No summary available.
ሐምል 11 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሪት ቤቴልሓም ታደሰ - ጠበቃ ዲንኤል ግርማ ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ አንድ ጉዲይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 5 መሰረት የመጨረሻ ፍርድ ያገኘ ጉዲይ ነው ልባል የሚችልበትን የሥነ ሥርዓት ሕግ አግባብ የሚመለከት ነው። ለዚህ የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው አመልካች ነሀሴ 11 ቀን 2001 ዓ/ም በተጻፈ ማመልከቻ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ ያቀረቡት ክስ ነው። አመልካች በክሳቸው ላይ 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በኮልፋ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ቀበላ 07 ክልል ውስጥ የሚገኝና የቤት ቁጥሩ 261 የሆነውን ፣ የአመልካች ድርሻም ጭምር ያለበትን መኖሪያ ቤት ለአሁኑ 3ኛ ተጠሪ ነሀሴ 12 ቀን 1998 ዓ/ም በተደረገ የቤት ሽያጭ ውል የሸጡት መሆኑን ፣ ይህ የሽያጭ ውል አመልካችን የሚጎዲና ሕገወጥ መሆኑን ጠቅሰው ውለ እንዱፈርስላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል። የአሁኑ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ለክሱ በሰጡት መልስም ውለ መደረጉን ሳይክደ የሕጉን ፍርማሉቲን ያልጠበቀና ረቂቅ በመሆኑ ቢፈርስ ተቃውሞ የላላቸው መሆኑን የገለፁ ሲሆን የአሁኑ 3ኛ ተጠሪ በበኩላቸው በጉዲዩ ላይ 1ኛ ተጠሪ ባሁኑ 3ኛ ተጠሪ ላይ የውል ይፈረስልኝ ጥያቄ አቅርበው አመልካች የጣልቃ ልግባ ጥያቄ ሲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ ውድቅ ያደረገባቸው መሆኑንና ውለም ሉፈርስ አይገባም ተብል በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ጭምር የፀና መሆኑን ጠቅሰው ጉዲዩ ዲግም ክስ ላቀርብበት አይገባም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበዋል። የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ አመልካች ያቀረቡት የውል ይፍረስልኝ ክስ ቀድሞ በፍርድ ባለቀ ጉዲይ በመሆኑ ዲግም ክስ ላቀርብበት የሚገባው አይደለም በማለት የአመልካችን ክስ ዘግቶታል። በዚህ ብይን አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም አመልካች በጉዲዩ ላይ ጣልቃ ልግባ የሚለውን ጥያቄ አቅርበው አቤቱታቸው ውድቅ የሆነው 1ኛ ተጠሪ ከ3ኛ ተጠሪ ክስ በመሰረቱበት ጊዜ የጠየቁት ዲኝነት አመልካች ጣልቃ ልግባ በማለት ከጠየቁት ጋር የተለየ ምክንያት ያለው በመሆኑ ሉስተናገድ አይገባም ተብል ሲሆን አመልካች በልላ መንገድ መብታቸውን ከማስከበርም የማያግዲቸው መሆኑ ተገልፆ የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ብይን ሰጥቶ እያለ ከዚሁ ብይን ውጪ በሆነ መንገድ ጉዲዩ ቀድሞ በፍርድ ያለቀ ነው ተብል መወሰኑ ያላግባብ ነው የሚል ነወ። አቤቱታቸው ተመርምሮም የስር ፍርድ ቤት የአመልካች ጥያቄ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 5 መሰረት ውድቅ ነው በማለት የሰጠው ብይን በመ/ ከሰጠው ብይን አንፃር ሲታይ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበውም በስር ፍርድ ቤት ከሰጡት መልስ ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያለው መልስ አቅርበዋል ፣ አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሯል።
በመሰረቱ የፍትሐብሕር የክርክር አመራር ሥርዓት ዓይነተኛ ዓላማ የክርክርን ሂደት ለማቀላጠፍና አንድ ደረጃ ላይ ሲደርስ መቋጫ ለማበጀት መሆኑ ይታመናል። የፍትሐብሕርን ክርክር አንድ ደረጃ ላይ ሲደርስ እልባት እንዱደረግበት በማቀድ ከተደነገጉት የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ጽንሰ ሐሣቦች አንደ የመጨረሻ ፍርድ ያገኙ ጉዲዮች /Res judicata/ የሚለው ሲሆን ይህ ጽንሰ ሀሣብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/ 5 ስራ በግልጽ ተቀምጧል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት የመጨረሻ ፍርድ ያገኙ ጉዲዮች ማለት በማናቸውም መልክ በሕግ በተቋቋመ ፍ/ቤት ቀርበው የመጨረሻ ውጤት ያገኙ ጉዲዮችን የሚሸፍን መሆናቸውንና በፍርድ፣ በብይን ፣ በውሣኔ ፣ በትእዛዝ ፣ ወይም በጊዜያዊ አገልግልት ባለው ትእዛዝ የመጨረሻ ውጤት አግኝተው በልላ መልክ ለመንቀሣቀስ የማይችለ የክርክር ነጥቦችን ሁለ የሚያጠቃልል ጉዲይ መሆኑን መገንዘብ የምንችለው ጉዲይ ነው። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5 ስር በተመለከተው አኳኋን አንድ ጉዲይ አስቀድሞ በፍርድ ያለቀ ነው ለማለት መረጋገጥ ካለባቸው ሁኔታዎች ውስጥ ቀደም ሲል ቀጥተኛ የፍሬ ነገር ጭብጥ የነበሩ ጉዲዮች በድጋሚ በቀረበው ክስም ላይ በቀጥታ በፍሬ ነገር ጭብጥ ሆነው መቅረባቸው ፣ ቀደም ሲል የነበረውን ክርክር አሁን በክርክር ተሣታፉ በሆኑ ወገኖች ወይም ከእነሱ መብት በተላለፈላቸው ወይም ተላልፍላቸው በነበረ ወገኖች መሆኑንና እነዚህ ጉዲዮች ቀደም ሲል በተካሄደው ሙግት የመጨረሻ ፍርድ ያረፈባቸው መሆኑን ነው።
No topics extracted.
ቀጥተኛ የፍሬ ነገር ጭብጥ በመጨረሻ ፍርድ መቃወሚያነት ሲቀርብ ተቀባይነት የሚኖረው ይኸው ጉዲይ በድጋሚ በቀረበው ክርክር ላይ መቅረቡ ሲረጋገጥ ነው ቀጥተኛ የፍሬ ነገር ጭብጥ የሚለው ሐረግ አጠቃላይ ይዘቱ ሲታይም በመጀመሪያው ክርክር ላይ በአንደኛው ወገን ተጠይቆ በልላኛው ወገን የተካደ ወይም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የታመነና በዚሁ ላይ የፍርድ ውሣኔ ያረፈበት የክርክር ነጥብ መሆኑን መገንዘብ አያዲግትም በመሆኑም በድጋሚ በቀረበው ክስ በቀድሞው ክርክር ተሣታፉ በነበሩ ወገኖች ወይም ከእነሱ መብት በተላለፈላቸው ወገኖች የሚካሄድ መሆኑና በሁለተኛው ክስም የተያዘው የፍሬ ነገር ጭብጥ ከመጀመሪያው ጋር ተመሣሣይ ሆኖ የመጨረሻ ፍርድ ያረፈበት መሆኑ ከተረጋገጠ እንዱሁም ጉዲዩ የመጨረሻ ፍርድ አርፍበታል የሚል ተቃውሞ በተከራካሪ ወገን ከተነሣ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5 እና 244(2) ድንጋጌዎች የምንገነዘበው ነጥብ ነው።
በተያዘው ጉዲይ አመልካች በ11/12/2001 ዓ.ም ለፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ድርሻቸው ባለው መኖሪያ ቤት ላይ የተደረገው የሽያጭ ውል የሚጎዲቸውና ሕገ ወጥ መሆኑን ጠቅሰው ውለ እንዱፈርስላቸው ዲኝነት የጠየቁ ሲሆን እህታቸው የሆኑት የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ ባሁኑ 3ኛ ተጠሪ ላይ በመሰረቱት የውል ይፈረስልኝ ክርክር ስርዓቱን ጠብቀው የጣልቃ ልግባ አቤቱታ አቅርበው የስር ፍርድ ቤት የአመልካች ጥያቄና የ1ኛ ተጠሪ ጥያቄ የተለያዩ ምክንያቶችን መሰረት ያደረገ ነው በሚል ምክንያት የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ አድርጎ አመልካች በተናጠል መብቷን ማስከበር እንደሚችለ ገልጾ አመልካችን ስለማሰናበቱ የስር ፍርድ ቤት መ/ በግልጽ ያሳያል። ከዚህ በሁዋላ አመልካች የውል ይፍረስልኝ ጥያቄ በተናጠል ሲያቀርቡ ደግሞ 1ኛ ተጠሪ በ3ኛ ተጠሪ ላይ የውል ይፍረስልኝ ጥያቄ አቅርበው ተቀባይነት እንዲጡ ፣ የአመልካች ጥያቄም ተመሳሳይ እንደሆነና በ1ኛ ተጠሪ በቀረበው አቤቱታም የክርክሩ ተሳታፉ ሁነው ተቀባይነት እንዲጡ ተገልፆ ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 5 መሰረት መዝገባቸው ተዘግቶባቸዋል።
ከዚህ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ መገንዘብ የሚቻለው የስር ፍርድ ቤት አመልካች በ1ኛ ተጠሪ በቀረበው ክስ የክርክሩ ተሳታፉ ነበሩ ከማለት በስተቀር በመ/ የተሰጠው ብይን ይዘቱ ምን እንደነበር በግልፅ ያልመዘገበውና ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 5 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ ጋር አዛምድ ያልተመለከተው መሆኑን ነው። አመልካች የውል ይፍረስልኝ ጥያቄ በሥርዓቱ መሰረት አቅርበው የስር ፍርድ ቤት በተናጠል ሉያቀርቡ የሚገባውና 1ኛ ተጠሪ ካቀረቡት ምክንያት የተለየ ምክንያት ያለው ነው በማለት ብይን የሰጠበት ጉዲይ ቀድሞ በፍርድ ያለቀ ነው ልባል የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። በዚህ ችልት እምነት አመልካችና 1ኛ ተጠሪ የቤት ሽያጭ ውል እንዱፈረስ የጠየቁት የተለያዩ ምክንያቶችን መሰረት በማድረግ ነው ቢባልም የውል ይፍረስልኝ ጥያቄው ውጤት ግን አመልካችና 1ኛ ተጠሪ በቤቱ ላይ አለን የሚለትን መብት መጠበቅ በመሆኑ አመልካች ትክክለኛውን መድረክና ስርዓት በመምረጥ የውል ይፍረስልኝ ጥያቄ በጣልቃ ገብነት አቅርበዋል ፣ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን በያዘው መዝገብ አስተናግድ ተገቢውን ውሳኔ መስጠት ነበረበት።
ፍርድ ቤት በፈጠረው ስህተት ተከራካሪ ወገን ተቀጪ የሚሆንበትና በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 37 መሰረት የተከበረለትን ፍትህ የማግኘት መብት የሚጣበበት አግባብ የለም።
ስለሆነም የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ራሱ በመ/ የሰጠውን ብይን ይዘት ባግባቡ ሳይመረምር የአመልካችን ጥያቄ ይዘት ከ1ኛ ተጠሪ ጥያቄ ይዘት ጋር መመሳሰለን ብቻ በመመልከት የአመልካችን የዲኝነት ጥያቄ ቀድሞ በፍርድ ያለቀ ነው በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 5 መሰረት መዝጋቱ መሰረታዊ የሆነ የሥነ ሥርዓት ሕግ ግድፈት ያለበት ሁኖ አግኝተናል።
በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ