No summary available.
ህዲር 14 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የምጥን መንደር መኖሪያ ቤቶች የህብረት ሥራ ማህበር ጠበቃ ዜና ደባሱ ቀረበ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ በሁከት ይወገድ ክስ መነሻነት ክርክር ተካሂድ የተሰጠውን ውሳኔ መሰረት በማድረግ የተጀመረውን የአፈጻጸም ክርክር የሚመለከት ነው። ከመዝገቡ እንደሚታየው የአሁኑ አመልካች የሁከት ይወገድልኝ ክስ በ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ላይ መስርቶ ክርክር ከተደረገ በኋላ፣ የፍርድ ባለመብት ሆኖአል። በውሳኔው 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪ በአመልካች ይዞታ ላይ ሁከት የፈጠሩ መሆናቸውን ስለመረጋገጡ ተመልክቶአል። አመልካች የአፈጻጸም መዝገቡን ያስከፈተው በውሳኔው መሰረት የፍርድ ባለዕዲ የሆኑት 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪ ይዞታውን ለቀው እንዱወጡላት ትዕዛዝ ለማሰጠት ነው። በልላ በኩል ደግሞ 3ኛ ተጠሪ አፈጻጸም በተጠየቀበት ቦታ ይዞታ ያለኝ እኔ ነኝ በማለት መቃወሚያ በማቅረብዋ የክርክሩ ተካፊይ ልትሆን ችላለች። አፈጻጸሙን የጀመረው የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአመልካችን ጥያቄ በመቀበል እንደውሳኔው እንዱፈጸም ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን የአሁንዋ 3ኛ ተጠሪ ለከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረብዋ ትዕዛዙ ተሽሮአል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካች በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ሰበር ችልት አቤቱታ አቅርቦ ክርክሩ በዚህ ደረጃም ተሰምቶአል። በመጨረሻም የሰበር ችልቱ የአመልካችን ክርክር ውድቅ በማድረግ አቤቱታ የቀረበበትን ውሳኔ አፅንቶአል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች መጋቢት 3 ቀን 2002 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ክርክሩን ሰምተናል። 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ባለመቅረባቸው ክርክሩ የተሰማው እነሱ በላለበት ነው። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተደረገው የሥር ፍ/ቤቶች የ3ኛ ተጠሪን መቃወሚያ በመቀበል የመወሰናቸውን አግባብነት ሉመረመር የሚገባው ሆኖ በመገኘቱ ነው። በዚህ መሰረትም ከሥር ጀምሮ የተደረገውን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከላይ ባጭሩ እንዲመለከትነው ለአፈጻጸሙ መሰረት የሆነው ውሳኔ በተሰጠበት ክርክር ተጠሪ ተከራካሪ ወገን አልነበረችም። አመልካች በ1ኛ እና በ2ኛ ተጠሪዎች ላይ ክስ የመሰረተው በሕጋዊ መንገድ በያዝኩት መሬት ላይ ሁከት ፈጥረውብኛል። ስለዚህም ያለ አግባብ የያዙትን መሬት ለቀው ይወጡ ዘንድ ይወሰንልኝ በማለት ነው። ክሱን የሰማው ፍ/ቤትም ተጠሪዎች (ተከሳሾች) ስፊቱ በካሬ ሜትር ተለክቶ ለአመልካች በተሰጠው መሬት ውስጥ ገብተዋል በሚል ምክንያት ከሕግ ውጪ የያዙትን መሬት እንዱለቁ ወስኖአል። ፍ/ቤቱ ይህን የመሰለ ውሳኔ ላሰጥ የቻለው መሬቱ በአመልካች የተሰጠ መሆኑን በማረጋገጥ ነው። 3ኛ ተጠሪ ክርክሩ ውስጥ የገባችው ከዚህ በኋላ ብቻ ሳይሆን መቃወሚያዋን ያቀረበችውም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.418 የተመለከተውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ የአፈጻጸም ክርክር በቀጠለበት መዝገብ ስለመሆኑ የሥር ፍ/ቤቶች ከሰጡአቸው ውሳኔዎች ለመገንዘብ ችለናል። የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት እና የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ሰበር ችልት የተጠሪን መቃወሚያ በመቀበል የሰጡት ውሳኔ እንዲየነው ክርክር የተነሳበት መሬት ለተጠሪ የተሰጠ ነው ወይም የተጠሪ ይዞታ ነው የሚል እንድምታ ያለው ነው።
ይህ ውሳኔ በይዘቱ ሲታይ በአመልካች እና በ1ኛና በ2ኛ ተጠሪዎች መካከል በተነሳው ክርክር መነሻነት የተሰጠውን ውሳኔ የሚሽር ነው።
ጉዲዩ የፍትሐብሕር ክርክርን የሚመለከት በመሆኑ የሚመራው በፍትሐብሕር ሥነሥርዓት ሕጉ መሰረት እንደሆነ ይታወቃል። የፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ የክስ አቀራረብን፣ የክርክር አመራርን፣ አወሳሰን እና አፈጻጸምን የሚመለከቱ ዝርዝር ድንጋጌዎችን ይዞአል። በዋናው ክርክርም ሆነ በአፈጻጸም ሂደት መብታችን ተነክቶአል የሚለ ሦስተኛ ወገኖች መቃወሚያ የሚያቀርቡበት እና መብታቸውን የሚያስከብሩበት ሥርዓት በዚሁ የሥነ-ሥርዓት ሕግ ተካቶአል።
በያዝነው ጉዲይ ሦስተኛ ተጠሪ ለጉዲዩ ሦስተኛ ወገን በመሆንዋ እና መብቴ በአፈጻጸሙ ሂደት ተነክቶአል ብላ በማመንዋ በአፈጻጸም ደረጃ ባለው ክርክር ላይ መቃወሚያ ማቅረብ የሚያስችለውን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.418ን መሰረት በማድረግ ክርክሩ ውስጥ ገብታለች። የሥር ፍ/ቤቶችም መቃወሚያው የቀረበበትን ሥርዓት በትክክል ቢገነዘቡም፤ አፈጻጸሙ የቀጠለበት መሬት የማን ይዞታ ነው ወይም በመሬቱ ላይ የተሻለ መብት ያለው የትኛው ወገን ነው የሚል የንጥጥር አይነት ጭብጥ በመያዝ ውሳኔ ሰጥተዋል። ፍ/ቤቶቹ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.418 መሰረት የቀረበውን መቃወሚያ ለመወሰን የተከተለት አካሄድ አግባብነት ያለው ነው ወይ? የሚለውን ጥያቄ ማንሳቱ ተገቢ የሚሆነውም እዚህ ላይ ነው።
No topics extracted.
በዋናው ክርክርም ሆነ በአፈጻጸም ሂደቱ መብታችን ተነክቶአል ብለው የሚያስቡ ሦስተኛ ወገኖች መቃወሚያቸውን የሚያቀርቡበት ሥርዓት በሥነ-ሥርዓት ሕጉ ስለመዘርጋቱ ቀደም ሲል ተመልክተናል። በዋናው ክርክር የሚሰጠው ውሳኔ እና በውሳኔው መሰረት ለማስፈጸም የሚደረገው ሂደት የተለያዩ በመሆናቸው በሚቀርቡት መቃወሚያዎች ላይ የሚሰጡት ውሳኔዎችም የተለያዩ ናቸው። መቃወሚያ አቅራቢው መብቱ የተነካው በአፈጻጸም ሂደቱ ከሆነ ከአፈጻጸም ሂደቱ ጋር የተያያዘ መፍትሄ ነው የሚሰጠው። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.418 መሰረት በሚቀርብ መቃወሚያ ላይ የሚሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.419 ተመልክቶአል። በዚህ መሰረት መቃወሚያው ተቀባይነት ያገኘ ከሆነ በአፈጻጸም የተያዘው ንብረት በከፉል ወይም በሙለ እንዱለቀቅ ትዕዛዝ ይሰጣል። ከዚህ አልፍ በአፈጻጸም የተያዘው ንብረት ለአንደ ወይም ለላላው ተከራካሪ ወገን ይገባል የሚል ዲኝነት አይሰጥም። ከሁለ በላይ ደግሞ በዋናው ክርክር የተሰጠውን ውሳኔ የሚሽር ወይም የሚያሻሽል ውሳኔ አይሰጥም። የዚህ አይነት ውሳኔ መስጠት የሚቻለው ዋናውን ውሳኔ በመቃወም አቤቱታ ሲቀርብ ነው። ይህ ደግሞ እራሱን የቻለ የአቀራረብ ሥርዓት እና የክርክር አመራር ሂደት ያለው ነው። በዚህ ረገድ ተገቢው ድንጋጌም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.358 የተመለከተው ነው።
በያዝነው ጉዲይ 3ኛ ተጠሪ በዚህ ቁጥር 358 መሰረት ወይም ዋናውን ውሳኔ በመቃወም አቤቱታ አላቀረበችም። የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ግን ዋናውን ውሳኔ የሚሽር ነው። ከዚህ የተነሳም ፍ/ቤቶቹ የሰጡት ውሳኔ (አቤቱታ የቀረበበት) በሕጉ አተገባበር/አተረጓጎም ረገድ መሰረታዊ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።