No summary available.
ጥቅምት 16 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጏስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካቾች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ አመልካቾች ተጠሪ ላይ ያቀረቡት ክስ ያላአግባብ የፍርድ ባለመብት የሆኑበት ቤት ይለቀቅልኝ ክስ በሥር ፍ/ቤቶች ተቀባይነት ባለማገኘቱ ነው።
በሥር ፍ/ቤት አመልካቾች ከሳሾች ነበሩ። የክሱ ምክንያትም ባልና ሚስት የሆኑት የሥር ተከሳሾች በቤቱ ላይ መብት ሳይኖራቸው የባልና ሚስት ንብረት በማስመሰል በፍርድ አፈፃፀም የተረከቡትን ቤት እንዱያስረክቡ /እንዱመልሱ/ ይወሰንልን የሚል ነበር።
የአሁኗ ተጠሪ ሥር ፍ/ቤት 1ኛ ተከሳሽ ሆነው የሰጡት መልስ ቤቱ በጋብቻ ውስጥ የተፈራ መሆኑ ተረጋግጦ በመ/ቁ. 45803 በ16/7/98 ዓ.ም በተሰጠ ውሳኔ በክፍፍል ያገኙት ንብረት መሆኑን ገልፀው የከሳሾች ጥያቄ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1149 መሰረት በይርጋ ቀሪ ልባል ይገባል የሚል ነው።
ጉዲዩን የተመለከተው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተከሳሾች ቤቱን የያዙት በፍርድ ስለመሆኑ ከሳሾች ያመኑት ጉዲይ ስለመሆኑ ጠቅሶ በሐሰት ማስረጃ ያገኙት ነው የሚለ ከሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 6/1/ መሰረት ከሚጠይቁ በስተቀር ክስ ለማቅረብ አይችለም በሚል ጥያቄያቸውን ሳይቀበል ቀርቷል። ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ የሥር ፍ/ቤት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 6/1/ን በመጥቀስ በውሳኔው ያመለከተውን የከሣሽ መብት ለተያዘው ጉዲይ አግባብነት እንደላለው ተችቶ ከሳሾች መብታቸውን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 ከሚጠይቁ በስተቀር አዱስ ክስ ማቅረብ አይችለም በማለት የሥር ፍ/ቤትን ውሳኔ ምክንያት በመለወጥ አጽንቷል።
አመልካቾች ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ ያቀረቡት በዚሁ ላይ ነው። የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ይዘት ባጭሩ። የቤት ቁጥር 260 የባልና ሚስት ሐብት ነው ተብል እንዱከፊፈለ በመ/ቁ.
45803 ውሳኔ መስጠቱን እንዲወቁ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት አቤቱታ አቅርበው ውሳኔ ከተፈፀመ በኋላ የቀረበ ነው በሚል ውድቅ የተደረገባቸው መሆኑን ጠቅሰው አዱስ ክስ የቀረበው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 421 መሰረት ስለመሆኑ ገልፀው የሥር ፍ/ቤቶች ፍትህ የማግኘት መብታቸውን በሚጏዲ ሁኔታ የሰጡት ውሳኔ እንዱታረም ጠይቀዋል።
የሰበር ችልቱም አቤቱታቸውን መርምሮ የሥር ፍ/ቤቶች የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 6 እና 358 ጠቅሰው የሰጡት ውሳኔ በአግባቡ ስለመሆኑ ለመመርመር ተጠሪ መልስ እንዱሰጡ አዝዟል።
የተጠሪ ጠበቃ ሚያዝያ 18 ቀን 2002 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርቧል። በይዘቱም የሥር ፍ/ቤቶች የአመልካቾችን የዲኝነት ጥያቄ ቀደም ሲል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቀጥር 358 መሰረት ውድቅ መደረጉን ተገንዝበው መወስናቸው በአግባቡ ነው በማለት ተከራክሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ይዘት ከፍ ሲል በአጭሩ የተመለከተው ነው።
እኛም ጉዲዩን ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ከሕጉ አገናዝበን መርምረናል።
ከመዝገቡ መረዲት እንደተቻለው የአሁኑ ተጠሪ እና ባለቴቷ መካከል የነበረ ጋብቻ በፍች እንዱፈ|ርስ መወሰኑን ተከትል የንብረት ክፍፍል ክርክር ተደርጏ በተሰጠ ውሳኔ መሰረት በኮልፋ ቀራንዮ ክ/ከተማ ቀበላ 04 የቤ/ቁ. አዱስ የሆነ በ400 ካ.ሜ ቦታ ላይ ያለ ቤት ተጠሪዋ በፍርድ አፈፃፀም የተረከበች መሆኑን ተከትል ይህ ቤት የባልና ሚስቱ ሳይሆን የአመልካቾች ነው ሲለ አመልካቾች ክስ ማቅረባቸው ተመልክቷል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍ/ቤት ተጠሪና ባለቤቷ በሐሰተኛ ማስረጃ ቤቱን አገኙ የሚለ ከሆነ የከሳሾች (አመልካቾች) ጥያቄ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 6/1/ መሰረት ላታይ የሚገባ እንጂ አዱስ ክስ መቅረብ አይችልም የሚል ድምዲሜ ላይ ደርሷል።
በመሰረቱ የከፍተኛው ፍ/ቤት ይህ የሥነ ሥርአት ሕጉ ድንጋጌ ተከራካሪ በነበሩ ወገኖች መካከል እንጂ ሦስተኛ ወገን ሉጠቀምበት እንደማይችል ጠቅሷል። በዚህ ረገድ የ3ኛው ፍ/ቤት የውሳኔው ምክንያት ተገቢነት ያለው እንደሆነም መገንዘብ ይቻላል። ነገር ግን አመልካቾች አዱስ ክስ ከማቅረባቸው በፉት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሰረት በዋናው መዝገብ ላይ አቤቱታ አቅርበው ውሳኔው ከተፈፀመ በኋላ የቀረበ ጥያቄ ነው ተብል ውድቅ የተደረገባቸው መሆኑ በግልጽ ተጠቅሶ እያለ ከፍተኛው ፍ/ቤት መልሶ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 358 መሰረት መብታቸውን ማስከበር ይችላለ ያለው እርስ በርሱ የሚጋጭ አቋም መሆኑን ያመለክታል። በአንድ ንብረት ላይ መብት አለኝ፣በክርክሩ ሂደት አልተካተትኩም በሚል ምክንያት መብቴ ተነክቷል የሚል ወገን መብቱን ሉያስከብር የሚችልበትን ሥርአት ሕጉ በየደረጃው ዘርግቷል።
ለዚህም ተጠቃሽ የሚሆኑት ውሳኔው ከመፈጸሙ በፉት ከሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት፤ውሳኔው በአፈፃፀም ሂደት ላይ ሆኖ ንብረቱ ያለአግባብ ተይዞብኛል የሚል ወገን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 418 መሰረት መብቱን ማስከበር የሚችልበት አግባብ ተደንግጓል ከዚህ ባለፈ በንብረቱ ላይ የተሻለ መብት አለኝ የሚል ወገን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ አንቀጽ 421 አልያም እንደነገሩ ሁኔታ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/አንቀጽ 455 መሰረት ክስ መሥርቶ መብቱን ማረጋገጥ እንደሚችል ተመልክቶ እናገኛለን።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካቾች ጥያቄ ያቀረቡበት ንብረት በፍርድ ለ1ኛ ተጠሪ የተላለፈ ስለመሆኑ በክርክር ሂደት የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። አመልካቾች ይህ ንብረት የባልና ሚስቱ ሳይሆን የአመልካቾች ነው ሲለ ያቀረቡት ክስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 455 በተደነገገው አግባብ ሉስተናገድ የሚችል ስለመሆኑ መረዲት ተችሎል።
የግራ ቀኙ ክርክር እንደማናቸውም ጉዲዮች በማስረጃ ተጣርቶ ውሳኔ ሉይገኝ የሚገባው እንደሆነ ግልጽ ነው።
ስለሆነም አመልካቾች በንብረቱ ላይ ያላቸውን መብት ለማረጋገጥ ያቀረቡትን ክስ የሥር ፍ/ቤቶች የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 6 እና 358ን በመጥቀስ ውድቅ ማድረጋቸው ለጉዲዩ አግባብነት የላለው እና የጉዲዩን ደረጃ እና የቀረበውን የዲኝነት ጥያቄ ያላገናዘበ በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 12351 በ29/5/01 የሰጠው ፍርድ እና የፋ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 78780 ጥቅምት 25 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የአመልካቾች የዲኝነት ጥያቄን ተቀብል የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥበት ብለን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341/1/ መሰረት መዝገቡን ለፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መልሰናል። ይፃፍ።
ግራ ቀኙ የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.