No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 5736ዐ ሐምል 15 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ/ማ - ሜሮን ሰልሞን ቀረበች ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - ዮናስ ለሜሳ ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የማቅረቢያው ጊዜ ያለፈበት ይግባኝ ይከፈት ዘንድ እንዱፈቀድ የቀረበውን ጥያቄ መነሻ ያደረገውን ክርክር የሚመለከት ነው። የማስፈቀጃ ጥያቄው የቀረበው ለፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ሲሆን፣ ጥያቄ አቅራቢው የአሁኑ ተጠሪ ነበር። የይግባኝ ማቅረቢያው ጊዜ ሉያልፍበት የቻለው ወይም ይግባኙን በሥነ ሥርዓት ሕጉ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ሉያቀርብ ያልቻለው ጉዲዩን ይዞ ሲከታተል በነበረው ነገረ ፈጁ ስህተት /ጥፊት/ እንደሆነም በማመልከቻው ላይ ገልጾአል። ፍ/ቤቱም ይህን መነሻ በማድረግ የአሁን አመልካች መልስ ሰጪን አስቀርቦ ክርክሩን ከሰማ በኋላ ጊዜው ያለፈው በነገረ ፈጁ ጥፊት ነው። ነገረ ፈጁም በዚህ ምክንያት የዱሲፔሉን እርምጃ ተወስድበታል የሚለትን ምክንያቶች በመስጠት የተጠሪን ጥያቄ ተቀብልአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች ሰኔ 17 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልቱ እንዱታይ የተደረገው የይግባኝ ማስፈቀጃው ጥያቄ በበቂ ምክንያት የተደገፈ ነው በሚል በሥር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 326/2/ ከተቀመጠው ድንጋጌ ጋር ተገናዝቦ ሉመረመር ይገባል በመባለ ነው።
በመሆኑም በዚህ ረገድ ግራ ቀኝ ወገኖች ያሰሙትን ክርክር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ተጠሪ የይግባኝ ማስፈቀጃ አቤቱታ ለፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ያቀረበው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.
323/2/ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ይግባኙን ባለማቅረቡ ከፍ/ቤቱ ፈቃድ ለማግኘት ነው። ጊዜ ካለፈ በኋላ ይግባኝ እንዱከፈት ጥያቄ የሚቀርበው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 325 በተደነገገው መሰረት ሲሆን፣ ጥያቄው ተቀባይነት ያለው ስለመሆን አለመሆኑ የሚመረመረው /የሚመዘነው/ ደግሞ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 326 መሰረት ነው። ጥያቄው ተቀባይነት አለው ወይንስ የለውም? የሚለው ነጥብ ሉወሰን የሚገባው እንደየአግባቡ በንኡስ ቁ/1/ ወይም /2/ መሰረት እንደሆነም ግልፅ ነው በንዐስ ቁ /1/ እንደተመለከተው አመልካቹ ወይም የፈቃድ ጥያቄ አቅራቢው ይግባኙን በጊዜው ለማቅረብ ያልቻለው በበቂ ምክንያት መሆኑ ፍ/ቤቱን ማሣመን ከቻለ ይግባኙን በአሥር ቀናት ውስጥ እንዱያቀርብ ይፈቀድለታል። በዚህ ረገድ ምክንያቱ በቂ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ፍሬ ነገር በፍ/ቤቱ የሚመዘን ከመሆን አልፍ በሕጉ የተቀመጠ የታወቀ /የተለየ/ መስፈርት የለም።
በንዐስ ቁ./2/ የተቀመጠው ድንጋጌ ግን አመልካቹ ያቀረበው ምክንያት በንኡስ ቁ./1/ አባባል ሉስተናገድ የማይገባ ወይም ተቀባይነት የላለው ነው የሚባልበትን አግባብ የሚያመለክት ነው።
በፈቃድ መጠየቂያው ማመልከቻ ላይ የተገለፀው ምክንያት ይግባኙን በጊዜው ማቅረብ ያልቻለው በአመልካቹ ጠበቃ ወይም ነገረ ፈጁ ወይም በወኪለ ያለመቅረብ እና በእነዚሁ ጉድለቶች መሆኑን የሚያመለክት ከሆነ ምክንያቱ በንኡስ ቁ./1/ እንደተነገረው በቂ ነው ልባል እንደማይገባ ድንጋጌው በግልጽ ያመለክታል። በዚህ ምክንያትም የይግባኝ ይከፈትልኝ ጥያቄው ተቀባይነት ለማግኘት አይችልም በማለት ግልጽ ድንጋጌ ሕጉ አስቀምጦአል።
ወደያዝነው ጉዲይ ስንመለስ ተጠሪ ይግባኙን በጊዜው ያላቀረበው በነገረፈጅ ጉድለት ምክንያት እንደሆነ በፈቃድ መጠየቂያ ማመልከቻው አረጋግጦአል። የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ይግባኙ እንዱከፈት የፈቀደው ነገረ - ፈጁ ሥራውን በታማኝነት እና በተገቢ የሥራና የሙያ ሥነ ምግባር አልፈፀሙም የሚል ምክንያት በመስጠት እንደሆነ ከውሣኔው ለመገንዘብ ችለናል። በእኛ እምነት ሕጉ ግልጽ ነው። የነገረፈጁን ወይም የጠበቃውን ወይም የወኪለን በታማኝነት ሥራውን አለመሥራት ወይም አለመሥራት እንደመስፈርት ተወስድ በሕጉ አልተቀመጠም። ለምዘና የሚቀርብ ፍሬ ነገርም አይደለም። ይህ ሁኔታ በአመልካቹ /የይግባኝ ማስፈቀጃ ጥያቄ አቅራቢው/ እና በነገረፈጁ በጠበቃው ወይም በወኪለ መካከል ለሚነሣ የኃላፉነት ክርክር አወሳሰን አግባብነት ይኖረው እንደሆነ ነው እንጂ ይግባኙ ይከፈትልን በሚለው ወገን እና በተቃራኒው ይግባኙ ሉከፈት አይገባም በሚለው ተከራካሪ ወገን መካከል የሚነሣ አይደለም።
ፍ/ቤቶችም የቀረበላቸውን ጉዲይ መወሰን ያለባቸው በሕጉ መሰረት እንደሆነ የሚያከራክር አይደለም። ግልጽ የሆነውን ሕግ በመተላለፍ የሚሰጠው ውሣኔ የሕግ መሰረት የላለው በመሆኑ ተቀባይነት የለውም። ከሁለ በላይ ደግሞ ውሣኔው ከሕጉ አተረጓጎም /አተገባበር/ አንፃር ሲታይ መሰረታዊ ስህተት ያለበት ነው የሚሆነው። ከዚህ የተነሣም አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት ችለናል። በዚህ መሰረትም ተከታዩን ወስነናል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት በፍ/ብ/ይ/መ/ቁ. 54164 ግንቦት 11 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሮአል።
ተጠሪ ያቀረበው የይግባኝ ይከፈት ጥያቄ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 326/2/ እንደተደነገገው ተቀባይነት የለውም ብለናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።