No summary available.
ሰ/መ/ ታህሣሥ 12 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ታከለ ባልቻ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አዜብ ፀጋዬ አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የሱማላ ብሓራዊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው።
ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። የክርክሩ መነሻ ዕቃንና ሰውን በየብስ ለማጓጓዝ በተደረገ ውል ምክንያት ለደረሰ ጉዲት ሉከፈል የሚገባውን የካሣ መጠን የሚመለከት ነው። በከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
ተጠሪ ለሥር ፍርድ ቤት የመለያ ቁጥሩ 2612 የሆነ ሻርኘ የፍቶና የፉልም ማባዥያ ማሽን ከሻርኘ ጄኔራል ትሬዱንግ ብር 2ዐዐ,ዐዐዐ/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ገዝቼ ንብረትነቱ የተከሳሽ/የአሁኑ አመልካች/ የሆነ የመለያ ቁጥሩ 3-12334 አይሱዙ መኪና እኔንና ዕቃውን ጅጅጋ እንዱያደርስ ተዋውለን ዕቃውን ጭኖ ወደ ጅጅጋ ስንጓዝ ሐምል 18 ቀን 1999 ዓ.ም. ከአዋሽ አስር ኪል ሜትር ዕርቀት ከምትገኘው ‛መድን“ ተብል ከሚጠራው መንደር አካባቢ መኪናው በመገልበጡ የፉልምና የፍቶ ማሽን ወድሟል። ስለሆነም በአደጋው ብር 2ዐዐ,ዐዐዐ/ሁለት መቶ ሺህ ብር ማሽኑ በመውደሙ የደረሰብኝን ኪሣራ እንዱከፍል ይወሰንልኝ። ከዚህ በተጨማሪ በአደጋው እግሬን የተሰበርኩ በመሆኑ ለደረሰብኝ ጉዲት ካሣ ብር 3ዐ,ዐዐዐ/ሰላሳ ሺህ ብር/ ለህክምና ያወጣሁትን ብር 4ዐ,ዐዐዐ/አርባ ሺህ ብር/ እና በመታመሜ ምክንያት የቀረብኝን ገቢ ብር 3ዐ,ዐዐዐ/ሰላሳ ሺህ ብር/ በድምሩ ተከሣሽ/የአሁኑ አመልካች/ ብር 3ዐዐ,ዐዐዐ/ሦስት መቶ ሺህ ብር/ እንዱከፍለኝ በማለት ተጠሪ ክስ አቅርበዋል። አመልካች በተከሣሽነት ቀርበው ማሽኑ እየሰራ ነው። ከሣሽ/ተጠሪ/ ለህክምና ብር 4ዐ,ዐዐዐ/አርባ ሺህ ብር/ ያወጡ መሆኑን ያቀረቡት ማስረጃ የለም ማሽኑ አዱስ ወይም ያገለገለ መሆኑ አልተረጋገጠም የሚል ክርክር አቅርበዋል።
የከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካችና ተጠሪ ባደረጉት የዕቃና ሰው መጓጓዝ ውል መሰረት ከሳሽ/ተጠሪ/ ማሽኑን ጭነው ወደ ጅጅጋ ሲሄደ አደጋው የደረሰ መሆኑን ተከሳሹ/አመልካች/ ያመኑ መሆኑንና የሚያከራክረው መሰረታዊ ጭብጥ የካሣው መጠን መሆኑን በውሣኔው ከገለፀ በኋላ ቁጥሩ 2612 የሆነው ሻርኘ የፍቶና የፉልም ማባዥያ ማሽን ተጠሪ ብር 2ዐዐ,ዐዐዐ/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ የገዙት መሆኑን የሚያረጋግጥና ማሽኑ የወደመ መሆኑን በመግለፅ ሻጩ ሻርኘ ጀኔራል ትሬዱንግ ማሽኑን ካየ በኋላ በፅሐፍ እንዲረጋገጠ በመጥቀስ፣ ጉዲቱ በድንገተኛ አደጋ የደረሰ በመሆኑ አመልካች ለተጠሪ ብር 18ዐ,ዐዐዐ/አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ብር/ ይክፈል ለህክምና፣ ለጉዲት ካሣና ተጠሪ ለቀረበት ገቢ ብር 54,ዐዐ/ሃምሣ አራት ሺህ ብር/ ተከሳሽ ለከሳሽ ይክፈል በማለት ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚው ችልት ሻርኘ ጄኔራል ትሬዱንግ ማሽኑን ከተረከበና ካየ በኋላ በማሽኑ ላይ የደረሰበት ጉዲት የለም ብለው በቃል ሲናገሩ ሰምተናል የሚል የአመልካችን ሁለት ምስክሮች ቃል ሰምቷል። ከዚያ በኋላ አመልካች ማሽኑ ጉዲት አልደረሰበትም ስለዚህ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ለተጠሪ ብር 18ዐ,ዐዐዐ/አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ብር/ እንድከፍል የሰጠው ውሣኔ አላግባብ ነው በማለት ውሣኔውን አሻሽል አመልካች ለተጠሪ ብር 25,ዐዐዐ/ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ለህክምና ለደረሰባት ጉዲት ካሣ እንዱከፍል በማለት ወስኗል። በዚህ ውሣኔ ተጠሪ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታ ለክልለ ሰበር ችልት አቅርበዋል። የክልለ ሰበር ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር የጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል።
አመልካች ሐምል 29 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ የፍቶና የፉልም ማባዥያ ማሽኑ ብልሽት እንደደረሰበት የቀረቡት ማስረጃ ሀሰተኛ ማስረጃ መሆኑን የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርበው የምስክርነት ቃል በሰጡ ሁለት ምስክሮች አረጋግጫለሁ። አደጋው የደረሰው ሹፋሩን ሽፍቶች ሉያስገድደት መሀል መንገድ ውስጥ በመግባታቸውና ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በመሆኑ ለደረሰው ጉዲት ሃላፉ ነህ መባለ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት። የከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ላይ ለደረሰው ጉዲት የወሰነው የካሣ መጠን የንግድ ህግ ቁጥር 597ን የሚቃረን ሆኖ እያለ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት እንዲለ ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩላቸው ማሽኑ የወደመ መሆኑ በፅሐፍ ከተገዛበት ድርጅት የተሰጠን ማስረጃ እያለ ስለ ማሽኑ ምንም አይነት ሙያ በልላቸው ሁለት ምስክሮች ቃል አስተባብያለሁ በማለት ያቀረቡት ክርክር የህግ ድጋፍ የለውም።
No topics extracted.
አመልካች ለሥር ፍርድ ቤት የላነሱትን መከራከሪያ ከአቅም በላይ በሆነ ኃይል ነው አደጋው የደረሰው በማለት የቀረቡት ክርክር በህግ በኩል ተቀባይነት የላለውና በማስረጃ ያልተረጋገጠ ነው።
የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ሰኔ 2ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. የተፃፈ መልስ አቅርበዋል። አመልካች የካቲት 1 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም አመልካች ለተጠሪ መክፈል ያለበት የካሣ መጠን አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ውሣኔ ለመስጠት ጉዲዩን መርምረናል።
የከፍተኛ ፍርድ ቤት አደጋው ስለደረሰበት ማሽን ዋጋ፣ እና አጠቃላይ ባህሪይ በማሽኑ ላይ ስለደረሰው ጉዲይ የሚያውቀው ሻርኘ ጀኔራል ትሬዱንግ ማሽኑ በአደጋው ምክንያት በደረሰበት ጉዲት ሙለ በሙለ ከጥቅም ውጭ የወጣ መሆኑን በፅሐፍ የሰጠውን ማረጋገጫ በመቀበል፣ አመልካች ለተጠሪ ብር 18ዐ,ዐዐዐ/አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ/ እንዱከፍል ወስኗል። የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ሻርኘ ጄኔራል ትሬዱንግ በማሽኑ ላይ ስለደረሰው ጉዲት ማሽኑን ከመረመረ በኋላ የሰጠው የሙያ አስተያየት ታዓማኒነት የለውም የሚል ከሆነ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 136(1) በሚደነግገው መሰረት ስለማሽኑ ልዩ ዕውቀት ያለው ባለሙያ በመመደብ እንዱመረመር ማድረግ ይገባው ነበር። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ስለ ማሽኑ ዕውቀትና ክህልት ያለው ድርጅት ማሽኑን ከአደጋው በኋላ መርምሮ በፅሐፍ የሰጠውን የሙያ ማረጋገጫ ማሽኑን ለሻርኘ ጄኔራል ትሬዱንግ ስናደርስ ማሽኑ ደህና ነው በማለት የድርጅቱ ሰራተኞች ሲናገሩ ሰምተናል የሚለ ስለ ማሸኑ ልዩ ዕውቀትና ሙያ የላላቸው ምስክሮች የሰጡትን የምስክርነት ቃል በመቀበል በሻርኘ ጄኔራል ትሬዱንግ በማሽኑ ላይ ስለደረሰው ጉዲት የቀረበውን የሙያ ማረጋገጫ ውድቅ ማድረጉ፣ ልዩ ዕውቀትና ክህልትን መሰረት በማድረግ አንድ ጉዲይ ተመርምሮ የተሰጠ የሙያ አስተያየትን ለማስተባበል የሚቻለው በጉዲዩ የተሻለ የሙያ ዕውቀትና ክህልት ያለው ባለሙያ ጉዲዩን መርምሮ በሚያቀርበው የሙያ አስተያየት ‛ነው“ የሚለውን የማስረጃ ህግ መርህና የፍትሐብሄር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 136(1) ድንጋጌ መሰረታዊ ይዘትና መንፈስና ዓላማ ጋር የማይጣጣም ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሙያ ምርመራ በማድረግ የቀረበን ማረጋገጫ መሰረት በማድረግ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ የሻርኘ ጄኔራል ትሬዱንግ ሰራተኞች ማሽኑ ደህና ነው በማለት ሲናገሩ ሰምተናል የሚለ ሁለት ምስክሮችን ቃል መሰረት በማድረግ መሻሩ ስህተት ነው በማለት የሰጠው ውሣኔ በአግባቡ ሆኖ ስላገኘነው አመልካች በዚህ በኩል ያቀረቡትን ክርክር አልተቀበልነውም።
አመልካች አደጋው የደረሰው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ነው በማለት ያቀረበው ክርክር ለሥር ፍርድ ቤት ያልቀረበና በይግባኝና በሰበር ደረጃ ያላነሱት በመሆኑ ውድቅ መደረጉ በአግባቡ ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም የመለያ ቁጥሩ 2612 የሆነው የተጠሪ ማሽን ጅጅጋ ለማድረስ ዋጋ ተቀብል ከጫነ በኋላ የማሽኑ ደህንነት በተጠበቀበት ሁኔታ ያላደረሰና መንገድ ላይ በደረሰው አደጋ ማሽኑ መለ በሙለ ከአገልግልት ውጭ በመሆኑ አመልካች ለተጠሪ ብር 18ዐ,ዐዐዐ/አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ብር/ እንዱከፍል የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ማፅናቱ ዕቃን በየብስ ትራንስፕርት ስለማጓጓዝ የወጡትን የንግድ ህግ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ በመሆኑ የአመልካችን ክርክር አልተቀበልነውም።
አመልካች ተጠሪ ብር 9,ዐዐዐ/ዘጠኝ ሺህ ብር/ ለህክምና ወጭ እንዱሆን የሰጡ መሆኑ ተረጋግጧል። ይህ ከሆነ ከላይ በጠቀስነው የህግ ድንጋጌ መሰረት አመልካች ለተጠሪ ሉከፍለት የሚገባው ቀሪ የካሣ ገንዘብ ብር 31,ዐዐዐ/ሰላሳ አንድ ሺህ ብር/ ብቻ ነው። ከዚህ አንፃር ስንመለከተው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በንግድ ህግ ቁጥር 597 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት ሣያሻሻል ተጠሪ በአመልካች መኪና ሲጓጓዙ ለደረሰባቸው ጉዲት አመልካች ካሣ ብር 54,ዐዐዐ/ሃምሣ አራት ሺህ ብር/ ሉከፍል ይገባል በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም ይህንን የውሣኔ ክፍል በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት በማሻሻል፣ አመልካች በተጠሪ ላይ ለደረሰው የአካል ጉዲት ሉከፍል የሚገባው ብር 4ዐ,ዐዐዐ /አርባ ሺህ ብር/ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ብር 9,ዐዐዐ/ዘጠኝ ሺህ ብር/ የከፈለ መሆኑ ስለተረጋገጠ አመልካች የሚቀርበት የብር 31,ዐዐዐ/ሰላሳ አንድ ሺህ ብር/ ብቻ ነው በማለት ወስነናል።
በአጠቃላይ ከላይ በገለፅናቸው ምክንያቶች የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በተጠሪ ማሽን ላይ ለደረሰው ጉዲት አመልካች ለተጠሪ ብር 18ዐ,ዐዐዐ/አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ብር/ ይክፈል በማለት የሰጠው ውሣኔ በአግባቡ ሆኖ አግኝተነዋል። አመልካች በተጠሪ ላይ ለደረሰው የአካል ጉዲት የሚከፍለውን የካሣ መጠን በማሻሻል አመልካች ለተጠሪ ከዚህ በፉት ከከፈለው ብር 9,ዐዐዐ /ዘጠኝ ሺህ ብር/ በተጨማሪ ብር 31,ዐዐዐ/ሰላሳ አንድ ሺህ ብር/ ብቻ ሉከፍል የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል። በአጠቃላይ አመልካች ለተጠሪ ሉከፍል የሚገባው ብር 211,ዐዐዐ/ሁለት መቶ አሥራ አንድ ሺ ብር/ ብቻ ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የሱማላ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ ተሻሽሎል።
አመልካች ለተጠሪ ብር 211,ዐዐዐ/ሁለት መቶ አሥራ አንድ ሺህ ብር/ ሉከፍል ይገባል በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ግራቀኙ ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ለየራሳቸው ይቻለ። መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።