No summary available.
ሰኔ 02 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጏስ ወልደ አልማው ወላ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሮ ዓለምነሽ አበበተጠሪ ፡- አቶ ተስፊዬ ገሰሰ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ፍቺን ተከትል የተነሳውን የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ጥያቄ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ አመልካች በተጠሪ ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው።የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡-ከተጠሪ ጋር ከ1970 ዓ/ም ጀምሮ አብረው እንደባልና ሚስት ከኖሩ በኋላ ታህሳስ 25 ቀን 1977 ዓ/ም በአዱስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የፈጸሙት ጋብቻ ከሚያዚያ 18 ቀን 1994 ዓ/ም በፍቺ መፍረሱን፣በጋራ የሰሩትን ቤት ቁጥር 398ሀ1 የሆነን ቤት እንዱከፊፈለ አመልካች ተጠሪን ጠይቀው ተጠሪ ፈቃደኛ ካለመሆናቸውም በላይ ከ1989 ዓ/ም እስከ 1992 ዓ/ም በወር ብር ከ800.00(ስምንት መቶ ብር)፣ከ1992 እስከ 1997 ዓ/ም ብር 900.00፣ከ1997 ዓ/ም ጀምሮ በአመት ብር 20,000.00 ተጠሪ ቤቱን እያከራዩ ገቢውን ለአመልካች ሉከፍሎቸው ያልቻለ መሆኑን ገልፀው በቤቱ ኪራይ የሚገኘውን ገቢ እንዱያካፍሎቸውና ቤቱን በስምምነት ሽጠው ለመከፊፈል ፈቃደኛ ካልሆኑ በሐራጅ ተሽጦ እንዱከፊፈለ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መከላከያ መልስም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርበዋል። ተጠሪ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት በማንሳት የተከራከሩት ጉዲዩ የመጨረሻ ፍርድ ያገኘ ነው በሚል ነው። የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም በተጠሪ በኩል በመጀመሪያ ደረጃ የቀረበውን መቃወሚያ በጭብጥነት ይዞ ጉዲዩን በመመርመር ጉዲዩ ውሳኔ ያረፈበት ጉዲይ በመሆኑ ድጋሚ ክስ ላቀርብበት የማይገባ ነው በማለትና የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 5 እና 244(2(ለ)) ድንጋጌዎችን በዋቢነት በመጥቀስ መዝገቡን ዘግቶታል። በዚህ ብይን አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሙለ ሙለ ጸንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም በአሜሪካን አገር የሚገኝ ፍርድ ቤት በግልፅ ዲኝነት የሰጠበት ስለሆነ ዲግመኛ ዲኝነት መጠየቅ አይቻልም በማለት መዝገቡ የተዘጋ
No topics extracted.