No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 5854ዐ ጥር 27 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ኪድስ ሉንክ ኢንተርናሽናል - ጠበቃ ቶማስ ገ/አብ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ሲስተር ገነት ወንድሙ ቀረቡ።
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩን ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ አዋጅ ቁጥር 377/96“ን“ መሰረት ያደረገ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- ከአመልካች ጋር የመሰረቱት የስራ ቅጥር ውል ከሕግ ውጪ የተቋረጠባቸው መሆኑን ገልፀው የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፍሎቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መከላከያ መልስም የስራ ቅጥር ውለ የተቋረጠው የአመልካች እናት ድርጅት በመክሰሩ ምክንያት መሆኑን በመግለጽ ስንብቱ ሕጋዊ ነው ብል ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ ካናዲ የሚገኘው የአመልካች ድርጅት እናት መስሪያ ቤት ስለመክሰሩ የአመልካች ድርጅት በማስረጃዎች አረጋግጠዋል፣ የተጠሪ ምስክሮች ቃል ግን ይህንኑ የአመልካች ማስረጃዎች ያረጋገጡትን ፍሬ ነገር የሚያስተባብል አይደለም የሚል ምክንያት በመያዝ የስራ ውለ የተቋረጠው በሕጉ አግባብ ነው ወደሚለው ድምዲሜ ደርሶ ተጠሪ ሉከፈላቸው የሚገባው የስራ ስንብት ክፍያና የ29 ቀናት የዓመት ፈቃድ ክፍያ ብቻ እንዱከፈል በማለት ወስኗል። በዚህ ውሣኔ ተጠሪ ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የስራ ውለ የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው በማለት በዚህ ረገድ የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ተሽሮ የስራ ስንብቱ ከሕግ ውጪ የተከናወነ ነው በማለት የስር ፍርድ ቤት ከሰጠው ክፍያ አይነት በተጨማሪ የካሣ እና የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያዎች እንዱከፍሎቸው ተወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የስራ ስንብቱ ሕገወጥ ነው የተባለው በስር ፍርድ ቤት በማስረጃ ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር ውጪ በመሆኑ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ተጠሪ ከስራ መሰናበት የነበረባቸው በቅነሣ መልክ መሆን ይገባው ነበር ተብል የስራ ስንብቱ ከሕገ ውጪ ነው በማለት መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመረመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል። በዚህም መሰረት ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው በጽሐፍ ባቀረቡት ክርክር በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ የሕግ ስህተት የላለበት በመሆኑ ሉፀና ይገባል ሲለ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል፡ ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ የሻረው የአመልካች ድርጅት ጠቅላላ ስራ መዘጋቱ በበቂ ማስረጃ አልተረጋገጠም፣ ስራው እየቀዘቀዘ ነው እንዲይባል ደግሞ በቅነሣ መልክ ስንብቱን አላከናወነም በማለት መሆኑን ነው።
ከሁለም በላይ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠው አመልካች ድርጅት ማዕከል ውስጥ በወቅቱ አንድ ህፃን ብቻ መቅረቱ በግራ ቀኙ ማስረጃዎች የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። ከሁለም በላይ የአመልካች ድርጅት እናት መስሪያ ቤት በመከሰር ላይ ያለ ስለመሆኑ የስር ፍርድ ቤት በሚገባ ማረጋገጡን የውሣኔው ግልባጭ ያስረዲል። የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይህንኑ የስር ፍርድ ቤትን ድምዲሜ ውድቅ ያደረገው በተገቢው መንገድ ሣይረጋገጥ የተያዘ ድምዲሜ ነው በማለት ነው። ይሁን እንጂ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤትን ድምዲሜ ውድቅ ያደረገው በደፈናው በተገቢው ሣይረጋገጥ ነው በሚል ከመሆኑ ውጪ ተገቢ ያልሆነበትን፣ በጉዲዩ ላይ የቀረቡት የአመልካች ማስረጃዎች የሰጡት ቃል ተቀባይነት የማይኖርበትን ህጋዊ ምክንያት ሣይጠቅስ ነው። የበላይ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ ሉሽር የሚችለው ሕጋዊና በቂ ምክንያት ሲኖረው ስለመሆኑ ስለ ፍርድ አሰጣጥ የሚደነግጉት ከቁጥር 341 ጀምረው ያለት የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች ያሣያለ። ያለሕጋዊ ምክንያት የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ በበላይ ፍርድ ቤት ሉሻር አይገባም። በመሰረቱ የበላይ ፍርድ ቤት በበታች ፍርድ ቤት የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮችንም የማይቀበልበትን ምክንያት በግልጽ ጽፍ ውድቅ ማድረግ እንጂ በደፈናው በተገቢው አልተረጋገጡም በማለት ሉያልፈው አይገባም። በመሆኑም የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ የደረሰበትን ድምዲሜ ያልተቀበለበት አግባብ የዲኝነት አካሄደን ያልተከተለ በመሆኑ ተቀባይነት የላለው ሁኖ አግኝተናል። በፍሬ ነገር ደረጃ የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የደረሰበት ድምዲሜ ሕጋዊ አይደለም ልባል የሚችልበት ምክንያት የለም ከተባለ ደግሞ የተሰጠውን ውሣኔ ሕጋዊነት መመልከቱ ተገቢ ይሆናል። የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ የተቀጠሩበት ስራ መቀዝቀዙን በሚገባ ያረጋገጠ ሲሆን አንድ አሰሪ ስራው በመቀዝቀዙ ምክንያት ሰራተኛውን ሉያሰናብተው የሚችልበት አግባብ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 መሰረት ተዘርግቷል። በተያዘው ጉዲይም የተጠሪ ስንብት በአዋጁ አንቀጽ 24/4/ መሰረት ሕጋዊ እንጂ ሕገ ወጥ ልባል የሚችልበት አግባብ የለም። በመሆኑም የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ አመልካች ተጠሪን በቅነሣ ሥርዓት ያሰናበታቸው መሆኑን አላስረዲም በማለት የያዘው ምክንያት የሕግ ድጋፍ የላለው ነው።
በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠው ነገር ተጠሪ ጋር በተመሣሣይ ሁኔታ ተቀጥረው ስራ በመስራት ላይ የሚገኙ ሰራተኞች ስራውን እየሰሩ ስለመሆኑ የተረጋገጠበት ሁኔታ የለምና። በአጠቃላይ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጉዲዩ ላይ የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ የሻረው በሕጉ አግባብ ባለመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሥነ ሥርዓትም ሆነ የመሰረታዊ ሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ ስለአገኘን ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 879ዐ1 ሰኔ 24 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የተሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 584ዐ7 ታህሣሥ ዐ7 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የተሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.