No summary available.
ሰኔ 13 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ አሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ፊሲል ታምራት - አልቀረቡም ተጠሪ፡- የሐዋሣ ከተማ ከፍተኛ መርማሪ ከሣሽ - አልቀረበም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የወንጀል ክስ ሲሆን የተጀመረው በአዋሣ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መደበኛ ጉዲይ ችልት ሲሆን የአሁን ተጠሪ በመግደል ሙከራ ክስ በአመልካች ላይ ባቀረበው መሰረት ነው። ቀርቦ የነበረው ክስ በአጭሩ፡- ተከሣሽ የወ/መ/ሕ/ቁ. 27 እና 539 /1/ /ሀ/ በመተላለፍ በቀን 06-9-2002 ዓ.ም ከምሽቱ በ4፡ዐዐ ሰዓት በሀዋሳ ከተማ መሀል ከተማ ክልል ጸሐይ ሆቴል ፉት ለፉት ባለው አስፊልት መንገድ ላይ አቶ ተስፊአብ ለተሞ ወደሚያሽከርክረው መኪና ተጠግቶ ምስራቅ ሆቴል ልታሰዬኝ ትችላለህ? በማለት ካልተያዘው ተጠርጣሪ ጋር ካነጋገሩት በኋላ ያልተያዘው የግል ተበዲይ እንዲይከላከል ከልል ሲያመቻች ተከሣሹ የግል ተበዲዩን በኋይል አንገቱን ሉወጋው ሲል ዞር በማለቱ ቀኝ ጉንጩን ወግቶ የፉት ለፉት 3 ጥርስ ከታች መንጋጋ 5 ጥርሶቹን በሣንጃ ወግቶ ያወላላቀበት በመሆኑ በፈጸመው የመግደል ሙከራ ተከሷል የሚል ነበር።
ተከሣሽ የቀረበበትን ክስ በመካድ ሲከራከር የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ቀርበው ከተሰሙ በኋላ የተከሣሽም መከላከያ ምስክር እንዱቀርቡ ታዘው ከተሰሙ በኋላ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን አንቀጽ ወደ 555 /ሀ/ /ለ/ በመለወጥ ጥፊተኛ መሆኑን ፍርድ በመስጠት በ8 ዓመት ጽኑ እስራት እንዱቀጣ ወስኗል። ፍርድ ቤቱ በሰጠው የጥፊተኝነት ውሣኔ እና ቅጣት ላይ ዐቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ካከራከረ በኋላ ተከሣሽ ጥፊተኛ መሆን ያለበት በወ/መ/ሕ/ቁ. 27 እና 540 መሆን አለበት በማለት ቅጣቱንም በ12 ዓመት ጽኑ እስራት እንዱቀጣ ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ቅሬታውን አቅርቦ ችልቱም በትዕዛዝ የበታች ፍ/ቤቱን ውሣኔ አጽንቷል።
አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን አመልካች ያቀረበው ቅሬታ ፍሬ ሃሣብ የተላለፈበት የጥፊተኝነት ውሣኔና ቅጣት ያለአግባብ በመሆኑ ተሽሮ በነጻ እንዱሰናበት ፣ ይሄ ካልሆነ ደግሞ የተላለፈበት ቅጣት ተሻሽል እስከአሁን የታሰረው በቂ ሆኖ እንዱለቀቅ ጠይቋል።
ተጠሪ በበኩለ ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ቀርቦ በሰጠው መልስ የተላለፈበት የጥፊተኝነት ውሣኔና ቅጣት በአግባቡ በመሆኑ የቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት የለውም በማለት ውድቅ እንዱሆን ጠይቋል።
አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የክርክር ሂደት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ይሄ ችልትም የቀረበውን ክርክር ከተያዘው ጭብጥና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል።
በዚሁ መሰረት ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ሲባል ተይዞ የነበረው ጭብጥ አመልካች ጥፊተኛ መባል ያለበት በከባድ የአካል ጉዲት ማድረስ ወይስ? በመግደል ሙከራ የነበረ በመሆኑ ይሄ ጉዲይ ከዚሁ አኳያ ታይቶ መፍትሓ ማግኘት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በመጀመሪያ ደረጃ አመልካች በተከሰሱበት የወንጀል ድርጊት ስላልተረጋገጠብኝ በነጻ ልሰናበት ይገባኛል በማለት የተከራከረውን በተመለከተ በዚህ ጉዲይ ላይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን የጥፊተኝነት ውሣኔ እና ቅጣት ያንሣል በማለት ይግባኝ ያለው ከሣሽ ዐቃቤ ህግ በመሆኑ በዚህ ነጥብ ላይ አመልካች ያቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም። ምክንያቱም በከፍተኛው ፍርድ ቤት የጥፊተኝነት ውሣኔ ላይ አመልካች ይግባኝ ስለማቅረቡ የሚያመለክት ነገር የለም።
በሁለተኛ ደረጃ የጥፊተኝነት ውሣኔ የተሰጠበትን አንቀጽ በተመለከተ የከፍተኛው ፍርድ ቤት በዐቃቤ ህጉ ክስ ውስጥ የተመለከተውን የወ/መ/ሕ/ቁ. 27 እና 539 /1/ /ሀ/ ወደ ወ/መ/ሕ/ቁ.
555 /ሀ/ /ለ/ የቀየረው እውነት ለመግደል ሃሳብ ቢኖረው ደጋግሞ በመውጋት ሃሳቡን ከግቡ ለማድረስ ይችል ነበር በሚል ሲሆን የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በበኩለ አመልካች ጥፊተኛ መሆን ያለበት በወ/መ/ሕ/ቁ. 27 እና 540 ስር መሆን አለበት ወደሚል መደምደሚያ የደረሰው አመልካች በያዘው ሣንጃ የተበዲይ አንገት ላይ ለመውጋት የሰነዘረ መሆኑና ተበዲይ በድንገት ዞር በማለቱ ጉንጩ ላይ በመውጋት ከወጋ በኋላ ደግሞ ሣንጃውን ነቅነቅ በማድረግ ባጠቃላይ 8 /ስምንት/ ጥርሶቹን ያረገፈ በመሆኑ እና መጀመሪያ እንደሰነዘረው አንገቱን ቢወጋ ኖሮ የተበዲይ በህይወት የመትረፍ አጋጣሚ ጠባብ የነበረ መሆኑ ስለመረጋገጡ በማስረዲት መሆኑን ከመዝገቡ መረዲት ይቻላል።
ይሄንን የይግባኝ ሰሚ ችልት መደምደሚያ ከወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀጽ 27/1/ ሁለተኛ ምዕራፍ ጋር ስናመዛዝን… ‛ወንጀለ እንደተጀመረ የሚቆጠረው የተደረገው ተግባር በማያጠራጥር ሁኔታና በቀጥታ ወንጀለን ለመፈጸም ወደ ታሰበበት ግብ ለማድረስ የተደረገ በሆነበት ጊዜ ነው“ ይላል።
በእርግጥም አመልካች ቀድሞ አስቦ ሣንጃውን በሰነዘረው መሰረት ተበዲይ ዞር ባይልና በቀጥታ አንገቱን ቢያገኘውና ቢወጋው ኖሮ ሞትን ሉያስከትል እንደሚችል መገመት አያስቸግርም።
አንገት ላይ በሣንጃ መውጋት ደግሞ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወ/መ/ሕ/አንቀጽ 24/1/ ሁለተኛ ምዕራፍ ላይ እንደተመለከተው በነገሮች የታወቀ ወይም የተለመደ ሂደት In the normal course of things…“ ሞትን ሉያስከትል የሚችል በመሆኑ በውጤቱና ምክንያቱ መካከል ቀጥተኛ ግንኙነት አለ የሚያሰኝ ነው።
ባጠቃላይ ከላይ የተመለከቱትንና ላልችንም የድርጊቱን አፈጻጸም ሂደቶች ከግምት በማስገባት የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አመልካች ጥፊተኛ መባል ያለበት በመግደል ሙከራ ስር ነው በማለት በወ/መ/ሕ/ቁ. 27 እና 540 ስር ጥፊተኛ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አላገኘነውም። የተላለፈበት ቅጣትም ከወንጀለ አፈጻጸም እና ጥፊተኛ ከተባለበት አንቀጽ አኳያ ሲታይ በተመሣሣይ መልኩ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አላገኘነውም።
በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የደ/ብ/ብ/ሕ/ብሓ/ክ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 45137 በቀን 09-3- 2003 ዓ.ም በዋለው ችልት እና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 43913 በቀን 06-01- 2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሣኔ ወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ/ቁ. 195/2/ /ለ/ /2/ መሰረት ጸንቷል።
ለአመልካች የውሣኔው ግልባጭ በሀዋሳ ማረሚያ ቤት በኩል ይድረሰው።
No topics extracted.