No summary available.
ታህሣስ 27 ቀን 2003 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኮንስትራክሽንና የቢዝነስ ባንክ አ.ማ - ነ/ፈጅ ነጋ አበበ ቀረቡ ተጠሪ፡-
ጉዲዩ የፍርድ አፈፃፀምን የሚመለከት ሲሆን የፍርድ ባለመብት የሆነው የአሁኑ ተጠሪዎች በአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት የአፈፃፀም ማመልከቻ እስከዚህ ሰበር ችልት እንዱከፈላቸው የተወሰነው ብር 1,307,607.00 /አንድ ሚሉዮን ሦስት መቶ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ሰባት ብር/ ከተለያዩ ወጪዎች ጋር እንዱፈጸምላቸው ጠይቀዋል። የስር ፍርድ ቤትም የተጠሪዎች አፈፃፀም መዝገብን በመቀበል እንደፍርደ የማይፈጸምበትን ምክንያት አመልካች ቀርቦ እንዱያስረዲ ወይም እንደፍርደ ፈፅሞ እንዱቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቶ የአሁኑ አመልካች ቀርቦ ተጠሪዎች በ27/07/1985 እና በ07/04/1986 ዓ.ም. በተፈረሙ የብድር ውልች ከአመልካች ላይ የወሰደትን ገንዘብ በውለ መሰረት ከሚያስከትለው ወለድ፣ የኢንሹራንስ ክፍያ እና ላልች ልዩ ልዩ ወጪዎች ጋር ብር 858,457.38 /ስምንት መቶ ሃምሣ ስምንት ሺህ አራት መቶ ሃምሣ ሰባት ብር ከሰላሣ ስምንት ሣንቲም/ እና አመልካች ሆቴል ቤቱን በጨረታ ከገዛው በኋላ ተጠሪዎች ባቀረቡት ክስ ምክንያት በየደረጃው ባለት ፍርድ ቤቶች ሆቴል ቤቱን እንዲይረከብ በማሳገድ ያላግባብ ስለተጠቀሙት አመልካች ሆቴል ቤቱን በወቅቱ ተረክቦ ቢሆን ኖሮ ከሆቴል ቤቱ ሉያገኝ የነበረውን የቤት ኪራይ ብር 604,000.00 /ስድስት መቶ አራት ሺህ ብር/ በድምሩ ብር 1,460,457.38/ አንድ ሚሉዮን አራት መቶ ስልሣ ሺህ አራት መቶ ሃምሣ ሰባት ብር ከሰላሣ ስምንት ሣንቲም/ ክስ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ከሚያስከትለው ወለድ እና ከክሱ ወጪ እና ኪሣራ ጋር እንዱከፍለት በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀጥታ ክስ ማቅረቡን በመግለጽ አፈፃፀሙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
377 መሰረት እንዱቆምለት ወይም ገንዘቡ ታግድ እንዱቆይለት አፈፃፀሙን ለያዘው ፍርድ ቤት አመልክቷል። አፈፃፀሙን የያዘው ፍርድ ቤትም አመልካች ያቀረበውን አቤቱታና እግድ ውድቅ በማድረግ አመልካች በፍርደ መሰረት ፈጽሞ እንዱቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል። በዚህ ትዕዛዝ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ ጥር 18 ቀን 2002 ዓ.ም. በጻፈት አራት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች የአፈፃፀም ትዕዛዝ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል።
ይዘቱም ባጭሩ፡አመልካች ከተጠሪዎች የሚፈለግ ዕዲ መኖሩን ገልፆ ቀጥታ ክስ በመመስረት ጉዲዩ እየታየ ባለበት ሁኔታ ተጠሪዎች የከፈቱት የአፈጻጸም መዝገብ እንዲይቆም መደረጉ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
377 ድንጋጌን መሰረት ያላደረገ በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም አመልካች የፍርድ ባለመብት በሆኑት ተጠሪዎች ላይ በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ በቀጠሮ ላይ ባለበት ሁኔታ አፈፃፀሙ የመቀጠለ አግባብነት ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 377 አንፃር ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጎአል። በዚህም መሰረት ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው የጽሐፍ መልሳቸውን ሰጥተዋል። የአመልካች ነገረ ፈጅም የመልስ መልሳቸውን በጽሐፍ ሰጥተዋል። ከዚህም በተጨማሪ አመልካች በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመሰረተው ቀጥታ ክስ በመ/ በሆነው ታይቶ ግንቦት 26 ቀን 2002 ዓ.ም. ውድቅ መሆኑን፣ እንዱሁም በዚሁ ውሣኔ ላይ አመልካች ይግባኙን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቀርቦ በመ/ በሆነው የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ መጽናቱ ተረጋግጧል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ፍርድ በተፈረደበት ማናቸውም ሰው ላይ ፍርድ የተፈረደለት ወገን ክስ ያቀረበበት እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ተገቢ መስል የገመተውን በቂ ዋስትና ወይም መያዣ እንዱሰጥ ካደረገ በሁዋላ ለክርክሩ ውሣኔ እስከሚሰጠው ድረስ አፈፃፀሙ ታግድ እንዱቆይ ትዕዛዝ መስጠት እንደሚችል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 377 ስር በግልጽ ተመልክቷል። ከዚህ ድንጋጌ መረዲት የሚቻለው በቀድሞው ክስና በአፈፃፀሙ ጊዜ በቀረበው ክስ ተከራካሪ የሆኑት ወገኖች ተመሳሳይ መሆን እንደሚገባቸው ነው። አመልካች ለተጠሪዎች እንዱከፍል በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ የተሰጠው የተጠሪዎችን ሆቴል ከግምቱ ውጪ ሸጧል በሚል ምክንያት ሲሆን ይህ ውሣኔ እስከዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ፀንቷል። አመልካች ከዚህ በሁዋላ በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ ክስ የመሰረተው በብድር ውለና በሐራጅ ገዝቼዋለሁ በሚለው ቤት የቀረበትን ጥቅም በመዘርዘር ነው።
No topics extracted.
አፈፃፀሙ እንዱታገድ የጠየቀውም ይህንኑ ክስ መሰረት በማድረግ ነው። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 377 ዓላማ የፍርድ ባለመብት የሆነ ወገን አፈፃፀሙን በሚቀጥልበት ጊዜ የፍርድ ባለዕዲው በበኩለ በፍርድ ባለመብቱ ላይ ክስ አቅርቦ ሲገኝ ምናልባት በክርክሩ ረቺ ቢሆን ፍርደን ጎን ለጎን ለማስፈጸም እንዱቻል ለማድረግ መሆኑ ይታመናል።
በተያዘው ጉዲይ አመልካች የፍርድ ባለመብት በሆኑት ተጠሪዎች ላይ ክስ የመሰረተው አስቀድሞ ታይቶ በተወሰነው ጉዲይ ሳይከፈለኝ የቀረ ዕዲ አለ፣ በጨረታ የተሸጠውን ሆቴል ደገሞ በጊዜው በመረከብ አከራይቼ ላገኝ እችል የነበረውን ጥቅም አስቀርተውብኛል በሚል ሲሆን ይህ አካሄድ መጨረሻ ላይ ጎን ለጎን ሉፈፀም የሚችል ፍርድ ባለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
377 ድንጋጌ ዓላማ ስር የሚወድቅ አይደለም። አመልካች ያቀረበውን ቀጥታ ክስ በመጀመሪያ ደረጃ ሲመለከተው የነበረው ፍርድ ቤትም ሆነ ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መደበኛ ችልት የአመልካችን ክስ ውድቅ ማድረጋቸው ተረጋግጧል። አመልካች አሁን የቀረው የመጨረሻ እድለ ጉዲዩን በሰበር ማሳየት ነው። በሰበር ሰሚው ችልት ጉዲዩ የሕግ ነጥብ አለበት የሚባል ከሆነም አመልካች ሥርዓቱን ጠብቆ ለተጠሪዎች የሚከፍለው ገንዘብ እንዱከበርለት ከሚጠይቅ በስተቀር አሁን የሥር ፍርድ ቤት የያዘውን አፈጻጸም ሙለ በሙለ እንዱቆም የሚያስችል አይደለም። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች የደረሱበት ድምዲሜ በአሁኑ ደረጃ ሲታይ ስህተት ነው ለማለት የሚያስችል ሆኖ አልተገኘም። በዚህም ምክንያት በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ስላልተቻለ ተከታዩን ወስነናል።
በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ሰበር ችልት የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
በዚህ ችልት