No summary available.
መጋቢት 23 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኦሮሚያ ከተሞች ፔላን ኢንስቲትዩት - ነ/ፈጅ ለገሰ ለማ ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ፍርድን መቃወም የሚቻልበትና አቤቱታው የሚስተናግድበትን አግባብ የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በአሁኑ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ የተጠቀሱት ተጠሪዎች ባሁኑ 4ኛ ተጠሪ ላይ ያስፈረደት ፍርድ የአመልካችን መብትና ጥቅም የሚነካ በመሆኑ ፍርደ እንዱነሳለት ባቀረበው አቤቱታ መነሻ ነው። የስር ፍርድ ቤትም አመልካችንና ተጠሪዎችን በአፈፃፀም መዝገቡ ላይ እንዱከራከሩ በማድረግ አመልካች ዋናውን ውሳኔ በይግባኝ ሳያሽር አፈፃፀሙን ሉቃወም አይችልም፣ ውለ የሚፈርስበት ምክንያትም የለም በማለት አፈፃፀሙ ሉቀጥል ይገባል ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል። በዚህ ትእዛዝ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለቦረና ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ የሰበር አቤቱታውን ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የአፈጻጸም ትእዛዝ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ ግንቦት 04 ቀን 2002 ዓ.ም በጻፈት አራት ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች በተሰጠው ትዕዛዝ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ አመልካች በሕጉ በተሰጠው ስልጣን ለክልለ ከተሞች እንደየደረጃቸው ከተማ አቀፍ መዋቅራዊ ፔላን እና የአካባቢ ልማት ፔላን (City wide structure plan and local development plan) እየሰራና እያሰራ ስራ ላይ እንዱውል የማድረግና ስራ ላይ መዋለን የመቆጣጠር ኃላፉነቱንና ተግባሩን ለመወጣት የሚችል ሁኖ እያለ ይህንኑ ስልጣንና ኃላፉነት መሰረት በማድረግ ተጠሪዎች ከከተማው ፔላን ውጪ ቦታ ሉወስደ አይገባም በማለት ያቀረበው የፍርድ ተቃውሞ ተቀባይነት ያጣው ያላግባብ መሆኑንና አቤቱታው የቀረበውም ዋናውን ፍርድ በመቃወም ሁኖ እያለ በአፈፃፀም መዝገብ ላይ እንደቀረበ ተደርጎ ትእዛዝ መሰጠቱ ተገቢነት የላለው መሆኑን፣ ዋናውን ፍርድ ሕጋዊ አይደለም በማለትም ተገቢው ክርክርና ማስረጃ ቀርቦ እያለና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 145 መሰረትም አግባብነት ያለው ማስረጃ በፍርድ ቤቱ እገዛ እንዱቀርብ ጥያቄ ቀርቦ እያለ ይኸው ታልፍ በዋናው ጉዲይ ላይ የተሰጠው ውሳኔ ሉሻር አይገባም ተብል የተሰጠው ትእዛዝ ሥነ ሥርዓታዊ አይደለም በማለት ዘርዝረው የአፈጻጸም ትዕዛዝ እንዱሻር ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም የአመልካች የፍርድ ተቃውሞ አቤቱታ ውድቅ የመደረጉን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጎአል። በዚህም መሰረት ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው መልሳቸውን በፅሐፍ አቅርበዋል፣ አመልካችም የመልስ መልሱን ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
በመሰረቱ አንድ የፍትሐብሕር ክርክር የሚመራበት ሥርዓት የሚገዛው በ1958ቱ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕጋችን እና በክልልች ስራ ላይ ባለት አግባብነት ባላቸው ሕጎች መሆኑ እሙን ነው። የ1958ቱ የፍትሐብሕር ስነ ሥርዓት ሕጋችን ከያዛቸው ስርዓቶች መካከል በፍርድ ላይ የሚቀርበው ተቃውሞ እና በፍርድ አፈጻጸም ጊዜ በተያዘ ወይም በተከበረ ንብረት ላይ የሚቀርበው ጣልቃ ገብነትን የሚገዙት ድንጋጌዎች ይገኙበታል። እነዚህ አቤቱታዎችን የሚገዙት ድንጋጌዎች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 እና 418 ስር የተመለከቱት ናቸው።
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 አንድ የክርክሩ ተካፊይ መሆን የሚገባው ሰው የክርክሩ ተካፊይ ሳይሆን ውሳኔ ተሰጥቶ ከሆነ እና ውሳኔውም ያረፈው በአንድ የክርክሩ ምክንያት በሆነ ንብረት ላይ ሁኖ ይህንኑ የክርክሩ ተካፊይ ያልሆነ ወገንን መብትና ጥቅም የሚነካ መሆኑ ከተረጋገጠ ፍርደ ይኸው ወገን ባለበት እንዱታይና እንዱነሳለት የሚደነግግ ነው። አቤቱታው የሚቀርብበት ሥርዓትም በቁጥር 359 ስር በተመለከተው መንገድ መሆን እንደአለበት የተቀመጠ ሲሆን ይህ ድንጋጌ የመቃወሚያ አቤቱታ አቀራረብ በክስ አመሰራረት አይነት ሁኖ የማስረጃ ዝርዝር ሁለ ይህንኑ ስርዓት ማሟላት እንደአለበት ያስገነዝባል። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 418 መሰረት የሚቀርበው አቤቱታ ደግሞ ለፍርድ ማስፈጸሚያ እንዱሆን የተያዘ ወይም የተከበረ ንብረት የፍርድ ባለእዲው ንብረት አይደለም፣ የራሴ ንብረት ነው የሚል ወገን አቤቱታውን የሚያቀርብበትን አግባብ የሚደነግግ ድንጋጌ ነው። በእነዚህ ድንጋጌዎች መሰረት አቤቱታ አቅራቢ የሚሆን ወገን በሕጉ አግባብ በተዘረጋው ስርዓት መሰረት አቤቱታውን ማቅረብ ያለበት ሲሆን ስርዓቱን ጠብቆ ያልቀረበን አቤቱታ ደግሞ ፍርድ ቤቱ ሉቀበል የሚችልበት አግባብ የላለ መሆኑን በፍትሐብሕር ስነ ስርአት ስለ ክርክር አመራር የተመለከቱት ድንጋጌዎች የሚያሳዩን ጉዲይ ነው። በተያዘው ጉዲይ አመልካች አቤቱታውን ያቀረበው በዋናው ጉዲይ ላይ የተሰጠው ፍርድ መብትና ጥቅሜን ይነካል በሚል ሲሆን አቤቱታውን የስር ፍርድ ቤት ያስተናገደው ግን በፍርድ አፈጻጸም መዝገብ ላይ ነው። ይሁን እንጂ የአመልካች የፍርድ ተቃውሞ አቀራረብ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 418 ድንጋጌን መሰረት ያደረገ ሳይሆን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358ን መሰረት ያደረገ ነው። የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን አቤቱታ በአፈጻጸም መዝገብ የሚቀበልበት ሥርዓት የላለ ሲሆን አመልካች ባቀረበው አቤቱታ መሰረት በዋናው ጉዲይ የተሰጠውን ፍርድ በያዘው መዝገብ ላይ ማስተናገድ ነበረበት።
No topics extracted.
ከክርክሩ ሂደት መረዲት እንደተቻለው አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሰረት በክርክሩ ጣልቃ ገብቶ እንዲይከራከር በስር ፍርድ ቤቱ የተከለከለው በአፈጻጸም መዝገብ አቤቱታውን እንደአቀረበ ተቆጥሮ ከመሆኑም በላይ ተጠሪዎች ከፍርድ ባለእዲው ነው ከተባለው 4ኛ ተጠሪ ጋር ያደረጉት ውል ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለውን ደንብ የሚጥስ አይደለም፣ ውለ ሲመሰረትም አመልካች አልተመሰረተም፣ በዋናው ጉዲይ ላይ የተሰጠው ፍርድ በይግባኝም አልተለወጠም በሚል ነው።
በእርግጥ እነዚህ ሁለት አካላት በአንድ መንግስታዊ መዋቅር (በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት አስተዲደር) ስር የሚገኙ አካላት ናቸው። ይሁን እንጂ በአንድ የክልል መንግሥታዊ መዋቅር ስር መገኘታቸው ብቻ አከራካሪውን የመሬት ይዞታ በተመለከተ ተመሣሣይ ጥቅምን የሚወክለ አካላት ናቸው ወደሚል መደምደሚያ የሚያደርስ አይደለም፤ እነዚህ ሁለት አካላት የክልለ መስተዲድሩ የተለያዩ እርከኖች ወይም አካላት ሆነው የየራሳቸው ሕጋዊ ሰውነት፣ ስልጣንና ተግባር እንዲላቸው የሚታመን ነው። ይህ ነጥብ በስር ፍርድ ቤት ግንዛቤ ውስጥ ያልገባ ከመሆኑም በላይ አመልካች በክርክሩ ቀደም ብል ከቀረበው ክርክር አመልካቹ የተለየ ላላ ክርክር ሉያቀርብ አይችልም የተባለውም ቢሆን ክርክራቸው ተመሣሣይና አንድ አይነት ጥቅም የሚወክል መሆኑና አለመሆኑ የሚታወቀው አመልካቹ አግባብነት ባለው የስነ ስርዓት ድንጋጌ ያቀረበው አቤቱታ ተገቢነት ካለው መዝገብ ጋር ታይቶ፣ ወደ ክርክሩ እንዱገባ ተደርጎ የሚያቀርበውን የክርክር አይነትና የሚወክለውን ጥቅም የአሁኑ 4ኛ ተጠሪ አቅርቦት ከነበረው ክርክር በማነፃፀር የሚታወቅ እንጂ አስቀድሞ ተመሣሣይ ክርክር አለው፣ ውለ አግባብነት ያለውን ደንብ የሚጥስ አይደለም የሚል ግምት በመያዝ አይደለም።
በመሰረቱ ከላይ እንደተጠቀሰው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት የሚቀርበው አቤቱታ በቁጥር 359 ስር በተመለከተው መንገድ መቅረብ ያለበት ነው። ድንጋጌው የአቤቱታው አቀራረብ የክስ አቀራረብ ሥርዓቱን ሉከተል እንደሚገባ የሚያሳይ ሲሆን እንዱህ ከሆነ ከሣሽ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 222 መሰረት አዘጋጅቶ ከሚያቀርበው የክስ ማመልከቻ ጋር በክሱ መሰማት ወቅት ለጉዲዩ ማስረጃ ይሆኑኛል የሚሎቸውን የሰውም ሆነ የጽሁፍ ማስረጃዎችን ዝርዝርና ዋናውን ወይም ትክክለኛ ግልባጮቻቸውን ማቅረብ ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥሕ/ቁ 223 ድንጋጌ የደነገገ ከመሆኑ ጋር ተጣምሮ ሲታይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት የሚቀርበው አቤቱታም ይህንኑ መከተል ያለበት መሆኑ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። በተለይም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 137/3/ የሰነድ ማስረጃዎችን በተመለከተ ማንኛውም ተከራካሪ ወገን ከአቤቱታው ጋር በማያያዝ ወይም ከቀነ ቀጠሮ በፉት ወይም በመጀመሪያው ቀን ቀጠሮ ካልቀረበ በቀር ማስረጃው ላቀርብ ወይም ይቅረብልኝ ተብል ሉጠየቅ እንደማይችል ተመልክቷል። ይሄው ጥያቄ ተቀባይነት የሚያገኘው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 256 ስር በተመለከተው አኳኋን ማስረጃዎቹ ሣያቀርቡት የቀሩት ከባድና በቂ በሆነ ምክንያት መሆኑን ፍ/ቤቱ ሲረዲ ብቻ ነው። የማስረጃ አቀራረብን በተመለከተ በሥነ ሥርዓት ህጉ የተመለከተው ላላው ደንብ የይግባኝ ሰሚውን ፍ/ቤት ሥልጣን የሚመለከት ነው በዚህም መሰረት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 345 ድንጋጌ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በራሱ አስተያየት ተገቢ ሆኖ ሲያገኘው ማናቸውም ዓይነት ሰነድ ወይም ምስክር ወይም ላላ ዓይነት ማስረጃ በተጨማሪነት እንዱቀርብለት የማዘዝ ህጋዊ ሥልጣን ያለው ስለመሆኑ ያሣያል። የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 145(1) ድንጋጌም በልላ ፍ/ቤት የሚገኝ ሰነድ የፅሁፍ ማስረጃ ወይም ፍርድ የተሰጠበት መዝገብ ለውሣኔው አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ፍ/ቤቱ በራሡ አነሣሽነትም ሆነ በተከራካሪዎቹ ጠያቂነት እንዱቀርብለት ማዘዝ የሚችል ስለመሆኑ ያስረዲል።
ከላይ እንደተገለፀው አመልካች በዋናው ጉዲይ ላይ በተሰጠው ፍርድ ላይ ያቀረበው ተቃውሞ ያላግባብ በአፈጻጸም መዝገብ ላይ ተያይዞ ጉዲዩ ከመታየቱም በላይ ዋናውን ፍርድ ለመቃወምና ለማሻር የሚያስችላቸውን ማስረጃዎች ዘርዝሮ ከማቅረቡም በተጨማሪ በፍርድ ቤቱ እገዛ መሰረት የሚቀርብለት ማስረጃ መኖሩንም ጠቅሶ እያለ ይህ ማስረጃ ሳይታይለት አቤቱታው ውድቅ መሆኑን የክርክሩ ሂደት በግልፅ ያሳያል። እንዱህ ከሆነ በአመልካች የተጠቀሰው ማስረጃ ሳይቀርብ በዋናው ጉዲይ ላይ የተሰጠው ውሳኔ በአመልካች መብት ወይም ጥቅም ላይ የሚያስከትለው ችግር የለውም ወደሚለው ድምዲሜ ሉያደርስ አይችልም። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን ተቃውሞ አግባብነት ባለው መዝገብ ሳይቀበልና ተገቢ ማስረጃዎችን ሁለ ሳይመለከት ውድቅ በማድረግ መወሰኑ የክርክሩን አመራር ከላይ በተመለከቱት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ የተቃውሞ አቀራረብና የማስረጃ አቀራረብ ደንቦች መሰረት አለመምራቱንና፣ በውጤቱም አመልካች በሕጉ የተጣለውን ኃላፉነትና ተግባሩን እንዲይወጣ የሚያደርግ በመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ሲጠቃለልም የበታች ፍ/ቤቶች በጉዲዩ ላይ ትእዛዝ የሰጡት አመልካች አቤቱታ ባላቀረበበት ሥርዓትና አቤቱታው ላቀርብ በማይችልበት መዝገብ ከመሆኑም በላይ የአመልካች አቤቱታ የተስተናገደው የማስረጃ አቀራረብ ሥርዓት ድንጋጌዎች በማይደግፈት፣ የፍርድ አካሄደ ባልተሟላ ሁኔታ በመሆኑ በእየርከኑ ባለ ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ትዕዛዞች ሙለ በሙለ ሉሻሩ የሚገባና የአመልካች አቤቱታ በዋናው የፍርድ መዝገብ ላይ ቀርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ተገቢውን ውሣኔ እንዱሰጥ ማድረጉ አግባብ ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም መሰረት የሚከተለውን ወስነናል።
ው ሣ ኔ