No summary available.
ህዲር 2 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ ብርሀኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወጋገን ባንክ (አ.ማ) - ኤፍሬም ፈቃደ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ሀብቶም ረዘነ ከጠበቃ ፉሉጶስ አይናለም ጋር ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የትግራይ ክልል የዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ስላመለከተ ነው። ክርክሩ በብድር የተወሰደ ገንዘብን የሚመለከት ነው። በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። አመልካች ተጠሪ በብድር የወሰደትን ብር 200,000 እና ይህ የብድር ገንዘብ የሚወልደው ወለድ በድምሩ 306,185.16 (ሶስት መቶ ስድስት ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ አምስት ብር ከአስራ ስድስት ሣንቲም) እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በተከሳሽነት ቀርበው አመልካች መኪና ሽጧል እንደዚሁም ወለደ በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 2024(ረ) ይታገዲል የሚለ መከራከሪያዎችን ያቀረቡ ሲሆን በዋነኛነት እዲዬን ሰርዞልኛል ምክንያቱም በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት በደረሰብኝ ጉዲት ለመክፈል እንደማልችል ተረጋግጧል በማለት መልስ ሰጥተዋል። አመልካች ተጠሪ በማስረጃነት የጠቀሱት የውስጥ መፃፃፉያ ነው። እዲው አልተሰረዘም የሚል ክርክር አቅርቧል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመዘነ በኋላ አመልካች ተጠሪ የተበደሩትን ብድር የሰረዘላቸው በመሆኑ ዕዲውን ተጠሪ (ተከሳሽ) የመክፈል ሀላፉነት የለበትም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኙን ሰርዞታል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ነሐሴ 19 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የተጠሪ ዕዲ ለጊዜው በተንጠልጣይ ሂሳብ እንዱቆይ (written off) አደረግን እንጅ እዲው የተሰረዘ መሆኑን ለተጠሪ አልገለፅንለትም። አንድ ዕዲ በተንጠልጣይ ሂሳብ መያዝ (written off) እና አንድን የብድር ዕዲ ሙለ በሙለ መሰረዝ የተለያዩ ናቸው። ፍርድ ቤቱ ይህንን ለማስረዲት ያቀረብናቸውን ማስረጃዎች በተሟላ መልኩ አላየልንም። ባንኩ ለተጠሪ ያበደረውን ብድር ሙለ በሙለ ምህረት አላደረገም። ተጠሪ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት የተበደሩትን ብድር እንዲይከፍል የፈጠረባቸው መሰናክል የለም ስለዚህ ተገቢውን ማጣራት ሣያደርግና ሙያዊ በሆኑ ነገሮች የባለሙያ አስተያየት ሣይሰማ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት መልስ ሰጥቷል። ተጠሪ በበኩለ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት እኔ በምኖርበት አካባቢ ጦርነት የነበረ መሆኑና በጦርነቱም ውድመት የደረሰ መሆኑ ፍርድ ቤቱ ዕውቅና ሉሰጠው የሚገባው ፍሬ ጉዲይ ነው። አመልካች ብድር ሲያበድር በመያዣነት ይዞት የነበረውን ተሽከርካሪ በራሱ ፈቃድ በግንቦት ወር 1997 ዓ.ም ነፃ በማድረግ ለቆታል። ይህም ዕዲውን በምህረት መልክ መሰረዙን የሚያሣይ ነው። በባንኮች ዝርዝር ፕሉሲና ፔሮሲጀር መሰረት ሁለት አይነት የብድር ዕዲ ሥረዛዎች መኖራቸውን ለመረዲት ይቻላል።
የመጀመሪያው ‛written off“ የሚባለው ሲሆን ሁለተኛው ለዘለቄታው ተበዲሪውን ላለመጠየቅ የሚደረግ የዕዲ ሥረዛ ነው። አመልካች ለተጠሪ ያደረገው ሁለተኛውን አይነት የዕዲ ስረሳ ነው በማለት መልስ ሰጥተዋል። አመልካች በበኩለ እኔ ያደረክሁት (written off) እንጅ ለዘለቄታው ተበዲሪው ብድሩን እንዲይከፍልና እንዲይጠየቅ ምህረት አላደረግሁም በማለት የመልስ መልስ ሰጥቷል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር በፅሐፍ የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን ችልቱም የአመልካችንና የተጠሪን የቃል ክርክር ሰምቷል። በቃል ክርክሩም አመልካችና ተጠሪ የሚከራከሩት አመልካች የተጠሪን ዕዲ በተንጠልጣይ ሑሳብ እንዱያዝ (written off) ነው ያደረገው ወይስ ተጠሪ በዕዲው እንዲይጠየቅ ለዘለቄታው እዲውን በመሰረዝ ምህረት አድርጎለታል በሚለው ነጥብ ላይ ሆኖ አግኝተነዋል። እኛም በዚህ መዝገብ አከራካሪ የሆነውን ይህንን ጭብጥ በአግባቡ ለመፍታት አመልካችና ተጠሪ የሚያቀርቡትን ማብራሪያና ደጋፉ ጽሐፍችን መመልከቱ ብቻ በቂ እንዲልሆነ ተገንዝበናል።
አመልካችና ተጠሪ የሚከራከሩበት ነጥብ የባንኮች የዕዲ አመዘጋገብ እና የዕዲ ሥረዛን ‛ፔሮሲጀርና“ አሰራር የሚመለከትና የሙያ ማብራሪያ የሚያስፈልገው ነጥብ ነው። ፍርድ ቤቱ ተከራካሪዎች የሚከራከሩበት ጉዲይ የልዩ አዋቂ ምስክርነትና ማብራሪያ የሚያስፈልገው ሆኖ በሚያገኝበት ሰዓት የልዩ አዋቂ ምስክር በመሰየም ጉዲዩ ተጣርቶ እንዱቀርብለት ማድረግ እንደሚገባው የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 136 ንዐስ አንቀጽ 1 ይደነግጋል። በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ አመልካች ግንቦት 12 ቀን 1997 ዓ.ም በፃፈው ደብዲቤ ዕዲውን ከእኔ በማናቸውም ጊዜ ላለመጠየቅ ሙለ በሙለ በመሰረዝ ምህረት አድርጎልኛል በማለት ያቀረቡት ክርክር የባንክ ባለሙያዎችን በመመደብና አስፈላጊም ከሆነ ከብሓራዊ ባንክና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስለ ባንኮች የዕዲ አመዘጋገብና የእዲ ሥረዛና የምህረት ፔሮሲጀር ተገቢው ሙያዊ ማብራሪያ እንዱሰጥ በማድረግ አመልካች የተጠሪን ብድር በተንጠልጣይ ሑሳብ ነው የመዘገበው (written off) ነው ያደረገው ወይስ አመልካች የተጠሪን ዕዲ በማናቸውም ጊዜ ቢሆን ላይጠይቅ ሙለ በሙለ በመሰረዝ ምህረት አድርጓል የሚለውን ጭብጥ መወሰን ሲገባቸው በጉዲዩ የልዩ አዋቂ ምስክርነትና ማብራሪያ ሣይሰሙ አመልካች የተጠሪን ዕዲ ሰርዟል በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የትግራይ ክልል የምስራቅ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የምስራቃዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች የተጠሪን የብድር ዕዲ በተንጠልጣይ ሑሳብ ነው የያዘው (written off) ነው ያደረገው ወይስ ዕዲውን በማናቸውም ጊዜ ላይጠይቅ ሙለ በሙለ በመሰረዝ ምህረት አድርጓል በሚለው ነጥብ ላይ የልዩ አዋቂ በመመደብና በማስመርመር የልዩ አዋቂ የሚያቀርበውን ሙያዊ አስተያየት ከሰማ በኋላ እንድወሰን ጉዲዩን በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343(1) መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ለየራሳቸው ይቻለ።
ራ/ታ
ህዲር 01 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፣ ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድአመልካች፣ የኢት/ያ የእህል ንግድ ድርጅች አልቀረቡምተጠሪዎች፣ 1ኛ. መርዕድ ተፈራ 2ኛ አያላው መኮንን ቀረቡ 3ኛ ስለሺ ኃ/ሚካኤል ቀረቡ 4ኛ ወ/ሪት ዙልፊ ከድር አልቀረበችም 5ኛ አቶ ጣሰው ነገዎ ቀረቡ 6ኛ አቶ አሰፊ ቱለ ጠበቃ አቶ ወንድአወክ አየለ ቀረበ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
የአሁን አመልካች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 6ኛ የተጠቀሱት ሰራተኞቹ በሥራቸው ምክንያት የብር 154,334.67/100 የገንዘብ ጉድለት አድርሶውብኛል በማለት እያንዲንደ ሰራተኛ ኃላፉ ላሆን ይገባዋል የሚልበትን ምክንያት በመጥቀስ ገንዘቡን እንዱተኩለት ባቀረበው ክስ መነሻ የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ተመልክቻለሁ በማለት ተጠሪዎች ኃላፉ ሉሆኑ የሚገባበት ምክንያትና ማስረጃ አልተገኘም በማለት በነፃ አሰናብቷቸዋል። በዚህ ውሣኔ ላይ ቅር ተሰኝቶ የይግባኝ አቤቱታውን ለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ያቀረበ ቢሆንም ተቀባይነትን አላገኘም።
አመልካች የጉዲዩ አካሄድ እንደ ሙግት አመራር ሥርዓቱ ባለመከናወኑ ምክንያት ተገቢውን ዲኝነት አላገኘም የሚለውን የመከራከሪያ ነጥብ በዋነኛነት በመጥቀስ የሰበር አቤቱታ አቅርቧል። ተጠሪዎችም በሥር የተሰጠው ውሣኔ የህግ ስህተት አልተፈፀመበትም የሚለበትን ምክንያት ከመግለፅ ጋር ውሣኔው እንዱፀናላቸው ተከራክረዋል።
እኛም ጉዲዩን ተመልክተናል እንደተመለከትነውም የአሁን አመልካች በተጠሪዎች ላይ ያቀረበውን ክስ ለማስረዲት ከቀረበው የኦዱት ምርመራ ውጤት በተጨማሪ የኦዱት ምርመራ ሥራውን ያከናወኑት ባለሙያዎች ሙያዊ የምስክርነት ቃል እንዱሰጡለት በማስረጃነት የቆጠራቸው መሆኑንና ነገር ግን እነዚህ የሰው ማስረጃዎች ሳይሰሙ ታልፍ ውሣኔ በመስጠቱ ፍትህ እንደተጓደለበት ገልፆ ቅሬታ ሲያቀርብ፤
በተጠሪዎች በኩል በሰበር ከቀረበው ክርክር መካከል እነዚህ ኦዱተሮች ከኦዱት ምርመራ ሰነደ በተለዩ ምን ሉያስረደ ይቻላለ? አንደኛውም ኦዱተር ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል ለመስማት የሚቻልበት መንገድ የለም በማለት ከመከራከራቸው ጋር ተገናዝቦ ሲታይ በእርግጥም የሥር ፍ/ቤት የአመልካችን ማስረጃዎች በሙለ አለመሰማቱን አረጋጋጭ ነው።
አመልካች በሰው ማስረጃነት የሙያ ምስክርነት እንዱሰጡለት የጠቀሳቸው ኦዱተሮች ሳይሰሙ የታለፈበት ምክንያት ምን እንደሆነ በውሣኔው ላይ ተገልፆ ባይገኝም ከላይ እንደተመለከተው የምስክርነት ቃል አለመስጠታቸውን ከውሣኔው ይዘት መረዲት ችለናል።
እነዚህ የሙያ ምስክሮች የሚሰጡት የምስክርነት ቃል ጉዲዩን በማስረዲት ረገድ የሚኖረው የማስረዲት ብቃትም ሆነ አግባብነት ቃላቸውን ከሰጡ በኃላ የሚታወቅ በመሆኑ ተጠሪዎች በሰበር ደረጃ ባቀረቡት ክርክር እንደገለፁት የኦዱት ምርመራ ውጤቱን ከያዘው ሰነድ የተለየ አያስረደም ብል ከወዱሁ መደምደም የማይቻል ከመሆኑም በላይ አንድ ተከራካሪ ወገን ያቀረበውን ክርክር ለማስረዲት የማስረጃ አግባብነትና ተቀባይነት መርህ ካለገደው ወይም ካልከለከለው በቀር ዘርዝሮ ያቀረበውን የማስረጃ በዓይነትም ሆነ መጠን የማስረዲት መብት ያለው በመሆኑ የሥር ፍ/ቤት የእነዚህን ምስክሮች የሙያ ምስክርነት ቃል ሳይቀበል በዝምታ አልፍ ውሣኔ መስጠቱ የሙግት አካሄድ ሥርዓትን የተከተለ ሆኖ አላገኘነውም እንዱሁም ጉድለቱ በጥፊት ወይም በቸልተኝነት የተፈፀመ መሆኑን ለማስረዲት የግምት መነሻ ይሆናል የተባለውና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 145 ከፕሉስ ኮሚሽን የቀረበ የተባለው የተሰየመው ሰነድ ቀርቦ ስለመታየቱም ሆነ ታይቶ ተቀባይነትን አጥቶ ስለመሆኑ የውሣኔው ይዘት የሚያስረዲው ነገር እንዲላለ ተረድተናል ስለሆነም የሥር ፍ/ቤት ጉዲዩን ተመልክቶ ከውሣኔ ለመድረስ አመልካች ያቀረበውን ክርክር በማስረጃ የማስረዲት መብቱን ሙለ በሙለ ጠብቆ ያከናወነ ስለመሆኑ የውሣኔው ይዘትም ሆነ በሰበር ግራቀኙ ያደረጉት ክርክር ስለማያስረዲ የጉዲዩ አካሄድ ሙለ የክርክር አመራር ሥርዓትን የተከተለ ሆኖ አላገኘነውም።
ው ሣ ኔ
የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ በ10/11/2000 እንዱሁም ይግባኝ ሰሚው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/መ/ በሐምል 07 ቀን 2001 የሰጠው ዲኝነት ተሽሯል።
የመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ የተመዘገበውን መዝገብ እንደገና አንቀሳቅሶ በአመልካች በኩል ማመልከቻው ላይ የጠቀሰውን ጉዲይ ለማስረዲት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 223 መሰረት አስቀድሞ ዘርዝሮ ያቀረበውን ማስረጃ በሙለ ሰምቶና አይቶ በጉዲዩ ላይ የመሰለውን እንዱወስን መዝገቡን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343/1/ መሰረት መልሰናል።
በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ግራቀኙ ያደረጉት ክርክር ላስከተለው ወጭና ኪሣራ ሁለቱም ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ። መዝገቡን ዘግተናል።
No topics extracted.