No summary available.
ጥቅምት 18 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ውጅራ ንዲ ቀረቡ ተጠሪ፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤትና የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ተከሳሽ አንደኛ ተጠሪ ከሳሽ በመሆኑን ተከራክረዋል። አንደኛ ተጠሪ በሥር ተከሳሽ የሆኑት አመልካች እኔ በሉቀመንበርነት የምመራው አዱስ ዘመን 83 የመኖሪያ ቤት የህብረት ሥራ ማህበር አለ በማለት ብር 20‚000 /ሀያ ሺህ ብር/ ተቀብለው በመውሰድ በልጽገውበታል። ተከሳሹ /አመልካች/ ማስጠንቀቂያ ብጽፍላቸውም መልስ አልሰጡኝም ስለሆነም ከእኔ የወሰደትን ብር 20‚000 /ሀያ ሺህ ብር/ ከነወለደ እንዱከፍለ በማለት ክስ አቅርቧል።
አመልካች ገንዘቡን ለእኔ በግላ አልሰጠኝም፡ ገንዘቡን የከፈለው ለቤት ሥራ ማህበር ሲሆን ገንዘቡን ለማህበሩ የከፈለ ስለመሆኑ ደረሰኝ ተሰጥቷል። እኔ ገንዘብ የተቀበልኩት በወቅቱ የማህበሩ ገንዘብ ያዥ በመሆኔ ነው። ስለዚህ ክሱ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክረዋል። የሥር ፍርድ ቤት ማህበሩ ህጋዊ ሰውነት ያለው ስለመሆኑ በቂ ማስረጃ አልቀረበም በማለት አመልካች ብር 20‚000 /ሀያ ሺህ ብር/ ከግንቦት 5 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር ይክፈለ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች አንደኛ ተጠሪን በአንደኛ መልስ ሰጭነት ሁለተኛ ተጠሪን በሁለተኛ መልስ ሰጭነት ስማቸውን በመጥቀስ ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበዋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ አጽንቶታል። አመልካች ይህንን ውሣኔ በመቃወም ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ ገንዘቡን እኔ በግለሰብነቴ ሣይሆን የማህበሩ ገንዘብ ያዥ ስለሆንኩ የተቀበልኩት መሆኑን ማስረጃ በማቅረብ ተከራክሬአለሁ። ከዚህ በተጨማሪ ሁለተኛው ተጠሪ በክርክሩ ጣልቃ ለመግባት ጠይቆ ገንዘቡ ለማህበሩ ገቢ መሆኑንና ገንዘቡ እኔን የማይመለከተኝ መሆኑን በጽሐፍ መልስ ሰጥቷል። ይህንን ሁለ በማለፍ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩለ ሁለተኛው ተጠሪ አለኝ የሚለውን የሰነድ ማስረጃ በማያያዝ በክርክሩ ጣልቃ ገብ ተከራካሪ ሆኖ እንዱገባ ያመለከተ ቢሆንም የሥር ፍርድ ቤት ማህበሩ ህጋዊ ህልውና የላለው መሆኑን በማረጋገጥ ጥያቄውን ሣይቀበለው ቀርቷል። ስለዚህ አመልካች ያቀረበው አቤቱታ የህግ ድጋፍ የለውም በማለት መልስ ሰጥተዋል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው አንደኛ ተጠሪ ለአመልካች ብር 20‚000 /ሀያ ሺህ ብር/ የከፈለ መሆኑን ለማስረዲት የቀረበው በአዱስ ዘመን 83 የመኖሪያ ቤት የህብረት ሥራ ማህበር ሥም የታተመ የገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ማህበሩ የራሱ የሆነ ማህደር ያለው ስለመሆኑ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ቡራዩ አስተዲደር ማዘጋጃ ቤትና የኮልፋ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ማህበራዊ ማደራጃና ማስፊፉያ መምሪያ የፃፊቸው ደብዲቤዎች ያስረዲለ።
ከዚህ በተጨማሪ ሁለተኛ ተጠሪ ገንዘቡ የተከፈለው መሆኑንና ክርክሩ አመልካችን ሳይሆን በቀጥታ እሱን የሚመለከተው መሆኑን ገልፆ በሥር ፍርድ ቤት ታህሣሥ 10 ቀን 2001 ዓ.ም ያመለከተ መሆኑን የሥር ፍርድ ቤትን መዝገብ በማስቀረብ ለመገንዘብ ችለናል።
የሥር ፍርድ ቤት ሁለተኛው ተጠሪ የከሳሽን /የአንደኛ ተጠሪን/ ክስና ማስረጃ ወስደው መልስ እንዱያቀርቡና በክርክሩ ጣልቃ እንዱገቡ ከፈቀደ በኋላ ሁለተኛው ተጠሪ ጥር 13 ቀን 2001 ዓ.ም በነበረው ቀነ ቀጠሮ መልስ ይዘው ባለመቅረባቸው የሁለተኛ ተጠሪን ጣልቃ ገብነት በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 41 ንዐስ አንቀጽ 3 እና በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 199 መሰረት ሰርዥዋለሁ በማለት ትእዛዝ የሰጠ መሆኑን ችልቱ አስቀርቦ የሥር ፍርድ ቤት መዝገብና አመልካች በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ቅር በመሰኘት ካቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተገንዝበናል። በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤት የተከተለው የክርክር አመራር ሥርዓትና በመጨረሻም ውሳኔ ሲሰጥ የደረሰበት መደምደሚያ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመመሥረት ጉዲዩን መርምረናል።
No topics extracted.
የሥር ፍርድ ቤት ሁለተኛ ተጠሪ ታህሣሥ 10 ቀን 2001 ዓ.ም ያቀረቡትን አቤቱታ በመቀበል በክርክሩ ጣልቃ እንዱገቡ ታህሳስ 10 ቀን 2001 ዓ.ም በዋለው ችልት ትእዛዝ ሰጥቷል።
ሁለተኛ ተጠሪ ያቀረቡት የጣልቃ ገብነት አቤቱታ አመልካች ገንዘቡን የተቀበለው የማህበሩ ገንዘብ ያዥ በመሆኑና ማህበሩም ገንዘቡ ገቢ የተደረገለት በመሆኑ ከሳሽ /ሁለተኛ ተጠሪ/ ስለማህበር አባልነትና ተመላሽ ገንዘብ መክሰስም ሆነ መከራከር ካለበት ከማህበሩ ጋር መሆን አለበት የሚል ይዘት ያለው ነው። የሥር ፍርድ ቤት ሁለተኛ ተጠሪ ለአንደኛ ተጠሪ በሥር ከሳሽ ክስና ማስረጃ ይዘው እንዱቀርቡ በተቀጠረበት ቀን ካልቀረቡ የሁለተኛ ተጠሪን መልስ የመስጠት መብት በማለፍ ውሣኔ መስጠት ሲገባው ህጋዊ ህልውና አለህ በክርክሩ ጣልቃ እንድትገባ ተፈቅዶል ያለውን አካል ከክርክር ውጭ እንዱሆን የሰጠው ትእዛዝ የአመልካችን መብት የሚያጣብብና አንድ በክርክር ተካፊይ የሆነ ሰው መልሱንና ማስረጃውን ባያቀርብ ፍርድ ቤቱ በላለበት ክርክሩን ሰምቶ የሚወሰን መሆኑ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 70 የተደነገገውን የሚጥስና የክርክር አመራር ጉድለት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ሁለተኛ ተጠሪ ሕጋዊ ህልውና እንዲለውና በክርክር ጣልቃ መግባት እንደሚችል የሥር ፍርድ ቤት ትእዛዛ ከሰጠ በኋላ ሁለተኛው ተጠሪ ህጋዊ ህልውና እንደላለውና አንደኛ ተጠሪ በማህበሩ ስም የታተመ ደረሰኝ ተቀብል ለከፈለው ብር 20‚000 /ሀያ ሺህ ብር/ አመልካች በግለ ተጠያቂነት አለበት በማለት መጋቢት 16 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ፍርድ ቤቱ የማህበሩ ህጋዊ ሰውነት ያለው ስለመሆኑ ታህሳስ 10 ቀን 2001 ዓ.ም ከሰጠው ትእዛዝ ጋር የሚቃረንና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ውሳኔ ነው በማለት ወስነናል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አመልካች ሁለተኛ ተጠሪና በአንደኛ ተጠሪ መካከል የቀረበውንና የሚቀርበውን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ውሳኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343(1) መሰረት መልሰን ልከንለታል።
ከሥር ፍርድ ቤት የመጣው መዝገብ ይመለስ
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።