No summary available.
የካቲት 24 ቀን 2003 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ሥላሴ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ዲሽን ባንክ ነገረ ፈጅ ትንሳኤ ተፈራ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሀመልማል መኮንን ጠበቃ አቶ ተስፊዬ ታደሰ - ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ በግራ ቀኙ ከተነሣው ክርክር አንፃር በማየት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5 የተመለከተውን ሥነ-ሥርዓታዊ ድንጋጌ አፈፃፀምን በሚመለከት በሥር የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እና ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሰጠውን ትርጉም አግባብነት ለማየት በሚል የቀረበ ነው።
የጉዲዩም መነሻ የአሁን ተጠሪ በሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 126261 በአሁን አመልካች ላይ ያቀረቡት ክስ ሲሆን ይዘቱም ባጭሩ፡ከወ/ሮ ፅዮን መኮንን በዲሽን ባንክ መሣለሚያ ቅርንጫፍ ብር 55,907.02 የተላከልኝን ገንዘብ ባንኩ ለላላ ግለሰብ ከፍሎል። ይህም ክፍያ የሥራ ግዳታውን በአግባቡ ካለመወጣቱ የተነሣ የተፈፀመ ስለሆነ ሉከፍለኝ ይገባል የሚል ነው።
አመልካችም በተከሣሽነት ቀርቦ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 244/2/ መሰረት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያውን በማስቀደም በዚህ ጉዲይ ወ/ሮ ፅዮን መኮንን ከሰውን የድሬዲዋ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ገንዘቡን የመክፈል ግዳታ እንደላለብን በመግለፅ ወስኖ አሰናብቶናል። የአሁን አመልካች ጥያቄ ከወ/ሮ ፅዮን መኮንን የመነጨ ስለሆነ አስቀድሞ ዲኝነት ባገኘው ጉዲይ ላይ ዲግመኛ ክስ ማቅረብ እንደማይቻል ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5 ስለተደነገገ ክሱ ውድቅ ነው የሚል ክርክር አቅርቧል።
ፍ/ቤቱም ይህንኑ ክርክር በማስረጃነት ከቀረበው ከመ/ ፍርድ ይዘት ጋር አገናዝቦ ከመረመረ በኋላ እንደ አመልካች ክርክር አስቀድሞ ውሣኔ ባገኘ ጉዲይ ዲግመኛ የቀረበ ክስ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም በማለት መዝገቡን ዘግቶታል።
በአኳያው ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍ/ቤት በይግባኝ ጉዲዩን ተመልክቶ በሁለቱም መዝገቦች ያለት ተሟጋቾች የተለያዩ ናቸው፣ የመብታቸውም ጥያቄ እራሱን የቻለ ነው እንዱሁም ጭብጡም የተለያየ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5 የተመለከተው ድንጋጌ ለዚሁ ጉዲይ ተፈፃሚነት የለውም የሚል ትርጉም ከሰጠ በኋላ በዋናው ጉዲይ ዘልቆ የአሁን አመልካች ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ከሕጋዊ ወለድ ጋር ይክፈል ሲል ወስኗል።
ጉዲዩ በሁለተኛ የይግባኝ ደረጃ የቀረበለት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አከራካሪ የሆነውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያው ክርክርም ሆነ በዋናው ጉዲይ የተሰጠውን ውሣኔ መርምሮ በተመሳሳይ አተረጓጏም ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የቀረበውም ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5 ጋር በተያያዘ በግራ ቀኙ ለተነሣው ክርክር ይግባኝ ሰሚዎች ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍ/ቤቶች የሰጡት ትርጉም አግባብነት በሚለው ነጥብ ላይ ግራ ቀኙን በሰበር አድምጦ አስፈላጊውን ትርጉም ለመስጠት በሚል ነው።
በዚህ ነጥብ ላይ ግራ ቀኙ በፍሬ ነገርም ሆነ ስለ ሕጉ ያቀረቡት ክርክር በሥር ፍ/ቤቶች ካቀረቡት በይዘቱ የተለየ ባለመሆኑ በዚህ ፍርድ ላይ በድጋሚ ማስፈሩ አስፈላጊ ሆኖ አላገኘነውም።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ዓይነት ከላይ ባጭሩ የመለከተው ሲሆን እኛም ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመርነውም ለዚህ የሰበር ጉዲይ መነሻ የሆነው የወ/ሮ ሀመልማል ክስ በኮ/መ/ቁ.
126261 በሆነው መዝገብ ከመቅረቡ በፉት ገንዘቡን በሃዋላ ለወ/ሮ ሀመልማል መኮንን ላኩ የተባለት ወ/ሮ ፅዮን መኮንን ይህንኑ ገንዘብ ብር 55,907.02 በሃዋላ ለወ/ሮ ሀመልማል እንዱከፍልልኝ ግዳታ ገብቶ ገንዘቡን ከተቀበለ በኋላ ለተላከለት ሰው አልከፈለም ስለዚህ ገንዘቡን ይመልስልኝ በማለት በአሁን አመልካች ላይ ክስ አቅርበው ገንዘቡን አስተላላፉ ነው የተባለው ባንክ ገንዘቡን በማስተላለፍና ለተላከለት ሰው ክፍያን በመፈፀም ረገድ ካለበት የሥራ ግዳታ አንፃር ያደረገው ተግባር ሁለ ታይቶ ተከሣሽ ግዳታውን በመወጣት በኩል ተግባሩን በአግባቡ ፈፅሟል።
ገንዘቡን የመመለስ ግዳታ የለበትም ተብል በመ/ቁ. 23357 ተወስኗል።
ይህ ውሣኔ ከተሰጠ ከሦስት ወር ተኩል በኋላ ደግሞ እንደገና ገንዘቡ ተላከላቸው የተባለት የአሁን ተጠሪ ከወ/ሮ ፅዮን የተላከልኝን ብር 55,907.02 ባንኩ ለእኔ መክፈል ሲገባው ለላላ ግለሰብ ከፍሎል ይክፈለኝ በማለት ክስ አቅርበውበታል።
No topics extracted.
በዚህም ሁለተኛ ክስ ላይ ሉነሳ የሚችለው ጭብጥ ገንዘብ አስተላላፉው በገባው ግዳታ መሰረት ገንዘቡን ለተላከለት ሰው ለመክፈል የሚጠበቅበትን ተግባር አከናውኗል ወይስ አላከናወነም? የሚለው በመሆኑና የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት እና ጠቅላይ ፍ/ቤት በተሳሳተ መንገድ ወደ ፍሬ ነገሩ ጉዲይ ዘልቀው በመገባታቸውም የተነሣ በግራ ቀኙ መካከል የተነሣው አከራካሪ ነጥብ ይህው ስለመሆኑ የወሣኔው ግልባጭ ያስረዲል። ስለሆነም በመ/ቁ. 23357 ሆነ በመ/ቁ. 126261 የተነሣው የፍሬ ነገርም ሆነ የሕግ ጭብጥ ተመሳሳይ ነው። ተከራካሪ ወገኖችም የተለያዩ ሰዎች ይሁን እንጂ የወ/ሮ ሀመልማል ገንዘብ የመጠየቅ መብት የሚመነጨው ከገንዘብ ላኪዋ በመሆኑና ገንዘብ ላኪዋ ባቀረቡት ክስ ረቺ ሆኖ በተገኙ ጊዜ እንዱሁም ገንዘብ ተቀባይ የፍርደ ተጠቃሚ የሚሆኑ ወገን ናቸው። ተመሳሳይ ዲኝነት ከአንድ ተከሣሽ የሚጠይቁ ወገኖች በመፈራረቅ የተለያዩ ክስ በማቅረብ በተከሣሹ ላይ አላስፈላጊ እንግልት እንዲያደርሱ በማሰብ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ በአንቀጽ 5/1/ ላይ ከተከራካሪዎቹ መብት ያገኙ ሦስተኛ ወገኖች በዚያው ነገር ሁለተኛ ክስ ለማቅረብ እንደማይችለ ተደንግጓል። የእነዚህ ለመጀመሪያው ጉዲይ ተከራካሪ ከሆኑት ወገኖች መብት ያገኙ ሦስተኛ ወገኖች እጣ ፈንታ በመጀመሪያው የክስ ውጤት ላይ የተወሰነ ውሣኔውም ጎጂ ከሆነ ስለአስከተለው ኃላፉነት በቅድሚያ በተከራከረው ወገን ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር እንጂ ዲግመኛ ክስ በዚያው በአንድ ተከሣሽ ላይ እንዱቀርብ የተፈቀደበት ሥርዓት አይደለም።
በዚህም የሕግ ይዘትና የሕጉ መሰረተ ሀሳብ መነሻ በሁለቱም ጉዲዮች በከሣሽነት የተሰየሙት ወገኖች ተመሳሳይ ወገኖች እንደሆኑ የሚቆጠሩ ናቸው።
ከሁለም በላይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5 የተቀመጠው ድንጋጌ ክርክሮችን ሥርዓት ባለው መንገድ እንዱመሩ በማድረግ በተቻለ ፍጥነት በአጭር ጊዜ እና በአነስተኛ ወጭ ታይተው እንዱቋጩ በማድረግ ረገድ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ የያዘውን ዓላማ ተከትል የተዘረጋ ሥርዓት እንደመሆኑ መጠን አንድ አስቀድሞ የተሰጠ ፍርድ ወደ ፉት ለሚነሱት ክርክሮች ያለውን ውጤት ለይቶ ደንግጓል። ይህንንም ድንጋጌ አስመልክቶ የትርጉም ጥያቄ ከተነሣ ልንሰጠው የሚገባው ትርጉም ከዚሁ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ዓላማ የራቀ ላሆን አይገባም። ከዚህ አንፃር ለሁለቱም ጉዲዮች መነሻ የሆነው አንድ የተላከ ገንዘብ ሆኖ እያለ በሁለቱም ጉዲዮች ለተነሣው ክርክር ዕልባት ለመስጠት በጭብጥነት የተያዘው ነጥብ ባንኩ በአግባቡ የሥራ ግዳታውን ተወጥቷል ወይስ አልተወጣም? የሚለው መሆኑ እየታወቀ እና ላኪ እና ተቀባይ የሚጠይቁት ዲኝነት በይዘቱ ተመሳሳይ ሆኖ እያለ በጊዜ ቅደም ተከተል በመፈራረቅ አንድን ተከሣሽ ሁለት ጊዜ በአንድ ጉዲይ በተለያዩ ፍ/ቤት በተለያዩ ጊዜ ለሙግት በሚደረግ አኳኋን የክርክሩ አንኳር ነጥብ ሲያያዝ በጭፍጫፉ የቃላት አጠቃቀም በመመራት ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5 እንደተመለከተው አስቀድሞ በፍርድ እንዲለቀ ሉቆጠር የሚችል አይደለም በሚል የተሰጠው ትርጓሜ የድንጋጌውን ይዘትም ሆነ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ዋነኛ ዓላማን መሰረት ያደረገ ሆኖ ስላላገኘነው ትርጉሙ መሰረታዊ የሥነሥርዓት ሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ