No summary available.
14/10/2ዐዐ3ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የሱ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጠበቃ አቶ ግሩም አየለ ቀረቡ ተጠሪ፡- 1- አቶ ደጀኔ በቀለ - ቀረቡ 2- አቶ አሸናፉ አብርሃም አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የአሁን ተጠሪዎች በሥር የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ከሣሾች የነበሩ ሲሆን አመልካች ደግሞ ተከሣሽ ነበር። ክሱም በተከሣሽ ድርጅት ተቀጥሬን እየሰራን ተከሣሽ ያለአግባብ የሥራ ውላችን እንዱቋረጥ ያደረገ ስለሆነ በህጉ መሰረት የተለያዩ ክፍያዎችን እንዱከፍለን ይወሰንበት የሚል ነው።
ተከሣሽም ለክሱ በሰጠው መልስ ከሣሾች በምርት ማምረቻ ማሽን ከመጠን በላይ ነዲጅ በመጨመርና ማሽኑ በፍጥነት እንዱሰራ በማድረጋቸው ሙቀት ጨምሮ የማሽኑ ኩሽኔታ ከመቃጠለም በላይ በሰርኩላሽን ዳስክ ብልሽት ደርሶ በቀጣይ ፈረቃ ማሽኑ የቆመ በመሆኑ በተከሣሽ ድርጅት ላይ ባደረሱት ጉዲት የተነሣ ከሥራቸው እንዱሰናበቱ ተደርገዋል ብሎል።
የሥር የፋ/የ/መደ/ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ ከመረመረ በኋላ በሰጠው ፍርድ ከሣሾች በአሰሪው ንብረት ላይ በከባድ ቸልተኝነት ጉዲት እንዱደርስ ያደረጉ በመሆናቸው ውለ እንዱቋረጥ የተደረገው በህጋዊ መንገድ ነው ብሎል።
ጉዲዩን በይግባኝ የመረመረው የሥር የፋ/ከ/ፍ/ቤት በበኩለ ማሽኑ የተበላሸው ይግባኝ ባዮች /የሥር ከሣሾች / ለቀጣዩ ፈረቃ ተረኞች በ2፡ዐዐ አስረክበው ማሽኑም ሥራውን እያከወነ ቆይቶ 5፡3ዐ ሲሆን የቆመ በመሆኑ እንዱሁም የማሽኑን ሁኔታ የሚቆጣጠር ኮምኘዩተር ተበላሽቶ ስለነበር ጉዲቱ የደረሰው በይግባኝ ባዮች ነው ለማለት አይቻልም ሲል ይግባኝ ባዮች ወደ ሥራቸው እንዱመለሡና መልስ ሰጪ /የአሁኑ አመልካች/ የ6 ወር ደመወዛቸውንም እንዱከፍል ፈርዶል።
በሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ፍርድ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት አመልካች የሰበር አቤቱታውን ለዚህ ችልት ያቀረበ ሲሆን በዋናነት የጠቀሳቸው የቅሬታ ነጥቦችም፡- ተጠዎች በአመልካች ንብረት ላይ ብር 2,ዐዐዐ,ዐዐዐ የሚገመት ጉዲት በማድረሣቸው ምክንያት የሥር የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ከሥራ የተሰናበቱት በህጋዊ መንገድ ነው ሲል የወሰነውን ከፍተኛው ፍ/ቤት መሻሩ፣ በልዩ ባለሙያዎች /Experts/ የተሰጠውን የምስክርነት ቃል ከፍተኛው ፍ/ቤት ከሙያው ወጪ ውድቅ ማድረጉ፣ ከፍተኛው ፍ/ቤት ለተጠሪዎች ካሣ ብቻ ይከፈላቸው ማለት ሲገባው ወደ ሥራ ይመለሡ ማለቱ ያለአግባብ ነው የሚለ ናቸው።
ተጠሪዎች በበኩላቸው በሰጡት መልስ የአመልካችና የተጠሪዎች ምስክሮች ተመሣሣይ ሥራ ያላቸውና በጊዜው ሥራ ላይ ሆነው ሁኔታውን የተመለከቱ እንጂ ለሙያዊ ምስክርነት ያስፈልጋለ ተብለው የተጠሩ አይደለም። ለቀጣዩ ፈረቃ ማሽኑን አስረክበን ከሄድን ከ5፡ዐዐ ቆይታ በኋላ ለደረሰው ጉዲት ተጠሪዎች ተጠያቂዎች አይደለንም በማለት የአመልካች የሰበር አቤቱታ ውድቅ እንዱደረግ ጠይቀዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር ከዚህ በላይ የተገለፀ ሲሆን እኛም በአመልካችና በተጠሪዎች መካከል የነበረው የሥራ ውል የተቋረጠው በህጋዊ መንገድ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ ይዘን የግራ ቀኙን ክርክር እንደሚከተለው መርምረናል።
የአመልካች ማሽን በደረሰበት ጉዲት መቆሙን ተጠሪዎችም የሚያምኑት ጉዲይ ሲሆን ዋናውና አከራካሪ የሆነው ጉዲይ ግን በማሽኑ ላይ ጉዲት የደረሰው በተጠሪዎች ፈረቃ ነው? ወይስ ተጠሪዎች ለቀጣዩ ፈረቃ ሰራተኞች አስረክበው ከወጡ በኋላ ነው? የሚለው ነው። በዚህ ነጥብ ላይ አመልካች ተጠሪዎች በፈረቃቸው ወቅት ያለአግባብ ነዲጅ በመጨመርና ማሽኑም ከሚገባው በላይ ፍጥነት እንዱጨምር በማድረጋቸው በተፈጠረ ሙቀት የተነሣ በተለያዩ የማሽኑ ክፍልች ጉዲት ደርሷል የሚል ሲሆን ጉዲቱ ግን የታወቀው ከኮምኘዩተር በተገኘው መረጃ መሰረት ሆኖ በቀጣይ ፈረቃ የሚሰሩ ሰራተኞች ሥራ ላይ ባለበት ጊዜ ነው ብሎል። ተጠሪዎች በበኩላቸው ማሽኑ በራሳቸው ፈረቃ አለመበላሸቱንና ብልሽቱም የደረሰው በቀጣዩ ፈረቃ በመሆኑ ለደረሰው ጉዲት ሃላፉነት የለብንም ሲለ ይከራከራለ።
የሥር የፋ/የ/መደ/ፍ/ቤትም ከግራ ቀኙ የቀረበውን የፍሬ ነገር ክርክር ለማጣራት ማስረጃዎችን የሰማ ሲሆን በአመልካች በኩል የቀረቡት ልዩ ዕውቀት ያላቸው /Experts / ምስክሮች ሲሆኑ በተጠሪዎች በኩል የቀረቡት ምስክሮች ደግሞ ልዩ አዋቂዎች ያልሆኑ በቀጣዩ ፈረቃ ሲሰሩ የነበሩ የማሽኑ ኦፔሬተሮች ናቸው።
ልዩ አዋቂዎች የሚባለት በትምህርት ፣ በሥልጠና እና በልምድ ዕውቀት ያካበቱ ሰዎች ሲሆኑ እነዚህን ሰዎች ፍ/ቤቱ በሚጠራበት ጊዜ በተፈለገው ጉዲይ አግባብ የሆነ ዕውቀት ያላቸው ስለመሆኑ ማረጋገጥ ይኖርበታል። ይህም ሲባል የኤክስፏርት ምስክርነት ለምሳላ በኢንጅነሪንግ /engineering/ የሚያስፈልግ ከሆነ መጣራት ያለበት በዚሁ በኢንጅነሪንግ ሙያ ዕውቀት ያለው ሰው መሆን ይኖርበታል። እንዱሁም በአርክቴክቸር /architecture/ ቴክኒዮልጂ /technology / እና በመሳሰለት ጉዲዮች ላይ የልዩ አዋቂዎች ምስክርነት አስፈላጊነት በፍ/ቤቱ ሲታመን ወይም ተከራካራዎቹ ቀርበው እንዱሰሙ በጠየቁ ጊዜና ፍ/ቤቱም የልዩ አዋቂዎች ምስክርነት ጉዲዩን ለማብራራት ወይም ለክርክሩ ውሣኔ አሰጣጥ ተገቢ ነው ካለ ከጉዲዩ ጋር አግባብነት ያላቸውን ልዩ አዋቂዎች ቀርበው የምስክርነት ቃላቸውን እንዱሰጡ ሉያደርግ ይችላል።
No topics extracted.
ይህ ከዚህ በላይ የተገፀው ሁኔታ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 136/1/ ሥር የተደነገገ ሲሆን የምስክርነት ቃላቸውን የሚሰጡ ልዩ አዋቂዎችም የሚሰጡት የምስክርነት ቃል በገለልተኝነት የሚሰጥ መሆን ይኖርበታል። በዚህ በተያዘውም ጉዲይ የአሁኑ አመልካች ባቀረባቸው የልዩ አዋቂ ምስክሮች ገለልተኝነት /impartiality of experts/ ከተጠሪዎች በኩል የቀረበ ክርክር የላለ ሲሆን በአንድ የፍትሃብሄር ጉዲይ ልዩ አዋቂዎች/Experts / እና ልዩ አዋቂዎች ያልሆኑ ምስክሮች ቀርበው በተሰሙ ጊዜ ‛ In the civil context … lay evidence should not be preferred to expert evidence with out good reason “ የሚለውን የማስረጃ ምዘና መርህ መከተል ይገባል።
ከዚህ በላይ ከተጠቀሰው የማስረጃ ምዘና መርህ መገንዘብ የሚቻለው ዳኞች በልዩ አዋቂዎች የተሰጠውን ምስክርነት ተቀባይነት የለውም በማለት ሉወስኑ የሚችለት ይህንኑ የልዩ አዋቂዎችን ምስክርነት ተቀባይነት ሉያሳጣ የሚችል በቂ ምክንያት መኖሩ ከተረጋገጠ ብቻ ነው። የልዩ አዋቂዎችን ምስክርነት ተቀባይነት ለማሳጣት በቂ ምክንያት ከላለ ግን ልዩ አዋቂ ያልሆኑ ምስክሮች ከሰጡት ምስክርነት ይልቅ በልዩ አዋቂዎች የተሰጡት ምስክርነት ተመራጭነት ይኖረዋል። በልላ በኩል ልዩ አዋቂዎች ከሰጡት ምስክርነት ልዩ አዋቂ ያልሆኑ ምስክሮች የሰጡት ምስክርነት አሳማኝ ሆኖ ከተገኘ ደግሞ የልዩ አዋቂዎችን የምስክርነት ቃል ውድቅ በማድረግ ልዩ አዋቂዎች ያልሆኑት ምስክሮች የሰጡትን የምስክርነት ቃል ዳኞች እንዲይቀበለ የሚከለክላቸው የህግ መርህ የለም።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ የአመልካች የልዩ አዋቂ /Experts / ምስክሮች ስለብልሽቱ የቴክኒዮልጂ ውጤት የሆነውን ኮምፑዩተር በማንበብ በሙቀት መጨመርና ከመጠን በላይ በሆነ ፍጥነት ማሽኑ እንዱሰራ በመደረጉ የተነሣ ብልሽት የደረሰበት መሆኑን ገልፀዋል። ይህን አግባብ ባለው ባለሙያ የተሰጠውን ምስክርነት ውድቅ ለማድረግ ምንም በቂ ሁኔታ ባልተገኘበት የሥር ከፍተኛው ፍ/ቤት ውድቅ በማድረግ ለጉዲዩ ይግባኝ ባዮች /ያሁን ተጠሪዎች/ ሀላፉት የለባቸውም ያለውና የሥራ ስንብቱም የተደረገው በህገወጥ መንገድ በመሆኑ የ6 ወር ደመወዝ ተከፍልአቸው ተጠሪዎች ወደ ሥራቸው ይመለሱ በሚል የወሰነው መሰረታዊ የሆነ የማስረጃ ምዘና መርህን ያልተከተለ ስለሆነ ውሣኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው።
ው ሣ ኔ
የሥር የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 26/04/2003 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የሥር የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ በቀን 11/8/2002 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በአመልካችና በተጠሪዎች መካከል የነበረው ውል የተቋረጠው በህጋዊ መንገድ ነው ተብሎል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።
መዝገቡ የተዘጋ