No summary available.
የካቲት 21 ቀን 2003 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ሥላሴ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ አፀደ ኤድ ጠበቃ አቶ ተስፊዬ ታደሰ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ትኩ ዋቅሹም ጠበቃ አቶ ይመኑ ገብረፃድቅ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው። የክርክሩ መነሻ አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያቀረቡት የክስ ማመልከቻ ነው። አመልካች ከተጠሪ ጋር ከ1966 ዓ.ም. እስከ 1987 ዓ.ም. እንደ ባልና ሚስት ስንኖር ያፈራናቸው የጋራ ሀብት አለ። ስለሆነም የጋራ ሀብቴን እንዱያካፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት አለ የሚለትን ንብረት ከተራ ቁጥር 1 እስከ ተራ ቁጥር 6 ዘርዝረው አቅርበዋል። ተጠሪ ጥቅምት 19 ቀን 2000 ዓ.ም. በተጻፈ መልስ ንብረቶቹን በግላ ያፈራኋቸው ናቸው። ከሣሽ /አመልካች/ የጋራ ንብረት ስለሆነ ያካፍለኝ በማለት ያቀረበችው ክስ ተገቢ አይደለም በማለት መልስ ሰጥተዋል። ከዚህ በኋላ በሥር ተከሣሽ የሆኑት ተጠሪ ቀደም ሲል በፍ/ቤቱ ያቀረቡት መልስ የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ያልተካተተበትና ጏድል ስለሆነ መልሴን እንዲሻሻል ይፈቀድልኝ በማለት ህዲር 2 ቀን 2001 ዓ.ም. በተጻፈ ማመልከቻ አመልክተዋል።
የሥር ፍ/ቤት ተከሣሽ /ተጠሪ/ መልሳቸውን አሻሽለው እንዱያቀርቡ ፈቅድላቸዋል። ተጠሪ /ተከሣሽ/ ታህሣስ 28 ቀን 2001 ዓ.ም. በተጻፈ የተሻሻለ መልስ የከሣሽ /አመልካች/ የተከሣሽ /ተጠሪ/ ግንኙነት 1987 ዓ.ም. ተቋርጧል። ስለሆነም የባልና የሚስት የጋራ ንብረት ክፍያ ጥያቄ በአሥር ዓመት ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ቀሪ የሚሆን ስለመሆኑ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት አስገዲጅ ትርጉም ሰጥቶበታል። ስለሆነም የከሣሽ /አመልካች/ ጥያቄ በይርጋ ቀሪ ይሆናል የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበዋል። የሥር ፍ/ቤት ተጠሪ አሻሽለው ባቀረቡት መልስ ላይ ያቀረቡትን የይርጋ ጊዜ ገደብ መቃወሚያ በመቀበል የከሣሽ /አመልካች/ የጋራ ንብረት ክፍያ ጥያቄ በአሥር ዓመት ይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበዋል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የሥር ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ አጽንቶታል።
አመልካች ግንቦት 4 ቀን 2002 ዓ.ም. በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ የጋራ ንብረት እንዱያካፍለኝ ላቀረብኩት ክስ ተጠሪ በጽሐፍ ሙለ መልስ ከሰጡና ግራ ቀኛችን የቃል ክርክርና ምስክሮች ተሰምተው ጉዲዩ ለውሣኔ ቀጠሮ ከተሰጠው በኋላ ተጠሪ መልሱን ለማሻሻል አቤቱታ አቀረበ። የሥር ፍ/ቤት ከፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 91 መሰታዊ ድንጋጌ ከሚፈቅደው ውጭ ተጠሪ መልሱን እንዱያሻሽል የፈቀደ ሲሆን በተሻሻለው መልስ አመልካች የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ሆኖ መቅረብ የነበረበትን የይርጋ ክርክር አካትቶ አቀረበ። የሥር ፍ/ቤት የግራ ቀኛችን ክርክር ከተጠናቀቀና ምስክሮች ከተሰሙ በኋላ ተጠሪ ያቀረበውን የይርጋ መቃወሚያ ተቀብል ክሱ በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት የሰጠው ብይን የፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 244/1/ እና የፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 91/1/ የሚጥስና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩለ መልሴን ለማሻሻል ጥያቄ ያቀረብኩት የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ አካትቶ ለማቅረብ እንደሆነ ለሥር ፍ/ቤት ገልጬአለሁ። የሥር ፍ/ቤትም በዚሁ ጥያቄ አምኖበት መልሴን እንዲሻሽል ፈቅድልኛል።
የሥር ፍ/ቤት የአመልካች ክስ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት ብይን የሰጠው የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመዝገብ የሰጠውን የሕግ ትርጉም በመከተል ነው። ስለሆነም የበታች ፍ/ቤቶች የፈፀሙት የሕግ ስህተት የላለ በመሆኑ የሰበር አቤቱታው ውድቅ ሆኖ እንድሰናበት በማለት ታህሣስ 11 ቀን 2003 ዓ.ም. የተጻፈ መልስ ሰጥተዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራ ቀኙ ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የሥር ፍ/ቤት ተጠሪ የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ በማካተት መልሱን አሻሽል እንዱያቀርብ መፍቀደና በተሻሻለው መልስ ያቀረበውን የይርጋ መቃወሚያ መሰረት አድርጎ ጉዲዩ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት የሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ተከሣሽ የቀረበበትን ክስ ለመቃወም የሚችልበት የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ለክሱ ከሚሰጠው ዝርዝር መልስ በፉት ወይም ከመከላከያ መልሱ ጋር ማቅረብ እንዲለበትና ፍ/ቤቱም በመጀመሪያ የክሱ መቃወሚያ ላይ ከሣሽ የሚሰጠውን መልስ በመቀበል ብይን መስጠት እንደሚገባው በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 244 ንዐስ አንቀጽ 1 እና በፍታብሓር ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 245 ንዐስ አንቀጽ 1 ተደንግጓል። አንድ ጉዲይ በይርጋ የጊዜ ገደብ ይታገዲል የሚለው መከራከሪያ ተከሣሽ በመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያነት መቅረብ ያለበት መሆኑ በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 244 ንዐስ አንቀጽ 2/ረ/ በግልጽ ተደንግጓል። ተከሣሽ በመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያነት ሉያቀርብው ይገባው የነበረውን የይርጋ መቃወሚያ ሣያካትት የመከላከያ መልሱን ካቀረበ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1856 ንዐስ አንቀጽ 1 በሚደነግገው መሰረት የይርጋ መከራከሪያውን እንደተወው የሚቆጠር መሆኑን የፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 244 ንዐስ አንቀጽ 2/ረ/ እና የፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 245 ንዐስ አንቀጽ 1 እና የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1856 ንዐስ አንቀጽ 1 ያጣመረ ይዘት፣ መንፈስና ዓላማን በማገናዘብ ለመረዲት ይቻላል።
የመጀመሪያ ክስ የሚሰማው ፍ/ቤት ተከሣሽ የመከላከያ መልሱን አሻሽል እንዱያቀርብ የሚፈቅደው ተከሣሽ መልሱን አሻሽል ማቅረቡ ጉዲዩን ለመወሰን አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው (Necessary for the Purpose of the Real Question in Dispute) መሆኑ በፍታብሓር ሥነ- ሥርዓት ሕግ ቁጥር 91 ንዐስ አንቀጽ 1 በግልጽ ተደንግጓል። የፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 91 ንዐስ አንቀጽ 1 ተከሣሽ በፍትብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 244 ድንጋጌዎች መሰረት በመጀመሪያ የክስ መቃወሚያነት ያላቀረበውን በተለይም በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 244 ንዐስ አንቀጽ 2/ረ/ መሰረት ማቅረብ የሚባውንና የተወውን የይርጋ ጊዜ ገደብ መከራከሪያ አካትቶ እንዱያቀርብ የሚፈቅድ ድንጋጌ አይደለም። ከዚህ በተጨማሪ ድንጋጌው ክርክሩ በሚሰማበት ጊዜ የክሱ ወይም የመከላከያ መልሱ መሻሻል በክርክር የተያዘውን ጉዲይ ለመወሰን አስፈላጊ ሆኖ ባልተገኘበት ሁኔታ ፍ/ቤት ክስ ወይም መልስ እንዱሻሻል መፍቀድ የላለበት መሆኑን የሚያስቀምጥ ነው። ስለሆነም የበታች ፍ/ቤት አመልካችና ተጠሪ የጽሐፍና የቃል ክርክር ካደረጉና ግራ ቀኙ ምስክሮቻቸውን አቅርበው ካሰሙ በኋላ ተጠሪ በፍታብሓር ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 244 ንዐስ አንቀጽ 2/ረ/ መሰረት በመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያነት ሉያቀርብ ይገባው የነበረውን የይርጋ መቃወሚያ አካትቶ ለማቅረብ የመከላከያ መልሱን ለማሻሻል የቀረበውን ጥያቄ ተቀብል ተጠሪ የመከላከያ መልሱን አሻሽል እንዱያቀርብ የሰጠው ትዕዛዝ የፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 91 ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ መሰረታዊ ይዘት፣ መንፈስና ዓላማ ያላገናዘበና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የሥር ፍ/ቤት ተጠሪ አሻሽል ባቀረበው የመከላከያ መልስ ውስጥ በማካተት ያቀረበውን የይርጋ መከራከሪያና የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በመቀበል የሰጠው ትዕዛዝ የፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 244 ንዐስ አንቀጽ 2/ረ/ እና የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1856 ንዐስ አንቀጽ 1 እና የፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 244/3/ ንዐስ አንቀጽ 2 የሚጥስና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም ከላይ የዘረዘርነው የሕግ ስህተት ያለበትን ውሣኔ በይግባኝ አይቶ ማረም ሲገባው የሥር ፍ/ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ የከፍተኛው ፍ/ቤት ማጽናቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እና የከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአመልካች ክስ ቀሪ እንደማይሆን በመገንዘብ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ውሣኔ እንዱሰጥበት በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 341 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍ/ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.