቅቱ በከፍተኛው ፍርድ ቤት በቃል ክርክር ወቅት በአመልካች ነገረ ፈጅ በኩል ተነስቶ የነበረውን ክርክር ፍርድ ቤቱ ውድቅ በማድረግ ባንኩ ንብረቶቹን በዕዲው ምክንያት ከተረከበበት ቀን ጀምሮ በግምቱ መጠን ዕዲው የሚቀነስ መሆኑን የወሰነ በመሆኑ በዚህ ነጥብ ላይ ተጠሪዎች ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም ብለናል።
በመሆኑም በዚህ ጉዲይ ላይ አከራካሪው ነጥብ አመልካቹ ለዋስትና የተያዙትን መጋዘንና መኖሪያ ቤት በተረከበበት ሐምል 09 ቀን 1994 ዓ.ም ወቅት በተጠሪዎች ላይ የነበረው ዕዲ ስንት የነበረ ስለመሆኑ፣ በወቅቱ የነበረው ዕዲ አመልካች ንብረቱን ሲረከብ የንብረቶቹ ግምት መጠን ከተጠሪዎች ዕዲ ላይ ሲቀናነስ ምን ያህል ዕዲ የሚቀርባቸው ስለመሆኑ እና አመልካች /ባንኩ/ ንብረቶቹን ከተረከበ በኋላ በግራ ቀኙ መካከል በነበረው ውል መሰረት የቀረው ዕዲ ክስ እስከቀረበበት ጊዜ ድረስ ያለው ስላት ስንት ይሆናል የሚለት ነጥቦች እንደሆኑ ግልፅ ነው። ይሄንን በተመለከተ ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች በዋስትና የተያዙትን ንብረቶች ስረከብ የነበረው ዕዲ ተቀናንሶ ብር 41 ብቻ በተጠሪዎች ላይ እንደሚቀር ይሄው ዕዲ ውሣኔ እስኪሰጥበት ቀን ድረስ በቀሪው ዕዲ ላይ ወለድ ታስቦ ብር 85.28 ብቻ እንደሚቀርባቸው ውሣኔ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ ወደ ዕዲው ስላት ሉገባ የቻለው በግራ ቀኙ መካከል በነበረው ክርክር በኃላፉነት መጠን ስላት ላይ ክርክር በመፈጠሩ ምክንያት መሆኑ ከክርክሩ አጠቃላይ ሂደት መገንዘብ ይቻላል። የዕዲው ሑሳብ ስላትን በተመለከተ አጠራጣሪ ሁኔታ ከተፈጠረ ዳኞች በራሳቸው የሂሣብ ስላቱን ለመሥራት ሳያስፈልግ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 136 /1/ /2/ መሰረት ልዩ አዋቂ /ኤክስፏርት/ በመመደብ እንዱሰሩት ማድረግ እንደሚቻል ያመለክታል። የበታች ፍርድ ቤቶች በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ያለመፈፀማቸው አሁን እየተነሣ ላለው የስላት ስህተት አለ የሚለውን ሉያስቀር የሚችል ነው። በዚህ መሰረት ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤት የዕዲውን ስላት መሥራቱ አስፈላጊ ነው ብል ካመነ ከላይ በተመለከተው በልዩ አዋቂ ማሰራት ሲገባው ፍርድ ቤቱ በራሱ ስላት የደረሰበት መደምደሚያ መሰረታዊ የክርክር ማጣራት ሂደትን ከላይ እንደተመለከተው የተከተለ ባለመሆኑ እና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ይሄንን ሳያጣራ ማለፈ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
የደቡብ ብሓ/ብ/ሕ/ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝ.ቁ. 32725 በቀን 14-12-2002 ዓ.ም በዋለው ችልት እና የቤንች አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝ.ቁ. 07373 በቀን 28-12-2001 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የቤንች አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከላይ በፍርድ ሐተታው በተመለከተው መሰረት በተጠሪዎች ላይ የቀረውን ዕዲ በልዩ አዋቂ /ኤክስፏርት/ እንዱጣራ ካደረገ በኋላ ተገቢ የሆነውን ውሣኔ እንዱሰጥ በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 343 /1/ መሰረት መልሰናል።
በዚህ ችልት በግራ ቀኙ ለደረሰው ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የማይነበብ አምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.