No summary available.
ኀዲር 8 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የፍትሕና ሕግ ጉዲዮች ቢሮ - ተስፊዬ ዘመድኩን ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ ከቤት ባለቤትነት መብት ጋር ተያይዞ የተነሣውን ክርክር የሚመለከት ነው።
ከመዝገቡ እንደሚታየው አመልካች የክርክሩ ተካፊይ የሆነው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 358 መሰረት መቃወሚያ በማቅረቡ ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ በ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ላይ ክስ አቅርቦ ከተከራከሩ በኋላ፣ ክስ ያቀረበበትን ቤት እንዱረከብ ውሣኔ አሰጥቶአል። አመልካች መቃወሚያ ያቀረበው ቤቱ ከጅምሩ የአስተዲደሩ ሲሆን ዋጋ ተቀብል ለ1ኛ ተጠሪ በሽያጭ ያስተላለፈው በመሆኑ ቀደም ሲል የተሰጠው ውሣኔ መብቴን ይነካል በማለት ነው። ፍ/ቤቱም መቃወሚያውን ከመረመረ በኋላ፣ ተቀባይነት የለውም በማለት ውሣኔ ሰጥቶአል። በዚህ ውሣኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሣኔው ጉድለት የለበትም በማለት ይግባኙን ሰርዞአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች ጥር 12 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው አመልካች መብቴ ተነክቶአል በማለት ያቀረበው የመቃወሚያ ክርክሩ ሣይሰማ ውድቅ መደረጉ አግባብ ነው ወይ? በሚለው ጭብጥ ላይ ነው። በዚህ መሰረት ግራ ቀኝ ወገኖች ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ ይዘት መገንዘብ እንደቻልነው አመልካች ባቀረበው መቃወሚያ መሰረት የክርክሩ ተካፊይ በመሆን ሉያቀርበው ይችል የነበረውን የሕግም ሆነ የፍሬ ነገር ክርክር እንዱያሰማ አልተደረገም። በሰበር አቤቱታው እንደገለፀው በጉዲዩ ያገባኛል የሚለው በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የአስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግልት አካላት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ. 2/95 እና በአዋጅ ቁ. 4/2ዐዐዐ /እንደተሻሻለ በአንቀጽ 29 መሰረት የተቋቋመ የአስተዲደሩ አስፈፃሚ አካል በመሆኑ ነው። በተጠቀሰው አዋጅ አንቀጽ 29/3/ መሰረት የከተማውን አስተዲደርና የነዋሪዎችን መብትና ጥቅም በሚመለከቱ ጉዲዮች ጣልቃ ገብቶ እንዱከራከር መብት የተሰጠው መሆኑንም በክርክሩ ገልጾአል። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 358 በተመለከተውን ድንጋጌ መሰረት መቃወሚያ ያቀረበው ለክርክሩ መሰረት ከሆነው ቤት ጋር በተያያዘ ያለውን የከተማውን አስተዲደር የነዋሪዎች መብትና ጥቅም ለማስከበር በሚል እንደሆነም ተገንዝበናል።
አስቀድሞ የተሰጠውን ውሣኔ ለማስነሣት መቃወሚያ ማቅረብ የሚችል ወገን በክርክሩ ውስጥ መግባት የሚገባው ሆኖ ነገር ግን ተካፊይ ያልነበረ፤ ተካፊይ ባልሆነበት ክርክር የተሰጠው ፍርድም መብቱን የሚነካበት የሆነ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 358 ተደንግጎአል። በያዝነው ጉዲይ እንደምናየው አመልካች በአስተዲደሩ የአስፈፃሚ አካልነቱ ሉያስጠብቀው የሚገባው የአስተዲደሩና የነዋሪዎች መብትና ጥቅም እንዲለ በመግለጽ መቃወሚያውን አቅርቦአል።
መቃወሚያው የቀረበለት ፍ/ቤት ግን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 36ዐ/2/ በተደነገገው መሰረት ክርክሩን አልሰማም። አቤቱታውን ውድቅ ያደረገው ቀደም ሲል በተሰጠው ውሣኔ መብቱ ከተነካ "በሕግ አግባብ ውሣኔውን ከሚያስለውጥ በቀር … በዚህ ረገድ ሉያቀርበው የሚችለው የመቃወም አቤቱታ … የለም" የሚል ምክንያት በመስጠት ነው። ይህን አይነቱ አካሄድ አግባብ ያለውን የሥነ ሥርዓቱን ድንጋጌ ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ አይደለም። አመልካች ቀድሞ በተሰጠው ውሣኔ መብቴ ተነክቶአል ማለቱ እስከተረጋገጠ ድረስ ውሣኔውን ለማስለወጥ የሚችለው መቃወሚያውን በማቅረብ ነው በፍ/ቤቱ ግንዛቤ ሣያገኝ ቀርቶአል የምንለውም ይህ ነው። በመሆኑም አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ በሥነ - ሥርዓት ሕጉ ድንጋጌ አተረጓጎም ረገድ መሰረታዊ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።
ው ሣ ኔ
2/ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአመልካችን የመቃወሚያ አቤቱታ ተቀብል በጉዲዩ ሥረ ነገር ግራ ቀኝ ወገኖችን አከራክሮ ተገቢውን ውሣኔ ይሰጥበት ዘንድ ጉዲዩ ይመለስለት ብለናል።
መዝገቡ ይመለስ።
No topics extracted.