No summary available.
ጥቅምት 18 ቀን 2003ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ገብሩ ኮሬ ጠበቃ ወልደስላሴ ብርቱ ተጠሪ፡- አቶ አመዱዮ ፋዳሬቼ ከጠበቃ መስፍን ጌታቸው ጋር ቀርበዋል።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በውለ መሰረት የግልግል ዲኛ ጉዲዩን እንዱመለከት ይወሰን ዘንድ ለፍርድ ቤት ጥያቄ ቀርቦ በፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት ጉባኤው ተቋቁሞ ጉዲዩን ማየት ከጀመረ በኋላ ጉባኤው የአባላቱን አበል በተመለከተ ትዕዛዝ ሲሰጥ በአበለ መጠን ቅሬታ ያለው ወገን ሉከተለው የሚገባውን ሥነ ሥርዓት የሚመለከት ነው።
ጉዲዩ በግልግል ጉባኤ እንዱታይና ጉባኤው እንዱቋቋም ለፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቤቱታ ያቀረቡት ያሁኑ ተጠሪ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ የሽምግልና ዲኛ እንዱሾም ብይን ሰጥቷል። በዚህም መሰረት ፍ/ቤቱ አንድ ሰብሳቢ ዲኛ ግራ ቀኙ ደግሞ አንድ አንድ የሽምግልና ዲኛ መርጠዋል። በፍርድ ቤቱ የተሾሙት ሰብሳቢ ዲኛ በግራ ቀኙ ከተሾሙት ዳኞች ጋር በመሆን ስራ ከመጀመራቸው በፉት ስለአበል ክፍያ አተማመን ይረዲቸው ዘንድ የግራ ቀኙ የጽሐፍ ክርክር እንዱቀርብ አድርገዋል። ከዚህም የሽምግልና ጉባኤ አባላት አበል ብር 60,000.00 (ስልሳ ሺህ ብር) እንዱሆንና ግማሹ ቅድሚያ እንዱከፈል ለግራ ቀኙ ተከራካሪ ወገኖች ተገልጾላቸዋል። ተጠሪ ይህ ሲገለጽላቸው አበለ ከአቅም በላይ የሆነባቸው መሆኑን ገልፀው ቀነ ቀጠሮ በጉባኤ ከተሰጣቸው በኋላ አባላቱ ጉዲዩን ለማየት የማይችለ መሆኑንና የተጠሪን በቀነ ቀጠሮ አለመቅረብ በመጥቀስ መዝገቡን ዘግተዋል። ከዚህ በኋላ ተጠሪ ላላ የሽምግልና ጉባኤ እንዱቋቋምላቸው /እንዱሾምላቸው/ እና የተዘጋው መዝገብ እንዱንቀሳቀስላቸው ለስር ፍ/ቤት አቤቱታ አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ፍ/ቤቱም የግልግል ጉባኤው አበለ ቀድሞ ካልተወሰነ ራሱ መወሰን እንደሚችል፣ ይህም በስራ ሑደት እንደተሰጠ ትዕዛዝ እንደሚቆጠር በትዕዛዙ ቅሬታ ያለው ወገን ማሳረም የሚችለው በይግባኝ እንጂ ላላ ጉባኤ እንዱቋቋም በማድረግ አለመሆኑንና ተጠሪ እንዱከፈል ትዕዛዝ የተሰጠበትን የጉባኤ አባላት አበል በመክፈል መዝገቡን ከማንቀሳቀሳቸው ውጭ ላላ የግልግል ዲኛ እንዱተካ ጥያቄ ማቅረብ የለባቸውም በሚል ምክንያት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 318/5/፣ 317/1/ እና 319/1/ ድንጋጌዎችን በዋቢነት በመጥቀስ ተጠሪ ላላ ዲኛ ተተክቶ መዝገቡ ይንቀሳቀስልኝ ሲለ ያቀረቡትን አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል። በዚህ ብይን ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በዋላ የስር ፍ/ቤት ብይን ተሽሮ የስር ፍ/ቤት ግራ ቀኙን አነጋግሮ ምትክ የሽምግልና ዲኝነት ጉባኤ እንዱያቋቁም በሚል ተወስኗል። በዚህ ውሳኔ የአሁኑ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ቢያቀርቡም ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ የካቲት 15 ቀን 2002ዓ.ም በፃፈት ሶስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ የሽምግልና ጉባኤ አበል በመደበኛ ፍርድ ቤቶች ክስ ለማቅረብ ከሚጠየቀው የዲኝነት ገንዘብ የተለየ ነው። በግልግል ዲኝነት ጉባኤ የተከፈተው መዝገብ የተዘጋው በአበል ያለመክፈል ብቻ አይደለም የሚለትን ምክንያቶች ዘርዝረው ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም የሽምግልና ጉባኤው የአበል መጠንን አስመልክቶ የሰጠው ትዕዛዝ በስራ ሑደት እንደተሰጠ ውሳኔ ስለማይቆጠር ተጠሪ ይግባኝ ማለት አያስፈልጋቸውም የመባለን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጓል። በዚህም መሰረት የተጠሪ ጠበቃ ቀርበው ሐምል 19 ቀን 2002ዓ.ም በተፃፈ 3 ገጽ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል። የአመልካች ጠበቃ በ8/02/03 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ብቻ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
በመሰረቱ የግልግል ዲኝነት የሚቋቋምበት አይነተኛ ዓላማ ተከራካሪዎቹ ወገኖች ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት በመሄድ የሚያጠፈትን ጊዜና ገንዘብ ለማስቀረት መሆኑ የሚታመን ነው።
No topics extracted.
ጉባኤው የሚቋቋመውም በተከራካሪ ወገኖች ስምምነት ሲሆን ተከራካሪዎቹ ባላቸው የመዋዋል ነፃነት ጉዲያቸውን ከፍርድ ቤት ውጪ በግልግል ዲኝነት ለመጨረስ የሚስማሙት ሁኔታ መኖሩ በራሳቸው ፍላጎትና ምርጫ የተቋቋመው ጉባኤ ጉዲያቸውን በተገቢው ጊዜና በአነስተኛ ወጪ ለመወሰን ይችላል የሚል እምነት ኑሯቸው ነው ተብል ይታሰባል። በሕጉ አግባብ በተደረገ የግልግል ስምምነት መሰረት የግራ ቀኙ ጉዲይ /ክርክር/ የግልግል ዲኛ መመልከት ከጀመረ በኋላ ሉከተል የሚገባው ሥነ ሥርዓትን በተመለከተ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉ መሰረት ስለመሆኑ የፍ/ህ/ቁጥር 3345 ድንጋጌ ያሳያል። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 317/1/ ድንጋጌ ሲታይ ደግሞ የግልግል ዲኛ ክርክሩን መምራት ያለበት በተቻለ መጠን የመደበኛ ዲኝነት አካሄድን ተከትል መሆኑን ያስገነዝባል። የዚህ ድንጋጌ መንፈስ የግልግል ዲኝነት አካሄድ የመደበኛ ፍ/ቤት የዲኝነት አካሄድን መከተል ያለበት ቢሆንም እንደመደበኛ ፍ/ቤት የዲኝነት አካሄድ የጠበቀ ወይም ሁል ጊዜ ጥብቅ የሙግት ሥርዓትን ተከትል ላሆን የማይገባ መሆኑን ነው።
በልላ በኩል የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 318/5/ ድንጋጌ ሲታይ የግልግል ጉባኤ ጉዲዩን ለማየት ሉከፈል የሚገባውን የገንዘብ መጠን በተመለከተ ተገቢ ነው ብል ያመነበትን ያህል መወሰን የሚችል መሆኑን ያሳያል። ጉባኤው ይህንን አይነት ትዕዛዝ ጉዲዩ መታየት ከመጀመሩ በፉት ወይም በኋላ ላሰጥ የሚችል መሆኑን ድንጋጌው ያስገነዝባል። ሉነሳ የሚችለው ጥያቄ ጉባኤው ተከራካሪ ወገኖች የማይሰማሙበትን የአበል መጠን እንዱከፍልለ የሚል ትዕዛዝ ቢሰጥ በትዕዛዙ ላይ ተቃውሞ ያለው ተካራካሪ ወገን ያለው መፍትሓ ምንድን ነው? የሚለው ነው። አንድ ሰው በፍርድ ሉያልቅ የሚገባው ጉዲይን ፍርድ ቤት ይዞ ሲቀርብ የዲኝነት አገልግልት ክፍያ መክፈል ያለበት መሆኑን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 215፣ ከ467 እስከ 479 ድረስ የተደነገጉት ድንጋጌዎች ያሳያለ። የዲኝነት አገልግልት መክፈል የማይችል ሰው ክስ ለማቅረብ የሚችልበት አግባብ ስለመኖሩም ተጠቃሽ ድንጋጌዎች ያስገነዝባለ። አንድ የዲኝነት አገልግልት ክፍያ ለመክፈል የማይችል ሰው በደሃ ደንብ ክስ ለማቅረብ የሚችል ሲሆን ለመክፈል አቅም እያለው ክስ ያቀረበ መሆኑ ከተረጋገጠ ግን መዝገቡ እንደሚዘጋ፣ የተዘጋ መዝገብ ደግሞ የዲኝነት አገልግልት ክፍያ/ገንዘቡን/ ለመክፈል ዝግጁ እስከሆነ ድረስ የሚንቀሳቀስለት መሆኑን የሥነ ሥርዓት ሕጉ ድንጋጌዎች መንፈስና ይዘት ያስገነዝባለ።
የግልግል ጉባኤ ከሚቋቋምበት ዋነኛ ዓላማ፣ ጉባኤው ሉከተለው ከሚገባው ሥርዓት እና ስለ ዲኝነት አገልግልት ክፍያ የተመለከቱት ደንቦች መሰረት ሲሆኑ አንድ ጉዲዩ በግልግል ዲኝነት እንዱታይለት የተስማማ ሰው በአካሄደ ቅሬታ እያለው ጉዲዩ በተቋቋመው ጉባኤ እንዱታይ ማድረግ ተገቢነት አለው ለማለት የሚያስችል አይደለም።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም ጉባኤው ጉዲዩን ለማየት ከመጀመሪያውኑ አበለን መወሰን የሚችል ሲሆን በዚሁ ደረጃ የሚሰጠው ትዕዛዝ ሙለ በሙለ የክርክሩ አካል አይደለም ለማለት የማይቻል ቢሆንም በተያዘው ጉዲይ ከላይ ከተመለከቱት ፍሬ ነገሮችና የሕጉ ድንጋጌዎች አንፃር ሲታይ በአመልካች መብት ላይ መሰረታዊ የመብት መጣበብ ያስከተለ ነው ለማለት የሚቻል አይደለም። ጉዲዩ በምትክ የጉባኤ አባላት እንዱታይ ማድረግ በአመልካች መብት ላይ የሚያስከትለው አለታዊ ውጤት የላለው ከመሆኑ አንፃር ስንመለከተው በውጤት ደረጃ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ለማለት የሚያስችል ሆኖ አልተገኘም።
በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ውጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።