No summary available.
ቀን የካቲት 22 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ወርቅነሽ ዋሴ -ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ባንተይርጋ ወርቁ - ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የቀረበው ፍርድን ለማስፈፀም ሲባል በተሸጠ ቤት ላይ የአሁን አመልካች ቤቱ የእራሴ ንብረት ነው። የፍርድ ባለዕዲ ንብረት እንደሆነ ተቆጥሮ የተሸጠው ያለአግባብ ስለሆነ የሐራጅ ሽያጩ ፈርሶ የቤቱ ባለመብትነቴ ይረጋገጥልኝ በማለት ያቀረቡት ጥያቄ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 447 (4) አንጻር ተቀባይነት ያለው መሆኑንና አለመሆኑን ለይቶ ተገቢውን ዲኝነት ለመስጠት ሲባል ነው።
የጉዲዩም መነሻ የአሁን ተጠሪ አቶ ባንተይርጋ ወርቁ እና ባለቤታቸው የነበሩት በዚህ ጉዲይ በፍርድ ባለዕዲነት የተሰየሙት ወ/ሮ አየሁብርሃን ወዲጆ በመካከላቸው የነበረውን ጋብቻ ካፈረሱ በኋላ በፍቺ ውጤቱ ይህ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን በወ/ሮ አየሁብርሃን ወዲጆ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው በቦራዩ ከተማ ቀበላ ለኩ ኮታ በዕድገት የመኖሪያ ቤት ሥራ ማህበር ተደራጅተው ያፈሩት የመኖሪያ ቤት የባልና ሚስት የጋራ ሀብት መሆኑን ገልፀው እንዱካፈለ ተስማምተው ስምምነታቸው በፍ/ቤት በመ/ ሚያዚያ 11 ቀን 1986 ዓ.ም. በተሰጠው ውሳኔ መሰረት ፀድቋል።
በዚህ ውሳኔ መሰረት ለማስፈፀም የአሁን ተጠሪ የፍርድ ባለመብት፤ ሚስት የነበሩት ወ/ሮ አየሁብርሃን ወዲጆ ባለዕዲ በመሆን የተሰየሙበት የአፈጻጸም መዝገብ በአ/ፈ/መ/ቁ በኮ/መ/ ተከፍቶ አፈጻጸሙ ቀጥል ሐምል 2ዐ ቀን 1997 ዓ.ም. የፍርድ ባለዕዲ ባለበት ቤቱ ክፍት ሆኖ በመቆየቱ የፍርድ አፈጻጸም መምሪያ ባለሙያ፣ ከቀበላና ከፕሉስ ጽ/ቤት በተገኙ አባላት አማካኝነት ቤቱ ተገመተ። ነገር ግን ግምቱ ቦታውን አላካተተም ተብል የመሬት አስተዲዲር የመሬቱን ዋጋ እንዱለካ በድጋሚ ሲታዘዝ የፍርድ ባለዕዲም ቤት የላትም የሚል መልስ መስጠቱን፤
ይህ በእንዱህ እንዲለ የአሁን አመልካች በሽያጭ አስተላለፈልኝ የሚሎቸው አቶ ቦጋለ ደገፊ በአፈጻጸም ይሸጥ በተባለው ቤት ላይ መብት አለኝ በማለት በዚሁ የአፈጻጸም መዝገብ ጣልቃ ገብተው በመከራከራቸው በኮ/መ/ ሐምል ዐ4 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በዋለው ችልት አቶ ቦጋለ የማህበር ማረጋገጫ ካርታ አቀረቡ እንጂ ቤቱ የግላቸው ስለመሆኑ የሚገልፅ ማስረጃ አላቀረበም።
መብት የላቸውም በማለት አሰናብቷቸዋል። አቶ ቦጋለ በአፈጻጸም ጉዲይ የተያዘው ንብረት የእኔ ነው በማለት አቤቱታ ሲያቀርቡ የፍርድ ባለዕዲ የነበሩት እና ቤቱ በስማቸው ተመዝግቦ ይገኝ የነበሩት ወ/ሮ አየሁብርሃን ወዲጆ እኔና ባለቤቴ የነበረው የአሁን ተጠሪ የጋራ ቤት የላለን ስለሆነ ቤቱ ለአቶ ቦጋለ ደገፊ ቢለቀቅ አልቃወምም የሚል መልስ ሰጥተው እንደነበሩ የክርክሩ አመጣጥ ያስረዲል።
የአሁን አመልካችም ይህ ክርክር የተነሳበትን ቤት ከፍርድ ባለመብትም ሆነ ከፍርድ ባለእዲ ጋር ግንኙነት ከላላቸው ከአቶ ቦጋለ ነሐሴ ዐ7 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. ገዝቻለው ስመ ሀብትነቱም በካርታ ቁጥር Bur/74/93/1ዐ በ11/12/2ዐዐ1 ወደ እኔ ተዛውሯል። የፍርድ ባለዕዲ ሳልሆን ንብረቴ ላይ የአፈጻጸም ትዕዛዝ ተለጠፈብኝ በማለት በአፈጻጸም መዘገቡ በፍ/ብ/ሥ/ሕ/ቁ 418 መሰረት ሰኔ ዐ2 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. አቤቱታ ሲያቀርቡ ቤቱን ሸጠልኝ የሚሎቸው ግለሰብ አቶ ቦጋለ ደገፊ በዚህ መዝገብ ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርበው ውድቅ የተደረገባቸው መሆኑን መነሻ አድርገው አሰናብቷቸዋል።
በዚህ ትዕዛዝ ላይ የይግባኝ አቤቱታ ሲያቀርቡ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በኮ/መ/ በ12/4/2ዐዐ2 በዋለው ችልት ቤቱ በሐራጅ መሸጡን ስለተረዲሁ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418 መሰረት የቀረበውን አቤቱታ መርመሮ አስፈላጊ ሆኖ አላገኘሁትም፤ለሥር ፍ/ቤት ያመልክቱ የሚል ዲኝነት ሰጥቶበታል በሚል ለዚህ ሰበር ጉዲይ መነሻ የሆነውን አቤቱታ የሐራጅ ሸያጩ ፈርሶ ቤቴን ልረከብ በማለት በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 445 መሰረት አፈጻጸሙን በያዘው ፍ/ቤት ጥያቄ ማቅረባቸውን የጉዲዩ አመጣጥ ያስረዲል።
አፈጻጸሙን የያዘው ፍ/ቤትም በኮ/መ/ በ27/4/2ዐዐ2 በዋለው ችልት ከላይ እንደተመለከተው የጉዲዩን አጀማመር፤ በመካከል አፈጻጸሙን ያሰናከለትን ሙግቶች ሁለ ከጠቀሰ በኋላ ንብረቱ የፍርድ ባለዕዲዋ የነበረ ስለመሆኑ በንብረት አገማመት ጊዜ በባለቤትነት የነበራቸውን ተሳትፍ የአሁን አመልካች በዚሁ ጉዲይ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418 መሰረት ዲኝነት ጠይቀው መሰናበታቸውን ሁለ መሰረት በማድረግ አመልካች ያቀረቡት ተቃውሞ ተቀባይነት የለውም።
No topics extracted.
በማለት ወስኗል።
ይህም ውሳኔ የይግባኝ አቤቱታ ቀርቦበት ተቀባይነት ባለማግኘቱ ይህን የሰበር አቤቱታ አቅርቧል። መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሞበታል የሚልበት ዋና የመከራከሪያ ነጥብ የንብረቱ ባለቤት እኔ ስለመሆኔ የቤቱ ስም ሀብትነት በእኔ ተመዝግቦ ይገኛል። የፍርድ ባለዕዲና የፍርድ ባለገንዘብ የተሸጠው ቤት ያልነበራቸው መሆኑን የቡራዩ ከተማ አስተዲደር ጽ/ቤት አረጋግጠውልኛል የሚለ ናቸው።
የአሁን ተጠሪም በሥር ፍ/ቤቶች ከነበረው ክርክር አንስቶ የተሰማቸውን ነጥቦች በማድረግ ንብረት የባልና የሚስት የጋራ ሀብት ስለሆነ ለክፍፍል በአፈጻጸም እንዱሸጥ መደረጉ ተገቢ ነው በማለት ተከራክሯል።
የጉዲዩ አጀማመር እና የክርክሩ ሂደት ከላይ የተመለከተው ሲሆን፤እኛም ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል። እንደመረመርነውም በቅድሚያ ላታይ የሚገባው ነጥብ ሆኖ ያገኘነው በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት እንዱሸጥ በተከበረ ንብረት ላይ የቀዲሚ መብት አለኝ በሚል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418 መሰረት በአፈጻጸም ጉዲዩ ጣልቃ ገብቶ ተከራክሮ ክርክሩ ውድቅ ከተደረገ በኋላ እንደገና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 444-447 በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት በዚያው የአፈጻጸም መዝገብ ገብቶ ለመመርመር የሚያስችለው መብት አለው ወይስ የለውም? የሚለው ነው።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418 ሆኖ ለዚህ ጉዲይ አግባብነት ባለው የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 447(4) የተመለከቱት ድንጋጌዎች ግብ ተመሳሳይ ሆኖ የሚለያዩበት ነጥብ ቢኖር እንዱሸጥ በተከበረው ንብረት ልዩ መብት አለኝ በሚል የቀረበው አቤቱታ መቼ ቀረበ በሚለው ላይ ነው። በቁጥር 418 አቤቱታ የሚቀርበው ከመሸጡ በፉት ሲሆን በቁጥር 447-(4)የሚቀርበው ደግሞ ከተሸጠ በኋላ መሆኑ ብቻ ነው። የአቤቱታው ይዘት ግን ተመሳሳይ ነው ይኸውም በሐራጅ ለማሸጥ የተከበረው ንብረት ወይም ደግሞ ተከብሮ የተሸጠው ንብረት የፍርድ ባለዕዲ ሳይሆን የእኔ ነው የሚል በመሆኑ ነው። ይህም ከሆነ በተመሳሳይ ክርክር ነጥብ በአንድ ጉዲይ እንደ አመልካች ባለ አቀራረብ ፍ/ቤቱ ሁለት ጊዜ ሉያስተናግድ የሚችልበት አግባብ የለም። ይህ ዓይነት አቀራረብ ክርክርን ሥርዓት ባለው መንገድ በመምራት ማስተናገድ ይገባል ከሚለው የሙግት አመራር አላማ ጋርም የሚጣረስ ነው በዚህም ምክንያት አፈጻጸሙን የያዘው ፍ/ቤት የአሁን አመልካች የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 445- 446ን በመጥቀስ ዲኝነት የጠየቀበት ጉዲይ ቀደም ሲል በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418 መሰረት ጥያቄ ቀርቦበት ዲኝነቱ ያረፈበት ጉዲይ ስለሆነ በድጋሚ ላታይ የሚችልበት አግባብ የለም በሚል የሰጠውን ውሳኔ መሰረት ማድረጉ በአግባቡ ሆኖ ተገኝቷል።
ንብረቱ ከተሸጠ በኋላም ቢሆን በዚያው የአፈጻጸም መዝገብ ለሁለተኛ ጊዜ ያቀረቡት ክርክር ይታይ እንኳ ቢባል ይህ ክርክር ያስነሰውን ንብረት አመልካች ከአቶ ቦጋለ ደገፊ ከመግዛታቸው በፉት በፍርድ አፈጻጸም ተይዞ ሻጭ የተባለት በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት ሉያዝብኝ አይገባም በማለት ተከራክረው በፍርድ ከተረቱ በኋላ ነሐሴ ዐ7 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. ገዛሁ የሚል በመሆኑ ይህ ከሆነ በኋላ የተላለፈው የግዥ ተግባር አስቀድሞ የተጀመረውን የአፈጻጸም ጉዲይ ሉያቋርጠው የሚችል አይደለም። በተለይም ሻጭ የተባለው አቶ ቦጋለ በአፈጻጸም ጉዲይ ጣልቃ ገብተው በተከራከረ ጊዜ የፍርድ ባለዕዲ ንብረቱ ይለቀቅለት የእኔና የፍርድ ባለመብት የጋራ የሆነ ቤት አይደለም የሚለውን ገልፀው መከራከራቸውን እና አመልካችም ይህንኑ ቤት በግዥ አገኘሁ የሚለት ቤቱ በአፈጻጸም ምክንያት በፍ/ቤት ከተያዘ በኋላ እንደመሆኑ መጠን ጥያቄያቸው ከፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 354 አንጻር ሲታይ የህግ መሰረት ያለው አይደለም።
ስለሆነም በዚህ ሁለ ምክንያት የአሁን አመልካች እንደአባባላቸው ቤቱን በሽያጭ አግኝተው የስመ ሀብቱም ዝውውር ወደ እርሳቸው ተዛውሮ ከሆነ ይህ ሁለ ሥርዓት የተፈፀመው አስቀድሞ የባልና ሚስት የጋራ ሀብት መሆኑ ታውቆ ፍርድ ያረፈበት፣በአፈጻጸም ተመርቶ በሐራጅ እንዱሸጥ ትዕዛዝ የተለላፈበት፤ በሐራጅ እንዱሸጥ በሂደት ላይ እያለ የአሁን አመልካች ሸጡልኝ የሚሎቸው ሻጭ በአፈጻጸም ጉዲይ ጣልቃ ገብተው ከተረቱ በኋላ የተደረገ የግዥ ተግባር በመሆኑ በእጅ የተያዘውን የሐራጅ ሽያጭ ለማስቆም የሚያስችል መብት የላላቸው በመሆኑ፤ እንዱሁም የአመልካች የአቤቱታ አቀራረብም ሥርዓቱን የተከተለ ሆኖ ባለመገኘቱ የሥር ፍ/ቤቶች በአሁን አመልካች አቤቱታ መነሻ የሰጠው ዲኝነት በአግባቡ የተሰጠ እንጂ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ባለመሆኑ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥቷል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን በይግባኝ ተመልክቶ በመ/ቁ 886ዐ6 ጥር 12 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. የሰጠውን የመጨረሻ ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1)መሰረት አፅንተናል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም መዝገቦቹ ይመለሱ
የካቲት 3ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። መዝገቡ ተዘግቷል።