No summary available.
ህዲር 03 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ተከሳሽ በላለበት የተሰጠ ውሳኔ ተነስቶ ተከሳሹ ባለበት የሚታይበትን የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ አግባብን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካቾች ላይ የቤት ሽያጭ ውል ተደርጓል የተባለው እንዱፈርስና ቤቱንም እንዱረከቡ ይወሰን ዘንድ ዲኝነት ጠይቀው በመሰረቱት ክስ የአሁኑ አመልካቾች በላለበት ታይቶ አመልካቾች በቀድሞ ወረዲ 24 ቀበላ 13 ውስጥ የሚገኝ ቁጥሩ 1099 የሆነ ቤት ለተጠሪ እንዱያስረክቡ የሚል ውሳኔ ተጠሪ አግኝተዋል። ከዚህ በኋላ አመልካቾች ውሳኔውን ለሰጠው ፍርድ ቤት በላለበት የተሰጠው ውሳኔ ተነስቶ ክርክሩ ባለበት እንዱታይላቸው አቤቱታ አቅርበዋል።
የአመልካቾች የስር አቤቱታ ይዘት ባጭሩ ለ1ኛ አመልካች የጋዜጣ ጥሪ የተደረገው ያላግባብ መሆኑን 2ኛ ተጠሪም በሚኖሩበት ቤት መጥሪያው ተለጥፎል የተባለው ባግባቡ አለመሆኑን ዘርዝረው መጥሪያው በአግባቡ ደርሷል ለማለት ስለማይቻል መጥሪያው እንደአልደረሰ ተቆጥሮ በላለንበት የተሰጠው ውሳኔ ተነስቶ ክርክሩ ባለንበት እንዱካሄድ ይደረግልን የሚል ነው።
የስር ፍርድ ቤትም ተጠሪ በአመልካቾች አቤቱታ ላይ አስተያየት እንዱሰጡበት በማድረግ ክርክሩን መርምሮ የአመልካቾችን አቤቱታ ውድቅ አድርጓል። ከዚህም በኋላ አመልካቾች ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ትእዛዝ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ የካቲት 02 ቀን 2002 ዓ.ም በጻፈት ሁለት ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ለ1ኛ አመልካች የጋዜጣ ጥሪ የተደረገው የመጥሪያ አደራረስ ቅደም ተከተልን ባልጠበቀ ሥነ ሥርዓት በመሆኑና ይህም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ ስለመጥሪያ አደራረስ የተመለከቱትን ድንጋጌዎችን የሚፃረር በመሆኑ አመልካች በላለበት የተሰጠው ውሳኔ ሉነሳ አይገባም ተብል የተወሰነው ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ትእዛዝ እንዱሻር ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም አመልካቾች ወደ ጉዲዩ ገብተን እንከራከር በሚል ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ የሆነው ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጎ ተጠሪ ቀርበው ሰኔ 01 ቀን 2002 ዓ.ም በተጻፈ ሁለት ገፅ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል። በመልሳቸውም መጥሪያው ለአመልካቾች የደረሰው በሥነ ሥርዓቱ የተቀመጡትንና የሰበር ችልቱም የሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ባገናዘበ መልኩ መሆኑን በማረጋገጥ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ትዕዛዝ ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል። የ1ኛ አመልካች ጠበቃም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካቾች በላለበት የተሰጠው ውሳኔ እንዱነሳላቸው አቤቱታ ያቀረቡት መጥሪያ በተገቢው ስርዓት ቅደም ተከተለን ተከትል አልደረሰም በሚል ምክንያት መሆኑን ነው። የሥር ፍ/ቤት የአመልካቾችን ጥያቄ ውድቅ ያደረገው መጥሪያውን አመልካች ቤት ድረስ ተሂድ እማኞች ባለበት ማግኘት ሳይቻል ቀርቷል፣ ይህም ብቻ ሳይሆን መጥሪያው በአመልካች ቤት ላይ ተለጥፍ ነበር፤ ሉቀርቡ ባለመቻላቸው በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸዋል። ይህም ሆኖ ሳይቀርቡ ቀርተዋል፣ አንድ ሰው በአካል ተፈልጎ ካልተገኘ በመኖሪያው ላይ መጥሪያ ተለጥፍ እና በጋዜጣ ተጠርቶ ካልቀረበ መጥሪያው እንደደረሰው እንደሚቆጠር በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት አስገዲጅ ውሳኔ ተሰጥቷል፣ አመልካች ታምሜ ወደ ላላ ቦታ ሄጀ ነበር በማለት የገለፁት ከ10/11/2001 ዓ.ም በኋላ ሲሆን ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ የተወሰነው ከመሄዲቸው በፉት ነው ስለዚህ መጥሪያው ደርሷቸው እንደነበር ፍርድ ቤቱ ስለተረዲና በቂ ምክንያትም ስላላቀረቡ አቤቱታው ተቀባይነት የለውም በሚል ምክንያት ነው። ይህ ችልትም የስር ፍርድ ቤት ዋናውን ጉዲይ የመራበትን የኮ/መ/ አስቀርቦ ተመልክቷል። መዝገቡ ሲታይም አመልካች መልሳቸውን ከመዝገቡ ጋር በ17/10/2001 ዓ.ም እንዱያያይዙ እና በ19/10/2001 ዓ.ም ለቃል ክርክር እንዱቀርቡ በ02/10/2001 ዓ.ም ትዕዛዝ መስጠቱን፣ የክፍለ ቀበላ ደንብ አስከባሪዎች ነን የሚለ ሁለት ግለሰቦች በ09/10/2001 ዓ.ም በፃፈትና ማህተም በላለው ደብዲቤ ቁጥር 1099 ወደሆነው ቤት ሄደን ነበር፣ ወ/ሮ አበበች በጅጋ በቤቱ ውስጥ እንደማይኖሩና የት እንደሚኖሩም የሚያውቅ ሰው አለመኖሩን ጠይቀን የተረዲን መሆናችንን እናረጋግጣለን በማለት ለፍርድ ቤቱ ማረጋገጫ የላኩ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ ከመዝገቡ ጋር ተያይዞ መገኘቱን የተጠሪ ጠበቃ በ16/10/2001 ዓ.ም በተጻፈ የቃለ መሐላ ማመልከቻ አንደኛ አመልካች በቤቱ ውስጥ አይኖሩም በሚል መጥሪያ ለማድረስ አለመቻለን ገልጸው በጋዜጣ ማስታወቂያ እንዱጠሩላቸው መጠየቃቸውን 1ኛዋ አመልካች በጋዜጣ ማስታወቂያ እንዱጠሩ ታዝዞም በ8/11/2001 ዓ.ም ስላልቀረቡ ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ መታዘዙን ክሱ ቤት ለመረከብ ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 36(4) መሰረት ቤቱን የያዘውን ሰው በተከሳሽነት መካተት አለበት ተብል የተሻሻለው ክስ እንዱቀርብ ታዞ ይኸው የተሻሻለው ክስ ለአመልካቾች ተልኳል ተብል መመዝገቡን የተላከው መጥሪያ ከስር ፍርድ ቤት መዝገብ ሲታይም በከሳሽ የፍርድ ባለመብት ዶ/ር ተስፊዬ አካለና በተከሳሽ የፍርድ ባለእዲ ወ/ሮ ሰብለወንጌል ታደሰ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዲይ የሚያወሳ መሆኑንና ‛ሰዎቹን ስላላገኘን በቤቱ በራፍ ላይ የለጠፍን መሆኑን እንገልፃለን“ የሚል ይዘት የያዘ ሁኖ የ1ኛዋን አመልካች ስም ግን የሚጠቅስ አለመሆኑን መጥሪያው በመኖሪያ ቤቷ ላይ ተለጥፎል የተባለችው ሁለተኛ አመልካች ወ/ሮ ሰብለወንጌል ታደሰ በሚል ስም ሲሆን የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 78 መሰረት ጥያቄውን አልቀበልም ያለው ወ/ሮ ሰብለወንጌል አበበ በሚል መዝግቦ መሆኑን ከመዝገቡ ተረጋግጧል።
No topics extracted.
የስር ፍርድ ቤት ዋናውን ጉዲይ ከመራበት መዝገብ ከተረጋገጡት፣ ከላይ ከተገለፁት ፍሬ ነገሮች በቀላለ መገንዘብ የሚቻለው አንደኛ አመልካች በቅድሚያ በአካል ሉሰጣቸው የሚገባን መጥሪያ ባግባቡ እንዱደርሳቸው ሳይደረግ እና በማትኖርበት ቤት ላይም ቢሆን የሷን ስም የሚጠራ መጥሪያ በተገቢው አካል ተለጥፎል ለማለት የማይቻል መሆኑን እንዱሁም ሁለተኛዋን አመልካች በተመለከተ ደግሞ የአባቷ ስም ተለውጦ የፍርድ አፈፃፀም መጥሪያ እንጂ ከተጠቃሹ ጉዲይ ጋር አግባብነት ያለው መጥሪያ አለመለጠፈ በሚገባ መረጋገጡን ነው።
ወደ ሕጉ ስንመጣ፤ በመሰረቱ የመጥሪያ አሰጣጥ ዘዳና ቅደም ተከተለ እንዱሁም መጥሪያው ለማን እንደሚሰጥ የሚመለከተው የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ክፍል ዓይነተኛ ዓላማ ከሆኑት መካከል አንደ ተከራካሪ ወገኖችን እኩል የመከራከር መብት እንዱኖራቸው በማድረግ ጉዲዩን ፍትሐዊ በሆነ አኳኋን ለመወሰን ማስቻል መሆኑን ይታወቃል። በመሆኑም ፍርድ ቤቱ መጥሪያ የሚደርስበትን ተገቢ መንገድና ለማን መድረስ እንዲለበት ማረጋገጥ ይገባዋል።
መጥሪያ በተገቢው መንገድ ደርሶት ተከራካሪ ወገን ካልቀረበ ወይም መጥሪያን አልቀበልም ካለ ፍርድ ቤቱ ሉከተለው የሚገባው ስርዓትም በሕጉ በግልጽ ተመልክቷል። ከእነዚህም ድንጋጌዎች መካከል አንደ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 70(ሀ)፣ 103፣ 104፣ 105፣ 106 እና 107 ስር የተመለከተው ሲሆን በእነዚህ ድንጋጌዎች መሰረት ተከሳሽ በላለበት ክርክሩ ታይቶ ውሳኔ ላሰጥ የሚችለው መጥሪያው በአግባቡ የደረሰው መሆኑ ሲረጋገጥ ወይም መጥሪያውን ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆኑ ወይም ሉገኝ ያልቻለ መሆኑ ሲረጋገጥ ወይም መጥሪያውን ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆኑ ወይም ሉገኝ ያልቻለ መሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ ተመልክቷል። ድንጋጌዎቹ መጥሪያው በትክክል ያልደረሰው መሆኑ ከተረጋገጠ ጉዲዩ ተከሳሽ በላለበት እንዱታይ የማይታዘዝ ስለመሆኑ ያስገነዝባለ። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 70(ሀ) ድንጋጌ ስር ላይ ‛መጥሪያው በትክክል መድረሱ“ የሚለው ሐረግ መኖሩም የሚያሳየው ስለመጥሪያ አሰጣጥና አደራረስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 94 እስከ 110 ድረስ የተመለከቱት ሁኔታዎች በአግባቡ መሟላታቸውን የሚያስገነዝብ ነው። አንድ ተከሳሽ በላለበት ጉዲዩ ታይቶ ውሳኔ ከተሰጠውም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 78 መሰረት መፍትሓ መጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ ተመልክቷል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት መፍትሓ ሉጠየቅ የሚችለው አቤቱታ አቅራቢው በሚያቀርበው አቤቱታ ላይ የጥሪው ትዕዛዝ ‛በሚገባ ያልደረሰው“ መሆኑን በመጥቀስ ይህንኑ ማረጋገጥ ሲችል ነው። ከእነዚህ ሁለ ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻለው አንድ ሰው የመከራከር መብቱን እንደተወው የሚቆጠረው መጥሪያው በሕጉ በተዘረጋው ሥርዓትና ቅደም ተከተል መሰረት ደርሶት ክርክር ያለው መሆኑን እያወቀ ሳይቀርብ ሲቀር ብቻ መሆኑን ነው።
ፍርድ ቤቱ በሕጉ የተዘረጋውን ስርዓት ተከትል አማራጭ የመጥሪያ አደራረስ ሥርዓት ከፈጸመ መጥሪያው ለተከሳሹ እንደደረሰ እንደሚቆጠርና በቂና ሕጋዊ ምክንያት ካለው ብቻ ወደ ክርክሩ እንዱገባ የሚፈቀድ መሆኑን ከላይ የተጠቀሱት ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ያስገነዝባል። ስለሆነም ማንኛውም ውሳኔ መሰጠት ያለበትም በሕጉ በተዘረጋው ሥርዓት መሰረት መጥሪያው መድረሱ በሚገባ የተረጋገጠና የተከሳሽ የመከራከር መብት የተጠበቀ መሆኑ ሲታወቅ ላሆን ይገባል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ ከላይ ከስር ፍርድ ቤት ዋና መዝገብ የተረጋገጡት ፍሬ ነገሮች የሚያሳዩት 1ኛ አመልካችን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ወደ ጋዜጣ ጥሪ የሄደበት አካሄድ ቅድሚያ ሉፈጸም የሚገባውን ሥርዓት በአግባቡ አሟጦ ሳይጨርስና ተገቢ ያልሆነ መግለጫ ስለቀረበለት ከመሆኑም በላይ ክሱ ተሻሽል ከቀረበ በኋላም ቢሆን የአመልካቿ ስም ተጠቅሶ መጥሪያው መላኩ ሳይረጋገጥ ነው። የሁለተኛዋ አመልካችም የአባት ስም ተለውጦ የፍርድ አፈፃፀም መጥሪያ እንጂ ከዋናው ጉዲይ ጋር አግባብነት ያለው መጥሪያ ያልተለጠፈላቸው መሆኑን የስር ፍርድ ቤት መዝገብ በግልፅ ያሳያል። የጋዜጣ ጥሪና በተከሳሽ መኖሪያ ላይ በአግባቡ መጥሪያ እንዱለጠፍ ማድረግ ውጤታቸው መጥሪያው እንደደረሰ የሚያስቆጥር የሚሆነው ተከሳሽ መገኘት አለመቻለ በሚገባ ሲረጋገጥ ነው። በመሆኑም ከላይ የተገለፁትና በስር ፍርድ ቤት መ/ የተረጋገጡት ፍሬ ጉዲዮች ለአመልካቾች መጥሪያው እንደሕጉ አነጋገር በሚገባ ያልደረሳቸው መሆኑን የሚያረጋግጡ ሁነው አግኝተናል። ይህ በተረጋገጠበት ሁኔታ አመልካቾች ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ የተሰጠው ትዕዛዝ ተነስቶ ገብተን እንከራከር ሲለ ያቀረቡትን ጥያቄ በበታች ፍርድ ቤቶች ውድቅ የሆነው በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕጉ ስለመጥሪያ አደራረስ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ከመከራከር መብት ጋር ባላገናዘበ መልኩ በመሆኑ ትእዛዙ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ህዲር 08 ቀን 2002 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ህዲር 23 ቀን 2002 ዓ.ም በትዕዛዝ የፀናው ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
አመልካቾች በላለበት ታይቶ የተሰጠው ውሳኔ ባለበት እንዱታይ ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ የሆነው ስለመጥሪያ አደራረስ ሥርዓት የተመለከቱትን ድንጋጌዎችን ይዘትና መንፈስ ከመከራከር መብት ጋር ባላገናዘበ መልኩ ነው ብለናል።
አመልካቾች በላለበት ታይቶ የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 78(2) መሰረት ተነስቶ ባለበት እንዱታይ ብለናል።
የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን አመልካቾች ባለበት በመመልከት የግራ ቀኙን ጉዲይ ሰምቶ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥበት በማለት ጉዲዩን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 341(1) መሰረት መልሰንለታል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።