No summary available.
ጥር 23 ቀን 2003 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ አስቴር አርአያ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አምሳለ በላይ - ጠበቃ ሽመልስ ሄይስ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
የሰበር አቤቱታው ወ/ሮ አምሳለ በላይ የካቲት 11 ቀን 2001 ዓ.ም. በተሰጠ ውሣኔ በዶ/ር አለኸኝ መኮንንና በወ/ሮ አስቴር አርአያ ላይ ገንዘብ በማስወሰን የፍርድ ባለመብት የሆንኩበት ይፈፀምልኝ ብለው ባስከፈቱት የአፈፃፀም መዝገብ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ግንቦት 4 ቀን 2002 ዓ.ም. የፍርድ ባለመብት በልላ መዝገብ ባለዕዲ ሆነው በመ/ቁ. 63974 በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አፈፃፀሙ እየታየ ስለሆነ በዚህ ችልት የተሰጠው ፍርድ ተቻችል እንዱፈፀም የፍርድ አፈፃፀም ማመልከቻው ከትዕዛዙ ጋር ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለ8ኛ ችልት ይተላለፍ በሚል የሰጠው ትዕዛዝ እንዱሁም በዚሁ ትዕዛዝ ላይ ይግባኙ የቀረበለት የፍዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/ይ/መ/ቁ. 56661 ሰኔ 14 ቀን 2002 ዓ.ም. ይግባኝ የተባለበት ትዕዛዝ ጉድለት የለበትም በማለት የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በሚል ምክንያት የቀረበ ነው።
አመልካች በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እንዱፈፀም አፈፃፀም የተጠየቀበት የገንዘብ ፍርድ እና በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አፈፃፀም የተጠየቀበት የገንዘብ ፍርድ ተቻችል እንዱፈፀም ለከፍተኛው ፍ/ቤት የቀረበውና ወደ ፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ይተላለፍ በሚል የተሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው የሚለባቸውን ምክንያቶች ሰኔ 17 ቀን 2002 ዓ.ም.
በተጻፈ ማመልከቻ ገልፀው አቅርበዋል።
አቤቱታው ተመርምሮ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ቀርቦ እንዱታይ ተብል በመታዘዙ ማመልከቻው ለአሁኗ ተጠሪ ተልኮ ቀረበው መልስ እንዱሰጡበት የተደረገ ሲሆን በተጠሪዋ በኩል በጽሐፍ የቀረበው መልስም ለአመልካች እንዱደርሳቸው ተደርጏ በጽሐፍ የመልስ መልስ ሰጥተውበታል።
በዚህ ጉዲይ በአንድ በኩል የአሁኗ ተጠሪ በአሁኗ አመልካች እና በልላ አንድ ሰው ላይ ገንዘብ በማስወሰን በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አፈፃፀም የጠየቁበት ፍርድ በልላም በኩል የአሁኗ አመልካች በአሁኗ ተጠሪ ላይ ብቻ ገንዘብ በማስወሰን በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አፈፃፀም የጠየቁበት ፍርድ መቻቻል ላደረግበት እንዱችል ለከፍተኛው ፍ/ቤት የቀረበው የአፈፃፀም ጥያቄ ወደ ፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተላልፍ ይታይ በሚል የተሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት የሚያስችል ምክንያት መኖር አለመኖሩ ሲመረመር፡በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 397/1/ ላይ እንደተመለከተው በዚህ ጉዲይ ሁለቱ ተከራካሪ ወገኖች በየበኩላቸው ክስ አቅርበው አንደ በአንደ ላይ የፍርድ ባለገንዘብ መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን ሁለቱም እንደፍርደ እንዱፈፀምላቸው ለፍ/ቤት የአፈፃፀም ማመልከቻና ለማቅረብ የአፈፃፀም መዝገብ አስከፍተዋል። ልዩነት የታየው የአሁኗ አመልካች የአፈፃፀም ማመልከቻውን ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቅርበው የአፈፃፀም መዝገብ ማስከፈታቸው እና የአሁኗ ተጠሪ ደግሞ የአፈፃፀም ማመልከቻውን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በማቅረብ የአፈፃፀም መዝገብ ያስከፈቱ ሆኖ መገኘታቸው ላይ ቢሆንም ፍርደ በአንድ ፍ/ቤት ዘንድ ሉፈፀም የሚችል ነው። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይህንኑ በመረዲት ፍርደ መቻቻል ላደረግበት እንዱችል አፈፃፀሙ በአንድ ፍ/ቤት እንዱታይ በአሁኗ ተጠሪ በኩል የቀረበው የአፈፃፀም ማመልከቻ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የቀረበው የአፈፃፀም ማመልከቻ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እንዱተላለፍ አድርጓል። የአሁኗ ተጠሪ የአፈፃፀም ማመልከቻ ያቀረቡበት ፍርድ ገንዘቡን የአሁኗ አመልካችና ላላው የፍርድ ባለዕዲ በአንድነትና በነጠላ ይክፈለ ተብል የተወሰነ መሆኑ ተገልጿል።
ስለመቻቻለም ጥያቄ አፈፃፀሙን በዝርዝር በማየት የሚወሰነው የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሁለቱ ተከራካሪ ወገኖች አንደ በልላው ላይ ያስወሰነው በፍርድ የበሰለ ገንዘብ በመቻቻል መፈፀም እንዱችል የአሁኗ ተጠሪ የአፈፃፀም ማመልከቻ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እንዱተላለፍ ማድረጉ የሕግ ስህተት ያለበት አይደለም።
የአሁኗ አመልካች የፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 1838 እና 1839ን በመጥቀስ ማቻቻል እንዱደረግ ባለዕዲው የሚፈልግ መሆኑ መረጋገጥ አለበት በሚል ያቀረቡትን ክርክር በተመለከተም በፍርድ የበሰለው የገንዘብ ዕዲ መቻቻል አፈፃፀም የሚመራው በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 397 መሰረት ስለሆነ ወደ ፍትሐብሄር ሕጉ ድንጋጌዎች የሚወሰድ ጉዲይ አይደለም። የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 397/1/ የሚጠይቃቸው ቅድመ ሁኔታዎች የተሟለ ሆነው ከተገኙ ማቻቻለ መፈፀም ይኖርበታል። በዚህ ጉዲይ መቻቻለ እንዱፈፀም በሕጉ ላይ የተመለከቱት መሰረታዊ የሆኑት ነገሮች ተሟልተው ስለሚገኙ አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረቡት ክርክር በሕጉ ተቀባይነት የሚሰጠው አይደለም።
No topics extracted.
ላላው አመልካች የአሁኗ ተጠሪ የአፈፃፀም ማመልከቻ ባቀረቡበት ፍርድ ገንዘቡን እንድከፍል የተወሰነው በእኔ ላይ ብቻ ሣይሆን በዶ/ር አለኸኝ መኮንንም ላይ ስለሆነ እኔ በተጠሪዋ ላይ ካስፈረድኩት ገንዘብ ጋር መቻቻል ላደረግበት አይችልም በሚል ያነሱትን የተቃውሞ ክርክርም በሚመለከት በአንድነትና በነጠላ ይክፈለ ተብል የተወሰነ መሆኑን ተጠሪዋ በጽሐፍ በአቀረቡት መልስ ላይ የገለፁት ሲሆን አመልካችም በጽሐፍ በሰጡት የመልስ መልስ ላይ በአንድነትና በነጠላ ይከፈል መባለን አልካደም። በአንድነትና በነጠላ ይክፈለ ተብል የተወሰነ ሆኖ ከተገኘ የፍርድ ባለመብቷ በሕጉ የአንደኛው የፍርድ ባለዕዲ ንብረት ብቻ ተሸጦ ወይም አፈፃፀሙ በአንደኛው የፍርድ ባለዕዲ ላይ ብቻ ቀጥል ገንዘቡ እንዱከፈላቸው መጠየቅ ይችላለ። መቻቻለም በተመሣሣይ መንገድ ተፈፃሚ የሚሆን ነው። የአሁኗ አመልካች በተጠሪዋ ላይ ብቻ አስፈርደው የአፈፃፀም ማመልከቻ ያቀረቡበት ገንዘብ የአሁኗ ተጠሪ አመልካችና ላላ ሁለተኛ ሰው በአንድነትና በነጠላ ይክፈለ ተብል ተወስኖ አፈፃፀም ከጠየቁበት ገንዘብ ጋር እንዱቻቻል ከተደረገ በኋላ አመልካች በሕጉ ያላቸው መፍትሄም ሆነ አማራጭ ሁለተኛው የፍርድ ባለዕዲ በድርሻቸው ያለውን ገንዘብ እንዱተኩላቸው መጠየቅ ስለሆነ ተጠሪ በእኔና በልላ ሁለተኛ ሰው ላይ በፍርድ ያስወሰኑት ገንዘብ እኔ በተጠሪዋ ላይ ብቻ ካስወሰንኩት ገንዘብ ጋር መቻቻል እንዱፈፀም ላደረግ አይገባም በሚል ያቀረቡት ተቃውሞ ተቀባይነት የለውም።
አመልካች የአሁኗ ተጠሪ የአፈፃፀም ማመልከቻውን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲያቀርቡ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 386 መሰረት ለእኔም ማመልከቻው ተልኮልኝ ቀርቤ መልስ እንድንሰጥ መደረግ ሲገባው ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህንን የመሰማት መብቴን አልፍ መቻቻል እንዱደረግ የተጠሪ የአፈፃፀም ማመልከቻ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ይተላለፍ ያለው ያለአግባብ ነው ብለው የገለጹትን በተመለከተም አሁንም ቢሆን ፍርደ እንዲይፈፀም የሚቃወሙበት የሕግ ምክንያት ስለመኖሩ ያስረደት ነገር ስለላለ በፍርድ ተወስኖ ባለቀ ጉዲይ ላይ እንደገና መልስ እንድሰጥ መደረግ ነበረበት የሚለው ተቀባይነት አይኖረውም። ሁለት ፍርድች በማቻቻል እንዱፈፀሙ በማድረጉ ሂደት ሉያነሱት የሚገባ ጥያቄ ካለ ማቅረብ የሚገባቸው የአፈፃፀሙን ጉዲይ በማየት ላይ ለሚገኘው ፍ/ቤት ነው።
በአጠቃላይ ሁለቱ ተከራካሪ ወገኖች አንደ በልላው ላይ በፍርድ ያስወሰኑትን ገንዘብ የአፈፃፀም ጥያቄዎች በአንድ ፍርድ ቤት ታይተው በማቻቻል እንዱፈፀሙ የአሁኗ ተጠሪ ለከፍተኛው ፍ/ቤት አቅርበውት የነበረው የአፈፃፀም ማመልከቻ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እንዱተላለፍ በሚል የተሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት የሚያስችል ምክንያት የላለ ሆኖ ስለተገኘ የሚከተለው ተወስኗል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/ይ/መ/ቁ. 56661 ሰኔ 14 ቀን 2002 ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።