No summary available.
የካቲት 21 ቀን 2003 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ሙባረክ ከድር - ጠበቃ አቶ ወንድም ጥላሁን ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1ኛ. ሚ/ር ሙዋንጋ ሲርል - አልቀረቡም 2ኛ. ወ/ሮ አሰለፈች ሰይድ በላለበት የሚታይ 3ኛ. ወ/ሪት አስቴር ጉግሳ “ “ 4ኛ. አቶ አወል ሽበሺ “ “ 5ኛ. አቶ መሐመድ ሺበሺ ወኪል አቶ ሙሣ መሐመድ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 158 መሰረት በንብረት ላይ የተሰጠ የዕግድ ትዕዛዝ እንዱነሳ አቤቱታ ያቀረበ ወገን በጉዲዩ ላይ ተከራክሮ ዲኝነት እንዲገኘ የሚቆጠር ወገን ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሰረት ዲኝነት የመጠየቅ መብት የለውም በሚል በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠውን ትርጉም ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ተመልክቶ አግባብነቱን ለማየት በሚል የቀረበ ነው።
የጉዲዩም መነሻ የአሁን 1ኛ ተጠሪ ህዲር 25 ቀን 1999 ዓ.ም. በተጻፈ የክስ አቤቱታ ከሟች ወ/ሮ አረጋሽ ሺበሺ ጋር ከ1968 ዓ.ም. ጀምሮ በግሪክ አገር ጋብቻ ፈጽመን እየኖርን እያለ ሟች ኢትዮጵያ መጥታ ሞታለች የእኔም ባልነት በፍ/ቤት ተረጋግጧል። የጋራ ሀብት 1ኛ በየካ ክ/ከተማ ቀበላ 13/14 የሚኘውን ቁጥሩ አዱስ/የፊይል ቁጥር ሉዝ 06 የሆነ ቤት፣ 2ኛ በቦላ ክ/ከተማ ቀበላ 15 ቀበላ 15 የቤት ቁጥር አዱስ የሆነ ጅምር ቤት፣ 3ኛ በሟች ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራዲ ቅርንጫፍ የሚገኝ መጠኑ ያልታወቀ ገንዘብ ስለአለ ግማሽ ድርሻ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት የጠየቀበት ነው።
በዚህ የክስ ማመልከቻ በተጠሪነት የተሰየመ ወገን ስላልነበር ክሱ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሟች ወራሾች ካለ ቀርበው ክርክር ያደርጉ ዘንድ ጥሪ ሲያደርግ የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ህዲር 20 ቀን 2000 ዓ.ም. በተጻፈ መልስ ከሣሽ የሟች አሰሪ እንጂ ባል አይደለም እርሱም ከሟች ቀድሞ የሞተ ስለሆነ የጥብቅና ውክልናው ዋጋ ያለው አይደለም ተጣርቶ ውድቅ ይደረግልን፤ ሟች ንብረቷን በሙለ በኑዛዜ አስተላልፊለች። ክስ የቀረበበት ንብረት የሟች የግል ንብረቷ መሆኑንም አረጋግጣለች። ስለሆነም የጋራ ሀብት መሆኑ ሳይረጋገጥ የቀረበው ክስ አግባብነት የለውም በማለት ሲከራከሩ፤ የአሁን 4ኛ እና 5ኛ ተጠሪዎች በበኩላቸው እኛም የሟች ወራሾች ስለሆን የንብረቱ ተካፊይ ልንሆን ይገባል የሚል መልስ ጥቅምት 20 ቀን 2000 ዓ.ም.
በተጻፈ ሰጥተዋል።
ክርክሩ በዚህ ደረጃ ላይ እያለ የአሁን አመልካች የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 158 እና 205 ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ ሐምል 20 ቀን 2001 ዓ.ም. በተጻፈ አቤቱታ ግማሽ ድርሻ ከተጠየቀበት ንብረቶች መካከል በየካ ክ/ከተማ ቀበላ 13 ክልል በካርታ ቁጥር ሉዝ/06/8328/02 8388 ተመዝግቦ የሚታወቀው ቤት የሟች የወ/ሮ አረጋሽ ሺበሺ የግል ንብረት የነበረ ሲሆን ሟች ይህንኑ ቤታቸውን ለ2ኛ ተከሣሽ ለአሁን 3ኛ ተጠሪ በግልፅ ኑዛዜ አስተላልፊልኝ የአሁን ተጠሪም የኑዛዜ ወራሽ መሆናቸው በደሴ ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት ተረጋግጦ ከተወሰነ በኋላ የቤቱ የይዞታ ማረጋገጫ ወረቀት በስማቸው መስከረም 09 ቀን 1999 ዓ.ም. ከተዛወረ በኋላ ለአሁን አመልካች በሽያጭ አስተላልፈዋል። የቤቱ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታም ሆነ ንብረቱ በእጄ ይገኛል። ስለሆነም የአሁን 1ኛ ተጠሪ መብት በላለው ንብረት ላይ የዕግድ ትዕዛዝ ማሰጠቱን ስለተረዲሁ በዚሁ ንብረት ላይ የተሰጠውን የዕግድ ትዕዛዝ የተከበረው ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 158 መሰረት እንዱነሳ ያድርግልኝ የሚል ዲኝነት ጠይቀዋል።
ፍ/ቤቱም በኮ/መ/ቁ. 50497 አቤቱታ በቀረበበት ዕለት ሐምል 20 ቀን 2001 ዓ.ም. በዋለው ችልት ዕግድ የሰጠበትን ንብረት ስለመግዛታቸው በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት የተረጋገጠ ውል ከመቅረቡ በቀር 3ኛ ወገኖችን ለመመለስ እንዱቻል ስለመመዝገቡ አላስረደም። ስለሆነም የዕግድ ይነሳልኝ አቤቱታ ለከሣሽ ደርሶ መልስ ይስጡበት በማለት ማዘዝ ሳያስፈልግ አቤቱታው ተቀባይነት የላለው ሆኖ ተገኝቷል የሚል ትዕዛዝ ሰጥቶበታል።
ከዚህም በኋላ ክርክሩ በከሣሽና በተከሣሾች መካከል ቀጥል ከተጠናቀቀ በኋላ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ ጥር 10 ቀን 2002 ዓ.ም. በዋለው ችልት የአሁን 1ኛ ተጠሪ ባልነት በአዱስ አበባ የመ/ደ/ፍ/ቤት ተረጋግጧል። የጠበቃው ውክልናም በግሪክ አገር ኢምባሲና በውጭ ጉዲይ ሚ/ር በኩል ተረጋግጦ ቀርቧል። ጉዲዩም በኢትዮጵያ ፍ/ቤትም ሆነ ሕግ መሰረት ይዲኛል። ተከሣሾች የጋራ ሀብት ናቸው የተባለት ንብረቶች የለም በሚል አልተከራከሩም። ስለዚህ ንብረቶቹ የጋራ ሀብት ናቸው። ግማሽ ድርሻ የመካፈል መብት አላቸው በማለት ወስኗል።
ይህ ውሣኔ ከተሰጠ በኋላ የአሁን አመልካች ይህን ውሣኔ ለሰጠው ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በ25/5/2002 ዓ.ም. በተጻፈ አቤቱታ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሰረት ክርክር ባስነሳው ንብረት ላይ ያላቸውን መብት ለማስከበር ዝርዝር የፍሬ ነገርና የሕግ ክርክር በማቅረብ ዲኝነት ሲጠይቁ ፍ/ቤቱ በኮ/መ/ቁ. 50497 የካቲት 03 ቀን 2002 ዓ.ም. በዋለው ችልት የአሁን አመልካች ከዚህ በፉት ተመሳሳይ አቤቱታ አቅርበው ይህ ፍ/ቤት ሐምል 20 ቀን 2001 ዓ.ም. በሰጠው ትዕዛዝ ውለ በማይንቀሳቀስ ሀብት መዝገብ ያልተመዘገበ ስለሆነ በ3ኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ አይሆንም በማለት የተሰናበቱ ስለሆነ በይዘቱ ተመሳሳይ አቤቱታ በድጋሚ ማቅረባቸው አግባብ አይደለም በሚል ትዕዛዝ አሰናብቷቸዋል።
በዚህ ትዕዛዝ ቅር ተሰኝተው የይግባኝ አቤቱታ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ቢያቀርቡም ይኸው ፍ/ቤት በፍ/ብ/ይ/መ/ቁ. 54796 በ11/9/2002 ዓ.ም. በዋለው ችልት የከፍተኛ ፍ/ቤቱ የሰጠው ብይን የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አልተገኘም በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት መዝገቡን በመዘጋቱ የአሁን አመልካች ለዚህ የሰበር ጉዲይ መነሻ የሆነውን የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል። ጥቅል ይዘቱ የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት የካቲት 03 ቀን 2002 ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ እና ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በይግባኝ ተመልክቶ የሰጠው ዲኝነት በንብረቱ ላይ ያለኝን የመፊለም፣ የመከራከር መብት ያለ ሥርዓቱ የነፈገኝ ስለሆነ ይታረምልኝ የሚል ሆኖ ዝርዝሩም፡- ከዚህ በፉት በባለቤትነቴ በንብረቱ ላይ የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ እንዱነሳልኝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 158 መሰረት አቤቱታ አቀረብኩ እንጂ ሙለ ክርክር ያቀረብኩበት አቤቱታ አይደለም።
የሟች ወ/ሮ አረጋሽ ሺበሺ ንብረት በኑዛዜ ለአሁን 3ኛ ተጠሪ ተላልፍ የ3ኛ ተጠሪ የኑዛዜ ወራሽነት በፍ/ቤት ከተረጋገጠ በኋላ የንብረት ስመ-ሀብትነት ወደ ስሟ መዞሩን፣ ከዕዲና ዕገዲ ነፃ መሆኑን በማረጋገጥ በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት በተደረገ ውል በግዥ የተላለፈልኝ ንብረት ነው። ይህም የሽያጭ ውል ከቤቱ ማህደር ጋር ተያይዞ የሚገኝ ሲሆን የንብረት /የይዞታ/ ማረጋገጫ ካርታ እና ንብረቱ በእጄ ይገኛል። ይህ ንብረት የጋራ ሀብት ነው እንኳ ቢባል አንደኛው ተጋቢ ያለ ሥልጣኑ ወደ ላላ ወገን አስተላልፍ ከተገኘ ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለው በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 69 የተመለከተው ድነጋጌ ነው። በዚህ መሰረት የአሁን 1ኛ ተጠሪ ይህንኑ የሽያጭ ውል አላስፈረሰም። ከሟች ላላ የሀብት ድርሻ ላይ በማካካሻነት ከሚጠይቁ በቀር ሀብቱን ሉከተለ አይችለም። በመሆኑም በሕግ መሰረት በሽያጭ ያኘሁት ሀብት ያለአግባብ የባልና ሚስት የጋራ ሀብት ነው የሚል ውሣኔ መሰጠቱን ስረዲ ስለ ጉዲዩ ዝርዝር የፍሬ ነገርና የሕግ ክርክር በማቅረብ የመከራከር መብቴን ያስጠበቁበት የሕግ መሰረት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
358 የተመለከተው ሆኖ እያለ ክርክር የማሰማት መብቴን የሚነፍግ ዲኝነት መሰጠቱ ሥነሥርዓታዊ ባለመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
በዚህ የሰበር አቤቱታ መነሻ ተጠሪዎች ቀርበው እንዱከራከሩ ጥሪ ሲተላለፍ ከተራ ቁጥር 2 እስከ 4ኛ ድረስ የተዘረዘሩት በጥሪው መሰረት ያልቀረቡ በመሆኑ ጉዲዩ እነርሱ በላለበት እንዱታይ ሲደረግ 1ኛ ተጠሪ በጠበቃው አማካኝነት፡- ሐምል 20 ቀን 2001 ዓ.ም. እና ጥር 25 ቀን 2002 ዓ.ም. በተፃፈ አቤቱታ አመልካች ያቀረበው ጥያቄ አርዕስቱና የሕግ አንቀጹ ተለያዩ እንጂ ይዘቱ አንድ ነው። የኑዛዜ ሰነድ የተባለው ተሽሯል። ስለሆነም በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ዲኝነት የሕግ ስህተት የተፈፀመበት አይደለም በማለት ሲከራከር፤
5ኛ ተጠሪ በበኩለ ሻጯ ቤቱን በስሟ ያዞረችው የቤቱ ባለቤት ሟች ወ/ሮ አረጋሽ በኑዛዜ ሰጥተውኛል በማለት ነው። ነገር ግን ኑዛዜው በፍ/ቤት ተሰርዟል። በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 69 የተመለከተው ድንጋጌ የውርስ ሀብት ክፍፍልን አይመለከትም። የሰበር አቤቱታው ተቀባይነት የለውም የሚል መልስ ሰጥቷል። አመልካች የመልስ መልስ የሰጠበት ሲሆን በይዘቱ ከዚህ በፉት ካቀረበው የተለየ አይደለም።
የጉዲዩ አመጣጥ ባጭር ባጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም ጉዲዩን አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመርነውም የአሁን አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ. 358 መሰረት ያቀረበውን ዝርዝር የፍሬ ነገር እና የሕግ ክርክር ተቀባይነት ያለው አይደለም በማለት የከፍተኛው ፍ/ቤት ለሰጠው ዲኝነት መሰረት አድርጎ የያዘው ይህ አቤቱታ በይዘቱ ከዚህ በፉት በ20/11/2001 ዓ.ም. ቀርቦ ዲኝነት ከተሰጠበት በይዘቱ የተለየ አይደለም። ተመሳሳይ አቤቱታ ሆኖ ስለተገኘ በድጋሚ ላታይ የሚችልበት አግባብ የለም የሚለውን በመንተራስ ነው። ይሁን እንጂ የአሁን አመልካች ሐምል 20 ቀን 2001 ዓ.ም. በተጻፈ አቤቱታ ለፍ/ቤቱ የጠየቀው ዲኝነት በጉዲዩ ላይ የክርክር ተካፊይ ሆኖ በተከራካሪነቱ አቋም ያቀረበው ክርክር ሳይሆን በላልች ተከራካሪ ወገኖች መካከል በተነሳው ሙግት ሳቢያ በንበረቴ ላይ ጊዜያዊ የማገጃ ትዕዛዝ መሰጠቱን ተረድቻለሁ፣ ይኸው ትዕዛዝ ይነሳልኝ በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 158 መሰረት ዲኝነት የጠየቀበት ነው።
ፍ/ቤቱም ከፍርደ በፉት ጊዜያዊ ማገጃ ትዕዛዝ የሰጠበት ንብረት የአመልካች ንብረት ነው ለማለት የሚያበቃውን የንብረት ምዝገባ ሥርዓት ያሟላ ባለመሆኑ በዚህ ጊዜያዊ ማገጃ ትዕዛዝ ይነሳልኝ አቤቱታ ላይ ላልች ተከራካሪ ወገኖች መልስ እንዱሰጡበት ማድረግ ሳያስፈልግ ጥያቄው ተቀባይነት የለውም በማለት በዕለቱ ዕለት አቤቱታው በቀርበበት አግባብ ዲኝነት የሰጠበት እንጂ የአሁን አመልካች በንብረቱ ላይ ያለውን መብት በሚያሳይ አኳኋን ሙለ የፍሬ ነገርና የሕግ ክርክር አቅርቦ በዚሁ ክርክር ላይም የከሣሽና የተከሣሾች ክርክር ተሰምቶ ዲኝነት የተሰጠበት ትዕዛዝ አይደለም።
ይልቁንም የዚህ ትዕዛዝ መነሻ ላልች ተከራካሪ ወገኖች በከሣሽነትና በተከሣሽነት በሚከራከሩበት ጉዲይ ስለሚሰጠው ፍርድ አፈፃፀም ዋስትና ይሆን ዘንድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ 3ኛ መጽሐፍ ምዕራፍ 5 ሥር በተመለከቱት ሁኔታዎች በአንድ ንብረት ላይ ጊዜያዊ የማገጃ ትዕዛዝ በተሰጠ ጊዜ በዚህ ትዕዛዝ ላይ ቅሬታ ያላቸው ወገኖች በሚስተናገደበት ሥርዓት መሰረት የቀረበ ጥያቄ እና የተሰጠ ዲኝነት እንደመሆኑ መጠን ለጉዲዩም ተፈፃሚነት ያላቸው ድንጋጌዎች በዚህ የሕግ ክፍል የሚገኙት ናቸው።
ከእነዚህም ድንጋጌዎች መካከል ፍርድ ከመሰጠቱ በፉት ንብረት በተከበረ ወይም ታግድ እንዱቆይ በተደረገ ጊዜ መብት አለን የሚለ እንደአሁኑ አመልካች ያለ ሦስተኛ ወገኖች አቤቱታ ባቀረቡ ጊዜ የአቤቱታው አግባብነት የሚመረመረው በፍርድ አፈፃፀም ላይ ያለው ንብረት የሦስተኛ ወገን መብት ያለበት መሆኑ በሚመረመርበት ዓይነትና ሁኔታ (በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418-421) በተመለከተው መሰረት ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 153/3/ ተመልክቷል። ይህም ዓይነት ምርመራ በንብረቱ ላይ ሦስተኛ ወገኖች ያላቸውን መብት ለመለየት ሲባል ቀለል ያለና አጭር ሥርዓትን የሚከተል እንጂ ሙለ የክርክር አካሄድን (Ordinary Judicial Proceeding) የሚጋብዝ ባለመሆኑ በጊዜያዊ ማገጃ ትዕዛዝ እንዱነሳ የቀረበ ጥያቄ ውድቅ በተደረገ ጊዜ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
421 መሰረት ለክርክሩ መነሻ በመሆነው ንብረት ላይ ክስ የማቅረብ መብትን በማይነፍግ ሁኔታ ተደንግጓል።
በዚህም በተያዘው ጉዲይ የከፍተኛው ፍ/ቤት ሐምል 20 ቀን 2001 ዓ.ም. በተጻፈ የቀረበለትን ጊዜያዊ የንብረት ማገጃ ትዕዛዝ ይነሳልኝ ጥያቄ ብቻ እንደቀረበለት በዚህ ጥያቄ ላይ ላልች ተከራካሪ ወገኖች /ከሣሽና ተከሣሾች/ መልስ መስጠት የማያስፈልጋቸው ሆኖ አልተገኘም በማለት በአጭር ሥርዓት ተመልክቶ ትዕዛዝ የሰጠበት እንጂ አመልካች የክርክር ተካፊይ ሆኖ በጉዲዩ ላይ የሚመለከታቸው ወገኖች ሁለ ያላቸው ክርክርና ማስረጃ ተሰምቶ የተሟላ የሙግት ሥርዓትን በመከተል የተሰጠ ዲኝነት ባለመሆኑ በዚሁ ንብረት ላይ የአሁን አመልካች አለኝ የሚለውን መብት ለማስከበር የመደመጥ መብቱ ተከብሮ ዲኝነት ማግኘት ይችል ዘንድ አዱስ ክስ ለማቅረብ የሚከለክለው ሥርዓት አልተገኘም።፡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሰረት የተዘረጋው ሥርዓት አስቀድሞ በተሰጠው ውሣኔ መብቱ የሚነካበት ወገን ባለበት እንደገና ውሣኔ እንዲልተሰጠበት ተቆጥሮ እንደገና ክርክር የሚጀምርበት ሥርዓት በመሆኑ በውጤት ደረጃ አዱስ ክስ ከማቅረብ ተለይቶ የሚታይ አይደለም። ይህም ሲባል አሁን የተነሣውን ክርክር መነሻና መድረሻ መሰረት በማድረግ ለጉዲዩ አግባብነት ካለው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ክፍል አንፃር በማየት የአሁን አመልካች ክርክር ባስነሳው ንብረት ላይ ያለው የመሟገት መብት የተጠበቀ ነው ለማለት እንጂ በማንኛውም ጉዲይ ቢሆን በአንድ ጉዲይ ላይ ክርክር መጀመሩን ያወቀ ወገን የክርክሩን ውጤት ጠብቆ መብቱን የሚነካበት ሆኖ ባገኘው ጊዜ ከውሣኔ በኋላ የመሟገት መብት አለው በማለት ለፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 የተለጠጠ ትርጉም ለመስጠት ተፈልጎ አይደለም። ይህ ዓይነት አተረጓጎም የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግን መሰረታዊ ዓላማ የተከተለ ባለመሆኑ ተቀባይነት ያለው አይደለም።
በዚህ ሁለ ምክንያት የከፍተኛው ፍ/ቤት ሐምል 20 ቀን 2001 ዓ.ም. የቀረበለት ጥያቄ እና ለጥያቄው የሰጠው ዲኝነት ከጊዜያዊ የማገጃ ትዕዛዝ አነሳስ ጋር የተያያዘ መሆኑ እየታወቀ አስቀድሞ ሙለ ክርክር ተደርጎበት ዲኝነት እንዲገኘ ጉዲይ በመቁጠር አመልካች በንብረቱ ላይ ያለውን መብት ለማስከበር ሲል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሰረት ያቀረበው የተሟላ የፍሬ ነገርና የሕግ ክርክር አስቀድሞ ዲኝነት ከተሰጠበት ጉዲይ ጋር ተመሳሳይ ስለሆነ በድጋሚ ላታይ የሚችል አይደለም። ተቀባይነት የለውም በሚል የተሰጠው ትርጉም መሰረታዊ የሆነ የሥነ-ሥርዓት ሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
54796 በ11/9/2002 እና በኮ/መ/ቁ. 50497 ጥር 10 ቀን 2002 ዓ.ም. የተሰጠ ትዕዛዝ እና ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ግራ ቀኙ ያደረጉት ክርክር ላስከተለው ውጭና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ።
/አተ
ታህሣሥ 13 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፣ ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድአመልካች፡- እነ አቶ በቀለ አማረ /ሁለት ሰዎች/ 1ኛው አመልካች ቀረቡተጠሪ፡- ወ/ሮ ብዙነሽ ግርማ ጠበቃ ጉታ ጫካ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ጋብቻን መሰረት ያደረገ የንብረት ክፍፍል ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካቾች ላይ በአርሲ ዞን ጢዮ ወረዲ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- ከአመልካቾች አባት ጋር ተጋብተው ሲኖሩ ባለቤታቸው ከዚህ አለም በሚያዚያ 07 ቀን 1981 ዓ.ም በሞት መለየታቸውን በሟች ስም የተመዘገበ የጋራ ቤት እንዲላቸው ተጠሪ ቤቱን በአደራ እያስተዲደሩ አመልካቾች ድርሻቸውን እንዱካፈለ ቢጠይቁም ሳይከፊፈለ መቆየታቸውን አመልካቾችን በማክበር የንብረቱን ክፍፍል ሳይጠይቁ መቆየታቸውን በመግለጽ አመልካቾች ድርሻቸውን እንዱካፈለ እና የእርሳቸውም ድርሻ እንዱሰጣቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካቾች ለክሱ በሰጡት መከላከያ መልስም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርበዋል። በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያቀረቡት ክርክር ጉዲዩ በእርቅ ያለቀ መሆኑን የሚጠቅስ ሲሆን በፍሬ ነገር ደረጃ ደግሞ አባታቸው ቤቱን ተጠሪን ከማግባታቸው በፉት የሰሩት የግል ሀብት መሆኑን ሟች ቤቱን በተመለከተ ያደረጉት ኑዛዜ አለመግባባት በመፍጠሩ ወራሾች ስለቤቱ አጠባበቅና ክፍፍል በተመለከተ ግንቦት 21 ቀን 1981 ዓ.ም የእርቅ ስምምነት ማድረጋቸውንና ተጠሪ የልጆቻቸው ሞግዚት በመሆን ፈርመው እና ስምምነቱ በፍርድ ቤቱ ፀድቆ ያለ በመሆኑ ክስ ላቀርብ እንደማይገባ በመዘርዘር ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲለ መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የወረዲ ፍርድ ቤትም ተጠሪ ከአመልካቾች አባት ጋር ሚስት በመሆኑ አብረው እስከኖሩና አመልካቾች ቤቱ የአባታቸው የግል ሀብት መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ እስካላቀረቡ ድረስ ሟችና ተጠሪ በጋራ የሚጠቀሙበት ቤት የጋራ ሀብት መሆኑንና ተደረገ የተባለውም የእርቅ ስምምነት በወራሾች መካከል የተደረገ በመሆኑ በተጠሪ ላይ ተፈፃሚነት የለውም የሚል ምክንያት በመያዝ ተጠሪ የቤቱ ግማሽ ድርሻ ይገባቸዋል ሲል ወስኗል። በዚህ ውሣኔ አመልካቾች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰበር አቤቱታቸውን ደግሞ ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካቾች ጠበቃ የካቲት 04 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት ሶስት ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- ቤቱ ከጋብቻ በፉት የተሰራ መሆኑን የሚያስረደ ማስረጃዎች ተቆጥረው እያለ ሳይሰሙ ውሣኔ መስጠቱ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት የአመልካቾች አባት እና ተጠሪ ከመጋባታቸው በፉት የአመልካቾች አባት የሰሩት ቤት ስለሆነ የጋራ ልባል አይገባም በማለት አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት ክርክር አቅርበው ቤቱ ከጋብቻ በፉት የተሰራ ስለመሆኑ ያስረደልናል በማለት የቆጠሯቸው ምስክሮች ሳይሰሙ የስር ፍርድ ቤቶች ቤቱ የጋራ ነው በማለት የሰጡት ውሣኔ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል። በዚህም መሰረት ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ግንቦት 30 ቀን 2002 ዓ.ም በተጻፈ አምስት ገፅ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል። በመልሳቸውም የአመልካቾች ጥያቄ በይርጋ ቀሪ እንደሚሆንና ጋብቻው መቼ እንደተፈጸመ ገልጸው ያልተከራከሩ መሆኑን በመጥቀስ ማስረጃ ሳይሰማ ውሣኔ ተሰጥቷል የሚለው ክርክር ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክረዋል።
የአመልካች ጠበቃም በመልስ መልሳቸው ላይ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ ክስ ሉመሰርቱ የቻለት አከራካሪው ቤት ከአመልካቾች አባት ጋር በጋብቻ ተሳስረው በነበሩበት ጊዜ የተፈራ መሆኑን ገልፀው አመልካቾች ተጠሪ የአውራሻቸው ሚስት የነበሩ መሆኑን ሳይክደ የሚከራከሩት አከራካሪው ንብረት ተጠሪ ከሟች አባታቸው ጋር ጋብቻ ከመፈፀማቸው በፉት የተሰራ በመሆኑ የጋብቻ ውጤት አይደለም በማለት መሆኑን ነው።
ከላይ እንደተገለፀው አመልካቾች አከራካሪው ንብረት የተፈራው አውራሻቸው ከተጠሪ ጋር ጋብቻ ከመመስረታቸው በፉት ነው በማለት ቢከራከሩም ተጠሪ ግን ቤቱ በጋብቻ ውስጥ የተፈራ ንብረት ነው በማለት ተከራክረዋል።
በአመልካቾች ክርክር እንደተገለፀው ቤቱ ከጋብቻ በፉት በአውራሻቸው ስለመፈራቱ ተጠቅሶ ይህንኑ ፍሬ ነገር ለማስረዲት ምስክሮችን ቆጥረዋል። ይሁን እንጂ አመልካቾች የቆጠሯቸው ማስረጃዎች በስር ፍርድ ቤት አልተሰሙም ፍ/ቤቱ በቂ የሆነ ማጣራትም አላደረም።
በግራቀኙ ተከራካሪ ወገኖች የተካደ ወይም ያልተማመኑበት የፍሬ ነገር ነጥብ የሚነጥረው በማስረጃ ነው። በግራቀኝ ተከራካሪ ወገኖች የተቆጠረና ለጉዲዩ አግባብነት ያለውን ማስረጃ በአግባቡ መስማት አንደና ዋነኛው የፍርድ አመራር ስርዓት መሰረታዊ መርህ ነው። በእርግጥ በተከራካሪ ወገን የቀረበ ማስረጃ ሁለ ያለምንም ምክንያት መሰማት አለበት ማለት እንዲልሆነ የማስረጃ ደንቦች የሚያሳዩን ጉዲይ ነው። የተቆጠረው ማስረጃ ለተያዘው ክርክር አግባብነት የላለው ሆኖ ከተገኘ ውድቅ የሚደረገው እንዱሁ በደፈናው ሣይሆን ምክንያቱን በግልጽ በጽሐፍ በማስፈር ነው /የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ/ቁ 138/። በተያዘው ጉዲይ እንደምናየው የስር ፍ/ቤቶች ወደ ውሣኔ ያመሩት በአመልካቾች የተቆጠረውን ማስረጃ አስቀርበው ሣያዩ እና ሣይመረምሩ ነው። ማስረጃው ቤቱ የተሰራበትን ጊዜና ሁኔታ ያረጋግጣለ የተባለት የሰው ምስክሮች ሲሆኑ ምስክሮች የሚሰጡት ቃል ደግሞ ቤቱ የጋብቻ ውጤት ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ ለመፍታት አግባብነት ያለው ማስረጃ ነው። በመሆኑም ፍርድ ቤቱ የምስክሮችን ቃል ሳይሰማና ክብደቱን ከተያዘው ጭብጥ ጋር አገናዝቦ ሣይመረምር ብቃት ያለው ማስረጃ አይደለም ወደሚለው መደምደሚያ ሉደርስ አይችልም አይገባምም። አንደ ሰው ለቀረበበት ክስ መከላከያ ማስረጃ ለጉዲዩ አግባብነት እስካለው ድረስ ማሰማት የሕግ ስርዓቱ /Due Process of law/ የግድ የሚለው ጉዲይ ነው። መብትም ነው።
ለጉዲዩ አግባብነት ያለው ማስረጃ ተቆጥሮ እያለ ማስረጃው ሳይሰማ ወደፍርድ ማምራት አይቻልም።
ፍርድ ላሰጥ የሚገባው የክርክር አመራር ሥርዓት በተገቢው መንገድ ከተሟላ በኃላ ነው።
የመከላከያ ማስረጃ በሥነ ሥርዓቱ አግባብ ተቆጥሮ እያለ ይኸው ሳይሟላ የሚሰጥ ፍርድ አካሄደ የተሟላ ነው ልባል አይችልም። የፍርድ አካሄደ ያልተሟላ ውሣኔ ደግሞ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው።
እነዚህን ሁኔታዎች ደምረን ስንመለከት ፍ/ቤቱ ወደ ውሣኔ ያመራው ምንም ዓይነት ማስረጃ ሣይሰማ እንደሆነ ነው። በግልጽ የቀረበን ክርክር በተቆጠረው ማስረጃ ወይም አግባብነት ባለው መንገድ ሣያጣሩ/ሣያነጥሩ/ መወሰን ደግሞ ዋነኛው መሰረታዊ የሕግ ስህተት መፈፀም ነው።
የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔም የአመልካቾችን የመከላከያ ማስረጃ ማሰማት መብት ያልጠበቀ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በአርሲ ዞን ጢዮ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ ግንቦት 18 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጥቶ በአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. ጥቅምት 21 ቀን 2001 ዓ.ም በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መደበኛ ችልት በመ/ ጥቅምት 10 ቀን 2002 ዓ.ም እንዱሁም በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ህዲር 14 ቀን 2002 ዓ.ም የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የጢዮ ወረዲ ፍርድ ቤት በተከፈተው መዝገብ ክርክሩ እንዱቀጥል በማድረግ እና በአመልካቾች የተቆጠሩትን ማስረጃዎች በመስማት እንዱሁም የተጠሪንም ማስረጃ የማሰማት መብት በመጠበቅ ክርክሩን መርምሮ ተገቢውን ውሣኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 343/1/ መሰረት መልሰንለታል። ይፃፍ።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ በተመለከተ ግራቀኙ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.