No summary available.
15/11/2ዐዐ3 ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አፓኖ ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ድርጅት ጠበቃ አቶ በረከት ቡሽራ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ጥሩነህ ይመር አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ተጠሪ ለሥር የጋምቤላ ከተማ አስተዲደር ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ በተከሣሽ ድርጅት /በአሁኑ አመልካች ድርጅት/ በዘበኝነት ተቀጥሬ እየሰራሁ የቆየሁ ቢሆንም በህመም ምክንያት ሥራዬን ያቆምኩ ስለሆነ ተከሣሽ አንዲንድ ያልከፈላቸውን ክፍያዎች እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ ብለዋል።
ተከሣሽ ድርጅት በበኩለ በሰጠው መልስ ከሣሽ በድርጅቱ ከታህሣሥ ወር 2ዐዐ1 እስከ ጥቅምት 2ዐዐ2 ለአሥራ አንድ ወራት በጥበቃ ሥራ ከቆዩ በኋላ በራሣቸው ፈቃድ ከተከሣሽ ድርጅት የተሰናበቱ ሲሆን በሰጡት አገልግልት መሰረት የስንብት ክፍያ የተከፈላቸው በመሆኑ ላልች የሚከፈላቸው ክፍያዎች የለም በማለት ተከራክሯል።
የሥር የከተማ አስተዲደር ፍ/ቤቱም በሰጠው ፍርድ ተከሣሽ የስንብት ክፍያ ለከሣሽ መክፈለን በማረጋገጥ ላልች ክፍያዎችን በሚመለከት ግን ከሣሽ በግልጽና በዝርዝር ያልጠየቁና በማስረጃ አስደግፈው ያላቀረቡ በመሆናቸው ሉከፈላቸው አይገባም በማለት ወስኗል።
ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የጋምቤላ ከተማ ዙሪያ ፍ/ቤት በበኩለ በሰጠው ውሣኔ ይግባኝ ባይ በመልስ ሰጪ ድርጅት ለአንድ ዓመት የሰሩ መሆናቸው ስለተረጋገጠ መከፈል ያለባቸው ክፍያዎች ማለትም የትርፍ ሰዓት ክፍያ የዓመት ዕረፍትና የበዓላት ቀን ክፍያ የተከፈላቸው ስለመሆኑ በማስረጃ ስላልተረጋገጠ መልስ ሰጪ ሉከፍላቸው ይገባል ብሎል።
በከፍተኛው ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ያለው ያሁን አመልካችም ለዚህ ችልት ባቀረበው አቤቱታ ተጠሪ በደፈናው አንዲንድ ያልተከፈለኝ ጥቅማ ጥቅሞችን አመልካች እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለታቸው ብቻ የትርፍ ሰዓት የዓመት ዕረፍት እና የበዓላት ቀን ክፍያ በገንዘብ ተለውጦ እንዱከፈላቸው መወሰኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ስለ ክስ አቀራረብ የተደነገጉትን መርሆዎችንና ስለማስረጃ አቀራረብ ሥርዓትን መሰረት ያላደረገ ስለሆነ ውሣኔው ሉሻር ይገባል ብሎል።
ተጠሪው ለሰበር አቤቱታ መልስ ለመስጠት ባለመፈለጋቸው መብታቸው የታለፈ ሲሆን እኛም የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ለተጠሪው የትርፍ ሰዓት ክፍያ፣ እንዱሁም የዓመት ዕረፍትና የበዓላት ቀናት የሰሩባቸው ታስቦ በገንዘብ ተለውጦ እንዱከፈላቸው መወሰኑ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
የሥራ ክርክር የፍትሐብሕር ባሕሪ ስላለው ክርክሩ መመራት ያለበት በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ መሰረት መሆን ይኖርበታል። በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 222 በክስ ጽሐፍ ላይ ስለሚሰፍሩ ነገሮች የተደነገገ ሲሆን በዚሁ በተጠቀሰው የሕግ ድንጋጌ ንዐስ ቁጥር /1/ በፉደል /ረ/ አንድ ክስ ለክሱ ምክንያት የሆኑትን ነገሮች መያዝ እንዲለበት ተገልጿል። ከዚህ ላላም በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 8ዐ/1/ እንደተጠቀሰው ከሣሽ የሚጠይቀውን ሁለ ዘርዝሮ በክሱ ወይም በአቤቱታው ማቅረብ እንደሚኖርበት በማያሻማ ሁኔታ ተጠቅሷል። ይሁን እንጂ በዚህ በተያዘው ጉዲይ ግን ተጠሪው ያልተከፈለኝን ክፍያዎች አመልካች ይክፈለኝ ከሚል ውጪ መክፈል ያለበትን ክፍያዎች በሕጉ መሰረት በዝርዝር ግለጽ አድርገው አላቀቡም። በግልጽ በዝርዝር ባልቀረበ ጉዲይ ደግሞ ላላኛው ወገን እንዱከራከርበት ማድረግ የተጠቀሱትን የፍትሐብሕር ሥነ ሥ/ሕ/ድንጋጌዎች መጣስ ይሆናል።
ግለጽነት የጎደው ክስ ወይም አቤቱታ በቀረበ ጊዜ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/ 91/1/ እንደተጠቀሰው ፍርድ ከመሰጠቱ በፉት ከተከራካሪ ወገኖች በሚቀርበው ጥያቄ ወይም ፍ/ቤቱ በራሱ አነሣሽነት ትክክለኛ ፍርድ ለመስጠት አስፈላጊ መሆኑን ከተረዲ ክሱ ወይም አቤቱታው እንዱሻሻል ለማዘዝ ይችላል። ሆኖም በዚህ በያዝነው ጉዲይ በዚህ መልኩ ክሱ እንዱሻሻል አልተደረገም። ይህ ሆኖ ሳለ ተጠሪው እንዱከፈላቸው የሚጠይቁት የዓመት ዕረፍት፣ የበዓላት ቀን እና የትርፍ ሰዓት ክፍያዎች ለየትኛው ጊዜ እንደሆኑ ተለይተው ባልቀረቡበት እንዱሁም በእነዚህ ጊዜያት ተጠሪው የትርፍ ሰዓት ሥራ እና በበዓላት ቀናት የሰሩ ስለመሆናቸው፣ የዓመት ዕረፍት ያልተጠቀሙበት መኖር አለመኖሩ ማረጋገጫ ባለቀረበበት አመልካች እነዚሁኑ ክፍያዎች እንዱከፍለ የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት መወሰኑ በፍትሐብሕር ሥ/ሥ ስለ ክስ አቀራረብ የተደነገጉትን ድንጋጌዎች ባልተከተለ ሁኔታ ከመሆኑም ላላ ተጠሪው ክሱን በማስረጃ ሣያስረደ የተወሰነ በመሆኑ ውሣኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተናል። ስለሆነም የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የሥር የጋምቤላ ከተማና ዙሪያ ከፍተኛ ፍ/ቤት በቀን 1ዐ/2/2ዐዐ3 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሣኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የሥር የጋምቤላ ከተማ አስተዲደር የመ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. ዐ3436 በቀን 28/1ዐ/2ዐዐ2 የሰጠው ፍርድ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
አመልካች ለተጠሪ የዓመት ዕረፍት፣ የበዓላት ቀናት፣ ትርፍ ሰዓት ሥራ ክፍያዎችን በገንዘብ ተለውጦ ሉከፍላቸው አይገባም ብለናል።
አመልካች የዚህን ፍ/ቤት ወጪ የራሱን ይቻል።
መዝገቡ የተዘጋ ስለሆነ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ሃ/ዱ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት